Tuesday, March 29, 2011

ቃል እንደገባነው

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!

ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።


ቃል እንደገባነው

ተወዳጅ የገጻችን ተከታታዮች እንዴት ናችሁ? በገባነው ቃል መሰረት የትግሬ ነጻ አውጪ ቅጥረኛ የሆነው የአዲስ አበባው መንግሥት ተወካዮች በከተማችሁ ላቀዱት የፕሮፓጋንድ ሥራ በ04/09/2011 ከቀኑ 2ፒ ኤም እስከ 6ፒ ኤም በዳላስ ፓርክ ዌይና በቤልት ላይን መንገድ በደቡብ ምዕራብ ዳርቻና በአድሰን ክፍለ ከተማ ውስጥ በሚገኘው በማርዮት ኮረም ሆቴል ውስጥ በሚገኘው ግራንድ ቦል ሩም አዳራሽ ውስጥ እንደሆነ ከሆቴሉ ለማረጋገጥ ችለናል። ይህ ቦታም የተያዘው በኤምባሲው ስም ለመሆኑ አብሮ የደረሰን ዘገባ ያስረዳል።

ቦታው የሚገኘው በ14901 Dallas Parkway
                      Dallas, Texas 75254
                      Tel. (972) 661-2800

ይህንንኑ አስመልክቶ በከተማችሁ የሚገኘውና የኛ ገጽ  ከሚደብራቸው ብሎጎች አንዱና የተቃዋሚ ልሳን አርጎ እራሱን የሚያቀርበው ብሎግ በገጹ ያወጣው የሚላመጥ ይኖረዋልና ጎራ እንድትሉና እንድትቃኙት እንጋብዛለን ። ለመግባት ይህንን መዛለያ ይጨቁኑ (ይጫኑ) http://www.ethiodallas.blogspot.com/
አልሆን ካለዎት እንዳለ ኮፒና ፓሴት በማድረግ ይጠቀሙ። በዚህ አጋጣሚ የዚህን ገፅ አቅራቢ በሀሳብ ልዩነት ቢኖረንም ለሚያደርገው ግልጋሎት እያመሰገንን ከብሔራዊ አጅንዳ በፊት የአካባቢ ሕብረተሰብ ባለው የመረዳጃ ማህበር ችግሮች ላይ ዝምታን በመምረጡ ትችታችን ታላቅና ባስቸኳይ መተግበር ያለበት በመሆኑ ሕዝባዊነት ከቄይ ይጀመር፣ ድምጡ ለታፈነበት መብቱ ለተረገጠበትና ለተቀማበት ቅድሚያ ይሰጠው እንላለን! አሊያ ለግል ጥቅምና ለሥልጣን ከሚያልሙት፣ መብትን ከሚረግጡት መፈረጅን ያመጣልና ይተግበር እንላለን። የዳላስ ወገናችን የጊዜው አንገብጋቢ ጥያቄ በጥቂት እብሪተኞች እየተፈጸመ ያለው ችላ የማይባል የነዚሁ የትግሬ ነጻ አውጪ ተቀጣሪዎች ተግባር ነውና ትግሉና ጽዳቱ ከቄይ መጀመር የግድ ነው እያልን ጥርያችንን በዚህ ገጻችን እናሻግራለንና መልሱን ለመተግባር እግዚሀብሔር ይጨመርልን እንላለን።

ተመሳሳይ ጥያቄና ጥሪያችን እንደዚሁ ለhttp://www.dfwethiopiancommunity.blogspot.com/
አዘጋጅ ወይዘሮ እያቀረብን ፤ በገጾ የጀመሩትን መውጋት ብቻ ሳይሆን ከዚህ በፊት እንደሚያደርጉት ባደባባይ መውጣትና በየስብስቡ ይገኙልን ዘንድ በትህትና  እንድንጠይቆት ተደጋግሞ በቀረበልን ጥያቄ መሰረት ነው። ባደረግነው ጥናት ያካበቱት ልምድና ያበረከቱትን አስተዋጾ አይናችን ስለገባ ይበርቱና መረዳጃ ማህበሩን ወግ እንዲይዝ የበኩሎን አጉሊ አስተዋጾን ያደርጉ ዘንድ የክብር ጥሪያችንን እናቀርባለን? የእርሶን ቢጤ እህቶቻችንን እግዚሀብሔር ያበርክትልን፣ ያበረታታልን። ካልጫ ሱሪ ቆራጥ ቀሚስ ይበልጣልና ትምህርት ለሁላችንም እንደምትሆኑ ተስፋችን የላቀ ነው።

እርሶስ ምን ይላሉ?

Sunday, March 27, 2011

በየፈርጁ ሲመተር

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!

ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።


በየፈርጁ ሲመተር

የተወደዳችሁ የገጻችን ተከታታዮች እንደምን አላችሁ? እንዲሁም የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ለሁናችሁ ሁሉ እንኳን ለደብረዘይት በሰላም አደረሳችሁ!  ፈቃዱን ላደረገው ለልዑል እግዚሀብሔር አሁንም እስከ ዘላለሙ ክብር ምስጋና ይሁን። አሜን! እንዲሁ ለበዐለ ትንሣኤው በሰላም ያድርሳችሁ!  የተጀመረውን ሁዳዴ ጾም በሰላም ያስጨርሰን፣ ጥበብና ማስተዋልን፣ ትህትናና መተሳሰብን፣ ፍቅርና ሰላምን ያብዛልን፣ የተቸገሩትንና እርዳታን ለሚሹት ሁሉ ደግ እናደርግ ዘንድ ልቦናችንን ይክፈትልን፣ አጽራረ ቤተክርስትያንን ያስታግስልን፣ለዓለም ሁሉ ሰላምን ይስጥልን፣ ፍቅርና በረከቱን ያበዛልን ዘንድ ምሕረቱን ያደርግልን! አሜን።

በዛሬው ልሳናችን ከዳላስ አካባቢ ካገኘናቸው አበይት ነጥቦችን ለመሰንዘር ስንዳዳ፣ ከመስመር የወጡትንም ፈጣሪ መክሮና አስተምሮ ይመልሳቸው ዘንድ ጸሎታችን ነው። ወደ ህብረተሰቡ ወቅታዊ ሂደቶች ከመግባታችን በፊት፤ በተለይም በዳላስ ቅዱስ ሚካኤል ደብር ላይ አጽራረ ቤተክርስትያን የሆኑ ጥቂት ግለሰቦች እራሳቸውም ተሳስተው ሌሎችንም አሳስተው ከቤተክርስትያናችን ሥርዐትና ሕግ ውጪ እራሳቸውን ኦርቶዶክስ ነን በማለት ነገር ግን ኢኦርቶዶክሳዊ ተግባራትን ዛሬም በዚህ ዓብይ ፆም ሰአት እየተገበሩት ይገኛሉ። ባለፈው 03/23/2011 የፍርድ ቤት ቀጠሮ ላይ ጉዳዩን የሚያየው ዳኛ ለከሳሽ ጠበቃ የይግባኝ ሰሚው ችሎት የበየነውና ለእርሱም ችሎት የሰጠውን መመሪያ በመጥቀስ ከመቃብር ውስጥ ሞቱ የተረጋገጠለትን ሕይወት አለው ይውጣና ይታይልኝ የማለት ሂደቱን በአመክሮ መንገድ እንደጠቆመው ከስፍራው ከነበሩት ስንረዳ፤ በዚህ ዕለት እንደ ክስ ማሻሻያ ብሎ አዲስ ሁለት የተከሳሾችን ሥም አክሎ በማቅረቡ ዳኛው ደስተኛ አለምሆኑን በሁኔታው የተረዱ ታዛቤዎችን አትርፏል። ከነዚህ አዲስ ታካይ ከሳሾችም ውስጥ፡-

1ኛ/ ኃይሉ እጅጉ የተባለውን ግለሰብ ባለፈው ጥሁፋችን ማንሳታችን ይታወሳል። ይህ ግለስብ የመተዳደሪያውን ዳንኪራ ቤት ጭምር ከፍቶ ስለቤተክርስትያን ጉዳይ መወዛገቢያና የአጽራረ ቤተክርስትያን ሴራ መዶለቻ አድርጎታል። ከዚህም በተጨማሪ የነተኮላን (ተኩላው) መኮንን ክስ በገንዘብ የምደግፈው እኔ ነኝ ያለና እግዚሀብሔር በሰጠው ንዋይ መልሶ የሚወጋ ነው። እንደምንሰማው ከሆነ ዶሮ ከነዕንቁላሏ ነው የምትጣፍጥ ብሎ አለ የተባለለት፤ ኢትዮጵያ በነበረበት ጊዜ በነበረው ወዳጅነት ታምኖ ያአሁን ሚስቱን እርሱ ዘንድ ተጠግታ እንድትማር ብትላክ የገባውን ቃል ሰብሮ ልጅቱን ደፍሮ የያዘ፤ ባለበት ያመንዝራ ጠባይ ካንዲት የጥቁር አሜርካዊ እህት ጋር በመጋለጡና ለዚያ መፍቴ ሴቲቱን በገንዘብ ሚሽቱን በቁርባን በማድረግ በፍቺው ምክንያት ለጊዜው የሚደርስበትን የንዋይ ኪሳራ ቢያተርፍም ፈጣሪውን ከማወክ ያላቆመ ነው። በእውነት ለመናገር ግለሰቡ ለዚህ ደብር ቀደም ሲል ከልቡም ሆነ ለመታያ የገንዘብ እርዳታ አድርጓል ፣ ያ ግን ደብሩን አቅጣጫ የመምራት መብት አይሰጠውም። እንግዲህ ይህ ሰው እንደ ኦርቶዶክስ ተከታይ የቆረበ ለምን ሲዋሽ ከርሞ ዛሬ በከሳሽነት ባደባባይ ያውም በአብይ ፆም ? የሚለውን ጥያቄ መልስ ለአንባቢያን እየተውን ምን አለ በዚህ ዕድሜው ከፈጣሪው ባይታገል? ምን አለ ንዋይም ካለው ከአብራኩ ለወጡት ልጆቹ መደጎሚያ ቢያደርገው? ትልቋም ልጁ እስከመቼ መረጃ የሌላት ሕገ ወጥ ነዋሪ ትሆናለች፣ በዕውነት ይህን ማስተካከል አቅቶት ይሆን? አይመስለንም እንደው ……..
ዛሬ ፈጣሪ በገንዘብ እየቀጣው እንደሆነ በቅርቡ ከነ በትሩ ገ/እግዚሀብሄርና በነመስፍን ገብሬ የተጀመረው የፓርክ ሌይን ፕሮጄክቱ ከመሬት ሳይነሳ ከ200መቶ ሺህ ዶላር በላይ ያስወጣው የኮንትራት ኪሳራ አይመክረውም ይሆን? ፈጣሪ ሲቆጣ አርጩሜ ቀጥፎ እንደማይመጣ አበው አስተምረውናልና ንስሀ መድሀኔት ነው። የገንዘብ ቅጣት ቀላል ነው በቤተሰብ ውስጥና በጤና ላይ ግን የሚመጣው ቀላል አይሆንምና ፈጣሪ ሁላችንንም ከዚያ ይሰውረን።

2ኛ/ ገነት ከበደ የተባለችው ነች። በዳላስ ኑሮዋ የምትታወቀው ከሀገር ቤት ጀምሮ ሴትኛ አዳሪ፣ ትምህርቷም ከሁለተኛ ክፍል ያላለፈና አሜሪካ እስከመጣችበት ድረስ እንደ ኢሕአፓና መሰሎቻቸው ሌላ በወንጀል የሚያስጠይቃት ስም እንደነበራት ነው የሚደርሱን ዘገባዎች። ዳላስ ላይ ህገወጥ (ዝጉብኝ) የተሰኘ ቀኑን የጫትና ምሽቱን የአልኮል መቸርቸሪያ በማድረግ የምትኖርበትን አፓርትመንት ስትጠቀም መኖሯ የታወቀ ነው። ከሰከረውም ኪሱ የምትገባ አለው ከተባለም ከትዳሩ ለማፈናቀል ያላደረገችው የለም። በእውነት ቤተክርስትያኑ ውስጥ ስትታይ ንስሀ የገባችና ሀይማኖቱን ያወቀች በመምሰል ተጠግታ የድብሩን የንዋየቅድሳት መሸጫ በመያዝ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ያለምንም ተመልካችና ቁጥጥር ይዛው እንደነበር ከምንጮቻችን ደርሶናል። እኛም ለምን በጥቅሟ መጣችሁባት በማለት ብናሾፍም ፣ ከፍተኛ የጤና ችግር እንዳለባት በመስማታችን ፈጣሪ ጤናዋንና ሕሊናዋን ይመልስላት ዘንድ እንመኝላታለን።

3ኛ/ በብሎግ ገጹ ባወጣው መሰረት ክሱን ተቀላቅያለው ያለው በነተፈራወርቅ መሪነት ተቋቁሜ ያለሁት ለማስታረቅ ነው የሚለው አጽራረ ቤተክርስትያን ቡድን ነው። ጭፍሮቹን በተለያየ ወቅት በመላክ ደብሩን ሲያስከስስና ሲያሳውክ የቆየ ከእጅ አዙር ወደ አደባባይ ወጣ እንጂ ምንም አዲስ ነገር የለም። ቀደም ብለን በገጻችን የዘገብነውን አረጋገጠ እንጂ እራሱን እንደሰየመው አስታራቂ፣ ሰላም አምጪ፣ ገለልተኛ እንዳልሆነና የኦርቶዶክስ ሥርዐትና ሕግ እንደዚሁም እምነቱንም የተከተለ መንገድ ባልጨበጠ ጎዳና የሚዳክር አናሳ ቡድን ነው። ትምህርትና ዕውቀቱ የበራላቸው ከሆነና 03/23 ፍርድ ቤት ታዘብን ብለው እንደዘገቡት ከሆነ ዳኛው የተናገረው ገብቷቸው ነው ወይንስ ቀድሞ እኛ እንደዘገብነው ለሌላ ጥቅም የቆሙና ይህንኑ ለማስፈጸም የማይፈነቅሉት ድንጋይ ላይኖር ነውን? እነዚሁ ቅጥረኞች ደብሩን የሚፈልጉት እውነት ለኃይማኖት ነውን? እንግዲህ ፤ ኃይማኖት ከሆነ ፆምና ጸሎት ለአማኞች ሲሰራ እንጂ በአለም ፍርድ ቤት ሲመለስ አላየንምና የምትከፍሉት ዋጋ ቀላል አይደለም፣ ከላይ እንዳልነው አርጩሜ ቀጥፎ አይመጣምና ከቅጣቱ ሁላችንንም ይሰውረን እንላለን።

ከዚሁ ሳንርቅ የዚሁ ቁጥር 3 ቡድን አውራዎች በመረዳጃው ማህበር ሲፈጽሙት የነበሩትን በደል ሕዝቡ በመረዳት ሊለውጣቸው መነሳቱን በመረዳታቸው የሰሩት ተጋልጦ ወደፊት በህግ እንዳንጠየቅ በማለት ቦርድ ኦፍ ትረስቲ በማዋቀር ካልሆነ አዲስ ተመራጮች ተመርጠው እንዳይረከቡ የማያደርጉት ተንኮልና ሴራ የለም። ይህንኑ በዛሬው የራዲዮ ፕሮግራማቸው ላይ ተወካያቸው አምሃ ታምሩ የተባለው አረጋግጧል። ዛሬም ደግመን የታዘብነው ቢኖር አቅራቢው ፤ ዶክተር ሳይሆንና ማረጋገጫ ሳይኖረው ሆን ተብሎ ንጹሀን የህብረተሰቡን ክፍሎች የተለቀ ትምህርት እንዳለውና ከፍታኛ ሚና እንደሚያበርክት አድርገው በሀሰት ያጠለቁለት ካባ መሆኑን በሚገባ አረጋግጠናል። ስንቶች ለፍተው ያካበቱት የትምህርት ደረጃ እንጂ ለመንገደኛና ለአማጺ የሚሰጥ አይደለም። የጠለቀ ትምህርት እንደሌለውም ማሳወቂያ ሲተዋወቅም ሆነ እራሱን ሲገልጥ የዶክተርነት ትምህርት እንደሌለው ነው። ነገር ግን በሌለው ዕውቀት ሲጠራበት ለእውነት የቆመ ቢሆን አይደለሁም ማለት ሲገባው አስመስሎ ማጭበርበርን እንደሙያ ማደሪያ ያደርገ መሆኑን በይፋ ያረጋገጠ ነው። ባለፈው እንዳስነበብነው የመረዳጃ ማህበር ሊቀመንበር ነኝ ባዩ ተራ የነዳጅ ማደያ ሱቅ ሰራተኛ ተዳዳሪ ሆኖ እያለ አዲስ ሰው አግኝቶ ሲተዋወቅ የሚሰጠው ካርድ ግን ኢንቨስትመንት አማካሪ ነኝ ብሎ ነው። ውሻ አጣቢውም ሆነ ሱቅ ሰራተኛው በሙያው መኩራትና ለተሻለ ነገር እራስን በዕውቀት ማጎልበትና ሌላ መንገድን በሀቅ መጨበጥ ሲገባ በአቋራጭ ያልዘሩትን ለማጨድ ማዋረድ ብቻ ሳይሆን በህግም ያስጠይቃል እንላለን።

ሌላው በራዲዮኑ ከአስመራጭ ኮሚቴ የቀረበውና ግርማ የተባለው የነርሱ ቅጥረኛና አስርገው ያስገቡት ነው። ባለፈው እሁድ የቀረበው ሮቤል የተባለውና ቁጥር ሁለት የተባሉት ህብረት ናጂ ቡድን አባል የሆነውና አስርገው ያስገቡት የተናገረው ፍጹም ተቃራኒ ሲሆን፤ የግርማ ግን ቀደም ብሎ ባለው ሪኮርድ መሰረት መረዳጃ ማህበሩት ሲያጨማልቁና ሲወጉት ከነበሩት የቀድሞ ተመራጮች ተርታ የተመዘገበ ሲሆን ከቁጥር 2 ቡድን ጋርም አብሮ የወገነ ነው። ለዚህም ነው ማንው የአስመራጭ ተወካይ ወይንም መሪና መግለጫ አቅራቢ የሚለውን ጥያቄ መሰተናገድ ያልተቻለው። አስመራጭ ኮሚቴው የተጣለበትን ሀላፊነት በነጻነት መወጣት አለመቻሉ ከራዲዮ ምልልስ ግልጽ ቢሆንም ማንኛውም የተመሰረተ ኮሚቴ የተሰጠውን የሥራ ኃላፊነት ስርቶ በተባለው ቀንና ሰአት ለማቅረብ ዝግጁ ከሆነ የተፈጥሮ እክል ካልሆነ በቀር አንድ እንኳን ሰአት ማሳለፍ የለበትም። ተጠሪነቱ ለመረጠው እንጂ ተርሙን ለጨርሰው ቦርድ አልነበርም። የንርሱ የሆነውንም አጀንዳ ውስጥ ጣልቃ መግባት የለበትም። እነርሱን ሲመርጥ ሕዝቡ በወቅቱና በሰአቱ ሌላውን የቦርድ አጀንዳ የተባለውን በሙሉ የጣለው ስለሆነ፣ አስመራጩ የዚያ ተጽኖ ወይንም እስረኛ መሆን ባልተገባ። ታላቅና ግዙፍ ስህተት እንለዋለን። አሁንም የህብረተሰቡ ጥያቄም ሆነ ችግር በየግለሰቡ ቡና ቤት ሳይሆን የሚፈታው በአንድ ወጥ ሲሆን ነውና የቡናቤቱ ቀጠሮ ለነገር ሸራቢዎችና ድርጅት ማብከን ስራዬ ብለው ለያዙት መተው መልካም ነው እንላለን። ይኸው አስመራጭ ቡድን የጠራና ገለልተኛ የሆነ አለመሆኑን ያረጋገጠ ስለሆነ የጉዳዩ ባለቤቶች የሆናችሁ ሁሉ ግንዛቤን መውስድ የግድ ነው። ከዚህ ጋር የምናያይዘው ቢኖር ትረስቲ የተባለው ቡድን ቢቋቋም አስተዳደር ቦርድ ከመምረጥ ይልቅ የቤሮ ጉዳይ ፈጻሚ መቅጠር የሚቀል ነው። ለዚህ ያበቃን ከምንጫችን በደረሰንና እኛም በገመገምነው አዲስ የታለመውን መተዳደሪያ ደንብ ካየነው በኃላ ነው። የትረስቲው አሽከር ለመሆን የሚመረጥና የሚያገለግል ንጹህና ገለልተኛ አስተዳደር ቦርድ ማግኝት ስለማይቻል እነዚሁኑ አመጸኛና አምባገነን ምልሶ አስቀምጦ አዲስ  ወጣትና ገለልተኛ የሆኑትን ትረስቲ በለያቸው መሾምና ለሌላው ያዘጋጁትን ጥዋ ለእነርሱ መጋቱ መልካም ነው።

ከዚሁ ቀጥሎ በትላንቱ ዕለት ሁለት ስብሰባ በከተማችሁ ተይዞ ነበር። አንደኛው የሕክምና ባለሙያዋች አንደኛ አመት አስታኮ እየደረገ ባለው የወገን ለወገን አገልግሎት ነበርና በዚሁ በርቱ እደጉ ስንል፤ ሌላው የቁጥር 2 የበታኙ ቡድን ስብሰባ ነበር። ይኸው 30 የማይሞሉትን ያካተተው ስብስብ ባለው የከተማዋ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ማተኮሩንና የወገኖቻችን ድምጽና መብት መገፋትን በማራቅ የተደርገው የውስጥ አርበኛ ቅጥረኞች ያደርጉት ሴራ ነው። የመረዳጃ ማህበሩ አመራር አፍንጫቸው ሥር ቁጭ ብሎ የሕዝቡን ድምጽ ሲቀማ ያልቆሙ ነገር ግን ወያኔ እየተባለ አህጉር ዘለል አስመሳይ ታጋይነትን የታየበትና እንዚሁ የትግሬ ነጻ አውጪ ተቀጣሪዎች ስብስብ መሆኑ ነው።

አሜሪካ እየኖሩ ስለመብት ተከራካሪ አድርገው ካቀረቡ የሌላውንም መብት ማክበር የግድ ነው። ከዚህ በፊት እንደጠቀስነው የትግሬ ነጻ አውጪ ተቀጣሪ የሆነው የአዲስ አበባው መንግሥት ተውካዩን ስለ 5ቱ አመት የዕድገት ዕቅድ በማለት የኢትዮጵያ ተውላጆች በሰፈሩበት የውጪው አለም በሙሉ እንደአሰራጫቸው የታወቀ ነው። በዳላሱ የመረዳጃው ማህበር የራዲዮ ስርጭት ማስታውቂያ በቀረበው መሰርት ይህንኑ የተልእኮው ቡድን በ04/09/2011 በማርዮት ኮረም ሆቴል ውስጥ እንዳለው ሲያስታውቅ፣ ለማረጋገጥ ባደረግነው ሙከራ በእለተ ሰንበት ምክንያት የሽያጭ ክፍሉ ዝግ ስለሆነ አልተሳካልንም። መርጃውን እንዳገኘን ልናጋራችሁ እንሞክራለን። ነገር ግን ቁጥር 2 ቡድን ትላንት እንዳካሄደው ስብስብ ሁሉ የትግራይ ነጻ አውጪ ቅጥረኞችም ስብሰባ የመጥራትና የማካሄድ መብታቸው የተጠበቀ ነው። ያለውን መንግሥት የሚደግፍና አሊያም የእድገት እቅዱን ለማወቅና በትውልድ ሀገሩ የሚካሄደውን ግንዛቤ ለመጨበጥ የመካፈል መብቱ የተጠበቀ ነው። የተሳተፈ ሁሉ ወይንም በሀገሩ ቅሪት ማድረግ የጀመረ ሁሉ የሕዝብ ጠላት አድርጎ መፈረጅ ስህተት ነው። የፓለቲካ ልዩነቶች እንደተጠበቁ ሆነው ለሀገር ልማትና እርዳታ ማድረግ ይቻላል። እንደዚሁም ደግሞ ያለውን አስተዳደር ችግሮችን እንዲቀበልና እንዲያሻሽል መንገዶችን መቀየስና ለዚያ መታገል የሁላችንም ግዴታ ነው። አንድ ወጥ የሆነ የጋራ እቅድ ሳይጨበጥ በተናጠል የሚደረግ ሩጫ ከምርጫ 97 መገንዘቡ መልካም ነው። ብዙዎቻችን በእድሜ በገፋን ወቅት የአቅም አድማሳችንን መለካት ያቃተን ይመስል እኛ ብቻ ካልመራን ወይንም እኛ ከሌለንበት ሁሉም መፍረስ አለበት የሚል የጨቅላ ጨዋታ ያልወጡትን ወገኖቻችንን ስናይ ያሳፍረናል።


በሰለጠነ አለም እየኖርን አህጉር ተሻግረን ጠመንጃ ለመማዘዝ የረፈደብን መሰለን። ፍትህና እኩልነትን መጀመርያ ከቤታችን ከዚያም አሳድገን በኮሚኒቲያችን ብሎም በሀጉር ደርጃ እንኳን ብናደርሰው የትግሬ መንግስት ከደጁ ሳይደርስ ሊንበረከክ ይችላል። ዋናው ነጥብ መደራጀትና ሪሶርሶችን በአግባቡ አቀናጅቶ መጠቀምን ልምድ ማድረግ መጀመሩ ለኛም ሆነ ለደረሰው ትውልድ ለማስገንዝብ እንወዳለን። ከቁጥር 2 ቡድን ካካተትነው ውስጥ ደጀኔ የተባለው በትላንቱ ስብሰባ በከተማችሁ ውስጥ እየተካሄደ ላለው ወቅታዊ ሂደትና የወገኖች መብት መረገጥን በመደገፍ አስመራጭ ኮሚቴውና ቦርዱ የተስማሙበትና ያለቀ ጉዳይ ነው በማለት እርሱን ፈቅዶ ያንበረከከና ሊኣሎችም እንዲበረከኩ ያደረገ የውስጥ ጠላታችሁ ነው። ትላንትና ቅንጅት በሌላ ጊዜ ደግሞ በሌላ ስም እየለዋወጠ ሌላ ሕዝባዊ ድርጅት እንዳያብብ የሚያኮላሽ አንዱ ጸረ ሕዝብ በመካከላችሁ የሚሽሎከለክ ጉድ ነው።

ትላንትም ሆነ ዛሬ የቅንጅት ስምና ማህተም በመጠቀም የሀሰት ሰነድ በማዘጋጀት በመሸጥ መተዳደሪያው ካደረገ ቆይቷል። እነዚሁ የሀሰት የፖለቲካ ጥገኛ ጠያቂዎችን መጠቀሚያ ባደረገበት ወቅት የተማረው ሌላው ወንጀል ሥራ ቢኖር አዲስ እንደሙያ የያዘው ኢ-ሐርሞኒ አይነት የፍሮጅ ጋብቻ በማድረግ በጋብቻ የመኖሪያ ፈቃድ አስወጣለሁ እያለ የጀመረው ሥራ ነው። እንዲ አይነቱ ሞላጫ ነው እንግዲህ ከሱ የተሰለፉ ሀቀኛ ታጋዮችን አንገት የሚያስደፋ ፣ እንግዲህ እንዲ አይነቱ ነው ለራሱ ጥቅም የታወረና የመረዳጃ ማህበሩ ችግር በማጣጣል ወደ ትግሬ ነጻ አውቼጪ የዳላሱ ስብስብ ተቃዋሚ ዝግጅት ላይ ብቻ እንዲተኮር ያደረገው ለግል ጥቅሙ ነው። በእርሱ የዳላስ ጩኸት የአዲስ አበባው መንግሥት ወይ ፍንክች! እርሱ ግን ተቃዋሚ በማለት በሀሰት ገንዘብ ለመስራት ብቻ ነው። ሌላው የእርሱ ቢጤና እኩዩ የሆነው ሰሎሞን አባተ የሚሉት ቀደም ሲል በፓርኪንግ ሥራ ሲወሰልት የነበር ከዚያም በሊሞ ብሎም በሱቅ የሚተዳደር የሀሰት ታጋይ ነው። በዛሬው የራዲዮ ፕሮግራም ላይ እንደጠቀሰው ’ጠላትማ ጠላት ነው አስቀድሞ መግደል አሾክሻኬውን ነው’ ብሎ ያለውን በየትኛው ጦር ኣንዳዘመተ ባናውቅም አቋም የሊለውና ለጊዜዊ ጥቅም ያደረና አንገብጋቤ የሆነውን የወገኖቻችንን መረዳጃ ማህበር መስተካከል ሲገባው፣ ባህር ዘሎ ነገር እንደማይደርሱበት አውቆ እንደው ዘራፍ ማለት ይስብላል።

አዎን ከስብሰባው አዳርሽ ውጪ ሕግን የተከተለ ተቃውሞ መውጣት ይቻላል፣ በአዳራሹ ውስጥም ገብቶ በመልካም ክርክር እነሱንም አስረድቶ የተሰበሰበውንም አሳምኖ የስብሰባውንም አላማ ማክሸፍ ሲቻል እንዴት በሀሳብና በአቋም በመለያየት የዛቻ ድምጽ በራስ ወገን ላይ በራዲዮ ይሰነዘራል። እንደነዚህ አይነቱ ነውን ፓለቲካውን ይመራል በማለት ተስፋ የሚጣልበት ወይስ የህዝቡን አቋምና ውሳኔ ስለመደፈሩ የተስማውን ወገናችንን ትግል በመላ (በዘዴ) ማስለወጥ ነው ትክክል?    

የሕዝብን አንድነትና ትግልን የሚቦረብሩ ይጋለጣሉ!
አንባገነን የመረዳጃው ማህበር መርዎች ይወገዳሉ!
አጽራረ ቤተክርስትያኖች በደሙ ይቃጠላሉ!

እርሶስ ምን ይላሉ?

        

Friday, March 25, 2011

ምርጫው ተሰረዘ!

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!

ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።


ምርጫው ተሰረዘ!


እንዴት ከርማችኃል? እኛ እግዚሀብሔር ይመስገን በእርሱ ፈቃድመልሶ በዚህ ጦመር ላገናኘን ምስጋና ለእርሱ ይሁን። አሜን።

ባለፈው ጥሁፋችን የፊታችን እሁድ የዳላስና ፎርትዋርዝ የኢትዮጵያን መረዳጃ ማህበር አባላት በወሰኑት መሰረት ታቅዶ የነበረው ጉባኤ በአንባገነኑ የቀድሞና የአገልግሎት ጊዜውን በ12/31/2010 የጨረሰው አመራር አሻፈረኝ ለምልዐተ ጉባኤው አልገዛም፣ ስብሰባውንም አላመቻችም፣ እኔ የምፈልገውንና የጥቅሜ አስከባሪ የሆኑትንና ከኔም ጋር አብረው ሲዘርፉና ሲያዘርፍ የነበሩትን የፈላጭ ቆራጭ ሥልጣን የሚሆን ትረስቲ አቋቁሜ ካልሆነ በስተቀር በማለት በትላንቱ ምሽት በነበረው ካስመራጭ ኮሚቴ ጋር ስብሰባ መገለጡ ከምንጮቻችን ያገኘነው መሆኑን ልንካፈላችሁ እንወዳለን። ባለፈው እሁድ በሕብረተሰቡ የሬዲዮ ፕሮግራም ላይ ሁለቱም ወገኖች ማለትም አስመራጭ ኮሚቲውና የቀድሞው የአመራሩ ሊቀ መንበር ከሰጡት ንግግር ማካፈላችን የሚታወስ ሲሆን አስመራጭ ኮሚቴው ከጉባኤው የተሰጠውን ኃላፊነትና በራዲዮ በገለጠው መሰረት ይወጣ ይሆናል የሚል ሙሉ እምነት ሊጣልበት እንዳልቻለና እርሱም እንደቦርዱ እድሜ በማራዘም፤ እራሱን አሉታ ውስጥ ከቶቷል።

በዚህ አጋጣሚ ለፊታችን እሁድ ታስቦ የነበረው ጉባኤና የምርጫ ሂደት መሰረዙን ስንገልጽ ሀዘናችን ጥልቅ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ የቀድሞ ተመራጮችና አጃቢዎቻቸው፣ በተለይም ሊቀመንበሩ ይልማ ፈለቀ በየቦታው እንደሚለው የያዘለት መስሎትም ይሆናል “ ምን ሰው አለ፤ ትራክ ታክሲና ሊሞ ነጂ ብቻ ነው፤ እኛ የሰጠነውን ሁሉ አሜን ብሎ የሚቀበል“ በማለት ደጋግሞ ሕብረተሰቡን ባጠቃላይ የሚያንቋሽሽ፣ ለመሪነት ያልተገባና ያልታረመ ሲሆን፤ እርሱም ቢሆን የሚተዳደረው በነዳጅ ማደያ ሱቅ ውስጥ ተቀጣሪ ሆኖ፤ የሌሎቻችሁን ሙያ፣ የትምህርት ደርጃም ሆነ ግንዛቤ ስላላችሁ ሰርቶ በማደር ከራሳችሁ አልፋችሁ ቤተሰብ የምታስተዳድሩ ብዙዎች እንዳላችሁ እሙን ነው። ሰርቶ አዳሪ ሁሉ በዚህ ሀገር የተከበረ ነው። እርሱና ቢጤዎቹ ምን ያህል ከማህበረሰቡ እንደዘረፉ በውል እስኪታወቅ ድረስ ጊዜ ገዙ እንጂ ከዕውነት እንደማያመልጡ ግልጥ ነው። እውነትነቱን ባናውቅም የዳላሱ አቶነሪ ጀነራል ቢሮ የጀመረውን ምርመራና ማስረጃ ስብሰባ አስመልክቶ ፋይሉን ኦስተን ወደአለው ዋና መስሪያ ቤት ማስተላለፉን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው መጠቆማቸውን ተረድተናል። ሌሎችም ግለሰቦች ተመሳሳይ እርምጃ ሊወስዱ በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ከምንጮቻችን ደርሶናል። እንግዲህ የተናቅከው፣ ትሰራልኛለህ ብለህ አላፊነት የስጠኸው፣ ድምጽህ ያልተከበረው፣ ምን ሰው አለና የተባልከው፣ ምናምን ታክሲ ነጂ የተባልከው፣ ሙያህ የተናቀው፣ ትምህርትህና ዕውቀትህ የረከሰው፣ ዲቪ የጣለው የተባልከው፣ጥሬና እንጭጭ የተባልከው፣ ከፋፍለው ስም የወጣልህ የዳላስና አካባቢው ወገናችን ወንድ አይል ሴት ለመብትህ መቆምና ጉዳዩ የራሴ ነው የምትል ሁሉ የጽዋው ቀማሽ አንተ ነህና፤ እስከ ዛሬ ባንተ ስም መነገዱና ጥቅም ማጋበሱን ስትደርስባቸውና ሀቀኛ የሆኑ ተቆርቋሪዎች ከማህል ብቅ ማለት ሲጀምሩ ለማኮላሸት የጀመሩትን ሴራ ሁሉ መገንዘብ የራስህ የባለጉዳዩ ነውና ፣ ፈረሱም ሆነ ሜዳው ይኸውልህ፤ ለራስህ መቆምና የሚጠበቅብህን ሚና መወጣት ያንተው ነው!

እርሶስ ምን ይላሉ?  

Wednesday, March 23, 2011

የሚታኘከውን አትልቀቁ!

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!

ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።


የሚታኘከውን አትልቀቁ!

እንደምን ከርማችኃል? በእርሱ ፈቃድ ጠብቆ ለዚህ ላበቃን ለልዑል እግዚሀብሔር አሁንም ክብር ምስጋና ይሁን። ወዳጃችን ከዳላስ በስልክ ያበሰረንን ላልደረሳችሁ ልናካፍል በማለት ከቢሯችን ይችን ለመጣፍ ስለፈቀደልን ለእርሱ ምስጋና ይሁን! አሜን።

በዳላስና ፎርት ዎርዝ የኢትዮጵያን መረዳጃ ማህበር አመራር የተመራጠበት የአገልግሎት ዘመን በ12/31/2010 መቃጠሉ የሚታወቅ ነው። ተተኪዎቹን አስመርጦ በወቅቱ ላለመተካት የሚያደርገው ህገወጥ ተግባር አምባገነንነቱን አረጋግጦበታል። ባለፈው ጠቅላላ ስብሰባ በተወሰነው መሰረት የተመረጠው አስመራጭ ቡድን በተቀበለውና በተመደበለት ጌዜ ገደብ አክብሮ እጩ ተመራጮቹን የፊታችን እሁድ በ 03/27/2011 ከዚህ በፊት ጉባኤውን በተደረገበት የሆቴል አዳራሽ ውስጥ ከቀኑ በ4 ፒኤም እንደሚያቀርብ ምንጮቻችን ገልጸውልናል። አሁንም ይህን ግባኤ እንዲሰናከል የቀድሞው አመራር የማይሞክረው እንደሌለም ተገልጦልናል። ቦታው ደብል ትሪ ካምብል ከሚባለው ቁጥር 75 አውራ ጎድና እንዲሁም ካምብል መንገድ መጋጠሚያ ላይ፣ በደቡብ ምዕራብ ወገን የሚገኘው ነው። አምባገነን የቀድሞ አመራር በምስጋና መውረድን የሚሻ ሳይሆን ለመረጠው ማህበረሰብ አልገዛ ባይነትና በግል ጥቅም የታወረ ለመሆኑ የመንኮራኩር ጠበብት የሚያሻው አለመሆኑን በአረቡና በተለይም በአፍሪካ አህጉር ከምናየው መገንዘብ አዳጋች አይሆንምና ሁላችሁም በተባለው ቀን፣ ቦታን ሰአት በመገኘት ግዴታችሁን እንድትወጡ እያሳሰብን፤ ለማንኛውም የኢትዮጵያ ተወላጅና የሕብረተሰቡ አባል የነጻ መብት ነው። ምንም አይነት የአባልነት ግዴታም ሆነ ክፍያ የማይጠየቅበትና ለሁሉም የተሰጠ መብት መሆኑን መተዳደሪያው በግልጥ አስቀምጦታል

ከዚህ ወጣ ስንል ደግሞ ከዚህ በፊት እኛ ቤተክርስትያን አልከሰስንም እያሉ ነገር ግን ከጀርባ ሲያደራጁ የነበሩ ዛሬ በነበረው የፍርድ ቤት ጉዳይ ላይ በይፋ መቀላቀላቸውን አረጋገጡ። ከአሁን በኃላ ኃይሉ እጅጉ ቨርስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ደብረ ምህረት ካቴድራል ደብር በጋርላንድ ቴክሳ ብለን እንድንጠራው ከስፍራው የተገኙት ምንጮች ጠቁመውናል። እንግዲህ እንደዚህ እያለ አጽራረ ቤተክርስትያን ወይንም ቀደም ብለን ያልነው ቀዩ ሰይጣን መውጣቱና ባደባባይ መቆሙ ሁላችንን ቢያሳዝነንም በሌላው በኩል “የሚታኘከውን አትልቀቁ!” ወደ አልነው እርእሳችን ይመልሰናል። እስካሁን ድረስ በመልዕክተኞቻቸው አማካኝነት ደብሩን ሲያደሙ ነበር፣ ዛሬ የሚወስዱት መዳኒት መስራቱን አቆመ ወይንስ መውሰዱን ዝንግተው ይሁን ባይታወቅም ከነዚህ አዲስ ክስ ተቀላቃይ አጽራረ ቤተክርስትያን ውስጥ እንዲህ ጥሪት አለው የሚባል መግባቱ መልካም ነው። እንግዲህ ስንልና ስንወተውት እንደነበር አዲሱ የደብር አስተዳደር ተመራጮች ሳይውሉና ሳያድሩ ውሳኔ በማድረግ የክስ ክስ ባስቸኳይ መመስረት አለበት። ደብሩ በሕጉ ሂደት ምክንያት በንዋይ የሚያጠፋውን መተክያ አሁን መጥቷልና የሚታኘከውን አትልቀቁ እንላለን።

እንግዲህ ቸር ወሬ ያሰማን! ለበዐለ ትንሣኤው በሰላም ያድርሰን!

እርሶስ  ምን ይላሉ?  

Sunday, March 20, 2011

የዳላሱ አስመራጭና መራጭ መብትና ሥልጣን

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና! 

ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።


አቤቱ የሠራዊት አምላክ ሁሉን የፈጠርክ አንተ ነህና ልዑል እግዚሀብሔር ሆይ ድክመታችንን አትቁጠርብን፣ በደላችንንም ሁሉ አስተስርይልን፣ የጀመርነውን ጾምና ጸሎት ተቀበልልን፣ ለትንሣኤ በዐል በሰላም እንድንደርስ ፈቃድህ ይሁንልን። በዚህ ወቅት ምንም አይነት ጥሁፍ ለማድረግ ፈጽሞ አልፈቀድንም ነገር ግን ሁኔታዎች አስገዳጅ ሆነው በመገኘታቸው በዳላስ ለሚገኙ ወጎኖቻችን የማካፈል ግዴታ ስላለብን በሚል ስለሆነ ብቻ ከቅንነትና በእውነተኛ መቆርቆር ተደርጎ ከዚህ በታች ያለውን እንዲነበብልንና ግንዛቤን እንዲጨበጥልን እንጄ፤ በዚህ ጥሁፍ በጦምና በጸሎት ለምትገኙ ወጎኖቻችን እንቅፋት እንዳንሆን የጀመርነውን ጥሑፍ እርሱ ፈጣሪ ይምራን! አሜን።

የዳላሱ ቅዱስ ሚካኤል እጅጉን በሚደነቅ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝና ብዙውን ምዕመን እየተባረከበት እንደሚገኝ ከሚደርሱን ዘገባዎች በጣም ደስ እያለን ለዚህ ፈቃዱ ላደረገው ለልዑል ግዚሀብሔር አሁንም ክብር ምስጋና ይሁን። ወጣቱ ዲያቆን እያደረገ ላለው ሥራዎች እያደነቅን አባቶችም በተለያየው ስጦታዎቻቸው ምዕመኑን ማገልገል ብቻ ሳይሆን እየባረኩት ይገኛል። ያርፋጅ ቁጥጥር ባይኖርም ምዕመኑ በተቻለው ሁሉ ቀደም በማለት ከበረከቱ እንዳይጎልበት ለመጠቆም ያዳዳናል።

ዋንኛው የዛሬው መልዕክታችን ያነጣጠረው በዳላስና ፎርትዎርዝ የኢትዮጵያን መረዳጃ ማሕበርን አስመልክቶ በዛሬው የማሕበሩ የራዲዮን ስርጭት ላይ በእንግድነት የቀረበው የዚሁ መረዳጃ ማሕበር ሊቀ መንበር ሆኖ ሲሰራ የቆየውና የአገልግሎት ጊዜውን በDecember 31, 2010 የጨረሰውና 7 አባላቱ ለሚተካቸው አዲስ አባላት በ01/01/2011 ማስረከብ የሚገባቸው ፣ አንባገነን የማን አለብኝና በገሀድ የሕዝብን ድምጽና ውሳኔ አልቀበለም በማለት ሥልጣንም ሆነ ኃላፊነት በመተዳደሪያው ደንብ ሳይኖረው፤ የሕብረተሰቡን መብትና ሥልጣን በፍጹም በተቃረነና በሕግም አግባብነት በሌለው መልኩ፤ ሕዝቡ ተሰብስቦና መክሮ የወሰነበትን የአስመራጭ አባላትን መብትና ሥልጣን በመጋፋት ለ03/27/2011 የተመደበውን የአስመራጭ አባላት የሥራ ውጤት ለማደናቀፍ እንቅስቃሴ መጀመሩን በራዲዮኑ መግለጫ ሰጥቷል። በተቃጠለ የሥራ ፈቃድ እርሱና ግብረአበሮቹ ለምን ከሕዝብ ድምጥ በላይ ለመንቀሳቀስ አስፈለጋቸው? ምንስ የፈሩት ነገር አለ? ባለፈው አጥቃላይ ስብሰባ ለምን ያቀረቡት አጀንዳ ወደቀባቸው? የግል ጥቅማቸው ተነካባቸውን? ለምን ከአስመራጭ አባላት ጋር ያልተፈጠረውን ሀሰት በራዲዮ መግላጫ ለመስጠት አበቃው? ከእርሱ በኃላ ለምን ያስመራጭ አባላት በሬዲዮ ምንም የቀን ለውጥ እንዳልተደርገና ሥራቸውን ለማቅረብ  በ03/27/2011 ዝግጁ ነን ብለው በተወካያቸው በዚሁ የራዲዮ ሰአት ውስጥ ገለጹ? ወዘተ……. ብለን ጥያቄዎችን ለማስተናገድ የጉዳዩ ባለቤት ለሆናችሁት እየተውን፤ ከራዲዮ ክፍል ዝግጅት አስተናጋጆች የተሰጠውን ወገናዊና ጨለማዊ አቋም ሕብረተሰቡን ብቻ ሳይሆን ሁላችንም አሳዝኖናል። ሽማግሌ ብሎ አስተያየትስ ለምን አስፈለገ ወይንስ እንደርሱ ጸጉርን እየቀቡና በሕብረተሰቡ መኃል ገብቶ መርዘኛ መሆንን ነውን? አሊያም የትግሬ ነጻ አውጪ ቅጥረኝነቱን በገሀድ ገልጦም ላመኑበት ራዲዮኑን መጠቀም በግልጥ ማን ከልክሎት ነው? ሁሉም ቅጥረኛ ብቻ አይደለም እንዴ በግል ጥቅም የታወረ? ለምን ብዙ ታናግሩን፣ ወጣቱ በመረዳጃው ማሕበር ሥር እንዳይደራጅ ያደረገው አንዱና ዋናው ምክንያት ለተተኪው ቦታ አለመልቀቅ አንዱ ችግር ለመሆኑ ከዚህ በላይ የተጠቀሰው የተመረጠበት ዘመኑ አልቆና ተቃጥሎ ላለመልቀቅ የባጡን የሚቀባጥረውና በእነቶኔ የሚመራው እንደ ሙባረክ በአመጽ ካልወረድኩኝ የሚልና እርሱን የሚያሽሞነሙነው የራዲዮ ዝግጅት አቅራቢ አብሮ መክሰም የግድ ነው። 

ራዲዮውን ከነካን አይቀር ሊቢያ ካሉት የኢትዮጵያ ተወላጆች ጋር አወራን ብለው የዘገቡት ሀሰት ነው። ኢትዮጵያዊ ብቻ ሳይሆን ጥቁር ቀለም ያላቸው ሊቢያኖች ብዙ ናቸው። ወደ ሊቢያ የስልክ መስመር አግኝቼ አናገርኩኝ የተባለው ፍጡም ሀሰትና የሌለ ወሬ ነው። እንኳን ግለሰብ አይደለም ድርጅቶችና ኤምባሲዎች የመገናኛ እክል አለባቸው። ቀይ መስቀልም አለው። ከውጪ ይዘው የገቡ የውጪ ዜና ማሰራጫዎችና የተወሰኑ ሀገሮች ብቻ ናቸው። ውሸት ይቁም። በነርሱ ስም ገንዘብ አሰባስቦ መብላት፤ በሌላው ሰቆቃ መኖር ልምድ ያካበቱ መቼ ይሆን የሚታቀቡ? ሰሞኑን ከሰማነው አሳዛኝ ዜና የአንድ ወጣት አሟሟት ልባችን ቢነካም በዚሁ ዙርያ ለቀብሩ የሚያስፈልገው ዝግጅት ከተጠናቀቀ በኃላ ፤ በሟች ቤተሰብ ስም ገንዘብ እንዲሰባሰብ የተጫወቱት ግለስቦች ጥያቄው ጥያቄ ሆኗል። ስንቶቻችን የሚከራዩ ቪላዎች በሀገርቤት ይኖሩን? ጥሩ ጡረታ ያለን? ስንቶቻችን ነን ውድ የስፖርት መኪናዎችና አፓርትመንት ኮሌጅ ላሉ ልጆቻችን የምናደርግ? በአካባቢያችን ስንት ችግረኛ ወገኖች ከነልጆቻቸው ባዶ የምግብ ማቀዝቀዣ ያላቸው ወይንም የመብራት መክፈል ያቃታቸው? አሊያም የቤት ኪራይ መክፈል አቅቷቸው በመኪናቸው ውስጥ የሚያድሩ ወይንም መጠለያ የገቡ? እንዲያው በደፈና ቤት ይቁጠርው? ብለን እናልፈው ይሆን። ስለዚህ የራዲዮ ዝግጅት ግለስቦችም የግል ጥቅማቸውን ለመንከባከብ ሲሉ ለጊቶቻቸው ያደሩትና የነሱን አስነዋሪና ሕገወጥ እንዲሁም አምባገነን ተግባር ሲያወድሱና ሲያሞካሹ ማየት ከሌላው ሀገራት የወደቁትና በመውደቅ ላይ ያሉ አምባገነን መሪዎች ዜና አውታሮች የተገበሩትን ተመሳሳይ ሂደትን እየደገሙ እንጂ ለሕብረተሰቡ የቆሙና ለማንም ያልወገኑ አለመሆናቸውን በዚሁ ስርጭታቸው ደግመውና ደጋግመው የብዙኃኑ ድምጽና ውሳኔ ይረገጥ ይታፈን፣ እንደ መድሀኒት ወይንም እንደምግብ ጌዜው አልፎ የተቃጠለበትን expired ያደረገበትን ምግብ ወይንም መድሀኒትን ውሰዱ የሚለውን ዲስኩር አሁኑኑ መቆም አለበት። እነርሱ ከፈለጉ ለራሳቸው ያድርጉት ብለን ለማለት እንኳ የማንዳዳው ፣ ነቀርሳ ነውና እራሳችሁን በጥቅም አትደልሉ። ለቦታው ብቃት እንደሌላችሁ ሀቅ ቢሆንም ሕብረተሰቡን አታወናብዱ፣ ቦታውን አሁኑን ልቀቁ። በስውር የምታደርጉትን ሕገወጥ ተግባር ዛሬም በራዲዮ advocate በማድረግ የሕዝብን ድምጽና ውሳኔ ይሻር የሚለውን አጀንዳችሁን ይዛችሁ ጥፉ።

አምባገነን የሆኑትና ተርማቸው የተቃጠለው የመረዳጃው ማህበር አመራርና ሎሌ ባለፈው ጠቅላላ ስብሰባ ጥሪ ሊሳተፉ የመጡትን የህብረተሰቡን አባላት በመለያየት የማይፈልጓቸው ግለስቦችን ብቻ በመለየት በሌለ የማህበሩ መተዳደሪያ ህግ አባል አይደላችሁምና በምርጫ አትሳተፉም በማለት የመለሷቸው ግለስቦች ወደ ቴክሳስ ግዛት የሕግ አስከባሪ ኃላፊ ቤሮ መብታችንን ከሕግ ውጪ ተደፍሮብናል በማለት ያቀረቡት ቅሬታ ተቀባይነትን አግኝቶ ምርመራው የተከፈተ መሆኑን ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸው የደረሰን መሆኑን ስናውቅ፣ ይህ ጉዳይ በቶሎ ካልተቋጨ ብዙ የሚያነካካ አሊያም ድርጅቱን የሚያዘጋ ደርጃ ያደርሳል የሚል ግምት ቢኖረንም፤ በኛ አስተሳሰብ ድርጅቱ ብዙ የሆነ የብሔራዊና የክልል ሕጎችን በመተላለፍ የሚንቀሳቀስ ስለሆነ ባስቸኳይ ካልታረመ መዝጋቱ አይቀሬ ነው።

አስመራጭ ኮሚቴ የተባለውም ከውስጡ ካቀፋቸው የኮሚቴ አባላት ውስጥ ገለልተኛ ያልሆኑና ቀደም ሲል አመራሩን ጨብጠው ካጨማለቁትና አሁንም ለአንባገነኖችና ለድርጅት የወገኑትን ያቀፈ ነው። እንግዲህ ምን ያህል አዲስ ሀይል ሆኖ ዘመናዊ ትምህርትና ልምድ ያቀፉትን ከሁለቱም ጾታ ያሉትን ወጣቶችን ይዞ ይቀርብ ይሆን? እንደኛ ለረዥም ጊዜ በዚህ ሀገር የቆየውና የጠለቀ እውቀትና ትምህርት ያካበተው የጊዜውን ጥያቄ ማስተናገድ የተሳነውና ወግኖ ያለው ትውልድ ከመኃል መውጣትና ለተተኪው መልቀቅ ግዴታችን ነው። እረኛም ሆንክ ሞፈር የጨበጥክ ፣ ሚልሻም ሆንክ ወታደር፣ ቤሮክራትም ሆንክ ምሑር፣ ፖለቲከኛም ሆንክ ካድሬ፣ ነጋዴም ሆንክ ቱጃር፣ ሴትም ሆነ ወንድ፣ ወዘተ…….. የሩቅ ተመልካችም ሆነ ተሳታፊ የነበረ ሁሉ እርስ በራስ ስትባላና ስትተረማመስ ለዚህ በቃን። ዛሬም ደግሞ መመረጥ ከደማችሁ የተዋሀደውን የሙጥኝ መርዝ addiction የሆነባችሁ ሲሆን በባለሙያ ታይታችሁ አስፈላጊውን እርዳታ እንድትሹ ስንመክር፤ ጊዜው መሽቶባችሁ የተሸፈናችሁበት ተገልጦ ለጠበል እንዳታውኩ ይሁን።

እርሶስ ምን ይላሉ?