ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም።
አንጀቴ ቅቤ ጠጣ!
ከውስጡ ትኩስ ዜና ስለ አቶ ብርሀን የመልቀቂያ ደብዳቤ የተሰጠውን አክለንበታል።
የተወደዳችሁ የገጻችን አንባቢዎች እንደምን አላችሁልን? በእርሱ ፈቃድ ደግመን ብዕራችንን ለመጭመቅ ፈቃዱን ላደረገልን ለልዑል እግዜአብሔር ክብርና ምስጋና ይሁን። አሜን። ስለ ታላቁ ስምህ አሁንም ክብር ምስጋና ይሁን።
በዳላስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ደብር የቅዱስ ያሬድ መንፈሳዊ ተቋም ከፊታችን ሀሙስ ጅላይ 7 እስከ 9 2011 ድረስ በደብሩ ውስጥ የሚያኬደው መንፈሳዊ ጉባኤ በአይነቱ ለመጀመሪያው ጊዜ በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ ተወላጆች ዘንድ ታላቅና ታሪካዊ ቦታ የሚሰጠው ነው። ይህ ተቋም በዚሁ ከቀጠለ ወደፊት ሀገር በቀል የኦርቶዶክሳዊ ዕምነት አገልጋይና ተረክቦ ጠባቂ የሚሆኑ የዕምነቱን ሊቃውንትና ካህናትን ማፍለቂያ ምንጭ ይሆናል የሚል ከፍተኛ ዕምነትን ሊያስጨብጥ የሚያስችል መሰረትን ይጥላል የሚለውን ራዕይ ያደርሰናልና ሁላችንም በያለንበት በጸሎታችን ሁሉ ልናስበው የሚገባን መሆኑን ገጻችን ታሳስባለች።
ከታሪክ እንደምንረዳው ከሆነ ደብሩ በዳላስ ኪንግ መንገድ ላይ ከሚገኘው የቀደምት ስፍራው አሁን በጋርላንድ ውስጥ በሰሜን ጁቢተር መንገድ የተዛወረበት ምክንያቶች ውስጥ አበይቱ ስለ ታዳጊ ልጆቻችሁ እንደሆነ ነበር። በየጊዜው ከሚመረጡት የደብሩ የስራ አመራሮች አብዛኛዎቹ ተደጋግመው የሚመረጡት አበይት ምክንያት ሆኖ ወደ አዲሱ ሕንጻ ያስገዛቸውን ጉዳይ ላይ የሰጡት ትኩረትና ያስመዘገቡት እድገት ለራሱ ምስክር ስለሚሆን ግምገማውን ለሚመለከታቸው እየተውን፤ ለወጣቱና ለህጻናቱ ተብሎ የተቀጠረው አዲሱ መምህርና አዲሱ የአስተዳደር አባላት እያስመዘገቡ ያሉትን ልዩነት በኛ ብዕር ብንከትበው ደግሞ ወገነኛ ያሰኘናልና እናንተው ገምግሙት የምንለው። ምክንያቶችን ዘርዝረን የአነጻጸርንበትን ነጥቦች ማቅረብ አይገደነም ነገር ግን የቀደሙት አመራሮች ምንም ሰሩ ምንም ባላቸው የዕውቀትና የአመራር ብቃት ለተተኪው አድርሰዋልና የአሁኖቹን ራዕያቸው ደግሞ ምንድን ነው ? የሚለውን እናንተው ዳላሶች ናችሁና የምትኖሩት፤ አብራችሁ በቅንነት ከአመራሩ ጎን በመሆን ለተተኪና ተረካቢ ልጆቻችሁ የሚጠበቅባችሁን በምትችሉት ሁሉ በመተባበር ለሀይማኖታችሁ ቀጣይነት አጋዥ በመሆን የበረከቱ ተካፋይ እንድትሆኑ ክርስትያናዊ ጥሪዋን ገጻችን ታቀርባለች።
ገጻችን በየጊዜው ከሚደርሷት መልዕክቶች ውስጥ አንዳንድ ጥቅማቸው የተነካባቸው አሊያም ከኛ ውጪ ወይንም እኛ ባልነው በማለት መልካምና ትሁት የሆኑትንና ያለምንም ጥቅም በበጎነትና በቅንነት እንባረክበታለን ብለው የሚያገለግሉትን ምዕመኖችን በተለያየ መንገድ ለማወክ እንቅፋቶች እየሆኑባቸው ይገኛሉ። እነዚህ ከውስጥ ሆነው የሚያውኩትን ልቦና ሰጥቶና መክሮ እንዲመልሳቸው ለፈጣሪ እየለመንን ፤ ቅን አገልጋዮችንም ትግእስትን እንዲሰጣቸውና በረከቱን እንዲያበዛላቸው ፈቃዱን ያድርግልን እንላለን። የወጣቶቹን ጉባኤ እንዲሳካ ለተሳተፉት ሁሉ እግዜአብሔር ይክፈላቸው፣ ልጆቻችንንም ይባርክልን፣ አጽራረ ቤተክርስትያንን ያስታግስልን። አሜን።
ከዚህ እልፍ ስንል ደግሞ የዳላስ ኢትዮጵያ መረዳጃ ማህበር የጁላይ 3 እሁድ የሬዲዮ ዝግጅትን በኢንተርኔት ለመስማት የሞከርነውን ድራማ አስቂኝና አሳዛኝ ነበር። ብዙ ጊዜ ገጻችን ያስጨበጠቻቸው እውነታዎች ዛሬም እየተደገሙ በመሆናቸው ‘አንጀቴ ቅቤ ጠጣ!’ የሚለውን ዘይቤ ያስታወሰን እውነትነቱ መዳገሙ እንጂ አስደስቶን አለመሆኑን ልናሰምርበት እንፈልጋለን።
ዝግጅቱ ጥራት የሌለው ብቻ ሳይሆን ብቃት ያጣ አስተናጋጅ ያቀረበው መሁኑን ያደመጠው ሁሉ ዋቢ ይሆነናል። ከሁሉም በላይ ሬዲዮኑ የማን ነው? ኃላፊና ተቆጣጣሪስ አለውን? የሚቀርቡትንስ ዝግጅቶች የሚገመግመው ማነው? አሊያስ በጣት የሚቆጠሩ የሬዲዮ መናገሪያውን ይዘው እንዳሻቸው የሚፈልጉትን መደስኮሪያ መሳሪያቸው ይሆን? ወዘተ……የመሳሰሉትን ጥያቄዎች የሚመለከታቸው የመረዳጃ ማህበር አመራሮችን መስሎ ስለማይታየን ማን ይሆን የሚመልሰው? የሚለውን አንባቢዎቻችን የቤት ስራ ይሁናችሁ እንላለን።
የመረዳጃው ማህበር ተመራጭ ያደረገውን የፊታችን እሁድ የስብሰባ ጥሪን አስመልክቶ ተቃራኒ የሆነ ዲስኩር ያደረገው ግርማ ንጉሴ የተባለው በምሬትና በቁጭት የተመራጩን ንግግር አጣጥሎና አዋርዶ የሰጠውን መግለጫ የለየለት ጸረ መረዳጃ ቅስቀሳ እንደነበረ አስደምጦናል። ቀደም ሲል መረዳጃ ማህበሩን አፍነው ከሚመዘብሩት ውስጥ አንዱ የሆነውና በታቀደው የአመቱ የኢትዮጵያ ቀን በዓል ተሳትፎ የግል ጥቅሙ እንደሚቀርበት ከወዲሁ በመረዳቱ ከነግብረ- አበሮቹ የከፈቱት አዲስ ዘመቻ ነው። ስለዚህ ግለሰብ ቀደም ባሉት መጣጥፎቻችን ውስጥ ብዙ የተካተተ ስለሆነ እንደ እነዚህ ላሉት ግለስቦች መረዳጃ ማህበሩና ወገኖቻችን ከወዲሁ ነቅተው መዘጋጀት ይገባቸዋል።
ከዚሁ ጋር ተያይዞ የስብሰባውን ጥሪ ያስደመጠው የመረዳጃ ማህበሩ ሊቀ መንበር ብርሀን መኮንን የተባለ ሲሆን፣ ከምንጮቻችን እንደተረዳነው ከሆነ ይህንን የስብሰባ ጥሪ አስመልክቶ ቦርዱ ምንም አይነት ስብሰባና ውሳኔ አለማድረጉንና ምንም አይነት ቃለ ጉባኤ ያልጨበጠ መሆኑን፣ በግሉ ያደረገው ጥሪ ነው በማለት ሌሎች ተመራጮች መናገራቸውን አስምረውልናል። በዚህ የራዲዮ ስርጭት ላይ ከተደመጠው ጋር ሌላው አቅራቢ ስለ በትሩ ገብረእግዚሀብሄር የኮሚኒቲ ጀግና የሚል እውቅናና ሽልማት መደረጉን ነበር። ይህች ገጽ ከዚህ በፊት የግለሰቡን አስነዋሪ ምግባርና በቴኔሲ ፍርድ ቤት ከነባለቤቱ የተወነጀለብትን በቀደምት ገጾቿ ማስነበቧ ይታወቃል። በዳላስም የተለያየ ግብረ- ሰናይ ድርጅት ስሞችን በመጠቀም አልፎም በወገኖቿችን ስም በመነገድ እንጂ በዳላስ አካባቢ ለሚኖሩት ወገኖቿችን ያበረከተውና ለኮሚኒቲ ጀግና ተብሎ የሚያበቃው ያየነው አንድም ጠብታ የለም። እርሱና የጥቅም ተካፋዮቹ ጥቂት ግለሰቦች የሚቀቡት ስያሜ ነው ሲል ምንጫችን አስረድቶናል። አሁን ደግሞ አዲስ የተመረጠው መረዳጃ ማህበር ቦርድ ሊቀ መንበርም ሕብረተሰቡን በመወከል በዚህ ግብዣ ቦታ መገኘቱን ራዲዮው ማስደመጡ ይህ ሰው ማነው ወደሚል ግምገማ ጋብዞናል። በዚህም መሰረት ብርሀን በሚል መጠሪያ የተመረጠው ግለሰብ ጥንድ ስም ያለው ለመሆኑ ከመረዳጃው ማህበር ድህረ ገጽ ለመረዳት በቅተናል። ስሙም ማክ መኮንን ነው። እንዴት በሁለት ስም ይጠራል? ለምንስ አስፈለገ? የሚለውን ጥያቄ ላንባቢ እየተውን የተጓደኛቸውንና አብሮ በአላቸውን ያዳመቀላቸውን በማስተዋል ሊታይ ይገባዋልና የወደፊቱ የድርጅቱን ጉዞ በዚህ አይነት ግለሰብ አመራር ስር ለመተንበይ አያዳግትም ያሰኛል።
የአስቸኳይ ስብሰባው አላማ እንደተደመጠው ከሆነ የኢትዮጵያን በዐል ቀን አስመልክቶ ቢሆንም በመረዳጃው ማህበር ድህረ ገጽ ላይ ቀኑንም ጨምሮ እንደሚከበር የተወሰነ ሲሆን፤ በግሉ የጠራው ስብሰባና የግርማ ዲስኩር ተዳምሮ ምን እየተሰራ መሆኑና አዲሶቹም ተመራጮች ከድጥ ወደ ማጡ እየተጓዙ መሆናቸውን ያሳያል። በሌላ በኩል በድህረ ገፁ በተቀመጠው መሰረት የሬድዮ ዝግጅቱ የመረዳጃ ማህበሩ መሆኑን ሲያስነብብ፤ አቅራቢዎቹ ግን የግላቸው በማድረግ ያሻቸውን እንደሚያደርጉና ለመረዳጃ ማህበሩ አመራር ውሳኔ እንደማይገዙና ተጻራሪ ዘመቻ እንደሚያደርጉ ግርማ የተባለው ግለሰብ በ07/03/2011 ያስደመጠው ጉልህ መረጃ ነው። ስለዚህም መቼ ነው ሕብረተስቡና መረዳጃ ማህበሩ እውነተኛ የሬዲዮ ባለቤትነታቸው የሚታወቀው? ውይስ ለጥቅም ሸጠውታል? የሚያሰኘው። ሌላው ከገጹ ላይ የታዘብነው ቢኖር እድሩን አስመልክቶ ተመሰረተ የተባለውና በመረዳጃው ማህበር ስር ነው የተሰኘው የተባለበት ወቅት መረዳጃው በሕግ ፈርሶ እንደነበር ከዚህ በታች ያለውን መረጃ ማየቱ ጠቃሚ ሲሆን፤ ድርጅቱም ቤሆን በገጹ ለምን ይህንን አልገለጸም? በመረዳጃው ማህበር ስር እንዴት ሕገወጥ ጋብቻ ተደረገ? በመተዳደሪያው ሕግ ላይስ ለምን በግልጽ አልተቀመጠም? እድሩ በሕግ መሰረት በመረዳጃው ማህበር ስርና አካል ከሆነ እንዴት አድርጎ ነው ለአባላቱ እርዳታን የሚሰጥ? ምንስ ሕጋዊ ከለላ አለው? ወዘተ……..

ሌላው መረዳጃ ማህበሩ በስሬ አቅፊ አለ የሚለውና እራሱን ግብረ-ሰናይ ድርጅት ነኝ የሚል ስለ ዐይን የተቋቋመና ከኤትዮጵያ ዐይን ባንክ ጋር ትስስር አለኝ የሚለውን ድርጅት አስነብቦናል። በየጊዜው አዳዲስና የመረዳጃው ማህበር አባላት ተሰብስበው ባልወሰኑት ላይ ጥቂት ግለሰቦች የሚፈጽሙት ሕገ ወጥ ጋብቻ ከመተዳደሪያ ደንቡና ሀገሪቱም ካወጣችው የግብረ-ሰናይ መተዳደሪያ ህጎች ተጻራሪ ተግባር መሆኑን ተረድተውት ይሆን? ወይስ በዳላስ አካባቢ ነዋሪ የሆኑት ወገኖቻችን መካከል እውቀትና ማስተዋል ያለው ማንም የኢትዮጵያ ተወላጅና ድርጅቱ የሁላችንም ነው ብሎ የሚነሳ ወንድ ወንድም ወይስ ሴት እህት ይጥፋ! ወይስ መሀይምና ደንቆሮ ብቻ ይሆን ብለን ለማስመር ባንዳዳም ጉዳዩ አስቸኳይና ታላቅነት ያለው ነው እንላለን። የሊቀ መንበሩን የትምህርት ደርጃ አጣርተን ባናውቅም ለጊዜው ቦርዱ ካቀፋቸው ውስጥ 2 የዶክተርነት ዲግሪ ያላቸውን ድሀረ ገጹ አስነብቦናል። የክብር ይሁን የዕውቀት ዲግሪ እኛ እስከምናውቀው ድረስ አምሃ የተባለው ግለሰብ ማንኛውም አይነት እንደሌለውና ከሚሰራበትም መስሪያ ቤት ያረጋገጥን ስለሆነ መረዳጃው የሀሰት ማዕረግ መቀባቱን ቢያርም ስንል፣ ስለሌላው ዶክተር ምርምራችንን ስላልጨረስን የምታውቁ ካላችሁ ብታካፍሉን እንወዳለን። እኛም ትምህርት ቤታቸውን ካወቅን እናረጋግጣለንና የዕውቀት ገብያቸው በሰጣቸው ደርጃ ሁሉ በቅን ከወገኖቻቸው ጎን ተሰልፈው ለሚቸሩ ሁሉ ገጻችን ምስጋናና አድናቆታን ለመለገስ አትቆጠብም። እንቅፋት ቢመታቸው እንኳን ትደግፋለች፣ አስፈላጊም ሲሆን እርማት ትለግሳለች ፣ ለመሻሻልም የሚጠቅሙ ጎኖችን ታካፍላለች፣ በጥፋቶች ላይ ትተቻለች፣ ተመሳሳይ አስተየየትና ነቀፌታዎችንም በእራሷ ላይም ትቀበላለች።
እንደተለመደው እርሶስ ምን ይላሉ ብለን ከመደምደማችን በፊት ከዳላሱ ምንጫችን የደረሰን ትኩስ ዜና እንደሚቀጥለው ይሆናል። ነገር ግን የኛ ዘገባ ሳይለጠፍ በፊት ይህ ቢደርሰንም አሳዝኖናል ሆኖም እራስን ብቁ አድርጎ ከልብ በቅንነት መቆምና በሌሎች ሳይደለሉና 2 ቢላዋ ሳይዙ የተጣለብዎትን መወጣት ያቃቶትና ከወጡበት ዳገት ለምን ተንከባለው ወረዱ? ይህ ሕዝባዊ መረዳጃ ማህበር እንጂ በግሎ የሚያስተዳድሩትና እንዳሻዎ በግሎ የሚወስኑበት የንግድ ድርጅት አለመሆኑን እንዴት ጋረደቦት? ከመልቀቂያ ጥሁፎ እንዳሰመሩት ለሁለት ጌታ የሚያገለግሉና የመረዳጃ ማህበር ቦርዱን የመከፋፋይ ንፏቄ እየተገበሩ መክረሞን በገሀድ አስቀምጠውታል። በተለይም ድርጅቱ እንዳያብብ ሲያቀጭጭ ለኖሩት ባልና ሚስት አንጓችና አዛኝ ሆነው የከተቡት ጥሁፎ የህሊናም ሆነ የዕውቀት አድማሶን ስፋትና ብስለትን መስታወት ሆኖ ለእርሶ ያልታየበትን? ወይም ለከተማው እንግዳና ባይተዋር ሆነው ይሆን? ይህም ባይሆን አመታት ያስቆጠረውንና ቃል የገቡለትን የመረዳጃ ማህበር የገንዘብ እርዳታ በጨበጣ ይዘው እያቁለጨለጩ በወገኖቻችን ሕዝባዊ ድርጅት ላይ ገበጣ መጫወቶ ይሆን? ቃሎንስ ጠብቀው ሊቸሩ ወይስ ቃሎን ሊያጥፉ? የቀድሞ ደም ያሏቸውን ግለሰቦች ማንነት ያውቃሉን? ተርማቸው ካበቃ በኃላ በጉልበት አንለቅም ያሉ መሆናቸውን ምስክር አይደሉምን? የሕዝቡን ምርጫ ምላሽን ከእነርሱ ጋር አብረው ሊድጡና ሊጨፈልቁ የተነሱ መሆኖን ከዚህ በታች ያቀረቡት መልቀቂያ የበተኑላቸው ሁሉ ቦርድ ውስጥ የሌሉና የማይመለከታቸው እንዲሁም እርሶን ከኃላ ሆነው የሚዘውሩት ጌቶቾ ለመሆናቸው ጥሁፎ በሚገባ አስቀምጦታልና አንባቢዎቻችን የራሳቸውን ግንዛቤ ይውሰዱ በማለት ከዚህ በታች ለጥፈነዋል።
---------- Forwarded message ----------
From: Mac Mekonnen
Date: Mon, Jul 4, 2011 at 1:39 AM
Subject: Resignation Letter
To: Ato Endeshaw Chckol , Ato Seyume Argaw , Ato Surafel Belay , Dr Ameha Gebremichael , "Dr. Sisay Teketel" , "Enge. Paulos Berhane" , "Enge. Samuel Kirub" , Wyzero Sene Yohannes
Cc: MAAEC InDFW , Yonas Liben , Hewan Yimer , solomon hamelmal , yilma.zerihun@gmail.com, YILMA FELEKE , ethdaydallas2011@googlegroups.com
To the Board (the original Board)…
I am resigning as Chairman and Board member of MAAEC at the conclusion of the General Assembly, on July 10.
Here are the reasons:
I can only work with one Board. Clearly, we have two Boards within MAAEC. Please refer to all email communications and some decisions made by the “other Board”. Refer to all emails that you received from these ‘Board” members.
I cannot work for or with a mob. Please look at some of the decisions made in the past 2 months. Please refer to all the decisions and direction you have witnessed by these Board members.
I cannot work with Board members who divide the community into two groups…the Old Blood and the New Blood. These Board members forget that the Old Blood was the reason for the position they are in. The Old Blood still flows into the heart of the MAAEC. The heartbeat of MAAEC you hear has the soul of the Old Blood. Having New Blood is good only when one recognizes the wisdom of the Old Blood.
I cannot work with Board members who by nature are designed to ruin what is built. When issues arise from the Old Blood, they will not stop to shut off the voice. Please refer to the genuine request that was made by the ED Committee. Please refer to the sincere comments that were made by the EDIR and other committee members.
I cannot be a witness to see the MAAEC going astray after so much sweat, money, and many scarifies.
I cannot stand a Board member who diminishes a human being. The punishment and treatment that Wizero Yordanos received is unforgivable. The treatment that Ato Daniel received was evil and no apology can heal it.
If requested, all records of events that transpired in the past two months will be available for the General Assembly.
I have extended all my apologies to the people who are hurt by all of the decisions that were made by the “other” Board.
I sincerely thank and apologize (for my departure) to Board members who are good at heart and have done everything possible to point out the ship is going astray…..
My regrets, I wish I were from the Old Blood!
Sincerely,
Mac Mekonnen
Chairman
MAAEC
እርሶስ ምን ይላሉ?