Monday, November 8, 2010

ይድረስ ለነአምን ዘለቀና ለታማኝ በየነ፡

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!

ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።


ይድረስ ለነአምን ዘለቀና ለታማኝ በየነ፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ፺፯ን አስመልክቶ በተፈጠረው ሕይወታቸው የተቀጩት ዜጎችን ለመዘከር በዳላስ ከተማ በግንባር ሀላፊነቱን ወስዶ የተንቀሳቀሰው ግለሰብና አበሮቹ፣ ዝግጅቱን አስመልክቶ ይደረግ በነበረው ሳምንታዊ የቴሌኮንፍረስ ላይ ከእውነት የራቀ መረጃዎችን ሲያዘግቡ እንደ ነበሩ የሚታወስ ነው። በከተማው የረጅም አመታት ነዋሪነትና የነዋሪ ወገኖቻችንን አመኔታና ድጋፍ ይዘናል የሚሉ እነዚሁ በጣት የሚቆጠሩ ግለሰቦች በፖለቲካው አሪና ፖለቲከኛ፣ በቤተ ክርስትያንም ሆነ መስጊድ ሀይማኖተኛ፣ በመረዳጃ ማህበሩም ውስጥ ለወገን ሀሳቢና ደራሽ አድርገው እርስ በራሳቸው ሲመራረጡና ሲሿሿሙ፤ የሀቀኛ ተጋይ ወገኖች መካከል በመስረግ ትግላቸውን በተለያየ ስልት ማኮሏሸት ላይ ብቻ የተካኑ ግለሰቦች ናቸው።

የማይወክሉትና እነሱ የሌሉበት የዳላስ የሙያም ሆነ የግብረሰናይ ድርጅት የለም። በወገኖቻችን ስም የማይመዘብሩትና ለግል ጥቅም የማያውሉትን አለ ለማለት ያዳግታል። ከመረዳጃ ማህበሩ ይዞ የሬዲዮ ክፍሉንም ጨምሮ ያ ሁሉ አልበቃ ብሏቸው ዛሬ ቤተ ክርስትያን የሚተናወጡ ወዳጆች ነው እናንተም እያተረፋችሁ ያላችሁት።  እንግዲህ የናንተ መመሪያ ይኼንን ሁሉ ያካትት እንደሆነ ባይገባንም ለናንተ የሰጡት ቃል ግን ፍጹም ከዕውነት የራቀ መሆኑንና በትላንት ዕለት ያዘጋጁት ስብሰባ የሚገባውን ያህል የቅስቀሳ ስራ ላለመደረጉ ምላሹ እነሱን፣ የነርሱን ቤተሰብና ወዳጆችን ጨምሮ ከነ ተናጋሪዎቹ በቁጥር ከ፵ በታች የሆኑ ብቻ እንደነበሩ በማስረጃ ተደግፎ የተቀመጠ ሆኖ ይገኛል።

ወደፊትም እናንተ ማወቅ ይገባችኃል በማለት የምናሳስበው ቢኖር፤ ይህ ወይም ሌላው ትግላችሁ በእንደዚህ አይነት ደካማና አፍራሽ ግለሰቦች ሰለባ ሆኖ እንዳይኮላሽ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንድትወስዱ ነው።

Sunday, November 7, 2010

የኮብራ እባቡን ያዙልንና እንለፍ ለሚሉ

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!

ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።


የኮብራ እባቡን ያዙልንና እንለፍ ለሚሉ

በዚህ አገር የኮብራ ዘር የሆኑት የእባብ አይነቶች አደገኛ ገዳይ ሀይል ያላቸው በመሆናቸው እጅጉን የተፈሩ መርዛሞች ናቸው። የኛም ገጽ እነዚህን መርዛም እባቦችን ለይተን ስናሳውቃችሁ አብረን ከርመናል።እንግዲህ የነቃችሁባቸውና እያደበያችሁ የጣሏችኃቸው ብዙዎች ናችሁ። ነገር ግን ዛሬም እነዚህን መርዛም እባቦችን ያዙልንና እንለፍ የምትሉ ቂላቅሎች ደግሞ እኛ መርዛም እባቦችን እናንተው ሞክሩና ከመርዙ ካመለጣችሁና ከተረፋችሁ፣ ብላችሁም ከልባሞቹ ጎራ ከገባችሁ እንያችሁ ነው የምንል። የተወደዳችሁ የገጻችን ተከታታዮች እንደምን ከርማችኃል? የእርሱ ፈቃድ ሆኖ ለዚህ ጊዜ ላደረሰን ለልዑል እግዚሀብሔር ክብርና ምስጋና ይሁን። አሜን።

በተለያየ ጊዜ አስረግጠን በደብራችሁና በመረዳጃ ማህበራችሁ ላይ የተደረገውንና እየተደረገ ያለውን ሂደት በሚገባ እያስጨበጥናችሁ አብረን ከርመናል። በየጊዜውም አዲስ አበባ እየደረሱ ለሚዘግቡት መረጃ ካሳ ጥቅማጥቅም ከሚደለሉት ውስጥ ብዙዎቹ ባለ መሬት ሆነዋል። መቃብር ቦታን ሳይቀር እያፈራረሰ እንዲሁም የገጠር መሬት ሳይቀር ለውጭ ባለ ሀብቶች በነጻ ለማለት በሚያስደፍር ዋጋ እየቸበቸበ ያለ መንግሥት፤ ምንም አይነት ለነዋሪው ዜጋ፣ ለአካባቢው አየርም ሆነ መሬት ብክለት ደንታ እንደሌለው ባለፉት ጥቂት አመታት ከአበባው እርሻ ሂደት የጨበጥነውን ዋቢ በማድረግ ስንተች ለወደፊቱ የተሻለ አቀራረብ እንዲሰነጽ ለሚመለከተው አካል የመጠቆም የትውልድ ግዴታችንን ለመወጣት በማሰብ ነው። ካካባቢው ከሚወጡት ዘገባዎች፣ በአበባው ምርት ምክንያት ካካባቢው ለተፈናቀሉት ዘለቄታዊነት የጎደለው የአኗኗር ልውውጥ (ትራንስፎርሜሽን) ፤ በምርቱ ምክንያት የተፈጠረው የተፈጥሮና የአካባቢ ብክለት ያስከተለው ፤ ባምራች ሰራተኞች ላይ የደረሰው የጤና ችግርና በምድረ ከርሱ ላይ ያተረፈው ብክለት በቀላሉ የሚታለፍ አይደለም።

ቤተ ክህነቱ ባለው የአስተዳደር ብልሹነትና የውስጥ ምዝበራ የተነሳ እያንዳንዱ የአዲስ አበባ ደብር ለንዋይ የሚያደርገው ሩጫ ወደ ሌላውም የሀገሪቱ ክፍሎች እንዳይሰራጭ እየተሰጋ ያለ ችግር ነው። አጽማቸው እየወጣ ያሉት ብዙዎቹ ለዚያ ቤተ ክርስትያን በዚያ ቦታ ከምስረታው እስከ ህልውናው በሕይወታቸው የከፈሉት የሚዘነጋ አይደለም። የመሬት ችግር የለብንም የሚል መንግሥት ተርፎት ለባእድ የሚቸረችር እንዴት ይህንን ጉዳይ በዝምታ ያየዋል። እኛ ሀገር አይሰልጥን አንልም ነገር ግን ሁሉም በአግባቡ ቢሆንና ለቀጣዩም ትውልድ በማስተዋል ይሁን ነው የምንል።

በመረዳጃ ማህበራችሁ ስር በሕገወጥ መንገድ የተለጠፈውን እድር በማደራጀት የያዙት የጴንጤ እምነት ካላቸው ውስጥ ወደ አዲስ አበባ ጎራ እያሉ መረጃ ባቀረቡ ቁጥር በጥቅማ ጥቅም እየተደለሉ የሚመለሱትን እያዩ ከእስልምና ሀይማኖት የያዙትም እሽቅድድም እየገቡ ነው የሚል ዘገባ በማየታችን ብዙም አልተገረምንም። አዲስ የሚመረጡ ከተገኙ ፣ እድሩን በፍጹም ከመረዳጃው ማፋታት የቅድሚያ አጀንዳቸው መሆን የሚገባ ነው። በአሁኑ ሰአት ህብረተሰቡ ሁኔታዎችን በሚገባ አላምጦ የጨረሰ በመሆኑ ተግባራዊ ያደርገዋል የሚል ተስፋ እየታየ ነው። በተለይም በአሁኑ ሰአት ለሁለት ተከፍሎ ያለው የመረዳጃው ማህበር አመራር በቅርቡ ራሱን እየቀረጸ ይመጣል የሚል ተስፋ እየታየ ነው። አንዳንዶች አመራር ላይ ያሉት አንጃ እየሆኑባቸው የመጡት በወንጀል ደም እጃቸውን ከታጠቡት ጋር ላለመስራት እራሳቸውንም ለመለየት ወስነዋል። አሁንም በነ ይልማ ፈለቀ የሚመራው የወያኔ ቡድን ቀስ እያለ መሬት እየከዳው ይገኛል። አዲሱ ምርጫም በፊት እራሳቸውን ያገላሉ ተብሎም ይጠበቃል። በሌላ በኩል ከወይዘሮዋ ጦመር እየተጋለጡና እየተመቱ ያሉት ፤ በህብረተሰቡ ስም በብዙ ሺህ ዶላር ሲዘርፍ የነበሩት የነ በትሩ ገ/እግዚሀብሔር ጉድ በማስረጃ እየተቀነባበረ እየተሰራ ለመሆኑ እንደዚሁም የመንግሥትም እጅ በቅርቡ ይገባበታል የሚባልም መረጃዎች ለመመዝገብ በቅተናል።

በሌላ በኩልም የእስስቱ ተፈራወርቅ ቡድን የተከላቸው እነ ፍቅረማሪያም ደረሰ ቡድን በመጋለጡና አዋቀርን ያሉትም ቡድን በመፍረሱ እነ ግርማቸው አድማሴ የጤና ቀውስ ውስጥ ከቶአቸው ይገኛል። እነዚህን መርዛም እባቦች የዳላስ ሕዝብ አንቅሮ ከተፋቸው እንግዲህ ከርሟልና መቃብራቸውን እየተመኙ ናቸው። ሰይጣናዊ ስራቸውን በመልካም ስም ለመሸፈን ሲሉ መለከት ያሉትም ገጻቸው እንደ በረዶ ከደረቀ ከርመ፣ ሀሰታቸው ሁሉ ተጋለጠ፣ እርቃናቸውን መቅረታቸውን ሀገር አወቀው። መሪዎቻቸው የሆኑት በቤተክርስትያኑና በዳላስ ነዋሪ በሆነ የኢትዮጵያ ተውላጆች ስም መነገዱን እንዲያቆሙ የሁላችሁም ግዴታ መሆን ያለበት፣ ባቆሙዋቸው የሀሰት ግብረ ሰናይና የባለሙያዎች ድርጅቶች ስም በሚንቀሳቀሱበት ሁሉ እየተገኛችሁ እናንተን እንደማይወክሉ ማጋለጥ ከሁላችሁም የሚጠበቅ ትግል ነው። በተለይም የወይዘሮዋ ጦመር ባለፈው ባወጣው መልዕክት ላይ በየሳምንቱ በሚካሄደው የቴሌኮንፍረስ የፓለቲካ ውይይት ላይ በመመዝገብ እየተሳተፋችሁ እነዚህን መርዛም እባበቦችን ማጋላጥ ግዴታችሁ ነው።

ፓለቲካው ውስጥም ፓለቲከኛ፣ ቤተ ክርስትያን ውስጥም ሀይማኖተኛ፣ በመረዳጃ ማህበር ውስጥም የወገን አሳቢ በመምሰል ለግልና ለወያኔ ጥቅም ማደሪያው ጊዜ አብቅቷልና ጥፉ በሏቸው። ከናንተ በተለያየ መንገድ የሚሰበስቡት ገንዘብ የት እንደሚገባ ታውቃላችሁን? እነሱና ቢጤዎቻቸው ኪስ ውስጥ ነው። ለምሳሌ የቅንጅቱ ብርሀኑ ነጋ በቅርቡ በጥሬ ገንዘብ ፩ ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣ መኖሪያ ቤት መግዛቱ፤ የማይበራ ባትሪ የሚሉት የናንተው የዳላሱ ደጀኔ ወይንም ፍቅረማሪያም ስንት ደርሷቸው ይሆን?

ለመሆኑ በደብራችሁ ቅዱስ ሚካኤል አዲስ የተቀጠረው መምህር ስለ ልጆቻችሁ የሚሰራውን ጎብኝታችሁ የጣላችሁልን ባይኖርም፤ እኛም የሱ የርቀት ተማሪ ሆነን ጀምረናል። ይህ በኢንተርኔት የምናገኘው ትምህርት አጀማመሩን ብንወደውም ለምስጋና ገና አልደረስንም። የሚነቅፉንን መነኩሴ አባትንም አዲስ አበባ ኮሌጅ ውስጥ እንዳስተማራቸውም የደረሰን መረጃ ይጠቁማል። እርሳቸው ግን እርሱ ባገኘው ተወዳጅነት ብዙም ተደሳች ባይሆኑም የስራ ቅጥራቸው እንዲፈረም በጣም የቸኮሉ ሆነው ተገኝተዋል። እንደሚደርሰን ዘገባ ከሆነ በጣሙን ከነክፈተው (ኢዮኤል) ነጋ ቡድን ጋር እጅና ጓንት እንዲሉ የዕለት ጎብኜ ወዳጆቻቸውና አማላጆቻቸው ሆነዋል። ምናልባት አንዳንዶቻችሁ ካንድም ሁለቴ አውግዘዋችሁ አልፎ እርግማን ስለጣሉባችሁ ነው ትሉን ይሆናል! ያ ለኛ አይደለም። እኛ ዕውነትን ዕውነት፣ ሀሰትንም ሀሰት እንደምንል ሁሉ ለሳቸው ወዳጆች የሰጠነው ዕውነተኛ ባሕሪያቸውን ነው እንጂ ፈጥረነው እንዳልሆነ በግልጽ የተቀመጠ ነው። እኛም የግለሰቡን መብትና ነጻነት ስለምናከብር ከመሰላቸው ሁሉ የመወዳጀት መብታቸውን በድጋሚ እናከብራለን። የነሱንም ተጽዕኖ ተቀብለው ቢያራምዱም እንዳመጣጡ በጊዜው የደብሩን ህልውና በማስቀደም እናስተናግደዋለን።    

ከዚህ ባለፈ እንግዲህ ለልጆቻችሁ ትምህርት በተመለከተ የምታደርጉት አስተዋጾ በጣሙን ከማስኮራት አልፎ የሚያስቀና ሆኖ አግኝተነዋል። በደብሩ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ከ፹ በላይ ፈቃደኛ ሆነው ለልጆቻችሁ የትምህርት ክፍል ለመርዳት የተመዘገቡ ተገኝተዋል። ልዑል እግዚሀብሔር ምስጋና ይግባው። አሜን። እንደምንሰማው ከሆነ አስተዳደሩ የተቀሩትንም ንዑሳን ክፍሎችን ሁሉ በሚገባ ማደራጀት ስለጀመረ የምትችሉ ሁሉ በሚመስላችሁ ንዑሳን ክፍል እየተመዘገባችሁ አገልግሎት በመስጠት እንድትባረኩ በዚህ አጋጣሚ ከሚካኤል ሰይፍ ተወካይ የቀረበውን ጥሪ እናስተላልፋለን። እየተዋቀሩ ካሉት ውስጥ የአባት መዘምራን፣ የመስተንግዶ ክፍል ተጨማሪ የሰው ኃይል፣ እንደዚሁም የበዐል ቀን ዝግጅት የመሳሰሉ ሲገኙ ፤ ለመጪው የቅዱስ ሚካኤል በዐለ ንግሥ የገንዘብና የሁለቱንም ጾታ የሰው ኃይል ፈቃደኞችን ስለሚያስፈልግ የተቻላችሁን ሁሉ እንትተባበሯቸው በቅዱስ ሚካኤል ስም ጥሪ እናቀርባለን?

እርሶስ ምን ይላሉ?

Wednesday, November 3, 2010

ውኃ ስላፈሰሱበት ብቻ የለበሱት ሸማ ንጹህ የሚመስላቸው

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና! 

ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።


የሰሞኑ የዳላስ አየር ዝናብና ቅዝቃዜ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ መረዳጃ ማህበሩንም ሆነ ቤተክርስትያናችሁ ውስጥ ውስጡን የነካካውንና የገባው አዲስ አየር የአንዳንዶችን ጎራ ጠአሙን እየለወጠ ይገኛል። በተለይም የወይዞሮዋ ጦመር ያስበረገጋቸው የሀሳብ ድውያኖች የመጣባቸው ቀዝቃው አየር ሳይሆን ሀፍረትና ክስረት ከየአደባባዩ እያሸሻቸው ነው። የተወደዳችሁ የገጻችን ተከታታዮች እንደምን አላችሁ? በእርሱ ፀጋና ምህረት ለዚህ ያደረሰን እግዚሀብሔር ክብር ምስጋና ለእርሱና ለገናና ስሙ ይሁን። አሜን።

ያለውንና ያለፈውን የዳላስ ኢትዮጵያ ተወላጆችን ስናስታውስ ፤ እንኳን ከዳላስ እራቅን ብለን ለመዳዳት ቢፈታተነንም፣ ላለን የወገን ክብርና ፍቅር ግን ምነው ገለባውን ሳንለይ አፋጥነህ ያወጣኸን የሚል ወኔን ያገሳናል። ይኹንና ካለንበት እርቀቱ ሳይገታን ሀዘንና ደስታችሁን እንድንካፈል ለተቀደሰውም ትግላችሁ በፀሎትም ሆነ በሀሳብ አብረናችሁ በመጓዝ ከቀን ወደቀን የምትከፍሉትን መስዋዕትና ፍሬ በማየት በውስጣችን ያበራችሁትን ተስፋ ወሰን የሌለው በመሆኑ ለሠራዊት ሁሉ ጌታና ፈጣሪ ክብር ምስጋና ይሁን። አሜን።

ከንቅቡ ተንገዋለው ከወደቁት ውስጥ እንደ ክፈተው ነጋ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ ፊርማቸውና ፎቶግራግ ታሪካቸው ተጠርዞ ገበያ ላይ ረክሶ ወድቆ ይገኛል። ከሩሲያዊያን ዘንድ ሲጀመር ያልነበረው እንደነበረ በሞቀበት ሁሉ እየገባ ሙሾ ማውጣት የሚወደው ክፈተው ዛሬ ደግሞ የነእስስቱ አለቅላቂ እንደዚሁም ጭፍራ ሆኖ መገኘትና ደብሩን በተለያየ መንገድ መውጋት ስራዬ ብሎ የያዘው፤ የመጨረሻ እስትንፋሱን ይዞ መነኩሴ ካህኑን ለመደለል ከስውር ወደ ገሀድ ገብቶበታል። ከ፩፪ አመት በፊት ደብሩ እንዳይቀጥራቸው ከወሰኑት ውስጥ አንዱ የነበረና በወቅቱ የሕግ ወጥ ቁማር በማጫወት ተዳዳሪ የነበረው ክፈተው ነጋ (ኢዮኤል) ከሳምንት በፈት በዋለው ሰንበት አርፍዶ ወደ ቤተ ክርስትያኑ ውስጥ ወደ ፊት ዘልቆ የተቀመጠው፣ እንደምዕመናኑ ተባርኮ እንደመውጣት፣ እርሱ ግን እስከመጨረሻው ቆይቶ መነኩሴው ጨርሰው ሲወጡ ጠብቆ ሲጠቀጥቃቸው የተመለከቱ ሁሉ ግርሞታቸው በፈታቸው እንደሚነበብ ፤ መነኩሴውም ቤሆን ሲሸሹት እንደከረሙና ቀንና ሰአቱን ተጠቅሞ የእልህ ድርጊትና መንፈሳዊነት የጎደለው አቀራረብ እንደነበር፣ እንደዚሁም የእርሳቸው ችኮላ ፈቃደኛ አልመሆናቸውን እንደሚያሳይ በቦታው የታዘቡትን አካፍለውናል።

ውኃ ስላፈሰሱበት ብቻ የለበሱት ሸማ ንጹህ የሚመስላቸው አጽራረ ቤተ ክርስትያን ድርጊታቸውን የጀመሩት ከተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅትና አድገውም በዳላስ የኢትዮጵያ መረዳጃ ማህበር ውስጥ ቢሆንም፤ በደበሩ ውስጥም በነበረው ችግር ዘው ብለው ሲገቡ ለሀይማኖታቸው በቆሙ ተገተው አሁን ለመበርከክ በቅተዋል። እነሱ መጀመሪያ ሸማቸው ከመቆሸሹ በፈት የራሳቸው ጭቅቅት ወደ ሸማቸው የተላለፈ መሆኑን ዛሬም አልገባቸውም። ብዙዎቹም በኢትዮጵያ ሕዝብ ገንዘብ ወደ ውጭው አለም ተልከው እስከ ዶክተርነት ማዕረግ ትምህርት የደረሱና ያስተማራቸውንም ሕዝብ የካዱ፣ ዕውቀታቸው የከፈተላቸውን ብርሀን ከመጠቀምና ለሀገራቸው ዕድገትን ከማምጣት ይልቅ ከስርዐቱ ጋር ተቆላልፈው አብረው የወደቁ ቅድመ አብዮትና የነሱ ጸር ሆነውም ገሚሱ አብዮተኛ ሌላው ተቃራኒ ሆነው ሀገርና ያጠፉ ብለውም በንጹህ የወገን ደም የታጠቡ፤ ዛሬ ደግሞ በሰከነ እድሜና ወደ ሞት በመጠሪያ ዋዜማቸው ንስሀ ገብተው በጎ እያደረጉ መጠሪያ ሰአታቸውን ከመጠባበቅ ይልቅ፤ በከተማችሁ የወያኔ ሎሌነትን መርጠውና ታዛዥ ሆነው በሱ መመሪያ ለሱ ስጋት የሆኑትንና ወደፊትም ስጋት ይሆነኛል ብሎ የሚያስባቸውን በራሱ ቅጥረኛ መቆጣጠር ካልሆነም ማጥፋት በሚለው የተሰማሩ ሆነው ተገኝተዋል። በቅርቡ ቅንጅት የተባለውን የከተማችሁን ድርጅት እንዴት ለሁለት እንደከፈሉትና እንዳከሰሙት። ከዚያም ደጀን ብለው የወያኔ ምርኮኛ እንዳደረጉት እናንተው ምስክሮች ናችሁ።

የማይበራ ባትሪ የሚሉት የተገንጣዩ ቅንጅት ደጀኔ ለአምስተኛው አመት የምርጫ ፱፯ ተያይዞ ኢትዮጵያ ውስጥ የተሰውትን ለመዘከር የበተነውን  በራሪ የላኩልን ተባባሪያችንን እያመሰገንን እንደ ሞኝ የራሱን ቁጥር አክሎበታል። እኛ ግን ከኃላው ያሉትን እነ ኪዳኔ አለማየሁ፣ በትሩ ግ/እግዚሀብሔር፣ ተፈራወርቅ አሰፋና ወዘተ ….. እንድሆኑና እነርሱም ይህንኑ ቀን በማስመልከት በዳላስ ስም ሰፋ ያለ ጊዜ በቴሌ ኮንፍረስ ያሳለፉና ይህንንም በተመለከተ ነዋሪው ግንዛቤ እንዳይጨብጥ አፍነው ይዘው የከረሙ ሲሆን ፤ በተመሳሳይ ጊዜ ለወያኔ መረጃ አስተላላፊ እንደነበሩ ያገኘነው መርጃ ያረጋግጣል። በተለይ እነዚህ ፫ ግለሰቦች ዳላስ የገቡት አላማናተልዕኮ ይዘው ነው። ለዚህም ነው ከዳላስ በፊት የነበረው ሕይወታቸው፤ ሸማቸው ላይ ውኃ በማፍሰስ የሚጠራ አይደለምና በተለይ የአሜሪካውን ለመቃኘት ጉግልም ይበቃል የሚያሰኝ።

አንዳንድ የዋህ የሆኑ በመረዳጃው ማህበር ስር የተቋቋመውን እድር በተለየ መልኩ ሲመለከቱት ታይተዋል። ሀቁ ግን የተለየ ነው። የመረዳጃው ማህበር አገልግሎቱና ሕጋዊ ፈቃዱ ፈፅሞ ከእድር ጋር በማንኛውም መንገድ የማይገናኝ በሕግ ወጥ መንገድ የተለጠፈ ድርጅት ነው፤ የ አይ አር ኤስ ህግን ያልተከተለና የተላለፈ ነው። ያለ ውዴታ በግዴታ በአመት ፵ ዶላር ከእድር አባሎች የሚነጠቀው ገንዘብ ሕገ ወጥ ድርጊት ነው። መረዳጃውም ይቀበል ከሆነ ሕገወጥ ብቻ ሳይሆን ሕግን በተጻረረ መንገድ ለእድሩ ጃንጥላ መሆኑ በራሱ ሕግን ተላልፎ ተጠያቂ ያደርገዋል። ሰሞኑን ምርጫ ተብሎ በእድሩ ስም የተጠራውና የሚካሄደው ማን ያቦካውንና የጋገረውን ማን ሊቋደስ እንደሆነና ማን ላይ ለመላከክ እንደሆነ ባይገባንም፤ እንደ ጀመሩትና እንደ አደራጁት እድሩ ከማህበሩ ተነጥሎ ራሱን እንደ ክለብ አሊያም የንግድ ድርጅት አድርጎ በትርፋማነት ለመንቀሳቀስ ባስቸኳይ ካልሆነ ፤ ነገ እስከነ አካቴው መረዳጃ ማህበሩንም ያጠፋዋል። የማይሆንም ከሆነ የቀረውን ገንዝብ ተከፋፍሎ ወይንም ለመረዳጃው ማህበር አሊያም ለተመሳሳይ ግብረ ሰናይ ተሰጥቶ መዘጋት የሚገባው ነውና። ይህንን የማይቀበል ወይንም ጥርጣሬ ላለው የራሱን የሕግ ባለሙያ ምክር መሻቱ ተገቢ ነው ስንል፤ የቀብር መድህን ዋስትና ግን በአይነቱም ሆነ በጥራቱ እንዲሁም በዋጋው አሁን አባላቱ ከሚከፍለው ጋር ማስተያየቱ ልዩነቱን ለማወቅ አያውክም።

ለመቛጫ ወደ ደብሩ ስንመለስ ቀደም ብለው ከቤተ ክርስትያኑ እርቀው የነበሩትና ቅያሜ አላቸው የሚባል አሉባልታ የሚናፈስባቸው የነበሩት ሁሉ ዛሬ ወደ ምንጩና ወደ ቤታቸው ተመልሰው ይገኛሉ። እንደ ምንጮቻችን አጠያየቅ የተረዱትን ሲያካፍሉን ፤ እነዚህ ወገኖቻችን እኛ ወደ ድብራችን የምንመጣው አብረን በህብረት ፈጣሪያችንን ለማመስገንና በሁላችንም ደስ እንዲለው ነው። ነገር ግን በእርሱ ቤት እርሱንም እኛንም የሚያሳዝነን ልናይ ስላልፈቀድን ፣ እዚህም በህብረት ባልጸለይንበት ጊዜ መጥተን ከውጭ ተሳልመንና ጸልየን ከመሄድና በያለንበት ተመሳሳይ የግል ጸሎታችንን ስላላቋረጥን መልሱን ስናገኝ ይኸው ተመልሰናል ብለው የነገሯቸውን ለኛም አካፍለውናል። እግዚሀብሔር አሁንም ይስማችሁ ነው የምንል። በሌላ በኩል አዲስ አባልነት ለመመዝገብ ጥያቄዎች እየበዙና እየተስተናገዱ ሲሆን አሁንም ቅሬታ አለን ብለው ከከሳሾች ጋር የወገኑና ራሳቸውን የቅዱስ ሚካኤል መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ብለው የሚጠሩና የቦደኑ አሁንም በአባልነት ያሉ ፲ የማይጠጉ ግለሰቦች ናቸው። እንደሚታወቀው ሁሉ የከሰሱም ሆነ በዚህ ቡድን የታቀፉት በሙሉ የደብሩ አባላት ያልሆኑ መሆናቸውን ለማንም የተሰወረ አይደለምና። እነዚህም ጥቂት ግለሰቦችም ቢሆኑ አላማና አጀንዳ ያላቸውና ዘወትር እንደ ውዳሴ የሚሉት የወያኔ የ፶፪ ገጽ ሎሌ እንጂ ምንም አይነት የተዋህዶ ኦርቶዶክስ ዕምነት የሌላቸውና መተግበሩንም ለማስመሰል እንኳን አልሆን ያላቸው አጽራረ ቤተ ክርስትያንና እንደዚሁም ጸረ መረዳጃ ማህበር መሆናቸውን በተግባር ያስመዘገቡ ናቸው። በተለይም መለከት በተባለው ገጻቸው በሴብተምበር 25 የቃዡትን በትላንቱ ዕለት በተደረገው የውስጥ ስብሰባ ላይ ቅዠት ተብሎላቸው ተደምድሟል። እነሱ የተከሏቸውና አስርገው ያስገቧቸውም እነፍቅረማርያም ሚስጥሩ ደርሷቸው ባይገኙም የበላይ መሪና አማካሪያቸው የሆነውና በሌላ ቡድን ያሰረጉት መልዕክቱን በሚገባ የተረዳው መሆኑን ተቀብሎታል ሲል የሚካኤል ሰይፍ ወኪል ካዛገበን ተረድተናል። በዚህ ስብሰባ ላይ የተገኙት በሙሉ የዕምነቱ አማኞችና ተከታዮች ብቻ ሳይሆን ከስራቸው የሚመራቸውና ያቀፏቸው በጎሳና በዘር የታቀፉ፣ በማህበር ፣ጥዋና በመሳሰለው በተለያየ  ከሁሉም ህብረተሰብ ውስጥ የተመረጡትን አቅፎና ተደራጅቶ የያዘ የደብሩ የጀርባ አጥንት መሆኑን ጨምሮ አስገንዝቦናል። በዚሁ ስብስባ ላይም ደብሩ በጥሩ ሁኔታ ላይ ያለ፣ የአባላትም ተሳትፎ ከፍ ያለ፣ የሚያኮራ ውጤት ላይ መድረሱንና አስተዳደር ቦርዱም ዕቅዶቹን ለመተግበር እያደረገ ያለው አመርቂ መሆኑን ተገልጧል። የምዕመናኑም እጅ ተከፍቶ ለደብሩና ለቅዱስ ያሬድ ትምህርት ቤት የሚያደርገው እርዳታ እያደገ ይገኛል ፤የተጨማሪ የትምህርት ክፍል ጥያቄ ወሳኝነት ደረጃ ላይ መድረሱም ተወስቷል።

በሚቀጥለው ጥሁፋችን በቸርነቱ እስክንገናኝ መልካሙን ሁሉ እንመኝላችኃለን።


እርሶስ ምን ይላሉ?    

Sunday, October 31, 2010

ጉድና ጅራት ከወደኃላ ነው እንዲሉ

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!

ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።


ጉድና ጅራት ከወደኃላ ነው እንዲሉ!

የተወደዳችሁ የገጻችን ተከታታዮች እንደምን አላችሁ? እኛ በእርሱ ጸጋ ለዚህ ላደረሰን እግዚሀብሔር ለገናናው ስሙ አሁንም እስከዘላለሙ ክብር ምስጋና ይሁን። አሜን።


ጋሼ ተኮላ (ተኩላው) ስለ ቀድሞው መሪያችን ቢል ክሊንተን መጽሀፍ በእርግጠኝነት አንብበህ በሚገባ ተረድተህ በራስህ የተረጎምከውን ስላካፈልከን እውነት ከሆነ በርታ በማንበብ ብዙ እውቀት ይገበያልና። ነገር ግን እንግሊዘኛ ችሎታህ ተርጉሞ ለሌላ ለማካፈል ቀርቶ ለራስህም ለመረዳት ገና ዳዴ እያልክ ነህና የተሳሳተ ትርጉም ላለመጨበጥ የቋንቋ ዕውቀትህን ለማሳደግ የግድ ትምህርት ለመቁጠር ወደ ባለሙያዎቹ መዝለቅ እንደሚገባህ እያካፈልንህ፣ ይህ ባይቻልህ እውቀቱ ያላቸው በትርጉሙ ቢረዱህ መልካም ነው። ትርጉም እራሱን የቻለ ሙያ ነውና።  ባለፈው ወዳጅህ ቀዳዳው ከዳኛ አንደበት የሰማውን የእንግሊዘኛ ቃል “እስብሊት“ የሚለውን አብሮህ ሲጨፈላልቀው ከርሟልና። በተለይ እያንዳንዱ የቃላት ሕጋዊ ትርጉሙ ጥንቃቄ እንድናደርግ
ለማሳሰብ ነው። ከዚህ ሌላ ዛሬም መዋሸት ይብቃህ ፣ ዕድሜ አልመክርህ ብሎህ ሰው በጣፈው ከመናገር የራስህን ደግመህ ደጋግመህ በየጊዜው የጣፍከውን ወደ ኃላ ተመልሰህ አንበው። ከስህተትህም ተማር‘። ‘ሀሰት አድርጌ ጥፌ ተገኝቼ ስለጠቆማችሁኝ አመሰግናለሁ‘ ብቻ ብትጥፍ እኛም ከሰው ስህተት አሊያም የሚሰራ ሰው ብለን በዘለልነው ነበር። ከኛም ጥሁፍ ሀሰት ካገኘህበት ጠቁመን በደስታ ለማስተካከልና ካለፈው ለመማር ወደኃላ የማንል ለመሆናችን ካንተ በላይ ዋቢ አንፈልግምና።

ከዚህ በመቀጠል ወደ እርዕሳችን ስንመለስ “ጉድና ጅራት ከወደኃላ እንዲሉ“ በቅርቡ የተጀመረው “http://www.dfwethiopiancommunity.blogspot.com/ “ ገጽ ጥሁፍ አጣጣሉ ወደፊት እንደኛ በሂደት እያደገና ተወዳጅነትን እያተረፈ እንደሚመጣ ተስፋችን ከፍተኛ ነው። በውስጡ አልፎ አልፎ የሚላመጥ ፍሬ አለው፤ በትላንትናው ጥሁፉ ባስነበበው ግን “ እግዚኦ “ የሚያሰኝ ነውና ፤ ኽረ ዳላስ ላይ ምን አደንዛዥ በሽታ ነው በኢትዮጵያ ተወላጆች መካከል የገባው? ምን አይነት ጉድ ይዛችሁ ነው የምትኖሩት? ለመሆኑ በወገኑ ላይ ይህ አይነት በደል ሲፈጸም የሚችል አንጀት መቼ ተጀመረ? ምን አይነት ልቦና ይዛችሁ ነው አብራችሁና አቅፋችሁ የምትኖሩት? በከተማው ያላችሁ የተማራችሁም ሆነ ያልተማራችሁ ፤ ወጣቶችም ሆነ አዛውንት ነን የምትሉ ሁሉ ፤ የሀይማኖትም ሆነ የግብረ ሰናይ ድርጅት ወይም የሰብአዊ መብት አባላትም ሆነ የሕግ ሙያተኞች የሆናችሁ የኢትዮጵያ ተወላጅና ወዳጆች ሁሉ የሞራልና የሕግ ግዴታችሁን ትወጡ ዘንድ እያሳሰብን አስቸኳይ እርምጃ እንደምትወስዱ  ተስፋ እናደርጋለን። እኛም የሞራልና የህግ ግዴታ ስላለብን መረጃዎች በእጃችን እንደገቡ ለዳላስ ካውንቲ አቃቤ ጽ/ቤት በማስተላለፍ ጉዳዩ በዚያ ተመርምሮ የህግ መጣስ ካለበት አግባባዊ እርምጃ እንዲወሰድ የተቻለንን ሁሉ እንደምናደርግ ቃል እንገባለን።

እርሶስ ምን ይላሉ?

Saturday, October 30, 2010

ጳውሎስ በቃለ ጉባዔው ላይ አልፈርምም አሉ

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!

ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።



የሚቀጥለው የተገኘው ከደጀሰላም ጦመር ላይ መሆኑን በቅድሚያ እንገልጻለን
OCTOBER 30, 2010

ሰበር ዜና:- አቡነ ጳውሎስ በቃለ ጉባዔው ላይ አልፈርምም አሉ
አርእስተ ዜና
(ደጀ ሰላም፤ ኦክቶበር 30/2010፤ ጥቅምት 20/2003 ዓ.ም):-
አቡነ ጳውሎስ ሐውልቱ እንዲፈርስ የታዘዘበትን እና የሁሉም ሊቃነ ጳጳሳት ስምምነት የተገለጸበትን ውሳኔ በያዘው ቃለ ጉባኤ ላይ ‹‹አልፈርምም›› በማለት እና ሲጠየቁም ዝምታን በመምረጥ ቀድሞ ሲገለጽ በቆየው እምቢታቸው ጸንተዋል፡፡

አቡነ ይሥሐቅ

አቡነ ጎርጎርዮስ
 ከፓትርያሪኩ ጋራ ሌሎች አራት ሊቃነ ጳጳሳትም በተለያየ ምክንያት የሐውልቱ መፍረስ የተገለጸበትን ቃለ ጉባኤ አልፈረሙም፡፡ ሲኖዶሱ ከ43 ያላነሱ በአገልግሎት ላይ የሚገኙ ጳጳሳት እና ሊቃነ ጳጳሳት በአባልነት ይገኙበታል፡፡
 የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የሐውልቱን ማስፈረስ ውሳኔ እንዲያስፈጽሙ በስማቸው ተለይቶ በመግለጫው ላይ መስፈሩን በመቃወም ለመፈረም ፈቃደኛ አልሆኑም፡፡ ብፁዕነታቸው ‹‹ከእኔ ስም ይልቅ ቢሮው ነው መጠቀስ ያለበት›› የሚል አቋም እንዳላቸው ተነግሯል፡፡
 አቡነ ይሥሐቅ፣ አቡነ መቃርዮስ እና አቡነ ጎርጎርዮስ (ከዚህ በፊት ሐውልቱን ሲቃወሙ ቆይተዋል) ‹ፓትርያሪኩ ሳይፈርሙ በፊት አንፈርምም› በሚል እና ሌሎች ምክንያቶች ለመፈረም ፈቃደኛ አልሆኑም፡፡
 በሕገ ቤተ ክርስቲያን ስለ ቅዱስ ሲኖዶስ የስብሰባ ሥነ ሥርዐት አንቀጽ ሁለት ንኡስ አንቀጽ 4/ሀ ሃይማኖትን እና ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን በሚመለከት ጉዳይ ከጠቅላላው አባላት ከአራት ሦስቱ እጅ በተገኙበት ሲኖዶስ በማድረግ በሙሉ ድምፅ ውሳኔ ማሳለፍ እንደሚገባ ተደንግጓል፡፡
በሕገ ቤተ ክርስቲያኑ አንቀጽ 15 ንኡስ አንቀጽ 1 ፓትርያሪኩ በተሰጠው ሐላፊነት መሠረት ሃይማኖትን እና ቀኖና ቤተ ክርስቲያን የመሠበቅ እና የማስጠበቅ፤ በአንቀጽ 16 ንኡስ አንቀጽ 1 መሠረት ደግሞ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ሃይማኖት የሚያፋልስ፣ ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን የማይጠብቅ፣ ቤተ ክርስቲያንን የሚያስነቅፍ ተግባር ፈጽሞ ከተገኘ፣ ታማኝነቱ እና ተቀባይነቱ በካህናት እና ምእመናን ዘንድ ተቀባይነት ያጣ ሆኖ ይህም በትክክል ከተረጋገጠ በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ከሥልጣን እንደሚወርድ ተደንግጓል፡፡
ፓትርያሪኩ ዛሬ ዘጠኝ ሰዓት ላይ በተጠራው ጋዜጣዊ ጉባኤ በቅዱስ ሲኖዶሱ አባላት ስምምነት የተደረሰበትን መግለጫ እንደሚያነቡ ይጠበቃል፡፡ መግለጫውን ለማንበብ ፈቃደኛ ካልሆኑ ብፁዓን አባቶች የወከሉት የሲኖዶሱ አባል እንዲያነቡት ይደረጋል ተብሏል፡፡

Wednesday, October 27, 2010

አቡነ ጳውሎስ ሐውልት እንዲፈርስ

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!

ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።


ቅጂ ከሪፖርተር

(በየማነ ናግሽ)

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ትናንት በዋለው ዓመታዊ ስብሰባ፣ በቦሌ መድኃኔአለም ቤተክርስቲያን ቅጥር ጊቢ ተሰርቶ የነበረው የፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ ሐውልት እንዲፈርስ፣ ከኢትዮጵያ ሚሌኒየም ጊዜ ጀምሮ በየቤተክርስቲያኑ ቅጥር ግቢዎች የሚገኙና ምስላቸውን የያዙ ቢልቦርዶች እንዲነሱ መወሰኑን ምንጮች ለሪፖርተር ገለጹ፡፡ ካለፈው ዓርብ ጥቅምት 12 ቀን 2003 ዓ.ም. ጀምሮ ቅዱስ ሲኖዶሱ ባካሄደው ዓመታዊ ስብሰባ ከፓትርያርኩ ጋር በተያያዘ ውሳኔዎችን ያስተላለፈ ሲሆን፣ በአዲስ አበባ ቦሌ መድኃኔአለም ቅጥር ጊቢ የሚገኘው በፓትርያርኩ ምስል የተሠራው ሐውልት፣ ከቤተክርስቲያኗ ሕግጋት ውጪ ነው በሚል እንዲፈርስ ቅዱስ ሲኖዶሱ በሙሉ ድምፅ መወሰኑን ምንጮች ገልጸዋል፡፡

እንደ ምንጮቹ ገለጻ ከሆነ፣ ቅዱስ ሲኖዶሱ በዚሁ ዓመታዊ ስብሰባው ከትናንት በስቲያ በፓትርያርኩ ዙሪያ አንዳንድ ጉዳዮች ለውይይት የቀረቡ ሲሆን፣ ከእነዚህም መካከል የፓትርያርኩን ምስል የያዙ በየቤተክርስቲያኑ ቅጥር ጊቢዎች የሚገኙ ቢልቦርዶች፣ የፓትርያርኩ 18ኛው በዓለ ሲመታቸውን በማስመልከት ስለተሠራው ሐውልትና ጳጳሳትን እርስ በርስ ያናቁራሉ ስለተባሉ አንዳንድ ግለሰቦች ማብራሪያ እንዲሰጡ ፓትርያርኩ ተጠይቀዋል፡፡

ለትናንትና ምላሽ ይዘው እንዲቀርቡ በቅዱስ ሲኖዶስ ጥያቄ የቀረበላቸው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ፣ በመጀመሪያ ምንም ስህተት እንዳልሠሩ የተከራከሩ ቢሆንም፣ በተለይ ሐውልቱን በተመለከተ ግን መመረቁን አላውቅም የሚል ምላሽ መስጠታቸውን ምንጮች አረጋግጠዋል፡፡

የሐውልቱንና የቢልቦርዶቹን መሠራት በተመለከተ ከቤተክርስቲያኗ ሕግ ውጪ መሆኑን ሕግን አጣቅሰው የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት የተከራከሩዋቸው ሲሆን፣ በመጨረሻም ስህተት መሆኑንና እንዲፈርስ ሲሉ የሲኖዶሱ አባላት በሙሉ ድምፅ መወሰናቸው ታውቋል፡፡

ቅዱስ ሲኖዶስ ይህንን ውሳኔ የሰጠው፣ ‹‹የተሰራው ሥራ ከአበው ትውፊትና ከቤተክርስቲያኗ ሕግ በተፃራሪ ነው›› በሚል መሆኑን ምንጮች አክለዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ፣ ወ/ሮ እጅጋየሁ በየነ የተባሉት ግለሰብ አባቶችን እርስ በርስ በማጣላት የሚታወቁ ስለሆነ ወደ መንበረ ፓትርያርኩ ቅጥር ግቢ እንዳይገቡ ሲኖዶሱ የተስማማ ሲሆን፣ ውሳኔው በቤተክህነት አስተዳደር ሥራ አስኪያጅ ደረጃ እንዲሰጥ መደረጉን ምንጮቹ አረጋግጠዋል፡፡

በአጠቃላይ ሲኖዶሱ ቤተክርስቲያኗን በሚመለከት ባደረገው ውይይት፣ የፓትርያርኩ አመራር ቤተክርስቲያኗን እንደጎዳት፣ ሥርዓት አልበኝነት መስፈኑን፣ ሙስና መንሰራፋቱንና አምባገነንነት በገሐድ መታየቱ በዋነኛነት ተጠቅሷል፡፡

ከትናንት በስቲያ በዋለው የሲኖዶሱ ስብሰባ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ የነበሩት ሊቀ ማዕምራን ፋንታሁን ሙጬ እንዲነሱና በሀገረ ስብከቱ ላይ ያደረሱት ጥፋት ካለ በኦዲት ተጣርቶ በሕግ ተጠያቂ እንዲሆኑ ተወስኗል፡፡

Friday, October 22, 2010

ከደረቅም ደረቅ ፣ ከእርጥብም እርጥብና ከበሰበሰውም ብስብስ መሆን ይቻላልን? ክፍል ፫

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!

ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።


ከደረቅም ደረቅ ፣ ከእርጥብም እርጥብና ከበሰበሰውም ብስብስ መሆን ይቻላልን?

ክፍል ፫

የተወደዳችሁ የገጻችን ተከታታዮች እንደምን አላችሁልን? ጸጋው የማያልቅበት እግዚሀብሔር ለዚህ ሰአት ፈቃዱ ሆኖ ሁላችንንም ስላደረሰን ለታላቁና ገናና ስሙ አሁንም ክብርና ምስጋና ይሁን። አሜን።

እንደምታስታውሱት ያለፈውን ጥሁፋችንን የገታነው የአካባቢያችሁ የመረዳጃ ማህበር ውስጥ ሾልኮ አመራሩን ጨብጦ የነበረውን ተፈራወርቅ አሰፋ የሚባለው እስስት ግለስብ ካቆመው የውንብድና ቡድን ውስጥ አንዱ ሕገወጥ ሰውን የማስተላለፍ (ሁማን ትራፊክ) ንግድ ነው። በሰብአዊ መንገድ ቢሆን መልካም ነበር ነገር ግን ከጅምሩ እስከመደምደሚያው የገንዘብ ጥቅም ለማግኘት ሆን ተብሎ የተፈጠረ ቡድን ነው። ከኢትዮጵያና ከሌሎች ሀገሮች ያሉትን ወገኖቻችንን ከፍተኛ የሆነ ገንዘብ በማስከፈል በዚያ ሀገር ባሉ ደላሎቻቸው አማካኝነት፣ እንደዚሁም በዚሁ አሜሪካን በተለያየ ከተማ ውስጥ በሚገኙ ወኪሎቻቸው አማካይነት እየተቀበሉ ያስገቡአቸው ሰዎች ቁጠራቸው ብዙ ነው። በለስ ያልቀናቸውም ከሜክሲኮ ይዞ በደቡብ ሀገሮች በእስር ያሉ ወይንም በተለያየ ምክንያት ሕይወታቸውን ያጡት፣ ብለውም ቴክሳስ ላይ ተይዘው ከብዙ ስቃይና መከራ በኃላ ወደመጡበት ሀገር የተመለሱትን በዚህም የገንዘብ መቅለጥ ብቻ ሳይሆን በራሳቸው ሕይወት እንግልት የከፈሉት ሁሉ የእስስቱ ተፈራወርቅና የሱ ቡድን ሰለባዎች ናቸው።

በለስ ቀናቸው ከሚባሉት ደግሞ ውስጥ በዳላስ ቤተሰብ ወይም ዘመድ ያላቸውና ወይንም የዚሁ ሕገወጥ ቡድን አባሎች ጋር በተለያየ መልኩ ንክኪ ያላቸው ብቻ ናቸው። ሌሎችም እድል ሆኖ ሳይያዙ የገቡ ሲኖሩ ሊሎቹ ቴክሳስ ላይ የተያዙት ግን በቤተሰቦቻቸው ግፊት አድርገውባቸው በመረዳጃው ማህበር ስም ከኢምግሬሽን አስከባሪው ክፍል ጋር በመነጋገርና በመጻጻፍ ያስለቀቁዋቸው አሉ። አንዳንዶችንም ተጨማሪ ገንዘብ አስከፍለዋቸዋል። የዚህ ቡድን አባል ከሆኑት ውስጥ ከፍተኛውን ሚና የሚመራውና ሕይወቱን ሙሉ ወግ ያለው ስራ የማያውቀው፣ የረባም ትምህርት የሌለው ፣ ሲፈልግም የፍቺ ባለሙያ፣ ሲፈልግ የኢሚግሪሽን ወይም የታክስ ባለሙያ ነኝ እያለ በከተማችሁ የሚያውደለድል፤ በእርሱ  የታክስ ስራ አይ አር ኤስ የባንክ ሂሳባችሁን የተያዘባችሁ ፣ በጋብቻችሁ ውስጥ እክል መኖር ሰምቶ ረዳት መስሎ ገብቶ ወይንም አንዳችሁ ችግራችሁን አዋይታችሁት ከሆነ፣ ገንዘብ አገኛለሁ ብሎ ነገር አበላሽቶባችሁ ከለፋችሁት ንብረት አፈናቅሎ ፣ ከልጆቻችሁና ከትዳራችሁ አለያይቶ፤ የኢምግሪሽን ጉዳያችሁን አበላሽቶ ፣አማርኛውን እንኳን ጠንቅቆ መናገር የማያውቅ አስተረጉማለው እያለ ያለችሎታው በየፍርድ ቤቱና ኢምግሬሽን መስሪያ ቤቶች በመውሰድ  ፈቃድ ሳይኖረው እያጭበረበረ ከወገኖቻችን የሚገፍ ነውረኛውና የህብረተሰቡ ዝቃጭ የሆነው መንግስቱ ታደሰ (ቴድ መርካቶ) ሰለባ የሆኑትን የዳላስ ነዋሪ የሆነው  ቤቱ ይቁጠረው። ይህ ግለሰብ ዋነኛው በከተማችሁ የሕግ ወጥ ሰዎችን አስተላላፊ ንግድ ውስጥ የተዘፈቀ በሱም ምክንያት ሕይወታቸው የተበላሸ ብሎም ሕይወታቸውን ባጡት ደም የታጠበ ሰው ነው። እንግዲህ ይህ ለገንዘብ ሰው የበላ ፍጡር በቆየ ጓደኛው ዘውገ ቃኘው በሚሉት ዝንጀሮ አማካይነት ነበር ከነእስስቱ ተፈራወርቅ ከሚሉት ጋር ይሰሩ የነበሩት። ከጥቂት አመታት በፊት ባንድ ወቅት ከረጀ በተባለው የከተማችሁ ምግብ ቤት የነሱ ሰለባ በነበረ ግለስብ ስሙ  እምሩ የሚባል ተጠርቶ በነበረው ስብሰባ የተገኛችሁ ሕያው ምስክር አሁንም አላችሁ። በተለይም በሕጋዊ የሙያ ፈቃድ የትርጉም ስራ ላይ የምትገኙና ዳላስ ውስጥ ነዋሪ ሆናችሁ በአስተርጓሚነት በአንዳንድ የኢምግሪሽን ፍርድ ቤት ወይም እስር ቤቶች የተገኛችሁ፣ በተለይም በደቡብ ቴክሳስ ጠረፍ ወደአለው የዘለቃችሁ፤ እስረኛ ወገኖቻችን ከዳላስ መሆናችሁን ስትነግሯቸው የነዚህን ግለሰቦችን ስም እያነሱ እንድትነግሩላቸው የተጠየቋችሁ ሁሉ እውነታው ለናንተ ግልጽ ነውና ይሉኝታ ሊይዛችሁ አይገባም። ለወገኖቻችሁ ጉስቁልና እንደዚሁም ሕይወታቸውን ባጡት በነዚህ ግለሰቦች ሕገወጥ ንግድ ሰለባዎች ስትሉ ለሚመለከተው ያላችሁን መረጃ (ኢንፎርሜሽን) እንድታስተላልፉ አበክረን እናሳስባለን።

ሌላው የመረዳጃ ማህበር መጠቀሚ በሆነ (ሌተር ሄድ) ና ማህተም በእስስቱ ተፈራወርቅ ፊርማ ባረፈበት ከእውነት ውጭ የሆነ ጥቅማጥቅም ያገኙ ግለሰቦችና ቤተሰቦች በተለይም የእርሱ አጋሮችና ቡድኖች በአሀዝ ለመጥቀስ የበዛ ነው። በተለይም በህብረተሰቡ ውስጥ ምንም ግልጋሎት ላላበረክቱት እንዳደርጉ ተቆጥሮና እንደ ሞዴል ተጠቅሰው በተለያየ መንገድ እስከ ከፍተኛ ተቋም ትምህርት እድል ካገኙት ውስጥ እንደ በትሩ ገ/እግዚሀብሔር ቤተሰብ ለናሙና ስናስቀምጥ፣ ለራሱና ለአጋሮቹ እስከ ገንዘብ ጥቅም እንዲያገኙ ያደረጋቸው ብዙ ነው። አሁንም የሱ አጋር የተባሉት እንቅስቃሴ በመያደርጉ ሰባዊ ድርጅቶች ስም ብዙ ምዝበራ እያደረጉ ናቸው። ለምሳሌ ጥቂቶችን  ለመጥቀስ እንደ ዓይን ባንክ ፣ በትሩ ዩዝ፣ ቼምበር ኦፍ ኮሜርስ፣ ወዘተ….. ኸረ ስንቱ ተወግቶ ሌላው የሚገርመው በዳላስ ቅዱስ ሚካኤል ስም በትሩ ግ/እግዚሀብሔር የምንትስ ሊቀ መንበር ፣ ይልማ ፈለቀ የምንትስ ሊቀ መንበር እያሉ የድፍረታቸውና የንቀታቸው ብዛት ዓይን አፍጦ በታቦት ስም ቁማር ሆኖ ነው የሚገኝ። እንግዲህ ፈረስ ያደርሳል እንደሚባለው ገብታችሁ ማበራየት የናንተው የዳላሶች ጉዳይ ነው። ሌላም ብዙ ጉዳዮች አሉ በዳላሶች ላይ እየተቆመረ የሚገኝ። በተከታታይ የጣፍነው ትንሹን ክፍል እንጂ የእስስቱ ተፈራ ያልተነካካበት ከፖለቲካ፣ ከሲቪክ ብሎም አጽራረ ቤተ ክርስትያን ድርጅት የለም። አንዳንዴም እርግጥ እንደ ሌሎቹ ወገኖቻችን በመድህን ዋስትና ሽያጭ ብሎም በታወን ካር (ሊሞ) ብቻ ገቢ ነው የሚተዳደረው ከዚህም አልፎ ቁጥሩ የበዛ ድርጅት ውስጥም የጎላ ተሳትፎ የሚያደርገው እንዴት ሆኖ ነው? ብለንም ራሳችንንም እንደ የዋህ ለመጠየቅ ያዳዳናል። ነገር ግን ሀቁ ከሊሞ የማስመሰያና የመደበቂያ ስራ ፣ የመድህኑም ስንት ከመቶ ቢሆን የተቀረው ስንት በመቶ ይሆን? ብለን ለናንተ እንተወዋለን። እንግዲህ  በእስስቱ ላይ ባለ ብዙ ተከታታይ መጽሀፍ የሚያስጥፍ ጉደኛና ነውረኛ ስለሚወጣው ለዛሪ በዚህ እንቋጭለት።

እንግዲህ ሰው ወደ ትውልድ ሀገሩ የመውጣትና የመግባቱን መብት ወያኔ የሰጠ ቢሆንም (ለሁሉም አይደለም)። እስስቱም ቢሆን የተለያየ የተቃዋሚ ቡድኖች አባል እንዲሁም አመራር ውስጥ የሆነ ብሎም የዳላስ መረዳጃ ማህበርም አንደኛው ተቁዋሚ ድርጅትን የመራ ፣ የደረሰን መርጃ እንድሚለው በቅርቡ በውን ወደ ኢትዮጵያ ይገባልን? እንደ ሀገሩ ዋ..ው..! ብለን ለናንተው ውድ አንባቢዎቻችን እንተወዋለን።

እንግዲህ እንደምትሰጡን አስተያየታችሁ ስለተቀሩት ግለሰቦች በቁ.፬ እንገናኝ ወይስ እንደነዚህ ግለሰቦች ባሕርይ  ከደረቅም ደረቅ ፣ ከእርጥብም እርጥብና ከበሰበሰውም ብስብስ መሆን ይቻላልን?  ይህ ነው የጥሩ ዜግነት መስፈሪያ? ይህንን አይነት ጉድስ እንዴት የዳላስና አካባቢ ነዋሪ የኢትዮጵያ ተወላጅ መለያ ምግባሩ ይሆናል? የተማርን ነን የምትሉና እናመዛዝናለን የምትሉ ለመሆኑ አላችሁን? ከኢትዮጵያ ነን የምትሉ ሁሉ ከደረቀውምም አብራችሁ ልትደረቁ ነውን ፣ ከእርጥብም አብራችሁ ልትረጥቡ ፈገለጋችሁን? ወይስ ከበሰበሰውም አብራችሁ መበስብስ መረጣችሁ?  መልሳችሁን አትንፈጉን?


እርሶስ ምን ይላሉ?