Thursday, September 30, 2010

ለማስታወስ ያህል

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!

ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።




ለማስታወስ ያህል

ባለፈው  ስለልጆቻችን ቀጣይነት በተመለከተ የተለያዩ አስታየቶችን ተቀብለናል። በዛሬው ደግሞ ትንሽ ወይም ትልቅ ሳይል ለሁላችንም ለማስታወሻ ይሆነን ዘንድ ከዚህ በታች ያለውን እንካፈለው ዘንድ አቅርበነዋል። የምንወዳችሁና የምንናፍቃችሁ የገጻችን ተከታታዮች በያላችሁበት እንደምን ከርማችኃል? በዚች ጦማር አማካይነትም የልዑል እግዚሀብሔር መልካም ፈቃዱ ሆኖ ላገናኘን ምስጋና ይሁን። አሜን።

ዘግይቶ እንደደረሰን የዘንድሮው የመስቀል ዳመራን የዳላሱ ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ከመቼውም ጊዜ አይነት በተለየ ታላቅና መንፈሳዊ በአል እንደነበር ነው የተረዳነው። እንደኛ እርቃችሁ ለምትኖሩም ሆነ ሳይሳካላችሁ ያልተገኛሁ ሁሉ የተዋጣለት የደመቀ በአል ነበር። የተጀመረው በተያዘለት መርሀ ግብር መሰረት በጸሎት ሆኖ ከዝያም በአሉን አስመልክቶ የቀረበው ወርብና መይዝሙር ብቻውን ባራኪ እንደነበር ነው። በተለይ ጣዕምና ለዛ የተሞላበት የእለቱ ትምህርት ታዳሚውን ሁሉ የባረከ እንደነበረ ለመረዳት በቅተናል። በተለይም ወጣቶቹ በትርዒት ያቀረቡት መንፈሳዊ ድራማ የተሰበሰቡትን በዐል አክባራዎችን እጅጉን ያስደሰተ ሲሆን፣ የእናትና የወጣት መዘምራን ተሳትፎ እንደዚሁም ሸነጥ ያደረጋቸው የቀድሞ መዘምራን እህቶችም በከበሮውና በዝማሬ እንዳደመቁት ለማወቅ በቅተናል።

ወደ እርዕሳችን ስንመለስ ፤ የዘመኑን ጥበብ ከእለት ወደ እለት ሳናሰልስ ለመታዳደሪያ የምንጠቀምበትም ሆነ ሲመቻቸው ብቻ ወደ ኮምፒተራቸው ቀርበው የኢተርኔት ተጠቃሚዎች ሁሉ በቅድሚያ ሊረዳን የሚገባ ምን አይነት ጥንቃቄ ማወቅ እንደሚገባን ነው። ልጆቻችንስ ምን ያህል ጥንቃቄን ያደርጋሉ? የምንጠቀምባቸው መገናኛዎች ሞባይል የስልክ ኢንተርኔትና እትመትን የምናደርግባቸውን ቁሳቁስን ጨምሮ ከአገልግሎት ስናወጣቸው ምን አይነት ዘዴ በመጠቀም እንሽራቸዋለን? የሚለውን ለማስረገጥ ስንሞክር ራሳችንን ባለሙያው ሳናደርግ እንደሆነ ግንዛቤ እንድትጨብጡልን በቅድሚያ እንጠይቃለን።

እያንዳንዳችን የተለያየ የእጅ ምልክት (አሻራ) ወይንም የዘር ምንጭ (ዲ ኤን ኤ) እንዳለን ሁሉ፣ እያንዳንዳቸው የዘመኑ ጥበብ ምርቶች ሁሉ የራሳቸው መለያ ግልጽ ወይም ስውር መለያ በአሀዝ፣ በፊደል፣ ወይም በስውር ምልክት (ባርኮድ) የራሳቸው መለያ እንዲኖራቸው ተደርገው እንዲመረቱ ለማንኛችንም ግልጽ ነው ። ይከውም መቼ ተሰሩ፣ ማን ሰራቸው፣ በየትኛው የማምረቻ መስመር ተሰሩ የሚሉትንና የመሳሰሉትን ጥያቄዎችን ሲያስተናግዱ፤ ከዚያም አልፎ በሰአቱ በምርቱ የተሳተፉትን  የሰው ኃይሎችን ብቻ ሳይሆን ከምርቱ ጅምር እስከ ሸማቹ ማንነት መረጃ ለማሰባሰብ የሚያስችል እንደሆነ እሙን ነው። በተመሳሳይ ሁኔታ ማንኛውም የኤሌክትሮኒክስ ልውውጦችንና ጉብኝቶችን በኢንተርኔት ስናካሂድ ይዘቱ በስውር ተቀርጾ ከምንገለገልበት ቁሳቁስ ጨምሮና በማለፍም በዳሰስናቸው ባዕዳን አገልግሎት ሰጪዎችም እጅ የሚገባ መሆኑን መረዳት አለብን። በአሁኑ ወቅት የተለያዩ መንግስታት በግልጽ እነዚህን የመሳሰሉ የኤሌክትሮኒክስ ልውውጦችን በገሀድ እንደሚከታተሉ ሲታወቅ በቁጥር ፩ ቅድሚያ ተጠቃሽ ሪፐፕሊክ ቻይና ስትሆን ትውልድ አገራችንም ወደዚሁ እያመራች መሆኗን የሚጠቁሙ ሂደቶች አሉ። ስለዚህም ይኽነን የመሰለ ልውውጥ የምናደርግ ሁሉ፤ የተለየ ግንዛቤን መውሰድ ብቻ ሳይሆን ቤተሰቦቻችንም ሆነ ወዳጆቻችንን ግንዛቤ አንዲኖራቸው ማድረጉን እናሳስባለን።

ልጆቻችን በተለይ የዘመኑን የኤሌክትሮኒክስ ግንኙነት ከህጻንነታቸው ስለሚጀምሩ አብረውት ነው የሚያድጉት ለማለት እንደፍራለን። እንደ ወላጆች አመዛዘን ምን ያህሉን እንዲጋለጡ ማድረግና በመገናኛው መስመር ላይ የወላጅ ቁጥጥር ወይም ማዕቀብ ማድረጉ ተገቢ ነው።

በተለይ ፌስ ቡክ፣ ቲውተር፣ ብሎግ፣ ወዘተ,,,,, ተጠቃሚዎች የሆንን በሙሉ በጣሙን መጠንቀቅ ያለብን የምንሰጣቸውን፣ የምንቀበላቸውን፣ ባጠቃላይ የምንሳተፍበትን ሁሉ ጥንቃቄ ማድረግ አስፈላጊ ነው።

ለምሳሌ በኛ የደረሰውን ለማካፈል ያህል፤ ከ1997 እ.ኤ.አ, ጀምሮ እስከ 2007 እ.ኤ.አ. በያሁ አገልግሎት የኢሜይል ግልጋሎታችንን ወደ ጉግል ስናዛውር ደልዘን የነበርናቸውን ከ፩፪ ሺህ በላይ የሆኑትን የላክናቸውንና ከዚያ የበለጠ የተቀበልናቸውን በሙሉ ባጋጣሚ ልንገልጣቸው በቅተናል። ይህም የሚያስረዳው ከኛ ወገን ከኮምፒተር ብንደልዝም አገልግሎት ሰጪው ግን አዝሎ እንደሚኖር ነው። በተመሳሳይ ማንኛውንም ዶሴ ከቆሻሻ መጣዩ ማኖር ብሎም ማጽዳቱ የሞኝነት እንድይሆንብን፤ በዋናው አእምሮ (ሀርድ ድራይቭ) ከጀርባ ተሰውሮ እንደሚኖር መዘንጋት በፍጹም አይኖርብንም። በተለይ እውቀቱ ያላቸው ወይም የጥበቡ ባለሙያዎች በቀላሉ ሊገልጡት ይችላሉና!

በልጅነት ወይም በወጣት አእምሮ በማንኛውም የብዙዋን መገናኛ በገሀድ የሚለቀቅ ሁሉ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቁሟት እንደዚሁም ወደ ሥራ ዐለም ለመግባት እንከን ሲሆን ለመመልከት በቅተናል። እንደዚሁም ሆነ ብለው ሌላውን በሚተናኮሉ (ለሳይበር ቡሊ) ተጋልጠው እስከ ሕይወታቸውን ማጣት (ለሞት) የበቁትን ወይንም የጤና ችግር የውደቁትን ታዳጊዎችን መዘንጋት የለባቸውም። የእለት እለት እንቅስቃሴቸውንም በነዚህ መገናኛዎች (በሶሻል ኔት ወርክ) የሚለጥፉም እስከ መኖሪያ ቤታቸው መመዝበርና ሌላም ወንጀል የደረሰባቸው እንዳሉ መታወቅ እንዳለበት ማስገንዘብ እንወዳለን።

የራስን ማንነት መሰረቅ (አይደንትቲ ስርቆት) ሰለባ ከመሆን ባሻገር ብዙ በገንዘብና በቁሳቁስ የወንጀል ሰለባ የተዳረጉት አስፈላጊውን ቁጥጥር ችላ በማለት ወይንም ባለማውቅ ስልሆነ ይህንኑም በየጊዜው እያነሱ ከቤተሰብ ጋር መወያየትና የተለያዩ ድኅረ ገጾችን ና ጥሁፎችን ማገላበጥ ጠቃሚ ነው።

ሌላው ማንኛውም  ጥሁፍ የምናትመው ማተሚያችን (ፕሪንተር) አይነትና መለያ ቁጥር ሁሉ ሳይቀር በታተመው ወረቀት ላይ (ወተር ማርክ) እንዳለው ማወቅ አለብን። ይኽ በዐይን የማይታይ ዱካ ነውና ከላይ እንደሰነዘርነው የማን እንደሆነ (ትሬስ) ለማወቅ በቀላሉ ማን እንደገዛው ብቻ ስይሆን በጥሬ ብር፣ በካርድ ወይንስ በብድር እንደገዛው ጭምር መረጃውን ማግኘት አይገድም።  ስለዚህም ማንኛውም በኤሌክትሮኒስ የሚዘገቡ ሁሉ ምንጫቸውም በቀላሉ እንደማይደርቅ ግንዛቤ ከጨበጥን ምንግዜም የመግቢያ ስማችንን ሆነ የሚስጥር መግቢያችን የሆኑትን ከኮምፒውተር ውጪ በሚገባ ቦታ መዝግቦ ማስቅመጥና ሚስጥሩነቱን መጠበቅ ተገቢ ነው። ይህንኑ ከማንም ሰው ሰውሮና ደብቆ መያዝ ያስፈልጋል፣ በቀላሉ ልናስታውሳቸው የሚገቡ ወይንም በአእምሯችን በቀላሉ የሚቀርጹና ለሌሎች ለመላ ምት የማይመች መሆን ይኖርበታል። አንዳንዶች የሶሻል ቁጥራቸውን፣ የትውልድ ቀኖቻቸውን፣ የቤተሰቦቻቸውን ወይም የቤት ውስጥ የእንስሳዎቻቸውን ስሞችና የመሳሰሉትን በቀላሉ የቀረቡዋቸው መላ የሚመቱበትን ይጠቀማሉና፤ አዲስ በምንከፍተው ማንኛውም አገልግሎት ሰጪ  ገጾች ማንነታችንን እንድንሞላ የሚጠይቁትን ገጾች በሚገባ ማስተዋልን ይጠይቃል።
እውነተኛ መረጃ አትስጡ ለማለት ሳይሆን ለማንና ለምን አላማ እንደምናደርገው ማወቅ በጣሙን ጥንቃቄን ይጠይቃል። ከዚህም ውጭ በግል በመሰረትናቸው የመገናኛ ምንጮችና በህዝብ መገልገያ በሆኑ አስተናጋጅ አውታሮች የምናስተላልፋቸውን ሁሉ መመርመር ይሻል።

በመጨረሻም ከአገልግሎት የምናሰናብታቸውን መጠቀሚያዎቻችንን በሚገባ ጠንቅቀን በውስጡ መረጃ (ዳታ) ይኖሩበት የሚችሉና የምንጠጠርባቸውን (ችፕስ) በሙሉ አውጠን ማጠናቀቃችንን ካወቅን በኃላ ቅሪት አካሉን በሚገባ ወደ (ሪሳይክል) ማስተናበሪያ ማስረከብ ሲሆን በእጃችን የቀረውን በጥንቃቄ ማስቀመጥ ወይንም ጥቅም ላይ እንዳይውል ማኮላሸት ተገቢ ነው።

ይኽንን በዚህ ቋጭተን እነ ተኩላው በከፈቱት ገጽ ያገኘነውን ለሚካኤል ሰይፍ ወኪል ላቀረብነው መጠይቅና ከናንተም ለደረሱን መልስ ለማግኘት ሞክረናል። እንዳገኘነው ከሆነ በተፈራ ወርቅ የሚመራውና በገጹ የለጠፈውን ቡድን ያነጋገረ እንደሌለና ከቦርዱ ጋር የተያያዘ ያውጡት ከእውነት የራቀና ውዥንብር የሞላበት ነው። ቀደም ሲልም ሆነ አሁንም እንቅስቃሴዎች ሊኖሩ ይችላሉ። እኛ እንደምናውቀው ከሆነና የዳመራው ዕለት አባታችን እንደአስተማሩን ስናገናዝብ የተገለጠልን፣ እነሱ የያዙት መስቀል የነዝያን ሁለት አማጺያን ወንበዴዎች ከጌታ ጎን የተሰቀሉበትን እንጂ የጌታችንና የመድሀኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን መስቀል አይደለም። ይህም ስራቸውን ሁሉም ምዕመን ተረድቶታል። እኛ ቀድሞ ልናነጋግራቸው ሞክረን ክሱን ለማቆም የሰጡት ምላሽ አባላት የመረጣቸውን አስተዳዳሪዎችን ለማውረድና ያለውን ሥርዐት ለመናድ እንጂ ለዘለቄታዊ ሰላም ፈላጊዎች አይደሉም። እነሱ ዛሬ ሊነዱ የተነሱት ሥርዐት አልበኝነትና ኢክርስቲያናዊነት ዛሬ ካልቆመ እነሱም ውንበር ሲይዙ ተመልሶ መጪና ሰይጣናዊ ጎዳና ነው ። ቤተ ክርስትያናችንም ሆነ ሥርዐቱ ለነሱ ተብሎ ለድርድር አይቀርብም።እያነጋገርናቸው ነው ያሉትንም  አዛውንቶች የምንውዳቸውና የምናከብራቸው ቢሆንም ከነዚህ ወገኖች ጋር ምንም አይነት ውይይት ቢያደርጉም ምንም አይነት ድርድር ውስጥ መግባት አያስፈልግም። ቦርዱም ማንንም አባል አላነጋግርም ያለበት ስፍራና ቀንም የለም። ቤቱ ቤተ እግዚሀብሔርና የሰላም እንጅ የአማጺያንና የኢክርስትያናት አይደለም። አባል ያልሆኑትን ስለ ቤተክርስትያናችን የውስጥ ጉዳይ አንወያይም። የከሰሱም ቢኖሩ ክሳቸውን ሳይዘጉ ምንም አይነት ውይይት ከፍርድ ስርዐት ውጭ አናደርግም የሚል ሲሆን፤ እኛም የሚካኤል ሰይፍ አባላትም ከየአቅጣጫው ያለውን እንቅስቃሴ በሚገባ የምንከታተል ሲሆን ማንኛውንም እውነተኝና ቀጥተኛ ችግር አስወጋጅ የሆነውን ፣ የቤተክርስትያናችንን ህልውና ከሁሉም በላይ ቅድሚያ የሰጠነው መሆኑንና የእነዚህ ጥቂት ግለሰቦች ህከትና እብጠት መስመር እንዲይዝ በጸሎት ሳይቀር ዝወትር የምናከናውነው ነው ። ባለፈው እናንተ እንደጣፋችሁት ወደ ምንጩ  ወደ ዕውንተኛው መንገድ  ወደ ቤታችንና ወደ ቤታችሁ በንስሀ እንቀላቀል ነው የምንል። የሀሰትና የጭፍንነት መንገድ ይጥፋ ነው የምንል ሲል የቡድኑ ተውካይ አስረድቶናል። የነዚያም ወገኖች ያላቸውን ምላሽ ቢልኩልን በደስታ እናወጣዋለን?


እርሶስ ምን ይላሉ?

Monday, September 27, 2010

ካለፈው የቀጠለ፣

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና! ማሳሰቢያ፡


ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።




እንኳን ለብርሀነ መስቀሉ በሰላምና በአንድነት ሁላችንም አደረሰን። የመስቀሉን ምስጢር ለተረዱት ሁሉና እውነተኛውን መስቀል ያገኙት መስቀሉ ወደ ቀናውና እውነተኛው መንገድ ሲመራቸው ፣ሌሎችን ግን አውቀውም ሆነ በግድፈት የተሳሳተውንየማይፈውሰውንና ኢክርስትያናዊ የሆነውን፤ የእነዚያን የሁለቱን ህግ አፍራሽና ከጊታችን ከቤዛችን የአለም መድሀኒት ጎን የተሰቀሉበትን መስቀል ተሸክመው  በደሙ የዋጃትን ቤተ ክርስትያን ከሚተናኮሉ ይጠብቀን።


ካለፈው የቀጠለ፣


ወደ ጀመርነው ስንቀጥል፤ እኛም ሆነ ልጆቻችን ከሀይማኖታችን ጋር ያላችውን ግንኙነት ከብዙ በጥቂቱ ለመዳሰስ እንደሚቀጥለው እንሞክራል።

በዚሁ የምዕራቡ ሀገር የተወለዱ ወይንም ያደጉ ወጣቶቻችን ከቤተክርስትያን አካባቢ ለምን አይታዩም? እነርሱስ የቤተክርስትያናችን ቀጣይነት ይረከባሉን? በማለት መንደርደሪያ ብናደርግ ወዴት ያለ ግምገማ ያደርሰናል?

የዛሬዎቹ ወጣቶች እዚሁ ተወልደው፣ እንደ ስርዐታችን በክርስትና ተጠምቀው አልያም እዚሁ አድገው፤ ተገደውም ሆነ ወደው  በእለተ ቅዳሴ ቁርባን ሲቀበሉ ለምስክርነት በቅተናል።የቀደሙት ወዴት አሉ? ያደጉበትንም ቤተ ክርስትያን የሸሹ ለምን ሸሹ? የአሁኖቹስ የነሱን ዱካ ይከተሉ ይሆን? ብለን ብንጠይቅ ፣ የመጀመሪያ ከቤተ ክርስትያናችን ለልጆቻችን እንደሚስማማ ሆኖ አለመቅረቡ ሲሆን ሌላው ምክንያት የኛው የወላጆች ቸግርን አገናዝበን ለመመልከት እድሉን ተጠቅመንብበት ቢሆን ለዚሁም ቀና አቀራረብ ብናደርግ ከዚህ ወቅታዊ ጥያቄ በልገባን ነበር። ግራ አልንም ቀኝ ከሀላፊነቱ ተጠያቂነት ወዴትም ማፈግፈግ አንችልም። ምናልባትም የመረጥናቸው አስተዳደር ኮሚቴዎች ድክመት ብለንም ልንቀባ መሞከርም ፍጹም ስህተት ነው። ተመራጩም ሆነ መራጩ  ሌላውንም ምዕመን ጨምሮ አንድ ወጥ የሆነ አቀራረብን መፍጠር የግድ ነውና መንፈሳዊ አገልግሎት የሚሰጡትም አባቶች የነባራዊ ሁኔታን ተገንዝበው  እቅዱ  እንዲጣጣም  የስኬታማነት ሚና ይጠበቅባቸዋል።እንደ ትውልድ አገራችን የመሰለ ቀጥተኛነት ያለው  ግልባጭ (ኮፒ) ኑሮ እንደማንኖር ሁሉ ለተተኪው ትውልጃችን እንደ ሀገሩ ነባራዊ የሚጣጣም አቀራረብ በማድረግ እየጠፉ ያሉትን ወጣቶቻችንን የመቅረብና አስተምሮ ማመቻቸት የወቅቱ ግዴታ በጫንቃችን የተሸከምን መሆኑን ከሁሉም በላይ የመተግበር ኃላፊነታችንን መውጣት ግዴታችን መሆኑን ልናናስገነዝብ እንሻለን።

ዳላስ በኖርንበትም ሆነ እድሉን አጋጥሞን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታይ የሆኑ ቤተ ክርስትያን ባሉበት ከተማዎች በቆየንበት ወቅት የግላችን የሆነ ጥናቶችን ወስደን ነበር።በህጻንነታቸው ድቁናን ወስደው የቀጠሉበት በአሀዝ ማስቀመጥ ባንደፍርም አብዛኞቹ ከቀሳውስቱ ቤተሰቦች ውስጥ ይገኙበታል። በተረፈ ከምዕመናኑ ልጆች ያገኘነውን አሀዝ አለ ብለን ለማለት ከኛ የተሻለና የተሟላ ጥናትን ይጠይቃል።

በሌላ በኩል ወጣቶቹን በማነጋግር ያገኘው  ውጤት ደግሞ ልብ የሚነካ ቅሬታቸውን ነበር።
እንደ ምሳሌ ለመጥቀስ ካስፈለገ፤ ወላጆቻችን ቀዳሚትን ይሰራሉ። እለተ ሰንበትን በማለዳ ቀስቅሰውን ቤተ ክርስትያን ይወስዱናል እንደደረስንም በማይገባን ቋንቋ ቅዳሴ ተብለን እንቅልፋችንን ሳንጠግብ ቁመን እናረፍዳለን፣ ቁረቡ እንባላለን፣ ምግብ ሳንበላ አናረፍዳለን፣ ከዛም  ዳቦ ቀምሰን ወደ ቤታችን ወይም ማህበር ብለው ወይም ድግስ ይወስዱናል፤ እነሱ ብቻ ራሳቸውን ያስደስታሉ፣ ቀኑን በዛ አሳልፈን ለሚቀጥለው የትምህርት ቀን ይጀመራል፤ ከወላጆቻችን ጋር የምናሳለፈው የሳምንት መጨረሻ መራራ ነው፣ የትምህርት ቤት ጓደኞቻችን ምን አድርገው እንዳሳለፉ ሲነግሩን እኛ ግን የተለየ ስሜት ነው የሚያድርብን ስለዚህም ዕድሜያችን ሲደርስና ማመዛዘን ስንጀምር ከነሱ ጋር ሰንበት ላለማክበር ሁኔታዎች ያስገድዱናል በዚያው ጨርሰን እንቀራለን።

ሌሎቹ ደግሞ በኛ እድሜ እንደምንኖርበት ህርገር የሚያስተካከል እኛ በሚገባንና ሊጣጣም በሚችል መልክ ቤተ ክርስትያኗ ያዘጋጀችልንትምህርትም ሆነ አስተማሪዎች የሏትም ፤ ወላጆቻችንን ግዴታ ብቻ መወጣት በእድሜአችን ግድ ስለሆነብን እንጂ የነሱን ህይወት ያሳለፉበትን በግዴታ(ረፕሊካ) እንድንደግም አሊያም የኔ ልጅ ከነቶኔ ልጆች አያንስም በሚል የትምክህት ዘይቤ ስለሆነ የልጅነት ዕድሜያችንን ስለቀሙንናስለገፈፉን ፊታችንን አዙረናል ያሉንን ተገንዝበናል። ሊሎችም በጓደኞቻቸው ተጋብዘው በሄዱበት የሌላ ክርስትና ዕምነት ተማርክው የራሳቸውን የጠሉና ወይንም ወደ ባዕዱ የገቡትንም አይተናል። የናንተንም የሜይ ፪ቱን ብጥብጥ የተመለከቱ ወይንም የሰሙ  አዝነውም ሆነ አፍረው ፤ በተለይም በትምህርት ወይንም በስራ ላይ ያሉትም ወጣቶች በሚቀርብላቸው ጥያቄ እንዲ ለዩ ምክንያት ያረጉትንም አግኝተናል።እድሜቸው የሚጠይቀውን የተቃራኒ ጾታ ጓደኝነት እንዳይኖራቸው የስጋ ዝምድና የሌላቸውንም ሁሉ ዘመድህ ወይንም ዘመድሽ እያልን ስለምንነግራቸው በዚያው አድገው ሲደርሱ በዚያው ይጠፋሉ።ሌላም ብዙና ከዚህም በአሀዝ የሚዘረዘሩ ነጥቦች ይኖራሉ።

እንግዲህ ወላጆች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ ምዕመናንና የነዚሁ የእድሜ ክልል ውስጥ ያሉና ከቤተክርስትያን ውስጥ የቀሩትን ወጣቶቻችን የጨምረ አንድ ወጥ ያለው አቀራረብ የሚወስድ ጥናትና ጉባኤን ማካሄድ የግድ ነው። ቤተክርስትያኗን አታስተምርም ብለን መናገር አንችልም። ነገር ግን ለምዕራቡ ሀገር ለሚኖሩት ተተኪዎቻችንከስር ጀምሮ እስከ አዋቂ እንደ እድሜው የሚስማማ አቀራረብ መንደፉ በተለይም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነትና ሥርዐትን በተመለከተ የአባቶች መልካም ፈቃድና ብቃትን የሚጠይቅ በመሆኑእነሱኑ መማጸን የግድ ነው። ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከምዕመናንም ሆነከአክራሪ አባቶች የከፋ ነቀፌታን እክል ሊገጥመው ስለሚችል ጥበብ የተሞላበት አቅርቦት እጅጉን ወሳኝ ነው። እንደ ቤተ ክርስትያኖቻችን አሀዝ ብዛት ቤተክርስትያኖቹ ውስን አገልግሎት ብቻ ሲሰጡ ነው የሚገኙት። ተከታዮቹ ወይንም ምዕመኑ ባጠቃላይ የኢትዮጵያ ተወላጆች ወይም ዘር ያላቸው ብቻ ናቸው ብለን አፋችንን ሞለተን በእርገጠኛነት ለመጥቀስ የሚገፋፉን ሂደቶች አያሌዎች ናቸው። ባለበት ከቀጠለም እድሜና የምዕመናኑ ቁጥር ውስን ሆኖ እንዳይቀጭ  እያሳሰበን ይገኛል። እንደምናየው ከሆነበአንድ ከተማ ከአንድ ቁጥር በላይ በተከፈቱ ቤተክርስትናት አንዱ የሌላውን ምዕመን ወደእርሱ ለማምጣት እንጂ ሀይማኖት የሌላቸውን ወይንም የሌላ እምነት ተከታዮችን ብሎም የኢትዮጵያ የዘር ሀረግ የሌላቸውን ወደ እምነቱ እንዲመጡ  የማድረጉ እንቅስቃሴ ወይንም ማስፋፋቱ ላይ አይታዩም። ለዚሁም የሚስማማ ጥራትና ብቃት ያለው አቀራረብ ይጎላቸዋልና ለተተኪ ትውልዱ እንደዚሁ መቀረጽ ያለበት ነው።

ይኽንኑ የእምነቱን ቀጣይነት በተመለከተ በቂ ጥናቶችን በሰፊው ያካተተ መርሀ ግብር መንደፍ ወርዶ ያለውንና የከበበውን ጉም ሊያጠፋ ባይሆን ሊቀንስ የምያስችልና ባስቸኳይ የሚተገበር መሆን ይገባዋል። የቤተክርስትያኖቹን አመራር  የጨበጠውም አካል ይህንን ለመተግበርና ለማመቻቸት ወቅቱ ዛሬ መሆኑን የመገንዘብ ግዴታቸው መሆኑንእናሳስባለን። እኛ ለህይማኖታችን ቀጣይነት ስንቆም በሌላ በኩል ደግሞ አንድ ሀይማኖትና ዕምነት አለን ብለን ራሳችንንየምናስቀምጥ ደግሞ ፈሪያ እግዚሀብሔር መንፈስ በውስጣችን ሰርጾ፣ የተለያየንና የተከፋን፤በመካከላችን ያለውን ልዩነትና ፍልሚያ ከራሳችን አውጥተን ልዩነታችንን አጥፍተንና ያሉብንን የግል ፍላጎታችንን አስወግደንይቅር ለእግዚሀብሔር ተባብለን ቤተክርስትያናችንን ጠብቀንለተተኪዎቻችን የማሳለፍ ግዴታችንን ዛሬውኑ በመጀመር  መተግበር የወቅቱ አንገብጋቢ ነው።


እርሶስ ምንይላሉ?

Friday, September 24, 2010

ከአብራካችን ለወጡት ልጆቻችን ምን እየተውን ነን?

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!


 ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።



ከአብራካችን ለወጡት ልጆቻችን ምን እየተውን ነን?

ዛሬም እንደ ድሮው ፣ ዘመን ከዘመን ሲለወጥ፣ የአምሮ እድገትና ብስለት ያልታደሉ፤ በአዲሱም አመት አዲስ መንፈስና አስተሳሰብ የጎደላቸው፤ ዘንድሮም ዝጎ በኖረ አእምሯአቸው የሚተፋውን የገጻቸውን ጥሑፍ ከጎናቸው እየተለዩ የሚገኙትን ጆሮ ቆራጭ መጣባችሁ በማለት ያምናውን ለዘንድሮ ማስፈራሪያ ሊያደርጉ ይዳክራሉ። ካለፈው ተምሮና ተጸጽቶ ማንነታቸውን ሲያውቅና እውነተኛውን መንገድ ሲመርጥ፣ እንዴት ትላንት ሲተቹህ ከነበሩ ጋር ተስማማህ? እየከዳኸን ነውን? አምና ባደባባይ ላሉህ እውነት እንደው ይቅርታ እንኳ ሳይሉህ? የሚለውን ገጻቸውን አይተን እናንተንም እውነቱ ይገለጽላቹ፣ ይሳካ ዘንድም እንጸልይላችኃለን ነው የምንል። የተወደዳችሁና የገጻችን አንባቢዎች እንዴት አላችሁልን? ፈጣሪ ሁላችንን በመንፈሱ ይምራን ይጠብቀን! የራቁንንም መክሮና አስተምሮ ወደእውነተኛው መንፈስ ይቀላቅላቸው ! አሜን።

ወደ እርዕሳችን ስንመለስ፤ ብዙዎቻችን ወደንም ሆነ ተገደን አሊያም ምርጫ በማጣት ከወላጆቻችን ወይም ካሳደጉን ፈቃድ ሆኖ የቀለም ትምህርት የጀመርነው ከቄስ ትምህርት ቤት ነበር። ፊደል ቆጥረን ወንጌል አንበን ዳዊት ደግመን የተመርጡ ወደ ድቁና ብለውም ወደ ከፍ ያለው መንፈሳዊ አገልግሎት ሌላውም ወደ ዘመናዊ ትምህርት የቀጠሉበትን ስናወሳ፤ የኢትዮጵያ ተዋህዶ ኦርቶዶክስ እምነትን አብረን ይዘነው አድገናል። ከዚሁ ጋር እንደ ኑሯችንና አመለካከታችን ዕምነቱን መተግበሩ ላይ በተለያየ ደረጃ ላይ ተቀምጠናል። አንዱ ሲያጠብቀው ሌላው ሲያላላው ክዚህ ደርሰናል። በተለይም በምዕራቡ ዐለም የምንኖር ደግሞ ባለፈው ፴ አመት ውስጥ በተለያየ ምክንያቶች ከአገር ከወጣን ጀምሮ ያለብንን መንፈሳዊ ፍላጎታችንን ለማርካትና የፖለቲካውን እንቅስቃሴ ለሚያኬሄዱትም የጥሩ መገናኛ አጋዥ መድረክ በመክፈቱ ወቅታዊ ድጋፍን አስመዝግቦ በብዛት ኢትዮጵያዊያን በሰፈሩበት ትላልቅ ከተሞች መመስረትን ጀመሩ። በ፩፱፻፺ዎቹ ውስጥ በሀገር ቤቱ የመንግሥት ለውጥ በኃላ በአንዳንድ ቤተ ክርስትያኖች ውስጥ በዘርና በፖለቲካ  ብሎም ምዝበራን በተመለከተ አንዳንድ ክስተቶች ቢፈጠሩም ሀይማኖቱ ቀጣይነቱን እንዲሁም እምነቱ ያላቸው አዲስ መጤ ቁጥር ከመጨመሩ ጋር ተያይዞ የቤተ ክርስትያን ቁጥሩ እየበዛ መጥቷል። በተለይም ቀሳውስቱ ቤተ ክርስትያኑን ለመቆጣጠር በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ለአሃዙ ማደግ አስተውጾ አድርጓል።

እዚህ ላይ መዝለል የማንችለው ራሱን ማኅበረ ቅዱሳን እያለ የሚጠራው የቤተ ክርስትያናችን በቀል የሆነው ቡድን በአንዳንድ ከተሞች የናንተን ዳላስ ሚካኤልን ጨምሮ ፖለቲካንና ስራውን ከቤተ ክርስትያን አካባቢ አጥፍቶታል ወይንም እንዲቀንስ ከፍተኛን አስተዋጾ አበርክቷል። በሌላ በኩል ይኸው ድርጅት ፖለቲከኞችን አመለካከት ቢያስለውጥም በአንጻሩ ወደ ቤተ ክርስትያኖች አመራርና ካዝና ምዝበራ ወይንም አክራሪ በሆነ ደረጃ ችግሮችን እየከሰተ ይገኛል። ልጆቻቸውንም ወደዚሁ ከራራ አስተሳሰብ እያስገቧቸው ይገኛል።

ሌላው መከፋፈልን በምዕራቡ አህጉር ያመጣው የአባቶች አልመግባባትና መለያየት ነው። ይኽ አደገኛ አዝማሚያ በቅርቡ ካልተቋጨ ቤተ ክርስትያኗን ወደ መከፋፈል ያደርሳል ብለን እንሰጋለን። ለምሳሌ ለማገናዘቢያ ብቻ እንጂ እንደማወዳደር እንዳይወሰድብን የምንጠቅሰው በሱኒና በሻይት የእስልምና ተከታዮች ጉዳይን ነው። እኛ አንድ ሀይማኖትና አንድ እምነት ተከታዮች የሆንንና በሰለጠነው ዓለም የምንኖር በሁለት ሲኖዶስ ለምን እንለያያለን?  ቤተ ክርስትያን ስናቋቁም እርስ በራሳችን ተረዳድተን ለብቻችን አልነበረምን? ሀገር ቤት የነበረው ሲኖዶስ ምንስ የረዳን ነበር? ቀሳውስትስ ለማምጣት ምን አይነት ችግር ነበረብን? ዛሬ ግን ይህንን ጽዋ የቀመሱም ሆነ ያልቀመሱ፣ ዛሬ የተመቻቹ ወይንም የተለየ ፍላጎት ያደረባቸው ግለሰቦች ያለ አባት ቤተ ክርስትያን እንዴት ይከፈታል ይሉናል። ጥያቄውን ብንቀበልም ባለው ያባቶች ልዩነት ከየትኛውም ላለመሆን የመረጡትን ለምን ያዋክቧቸውል? ለመሆኑ ትላንት እንዴት አብረው ያለ ሲኖዶስ እውቅና አብረውን ቤተ ክርስትያን ከፈቱ? ትላንት ያለ ስልጣናቸው ከተሰጣቸው ሀላፊነት እንደዚሁም አስተዳደር ረግጠው (በስደት ስም) የወጡ አባቶች አልነበሩምን ከከተማ ወደ ከተማ እየተዘዋወሩ የምዕራቡን ሀገር ነወሪ ለሆኑት የእምነቱ ተከታዮች ለሚመሰርቱት ቤተ ክርስትያን የሚባርኩ? ሕጉንና ስረአቱን አፍርሰው ከተመደቡበት ሀገር ለቀውና የፓለቲካ ስደተኛ መሆን ምንድን ነው? ሲሆን ወደ ገዳም ገብቶ የሚያስፈልገውን መወጣትን እንዴት አጡት? እንደ አ. አ. የ፹ ዎቹ ስደተኛ በ፺ኛው ዓ.ም.   ተራ ደርሷቸው  የልዑል ፈጣሪም ዝምታ ይሁን ፈቃድ አመራሩን የያዙትም ቢሆኑ የነገሩ ጀማሪያት የሚደመሩ መሆናቸውን እንዴት መገንዘብ ይሳናል?

እኛ ተራ የእምነቱ ተከታዮች ብቻ ሳይሆን ያለእኛ ወይንም ተከታይ የሌለው እምነት እድሜው እንደሚያጥር ሁሉ፤ አባቶችም ወደ አባትነት ለመብቃት ብቻ ሳይሆን ወደዚያ የመሰለ መንፈሳዊ አገልግሎት መግባት በርሱ የመመረጥና የመቀባትን እድል እንደሆነና ብጹህ ተብሎ ለመጠራት ይቅርና የቄስን ቅስናውንም እንዳይጠይቅ ሲነገረን እንዳልኖርን፤ ዛሬ የምን ቁጣ ነው በላያችን የተሸከምነው? የበጉ እረኛ የተመረጡ ብለን ስንቀበላቸው ፣ ከነሱ ብዙ መማር ሲገባን፣ እነሱን ሀዘናችንን አስወጋጅ፣ለቅሶዎቻችንን ኣባሽ ፣ ጥፋታችንንም ሆነ የመንፈስ መታወካችንን ይዘን ወደ ነሱ ስንጠጋ ሀኪሞቻችን፣ ባጠቃላይ የስጋና የመንፈስ ሕይወታችንን የሚያስተካክሉ ብለን የተቀበልናቸው፣ እኛ እነርሱንም ፈጣሪንም አክብረንና ፈርተን የቤተክርስትያናችን ሁኔታ እያሳሰበን የነሱ አለመግባባት ለኛም እየተረፈን በመካከላችን አለመጣጣምን እያጎላ መጥቷል። አንዳንዶችንም እምነትና አመለካከትን እንዲለውጡ እስከማድረግ በቅቷልና ይህንን የጀመረንን በምዕራቡ ሀገር የምንገኝ የእምነቱ ተከታዮች የሆንን በጥልቅ የማጤንና የጋራ የሆነ አንድዮሽ መንገድ ለመፍጠር ልዩነታችንን በቀና መንፈስ መፍታት አማራጭ የሌለው የወቅቱ ጥያቄ አድርገን በመውሰድ ዛሬውኑ እልባት ማግኘት የሚገባን ወቅታዊ ጥያቄ ነው።

ማሳሰቢያ ፣- የዚሁ አርዕስት ቀጣይ በሚቀጥለው ጥሁፋችን ይጠብቁ።

ይድረስ ለዳላስ ኢ.ኦ.ቲ.ሲ.

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!

ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።

የሚለጥቀውን በመልዕክት መቀቢያችን የተውልን ታዳሚያችን እንዳለ ለጥፈነዋል፤



ይድረስ ለ ዳላሰ ኢ. ኦ. ቲ. ሲ ደራሲ፤ ይህቸን በሚካኤል በቤተክርስቲያናቸን ዉስጥ የሚደረገውን ተንኮል በማየት የተሰማኝንና የተገነዘብኳቸውን አንዳንድ ዘገባዎች ከዚህ ከ (Comment) ቦታ አውጥተው ወደ በዋናው መድረክ ላይ ያስገቡልኝ ዘንድ በትህትና እጠይቃለሁ። እምን ጊዜ ደረስን !!!! ስምንተኛው ሽህ የሚባለው ጊዜ እየደረሰ ይሆን ??? ክርስቲያን ወደ ቤተክርስቲያን የሚሄደው ለመጸለይ ! የመንፈሳዊ ትምህርት ለመማር ! ጥፋት ሰርቶም እንደሆነ ንስሃ ለመግባት !.... ነበር ። በአሁኑ ጊዜ ግን የምናየው ብዙዎቹ የሚመጡት ለመጸለይ ስይሆን፤ ዛሬ ቤተክርስቲያናችን ውስጥ ምን ጥፋት ይሰራ ያሆን? ምን ይነገር ይሆን? ምን ይባል ይሆን? እነማን ይመጡ ይሆን? ሄደን እናደናግር እንጅ በልባችን ያለውን ቂምና በቀል “ይቀር በለን እኛም የበደሉንን ይቀር እንል ዘንድ” የሚለውን ጸሎት ልንጸልይ እንዳልሆነ በዛኛው እሁድ (August 29,2010) የነበረው የህዝብ ብዛት ያሳይ ነበር። ከነበሩት አዛውንት መካከል! ሁለተኛ እዚህ ቤተክርስቲያን እልደርስም ያሉት! ቤተክርስቲያን የከሰሱት! በሰላም ቀን ቤተክርስቲያን ይማይሄዱ ግር ግር አለ ሲባል ብቻ ካሜራቸውን ይዘው ብቅ የሚሉ! እነሱ የኛ ነው የሚሉት ቄስ ከሌለ ቀሳውስት ሲያስተምሩም ሆነ ሃሌ ሉያ ሲል እጆሮዋቸው ውስጥ ስፒከር ወትፈው መንፈሳዊ ያልሆነ መጽሃፍ የሚያነቡና ቄስ የሚዘልፉ! በሃሰት ፍርድ ሸንጎ ላይ ቀርበው በመሃላ የሚዋሹ! ባይ ሎው ለመለውጥ ብዙ ጊዜ አባክነን፤ እንዳንለውጥም ተከለከልን በዚህ ምክንያት ቤተክርስቲያኑን ማፍረስ አለብን ብለው የተነሱ ወንዶችና ሲቶች! የሸማቸውን ዘርፍ በግራና በቀኝ ትካሻቸው የለበሱ ተሳዳቢወችና ዘላፊውች! ቤተመቅደሱን ሞልተውት ማየት ትልቅ ትይንት እንደነበረ የማይካድ ሃቅ ነበር። ድሮ አገራቸን በነበርንበት ወቅት ሃይማኖትህ ምንድነው? ሲባል! የምንሰማው እስላም ውይም ክርስቲያን ነኝ ይሚለውን መልስ ለመጠበቅ እንደነበረ ሁላችንም የምናውቀው ጥያቄ ነበር። ክርስቲያን ነኝ ካለ ጥያቄው ያቆም ነበር በዚህ በዳላስ አካባቢ ግን ክርስቲያንነት ሌላ ጥያቄ ይዞ እንደቀረበ የምናየው ነው። ሲኖዶስ እንደ ሃይማኖት ተቆጥሮ የየትኛው ሲኖዶስ ክርስቲያን ነህ ወይም ነሽ? መባል ተጀምሯል። በበኩሉም አሜሪካ ያለ ክርስቲያን ቄስ ልጆችን ድቁና ከሰጠ እንደ ትልቅ ሃጢአት ተቆጥሮ በየ ብሎጉና በአፍ ድቁና በተቀበሉት ልጆች ላይ ውርጅብኝ መከናውኑ ይሚያስገርም አስጠያፊ ድርጊት መሆኑን የማያውቅ ምእመን ካሉ ንስሃ ግቡ መባል ይገባል። በመጨረሻው ሰንበቴ ብሎግ እንድተገለጸው የሚካኤልን ቤተክርስቲያን በቦርድና፤ ባስተናጋጅነት ሲያገለግሉ የነበሩት ባልና ሚስት ከኢትዮጵያ መንግስት ይዘው የመጡትን የሚካኤልን ቤተክርስቲያን መውረስ ባይሆንም ማዘጋት ዘዴና ተንኮል ለ ከሳሾችና ተባባሪዎች ለማስተላለፍ እቤታቸው ውስጥ የደረጉትን የማስተባበሪያ ግብዣ! ይሄን ቤተክርስቲያን አዘጋለሁ ትልቅ ቂም አለኝ! በህይዎቴ ለስልጣን ተዎዳድሬ ወድቄ አላውቅም! የሚካኤል ምእመን ግን ሳይመርጠኝ ቀርቶ አዋረዶኛል! የሚሉት ሻለቃ ለጋባዧ የላኩትን ኢማል ሳታነቡት የቀራችሁ ካላችሁ እንደገና አንብቡትና የሚካሄደውን ደባ ሁሉ ተረዱ። በነገራችን ላይ ፍርድ ቤት ቀርቦ በመሃላ ያነሳሁትን ቪዲዮ አልቆራረጥኩም (Edit ) አላደረግሁም ቪድዮ የማነሳው ክልጅነቴ ጀምሮ ነው በማለት የዋሸው ግለሰብ በ ጋርላንድ ፖሊስ የ ኢምግሬሽን አቋሙ እየተጠና መሆኑን ሰምተናል። ባፍ ይጠፉ በለፈለፉ ይባላልና በጥያቄን መልስ ጊዜ ከመዋረዱና ከመታሰሩ በፊት አገሩን ጥሎ ቢጠፋ ይሻለዋል ምንም አይነት ችግር እንዳይደርስበት ስለምንፈልግ ምክራችንን እናስተአልፋለን። የቀዳሐውን ኦሪጂናል ቪዲዎ አቅርብ ሲባል ምን ያቀርብ ይሆን? የለኝም ካለ በሃሰት መሰከርክ ሊባል ነው። ካቀረበ ቪዲዎው ሊፈተሽ ነው። በሁለቱም አቅጣጫ ጥፋት ላይ መውደቁ የማይቀር ስለሆነ ቢያስብበት ይሻላል። በልጅነቱ ኢትዮጵያ በነበረበት ጊዜ አባቱ ወይም ዘመዱ የገዙለት ቪዲዮ ማንሻ ምን የሚባል ነበር ሲባል አላስታውሰውም ሊል ነው ወይም ዋሸሁ? በማንኛውም ኢትዮጵያዊ መጥፎ ነገር እንዳይደርስበት መመኘት አግባብ ስለሆነ ይሄ ምክር ይድረሰው። መረዋ በተባለው ብሎግ “ ይህ ቤተክርስቲያን በአሜሪካ የሚገኙትን ጳጳስ ከተከተለ ደሜ ይፈሳል” የሚለውን አነጋገር አሁን ብቻ ሳይሆን ገና ሲጀመር ጀምሮ “የአሜሪካውን ሲኖዶስ ከተከተለ እንጋደላለን! ያለንን መሳሪያ ቡጢም ቢሆን ይዘን እንቀርባለን” ሲል የነበረውን ማስታወስ ይገባል! ደራሲው በተደጋጋሚ ቤተክርስቲያኑ በኢትዮጵያው ጳጳስ መተዳደር አለበት እያለ መጻፉን የማያውቅ ምእመን ይኖር ይሆን! ለምን ይሆን? ምን አጀንዳ አለው? ቤቱን አሽጦ ኮሚሽን ለማግኘት ይሆን? ወይስ ለጳጳሱ ከሚላከው ከገቢው 20% ለሱ ምናልባት 5%ቱ ቃል ተገብቶለት ይሆን። ሰሞኑን የሚነፍሰው ሌላው የተረመረዘ ዎሬ በማዎቅም ይሁን ባለ ማወቅ የተጻፈው፤ የቦርድ አመራረጥ ዘዴ ሲሆን ቤተክርስቲያንን በነጻ ማገልገል ለተማረና ላውቀ እንጅ ያልተማረ ወይም እንግሊዝኛ በደንብ ያላወቀ አይመረጥ፤ ሊቀ መንበርም አይሁን የሚል የተሳሳተ አስተያየት በዚሁ ብሎግ ማንበቤ አሳዝኖኛል። እነዚህ ግለሰቦች ትቂት ቆይተው ያልተማረ እቤተክርስቲያኑ አይድረስ ይሉ ይሆን ብየ ፈራሁ። ያለነው አሜሪካ ነው ፍርድ ቤት የቀረበ ሁሉ እንግሊዝኛ ካላወቀ አስተርጓሚ ይሰጠዋል። ቤተክርስቲያን የሚያገለግል በታማኝነት በትህተኝነት በመልካም ፈቃድነት እንጅ በመማር ወ ይም ባለመማር አይደለም። በዚሁ አጋጣሚ እንድታውቁት ያህል ያሁኑ ሊቀ መንበር ከማንም ያላነሰ እውቀት ብቻ ሳይሆን ትምህርትም ያለው መሆኑን ተረዱ። ከማንም የበለጠ ትህትና እና አስተያየት እንዳለው ለማሳየት የማይፈልግ የተቆጠበ አገልጋይ ለመሆኑ ማስረጃ አያስፈልገውም። እግዚአብሄር ይቅር ይበላችሁ። የሄን ጽሁፍ በብሎግዎ ካቀረቡልኝ፡ በሚከተለው ጊዜ የአሜሪካውን ሲኖዶስ መከተል ለቤተክርስቲያናችን ጥቅሙንና ጉዳቱን በዝርዘር እጽፋለሁ። እግዚአብሄር ይስጥለኝ። ለሁላችንም መልካም ቀን ይሰጠን ዘንድ አጸልያለሁ!!!! አሜን!.
By Anonymous on ከምንጩ ሁነው ያላገኙትን ከውጪ ይረካሉን? on 9/19/10  እርሶስ ምን ይላሉ?

Friday, September 17, 2010

ከምንጩ ሁነው ያላገኙትን ከውጪ ይረካሉን?

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!


ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።



ከምንጩ ሁነው ያላገኙትን ከውጪ ይረካሉን?

ከብዙ ውጣና ውረድ በኃላ የዘገየው ከባሕር በታች ያለውን የጥልቅ ውቅያኖስ የነዳጅ ሀብት ውጤት ማምረቻ ጉርጓድ ዛሬ ፻፶ ቀናት በላይ ያስቆጠረውንና በሜክሲኮ ጎልፍ የሚገኘው እንደዚሁም እኛንም ከዳላስ የመልቀቂያ ምክንያት የሆነን፤ ይህንኑ ጉርጓድ ለመጨረሻ ጊዜ ለመዝጋት (ለመግደል) ከቀናት ባሻገር በመድረሳችን ተደስተናል። የተወደዳችሁ የገጻችን ተከታታዮች እንደምን ሰነበታችሁ? የምትልኩልንን አስተያየቶችን ይደርሱናል። የምንለጥፋቸው ጥቂቶቹን ብቻ ነበር ነገር ግን አንዳንዱ አስተያየት የግል ፍላጎቶችን ብቻ የሚያንጽባርቁና ያነጣጠሩበትን አላማ እስክንገነዝብ መያዝን እየመረጥን ስለመጣን በዚህ እንደማትከፉብን እርግጠኞች ነን።

ወደ እርዕሳችን ስንመለስ፤ ከምንጩ ሆነው ያረኩትን ወይንም ምንጩን ረግጠው የሄዱትን ለመገንዘብ ስንሞክር የራሳችንን ግምገማ እንዲያስከፋቸው ፈጽመን አንሻም። ምንጩ ደርቆም አያውቅም፣ በጥባጭ ካለ እንደሚሉት ሆነና በጥባጩ ሆነና መንፈሱን ያልለበሰ፣ የበጠበጠውን እንኳን ማጥራት ያቃተው፣ ከፈጣሪ ይሆን መንፈሱን የተገፈፈው? ስልጣኑን ያላበሰው ልዑል እግዚሀብሔር ከሆነ ፤ አደራ የተሰጠውን የእረኛ ሀላፊነት በፈቃዱ ጥሎ፣ እንደርሱ ቢሆን ምንጩንም አድርቆ ፣ ባትሪዬን ጨረስኩኝ ማለት ምንኛ ፈጣሪንመክዳት ይሆን? ምንኛ አሳዛኝና አስለቃሽ ይህን? ከምንጩ ሳሉ ድፍርሳቸውን ችሎ ከልቡ ፈጣሪን አምኖና ተቀብሎ የነበረው ፤ ዛሬ የበርከቱ ትሩፋትን የበዛላቸውና ምንጫቸውን አጥርተው እየጠጡ የሚጠብቁት ምንኛ የተመረጡና የተመሰገኑ ናቸው።

በሌላ በኩል ምንጩን ያደፈረሱት የተጠናወታቸውን መጥፎ ምግባር እርሱ መዳህኒተ ዓለም ያስተምራቸው፣ ለነሱም ልቦና ይስጣቸው እንጂ አሁንም ከምንጩ ማደፍራስ ተግባር አላሰለሱም። ምንጩ እንዲደርቅ ወይንም ከመጀመሪያ በመግቢያችን እንዳሰፈርነው የጥልቅ ውቃያኖሱ የነዳጅ ጉርጓድ እስከመጨረሻው ለማዘጋት በቡድን በመሆን በተለያየ አቅጣጫ ቢዳክሩም፤ እርሱ ራሱ በደሙ የዋጃትን የእነቶኔ ሴራ በየደረጃው እየከሸፈ ተንኮላቸውም እጅጉን እያራቃቸውና እያረከሳቸው ይገኛል። በረከቱንና ሰላሙን ስለነሳቸው በምንጩና በዙሪያው ተሰልፈው ለማደፍረስ የመጨረሻ ምዕራፋቸው ላይ ናቸው። እውነትም መንገድም እኔ ነኝ ያለውንና ምንጩንም ባርኮ ያከበረውን ፈጣሪ ስራ የማን ፍጡር እውቀት፣ ሀብት ወይስ ልብ ነው የሚያሸንፍ? ምንኛ ትዕቢት ያለው ነው በፈጣሪው ላይ የሚጠራራ? እውነትስ ፈጣሪውን ያውቃልን? እውነትስ ከልቡ አምኖ የተጠመቀና ልዑል እግዚሀብሔርን የተቀበለ ነውን? ስንትስ ጌዜ ነው እየወደቀ የሚነሳ? ስንትስ ጌዜ ነው በይቅርታ የሚመለከተው? መቼ ነው ለስራው መጥፎ ተግባርና ምንጩን እያወከ የሚቀጥል? አቤቱ ከቁጣህና ከቅጣትህ ሰውረን ምህረትህን ስጠን።

በዳላሱ የቅዱስ ሚካኤል ደብር ላይ ቦድነው ያሉት ጥቂት ግለሰቦች ከሳሽና አስከሳሽ ብቻ አይደሉም፣ እኛ ካልመራነው (እኔ ከሞትክ ያለችው አህያ) ፣ እግዚሀብሔር የፈቀደውን እንዳስቀመጠ ሁሉ የእርሱን የማንሳት ሀይል የሳቱ፣ እርስ በራሳቸው ተመራርጠውና ተሻሽመው የጠነሰሱት ፣ እሱን ከማስቀደም ይልቅ እራሳቸውን ለግል ፍላጎታቸው ያስቀደሙ፣ የተለያየ ክሶች በተለያየ ጊዜ በቤተ ክርስትያኑ ላይ እንዲከፈቱና በዚያም ባለው ወጪ እንዲዳከም ብሎ እንዲዘጋ ፣ የሀሰት የሰላም ዘንባባ አንግበናል የሚሉና አመራሩን አምባ ገነን ብለው የሚቀቡ፣ እነሱ ተክለው ካሳደጓቸው የቤተ ክርስትያን ከሳሾች ጋር ክሳቸው እልባት ሳያገኝ እንዲነጋገሩ የቆሙ፣ ወዘተ…….. ደጋግመው በገጾቻቸው የሚያወጣቿው በቂ ማስረጃዎች ናቸው። ለምን አርዮስ እንዲለይ ተደረገ ብለን እራሳችንን ጠይቀን ለመረዳት መሻት ይገባናልና ለነዚህም እርሱ ልቦናቸውን ለውጦ መክሮና አስትምሮ ከምንጩ ይመልሳቸው፣ የተትረፈረፈውንም ከምንጩ የሞላውን እውቀትና በረከት ለመሳተፍ ያብቃቸው እንላለን።

በሌላ በኩል ገንዝብና ስልጣን ማምለክ የተያያዙት ከፈጣሪያቸው መራቃቸውን እንዴት ይረዱት ስንል ከነዚሁ ውስጥ ቀዳዳ ዋሾች በቅርቡ ከማን አንሼ ብሎ ለኮሚኒቲው ማእከል ቃል የገባውን ግለሰብ እውነቱን ከሆነቃሉን በአስቸኳይ እንዲፈጽም በዚህ አጋጣሚ ለሚመለከታቸው ስናሳስብ፣ ዋሾን ማመንና ጉም መጨበትን አንድ ነው እንዳያባብል ከመጦቆም ወደ ኃላ አንልም።


እርሶስ ምን ይላሉ?

Tuesday, September 14, 2010

የዳላሱ ቅዱስ ሚካኤል ጥሩ ነገር አይወድለትም ለሚሉ

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!


ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።



የዳላሱ ቅዱስ ሚካኤል ጥሩ ነገር አይወድለትም ለሚሉ

አዲሱን የዘመን መለወጫ ምክንያት በማድረግ በዕለቱ ምሽት አዳራሹ የሞላና የሞቀ የራት ምሽት ቀዳሚት መሰከረም ፩ ቀን አድርጓል። ከህፃናት እስከ አዋቂ የተሳተፉበት በየደረጃው የተዘጋጁት ትርዒቶች ታዳሚውን ያዝናኑና ያስተማሩ መሆናቸውን ከዳላስ የሚካኤል ሰይፍ እየተባለ የሚታወቀው ቡድን ካቀበለን ለመረዳት ችለናል። የተወደዳችሁ የገጻችን አንባቢያን እንደምን አላችሁልን? አዲሱ ዐመት ካለፈው የተሻለ የሰላም፣ የፍቅር፣ የጤንነት፣ የአንድነት ፣ የመቻቻልና የብልፅግና አመት እንዲሆንልን የልዑል እግዚሀብሔር ፈቃድ ይሁንልን። አሜን።

የበግ ለምድ የለበሱ ተኩላዎችም በምሽቱም ሆነ በሚቀጥለው ዕለተ ሰንበት የመጀመሪያው የዘመነ ሉቃስ ጸሎተ ቅዳሴ መቋጫ ላይ እንደ ልማዳቸው ብቅ ብቅ ያሉትና ከበጎቹ የተቀላቀሉትን እረኛው ጠንቅቆ የሚያውቃቸው ማፈሪያና ማዘኛ መሆናቸውን በዲሱም አመት የተጸናወታቸው ጸረ ቤተክርስትያናዊነትና እምነት ይለቃቸው ዘንድ የሁላችንም ጸሎት ነው። ምን ጊዜም ከነሱ በዕውቀትም ሆነ በተግባር ተሽሎ የተገኘ ሁሉ የሚያስፈራቸው እነዚሁ ግለሰቦች መርዝ እንደቀመሰ ውሻ ከመሆን ወደ ትክክለኛ ህሊና ፈጣሪ ይመልሳቸው እንላለን። በገጻችን የአስተያየት መስጫ ላይ ከምንለጥፋቸው ከነዚሁ ግለሰቦች አስተያየት እንደምንገነዘበው በአንድ ወቅት የአሁኑን የደብሩን ለቀ መንበር ላይ የሰጡትን አስተያየት ለምሳሌ ብንጠቅስ፤- ሊቀ መንበሩን ከነሱ ስላልወገነና የነሱን የርኩስ መንፈስ ስለተቃወመ፤ ከነርሱ የተሻለ አመለካከት ያለው ብቻ ሳይሆን በእምነቱም ሆነ ከደብሩ አመሰራረትት ጀምሮ ያበረከተውንና እያበረከተ ያለው አገልግሎት በአሀዝ የማይሰላና በዕውቀትም የማይመዘን ንጹህና ፈሪያ እግዚሀብሔር ያለበት ታላቅ ግለስብ፣ በትዳሩም ሆነ በኑሮው ልዑል ፈጣሪ የፈቀደውን ያላበሰው፤ የቻሉትን ያህል ቢቀቡትም እራሳቸውን ደግመው ዝቅ አደረጉ እንጂ አላማቸው አለመሳካቱን አውቀውታል። ይህ ግለሰብ ከአነስተኞቹና እንደ ተኩላ በመካከላችሁ ከሚሹለኮሎኩና በምግባራቸው ገጻችን ስማቸውን ስንኳ ለመጥቀስ ከምትጸየፋቸው ጋር በምንም መንፈስና ደረጃ ተመሳስሎ የማይመዛዘን መሆኑ የሚታወቅ ነው። ሌላው የተገነዘብነው ከነሱ የተሻለ አእምሮ ብስለትና እውቀት ካለው ጋር ተቀምጦ መስራት የተሳናቸው፣ ግለሰቦች ከቦርድ አመራር የተሰጣቸውን ሀላፊነት ጥለው ከሄዱት ውስጥ በኮሚኒትው የጋራ መረዳጃ የልማት ክፍል ውስጥ መግባትን በአሉታ እናልፈዋለን።

ስለ ኮሚኒቲውም ከነካን አይቀር ብዙ የምንለው አለን። የድርጅቱን መኖርና ለወደፊት በብቁ አመራር ጥሩ ደረጃ ደርሶ ከተመሳሳይ ድርጅቶች ጋር ለመነጻጸር እስኪበቃ ድረስ፣ የቀድሞ አመራሮች ካለችሎታ ወይንም ለግል ጥቅማ ጥቅም ሲሉ አጫጭተውት ነው የሚገኘው። እኛ ዳላስ በቆየንበት ጥቂት ጊዜ ለመዳሰስና ተሳትፎ ለማድረግ በሞከርንበት ወቅትም ሆነ በውይይታችን ከታዘብነው፤ የህብረተሰቡ ተሳትፎ በጣሙን ቢያሳዝነንም ምክንያቶችን ለማወቅ ጠለቅ ያለ በመረጃ የተደገፈ ጥናትን ይጠይቃል። ያለህብረተሰቡ ተሳትፎ ስንል ቢያንስ ሲሶውን ማቀፍና ማሳተፍ ካልቻለ የተፈለገውን አቅም ይዞ እድገትን በህብረተሰቡ ውስጥም ሆነ ከአቻዎች ማህበራት ለማነጻጸር አይቻለም። በመጀመሪያ ጥሩ ተመሪ መሆን ያልቻለ መሪ ሊሆን አይችልም። ፪ኛ/ ከፍተኛ እውቀትና ልምድ በሀገሩ ያካበቱና በተለያየ ከፍተኛ ሀላፊነት ግዳጃቸውን የተወጡና ውጤትንም ያስመዘገቡ። ፫ኛ/ አዲስ ሀሳብን የመቀበልና ሁል ጊዜም ለመማር የተዘጋጀ ፣ ህብረተሰቡን በሚገባ የሚረዳና ሊያስተባብር የሚችል፤ ከሀይማኖትና ከፖለቲካው ከራራ አስተሳሰብ የራቀና ጊዜውንና እውቀቱን ሊሰዋ እንጄ ለግል ጥቅሙ ማካበቻ የማያደርግ አመራርን ማስቀመጥ የግድ ነው። ለምሳሌ ለመጥቀስ የታሰበውን ማዕከል ኮሚቴ አባል ከሆኑት መካከል የብሔራዊ ባንኩ ተቀጣሪና ሌላው ቀደም ሲል በዘይት ክባንያ ውስጥ ተቀጣሪና ለቅዱስ ሚካኤል ደብር እድገትን ካስመዘገቡት ግለሰቦች አንዱ የሆነው ተሳተፎ ማግኘት ውጤት ሊያመጣ ሲችል፤ በአንጻሩ አመራሩ ባጠቃላይ የሰው ሀይል ይጎለዋል። የግድ ያሉት አመራሮች አእምሮቻቸውን በመክፈትና ወንበራቸውን ለማስረከብ በሩን እስከከፈቱ በዳላስ አካባቢ በቂ ቁጥር ያለውና ለቦታው ብቃት ያላቸው ኢትዮጵያውን፣ የኢትዮጵያ ተወላጅና ወዳጆች ሞልተዋል። አሁን ያለውም አመራር ከልብ የገንዘብና የሰው ሀይል በመጠቀም የአባላቱን ቁጥር ማሳደግ ግዴታው ሲሆን ፤ የራዲዮን አገልግሎቱን በሚገባ ተቆጣጥሮ ሊጠቀምበት ይገባል እንላለን።

ወደ እርዕሳችን ስንመለስ ደግሞ የቅዱስ ሚካኤል ደብር ደግሞ ደጋግሞ ልዑል እግዚሀብሔር እየባረከው ይገኛል። ለዚህም ሁላችንም ምስክሮች ነንና ምስጋን ለሱ ይሁን። ጥሩና ብቃት ያላቸውን ባለሙያዎችን የክርስትና አስተማሪዎችን ከጉያው ማቀፉ ብቻ ሳይሆን በየጊዜው እየተጋበዙ የሚቀርቡት አባቶችም በትምህርት እየባረኩት ነው። ለምሳሌ ያለፈውን እሁድ ያስተማሩት ሊቅ ቤተ ክርስትያኗ ከአብሯኳ ካፈራቻቸው ብርቅዬና አኩሪ ከሆኑት አንዱ ከእኩለ ሌሊት ጀምሮ የተሳተፉበት ድንቅ ማህሌትና ከቅዳሴው በኃላም የሰጡት ትምህርት የተሳተፉት ሁሉ በመደነቅ የተባረኩበት መሆኑን የደረሰን መረጃ ያስገነዝባል። እኝ አባት ያስተማሩትን የቤተክርስትያናችንን የቀናትን ቀመር ሲሆን ይህ ስሌት ለእምነቱ ተከታዮች ብቻ ሳይሆን ለሀገሪቱም ታሪክ፣ እድገትና አስተዳደር መሰረት ጭምር መሆኑን የተገነዝቡ ሁሉ የሚደነቁበት ነው። ከአገሪቱ ውጭም ያሉ ጠበብቶች ሁሉ ምንግዜም የሚያከብሩትና ከፍ ያለ ምርምርን ያካሂዱበት መሆኑን ብዙ መረጃዎች ይጠቁማሉ። ባትሪያችንን ጨረስን ለሚሉ አሊያም ሰዐታትና ኪዳን መቆም ብቃት የጎደላቸውን የስም ቄሶችን የሚሰሙና የሚከተሉ ቢኖሩ፤ አሊያም የደብራችሁን ውድቀት ለሚመኙና ለዚሁ እኩይ ተግባር ቀን ከሌት ለሚፈጉ ሁሉ እንግዲህ እረፉት። ትሩፍቱና በረከቱን በምግባራችሁ ሲነሳችሁ፤ የይቅርታ አምላክ ይጎብኛችሁ ነው የምንል።ክርስትያን የሆነና እምነቱን የተረዳ አማኒያን መሰማርት ከሌሌበት ምግባር መቆጠብ እምነቱ የሚያስገድደው ሲሆን እንደተገነዝብነው ከሆነ የበግ ለምድ የለበሱ ተኩላዎች በሰንበት ለጸሎት ወደ ደብሩ መጥተው ከመሳተፍ ይልቅ በአዳራሹ በመሰባሰብ ሳይባረክ ለእለቱ እንዲቀመስ የተዘጋጀውን ሲሳተፉና የማይገባ ውይይት ሲያደርጉ መታየት ከጀመሩ ሰንብተዋልና ድርጊታቸው ያለቦታውና ያለጊዜው መሆኑን ተረድተው እንዲቆጠቡ ልንገልጽ እንወዳለን። አዳራሹም የቤተክርስትያኑ አካል ነውና።

የእግዚሀብሔርን ለእግዚሀብሔር መስጠት ለአማኒያን ተገቢ ነውና፣ አማኒያን ነኝ ብሎ እንደአማኒያን ወደ ቤተክርስትያን የሚገባ ሁሉ የተቻለውን ስጦታን ሲችል ካልሆነም ቢያንስ ምዳየ ምጽዋት ማድረግ ተገቢ ነው። ልቦናን ሳያጸዱ በእግዚሀብሔር ፊት መቆም ምንኛ ጎዶሎነት ይሆን? በምንሮበት ሀገር እንኳ ለማንኛውም አለማዊ ግልጋሎት ለምንቀበለው ዋጋ እንደምንከፍል ሁሉ፤ እድሜና ጤና ጊዜም ሰጥቶን ፣ ቤቱንም እንድንገባ ፈቃዱ ለሆነው ልዑል እግዚሀብሔርማ ምን ይገባዋል? ከሱ የሰሰትነውን እራቆታችንን እንደመጣን እራቆታችንን እንደምንሄድ መገንዘብ እንዴት ይሳነናል? የማይጠቅም ጥላቻችን ይዘን የሱ ተገዢ በመሆን አማኒያን ነን ለማለት እንዴት ያስችላል? በዚህ አዲስ ዘመን መጀመሪያ አዲስና የተቀደሰ መንፈስን በውስጣችን ይሰርጽልን ዘንድ የሁላችንም ጸሎት ይሁንልን እርሱም ይቀበልልን አሜን።

እርሶስ ምን ይላሉ?

Saturday, September 11, 2010

አፕልን ከአፕል ጋር ካለማነጻጸር ውድቀት

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!


ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።



አፕልን ከአፕል ጋር ካለማነጻጸር ውድቀት

በምኖርበት ሀገር የተለመደ የአባባል ዜይቤ ነው። የተወደዳችሁ የገጻችን አንባቢዎች እንዃን ለ፪ ሺህ ፫ የኢትዮጵያ አዲስ ዘመን በሰላም አብሮ አደረሰን፤ መጪው ዘመን የሰላም፣ የጤና፣ የፍቅር፣ የአድነት፣ የመቻቻልና የእድገት ዘመን ይሁንልን!

ቢያንስ የኢትዮጵያ ኦርቶድክስ ተዋኅዶ አነስተኛውን መስፈርት የሚጠይቀውን እውቀት ሳያሟሉ በሀይማኖቱ ስም ቅዱስ መጽሀፍን አስመልክቶ መንፈሳዊ ትምህርትን በገጾች እያወጡ ንጹኃንን ወደ ስህተት መንገድ መምራት ተገቢ አለመሆኑ እሙን ነው። በዚህ ምክንያት በተለያየ አጋጣሚ እንዳስገነዝብነው ዛሬም ዳላስ ላይ ተቀምጠው ከዚሁ ድርጊታቸው ያልተመለሱ ግለሰቦች የደብራችሁ የቅዱስ ሚካኤል እንዲሁም የአስተዳደር ቦርዱን በገጾቻቸው እየተተናኮሉ ቢገኙም የመጨረሻ እስትንፋሳቸው ላይ መሆናቸው የማይታበል ሀቅ ነው። እነዚሁ ገለሰቦች የሜይ ፪ በደብሩ ውስጥ የተፈጠረውን ብጥብጥ ጠንሳሽ፣ አድራጊና አስፈጻሚ በመሆን ያቀዱትን የልዑል እግዚሀብሔር ፈቃዱ ሳይሆን ቀርቶ በመክሸፉ ለሱ ክብርና ምስጋና ይሁን። ይህንኑ ድርጊታቸውንም ይዘውት በገቡት ምስል መቅረጫ በመዘገብ የቀረጹትን በዘመኑ እውቀት በመታገዝ ባሻቸው ከላልሰውና የነሱን ፍላጎት ሊያራምድ በተመቻቸ መንገድ አቀናብረው ከቴሌቪዥን እስከ ዩ ቲዩፕ በማሰራጨት በደብሩ ላይ ብቻ ሳይሆን ለማንኛውም የኢትዮጵያ ተወላጅና ወዳጆች፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮችና መሪዎች፣ በታሪካችንና በማንነታችን ላይ ውርደትን ያመጡ ከጉያችን የወጡ ወገኖቻችን ናቸው።

እናንተ የዳላስ ነዋሪ የሆናችሁ የኢትዮጵያ ሀረግ ያላችሁ ከፖለቲካ፣ ከዘር እንዲሁም ከእምነት ልዩነት ባሻገር በአንድነት በመሆን ይህን ደብር ያለበት እድገት ደረጃ በማብቃታችሁ ልትኮሩ ይገባችኃል። እኛም በዳላስ ጥቂት አመት ቆይታችን ከተረዳነው በጥቂቱ ደብሩ ከሚሰጣቸው አገልግሎት በተለይም አዳራሹን ለሀዘንና ለሰርግ እንዲሁም ለኮሚኒቲው መረዳጃ መሰብሰቢያ ማድረጉ በቀላሉ የሚታይ አይደለም። በዚህ አጋጣሚ ስለ ኮሚኒቲው ካነሳን በዋቢነት ከመጥቀስ የማናልፈው ከሳምንት በፊት የደብሩ አስተዳደርና የኮሚኒቲው አመራር ተገናኝተው በመካከላቸው ሊያቃርኑ የደረሱትን ችግሮቻቸውን ተወያይተው እልባት ሲሰጧቸው፣ በመካከላቸው ፈጥረው ሊያራርቋቸው የተንቀሳቀሱትን ግለሰቦች በተለይም የሁለቱም ወገን የቀድሞ የስራ አመራር አባላት ከነበሩት ውስጥ እንደሚገኙ ግንዛቤ ሲወስዱ፤ ሌሎች በገጾቻቸው እንደሚሉት የደብሩ አመራር አምባገነን፣ ውይይት የማይፈልግ፣ ወዘተ….. እንደሚሉት አለመሆኑን በተግባር አስመስክሯል። እንደቦርዱ አቋምና እኛም እንደምናምንበት ማንኛውም በክስ ፍርድ ላይ ያለ ጉዳይ ክሱ እልባት ሳያገኝ ከሳሽና ተከሳሽ ጉዳያቸውን በተመለከት ምንም አይነት ግንኙነት ማድረግ ብቻ ሳይሆን ይህንኑ በተመለከተ ከከሳሽ ወገን ወይንም የነሱን ሀሳብ ከሚያራምድ ጨምሮ ጋር መወያየት አይገባቸውም።

በተለይም በአንደኛው ገጻቸው ሰሞኑን የዳላስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ደብርን በወሲብ ምክንያት ችግር ካለበት የሌላ እምነት ድርጅት ጋር አነጻጽረው የጣፉት ጽሑፍ፣ በመላ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ እምነት አባቶችን እጅግ እያሳዘነ ይገኛል። እንደርእስ እንዳስቀመጥነው የአፕል ዘይቤን አስረግጠን በሜይ ፪ ካደረጉት አስነዋሪ ተግባር ያላነሰ አርገን ስለምናየው እነዚህ ወገኖች መልእክቱ እንደሚደርሳቸው እምነት አለን። ከዚህ ጋር አያይዘው የዘገቡት አሀዝ ከእውነት የራቀና ማንኛውም የደብሩ አባል እውነቱን ከሚመለከተው በማግኘት የነዚሁን ሀሰተኞችን ሴራ በመገንዘብ ቤተ ሚካኤልን መጠበቅ ይገባዋል።

እርሶስ ምን ይላሉ?

መልካም ዐመት!

Tuesday, September 7, 2010

ከማያዳምጥ ጋር መወያየት ትርፉ የራስን ቃል መልሶ ማዳመጥ ብቻ ነው። ቁጥር ፵፩

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!


ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።



ከማያዳምጥ ጋር መወያየት ትርፉ የራስን ቃል መልሶ ማዳመጥ ብቻ ነው። ቁጥር ፵፩

መልካም አባባል ነበር ነገሩ እንዳመልካች ጣት ሆነና ተሙሾ አልቆ ደቆ ፵ው ወጥቶለት በ፵፩ኛው ቀኑ የተረዳው የነተኩላው ገጽን ለእረፍት በወጣንበት ወቅት ትንፋሽ ያገኘ መስሎት ከመቃብር የንስሐ ጩኸት ካነበነበው ነበር። እንደምን ሰንብታችኃል? በፈጣሪ ጸጋና ቸርነት መልሰን ለመገናኘት በመብቃታችን ለልዑል እግዚሐብሔር ምስግና ይሁን‘።

ወግና ሙያ ለብቻ መሆኑን ያልተረዳው የነ ጋሼ ተኮላ (ተኩላው) ገጽ የቻለውን ተንፈራገጠ እንጂ የመቃብር ውስጥ ጩኸት ከምንም እንደማያወጣው መገንዘብ ከተሳነው ዛሬ አይደለም፣ ባሕሪው ሆኖ አብሮት ኖሮታልና። የቅርቡ ጊዜ ምሳሌ ብንጠቅስ ያለውቀቱ ገብቶ የቅዱስ ሚካኤል ደብር መተዳደሪያ ደንብ የማሻሺያ ሀሳብ እንዲያያዘጋጁ ተብሎ የተሰየመ ኮሚቴ ውስጥ ገብቶ፣ አብረውትም የተሰየሙት ከእጅ አይሻል ዶማ ሆነው ፤ ማሻሻያ የሚለውን ትርጉም ገብቷቸው ይሁን ወይም ሌላ ተልኮ በወቅቱ ይዘው ፤ ያቀረቡት ከተጣለባቸው ኃላፊነት ውጪ ወጥተው ሕጉን በመለወጣቸው ነበር። ምዕመናኑ የቀረበለትን አዲስ ሕግ በሙሉ በመቃወሙ በደረሰባቸው ኪሳራ መቀበል ተስኖቸው በአደባባይ ዛሬም ቤተክርስትያናን እየወጉ ያሉት። የዚሁ ኪሳራ ሰለባዎች የሆኑትና አሁንም በግምባር ቀደምትነት ደብሩን የሚወጉት የዚሁ የፈረሰ ኮሚቴ ውስጥ የነበሩት መሆናቸው ሁሉም የሚያውቀው ሀቅ ነው። እኔ ያልኩት እንጂ ልዑል እግዚሀብሔር የፈቀደው አይደለም፤ ወይንም የሀይማኖቱ ጥልቅ እውቀት ያላቸውንና በሚገባ በስደተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ አማኒያን በምዕራቡ አለም በገለልተኝነት እየተቋቋሙ ያሉትን ቤተክርስትያን በቂ ግንዛቤ ያለውን ጥናቶችን ማካሄድ ሲገባ፤ በዘፈቀደ ወይንም በሌላ ተጽዕኖ ሆኖ፤ አሊያም ግርማቸው የሚሉት የዚሁ ኮሚቴ አባል ከአዲስ አበባ በሚሰጠው አመራር የተቀነባበረ ሕግ ፤ ከመድረሱ መፍረሱን እንደ ግል ጥቃት አድርጎ መውሰድ አንዱ ነው። ስለ ህግና መብት መቀባጠር የማይሰለቸው ተኩላው እስረኛው ሁኖ የሚያመልከው የሰይጣኑን ብቻ ሆናል። ይህንኑ የተጠናወተው የመንፈሳዊውና የአለም ኑሮና ህግ ተምታቶበት ያንቧርቃል።

እኛን ተሳዳቢ ሌላም ብትለን ከቆምንለት የማናወላውልና ለማንም የማንወግን፤ እውነትና ቀጥተኛ መንገድ ይዘን የምንነጉድ ለመሆናችን እየተገለጸልህ ስለመጣ ፤ ቀድሞ እንደምታስበው አፍንጫህ ስር ተቀምጠን ፤ የቦርዱ ልሳን፤ አንዳንዴም ቦርዱ፤ ወይም ያንተ ስራ ከሚተባበሩ ጥቂት ቆራቢ ነን ብለው የጠረጠሩትን ሁሉ ማሉልኝ ያሏቸውን ወይንም ገጻችን አንቦ የተነፈሰውን ሁሉ የዚህ ገጽ አዘጋጅ አለምሆኑን አንተና ቢጤዎችህ በሚገባ እየተረዳችሁ በመምጣታችሁና ፤ ፈተና ስለሆንባችሁ የኛን ገጽ ወዳጆችን እንዳያነባት ምልጃ ጀመራችሁ። ባደባባይ አታንቡ ፣ አትረዱ ፣ የራሳችሁንም አቋም አትወስኑ፣ እኔ ብቻ ነኝ የማውቅላችሁ (እንደከሸፈው የመተዳደሪያ ደንብ) ፣ ወዘተ……. ከሆነ ያቺ እንደ አቡነዘሰማያት የምትደጋግማት የአለም መብት ጥያቄህን የትኛው ጉያህ ልትደብቃት? አንተ የገጻችን ወድጅና እድምተኛ እንደሆንክ ሁሉ እነርሱም ካንተ ያላነሰ መብት ገጻችን የሰጠቻቸው መሆኑን እንዴት አይገባህም? ልክ በ ፵ኛህ የአደባባይ ሞተ ገጽህ ማግስት እንደጠቀስከው ሆነብህና እንግዲህ እረፈው። እኛ ለቦርዱም፣ ለካህናቱም፣ ለዳቢሎሱም (አንተንና ቢጤዎችህን ለርሱ ያደራችሁትን) ሁሉ እንደ ፍጡራን እኩል ስናያችሁ በተግባራችሁ ግን እንለያችኃለን።

ጋሼ ተኩላው በብጥብጡ በወርድክ ነበር ግን ፈቅዶ እድሉን ቢሰጥህም ከታች ሁነህ የምትወጋ ፍጡር፤ አንተ ትላንት እቃወመዋለው የምትለውን ወያኔ ዛሬ ደጋፊ ሆነህ ደብሩን የእጅ መንሻ ለማድረግ መራራጥህ ቤተክርስትያኑ ለድርድር እንደማይቀርብ በተረዳኸው። የአንተን ወያኔ ደጋፊነት መግባትህን የግል መብትህ መሆኑን ባለፈው ጥቂት ወራት የተሳተፍካቸው ስብሰባዎች ያስረግጣሉ። በመጀመሪያ አባል ባልሆንክበትና ባቋቋሚነትም ስምህ በሌለብት ከሳሽ ፣ በሁለተኛ በማያገባህ ገብተህ ስደትኛ ሲኖዲስ ምናምን እያልክ መዘላበድ የራስህን ጎራ በግልጽ እያስበላህ መጣህ! እንግዲህ የወያኔ ሎሌ መሆን የጥቅል ውል አለበትና ኃይምኖቱም የዚሁ ሰለባ መሆኑ ሀቅ ነው፣ አንተም እያራመድከው ነው። እኛ ግን ካንተ የምንለየው ፤ ማንኛውም ከሀገር ውጪ በግሉ የሚከፍተውና እያስተዳደረው ያለውን ደብር መብቱ ይጠበቅለት፣ የራሱን መብት ራሱ ያቋቋመውና የሚያስተዳድረው ምዕመን ይወስን ነው። አንተና ያንተ ቢጤ ቅጥረኛ መቋመሪያ አይሁን ነው። የዚህ ሂደት ተሳታፊ ለመሆንም የተቀመጠውን መብትና ግዴታ መወጣት እንደሚያስፈልግ የጨለመብህ። አንተ ለኑሮ ውድነት መደጎሚያ እንደምትጠይቅ ሁሉ ደብሩም ካለው ሁኔታ ጋር አመዛዝኖ በቀን አንድ ብር በወር ድምሩና አባላት ክፈሉ በማለቱ አንተ በድሮ በሬ ሂደህ ለምን ከአምስት ብር በላይ እከፍላለሁ ብለህ ያኮርፍክና የወጣህ (ሊያው የትንሽ ጊዜ አባል) ትልቅ አያርጉህ ሕጻን። በተለያየ ቀን የዘባረከውን ስታውሳ ዛሬም እዛው አልንህ። ትላንት የድሮውን ሕግ ተቃውመህ አሻሻይ ኮሚቴ ዛሬ ደግሞ የተሻሻለውን ተቃውመህ በድሮው የምትል፣ አንተና ቢጤዎችህ የቤተ ክርስትያኑን ገንዘብ የዘርፉትን (ከፈጣሪ የሰረቁትን) በሱ ገንዘብ አንተና ቢጤውችህን ማን ወኪል አደረጋችሁ፣ ያው የለከፋችሁ የቤትክርስትያን ጠላትነታችሁ በሽታ የሌባ ጓደኛ አደረጋችሁ እንጂ። ባለፈው የመጽሀፍ ቅዱስ አንባቢ ብሎም ፈቺ ለመሆን ዳዴ ለማለት ቢያቅታችሁም፤ የድቁርና ስራችሁ እንደቀጠለ ለመሆኑና ላለፈው ስህተታችሁ የማትማሩ፣ ማስተዋል የጎደላችሁ ፣ ለመንፈሱ ማደሪያ የማትሆኑ ቀፎ ጭንቅላት የተሸከማችሁ መሆናችሁንና ስለሀይማኖቱ የእንጭጭ ስንኳ እውቀት የሌላችሁ በአስሩ ቃላት የተጻፈውን የማታውቁ ፣ “አትስረቅ“ የሚለውን ህግ ለተላለፉት ያውም የቤተ እግዚሀብሔርን ገንዘብ ሰረቁ የተባሉትን ዋሻ የሆናችሁና ከነሱ የወገናችሁ መሆናችሁን ዛሬም ደግማችሁ ያስረገጣችሁ የሰይጣን ማደሪያዎችና የሁላችን ማፈሪያዎች።

ሌላው ደግሞ ከላይ ስሙን ያነሳነው ግርማቸው አድማሴን ብዙ ከርሱ የቀረቡ ቢመክሩት አልሰማ ያለና ፤ እንደሰማነው ትምህርትን የሚችለውን ያህል የገረፈ የተባለለት፣ ልዑል እግዚሀብሔር ሳይሆን እኔ ያልኩት የሚል እልህ የተጠናውተው ያላዋቂ ሳሚ ሆኖ ከሰይጣን ወግኖ የወዳጆቹና የቤተሰቦቹ መሸማቀቂያ ሆኖ ሰንብቷል። በዚህ የቤተክርስትያን ጉዳይ ተመሳሳስይ ሁኔታ ውስጥ የገቡትና የተሸካካሩ ብዙ ናቸው። ሀይማኖታዊ እምነትንና የልብን ፍላጎት ነጥሎ አለማውቅ ውጤቱ ከዚህ የተለየ አይሆንም።

እኛን መቃረን ያልሰለቸው ኮሚኒቲውን አስመልክቶ ጥሩ በአል እንደነበር ሊቀባ ሞክራል። በስፍራው ከተገኙት እንደ ተረዳነው የቅዳሜው ከምን ጊዜውም በጣም ያነሰ እንደነበር ስንረዳ ከቀዳዳው (ሙላው) የተጋባበትን ተኩላው ሀሰትን እውነት ብሎ ዘግባል። በርግጥ በእሁዱ ጥርያችንያልደረሳቸውና የነሱንም በቤትሰብና ወዳጅ ልመናና ውትወታ ከእደረተኛው ቁጥር አካባቢ የሚቃረብ ጎብኚ እንደጣለላቸው ለመረዳት በቅተናል። ከሁሉም በላይ ጥሪያችንን ተቀብላችሁ እራሳችሁንን ከወያኔ ቀን በአል ላራቃችሁ ሁሉ ከፍተኛ አድናቆትና ክብር እናቀርባለን፣ በቆራጥና በንጹህ የኢትዮጵያ ውዳጆችና ተቆርቃሪ ሁሉ ስላደረጋችሁት ተሳትፎ ምስጋናችን ይድረሳችሁ።

ከዚህ ሌላ ቦርዱ ያለፉትን አመታት በተደረገው የሂሳብ ማጣሪያ መሰረት በኃላፊነት መጠየቅ ያለባቸውን ምን አደረሰው? ያለፈው አመትን በተመለከተ የሂሳብ ማጣርያ መቼ ነው? ለህጻናት አስተማሪ ተገኘ የተባለው ወሬ የት ገባ? ክሶችን በተመለከተ ምን እየተሰራ ነው? ይኼን በተመለክተ አስተዳደር ቦርዱ ምላሽ ሊሰጥ ይገባዋል እንላለን።


እርሶስ ምን ይላሉ?