Friday, June 17, 2011

እርሶስ እንደኛ እንባዎ ታብሷል?

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!

ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።


እርሶስ እንደኛ እንባዎ ታብሷል?


እንደምን ሰነበታችሁ? እንኳንም ለሰኔ ሚካኤል በሰላም አደረሰን። አሜን አሁንም ቸርነቱ ለማያልቅበት ለልዑል እግዜአብሔር ክብርና ምስጋና ይሁንልን። ከቀን ወደ ቀን ብሎም ለዳግም አመቱ ላደረሰን እንዲህ በዋዛ እንዳልሆነ ፣ ሕሊና ያለው ሁሉ ያስተውል። ለኛ እንባችንን አብሶታልና የናንተስ? ብሎ በጥያቄ የጀመረን የዳላስ ቅዱስ ሚካኤል ሠይፍ አባልና የገጻችን ታዳሚ ነበር።

የተወደዳችሁ ውድ ወገኖች! እኛም በፈጣሪ ሥራ እየተደነቅን ተዐምሩን እየመሰከርን ለቅሷችንን እያበስን ታላቅ ምስጋናን እናቀርባለን። ከምንጫችን በቀረበልን የትላንትናው የዳላስ ቅዱስ ሚካኤል ደብር የሰኔን ሚካኤል ክብረ በዐልን አስመልክቶ የጀመረው ታላቅ ጉባኤ፤ በባዶ አዳራሽ ውስጥ የተጋበዙት እንግዳ መምህር ሳይገኙ፣ ዘማሪ ዘርፌ በሌለችበት ፣ ማንም ምዕመን ሳይሳተፍበት የከሰረ ጉባኤ ነው የሚሆነው። እኛ ከሌለንበትና እኛ ካልመራነው ምንም አይሳካም። በማለት ሌላውን የሚንቁ ፣ በቁጥር 10 የማይሞሉና አጃቢዎቻቸው በቁጥር 20 ውስጥ የሚሆኑ፣ ከውስጥ ሆነው ደብሩን የሚያውኩ ፣ ባለፈው 2 የአባላት ጠቅላላ ስብሰባ ላይ ብቻቸውን የፈጠጡ፣ ያለውንና ሙሉ አባላት የመረጡት ድንቅዬ ስራዋችን እየከወነ ባለው የደብሩ ቦርድ በቅናት የተቃጠሉ፣ አላሰራም በማለት ዝባዝንኬ ወረቀት እየፈረሙ የደብሩን ስራ እንዳይሰራ የሚያስቸግሩ፣ ደብሩን ለግል ጥቅምና ዝና የሚሹ፣ እነርሱም ሆነ ቤተሰቦቻቸው ባለመመረጣቸው ያኮረፉና በትላንትናው ጉባኤ ላይ አለመገኘታቸው፣ ወዘተ….. በረከቱ ላመለጣቸው እነዚህ ወንድሞችና እህቶች ፈጣሪ መክሮና አስተምሮ ይመልሳቸው ዘንድ እየጸለይን ነውና እናንተም ተሳተፉ ብሎ ያቀረበልንን ጥሪ ተቅብለን ፤ እኛም አጽራረ ቤተክርስትያንን አስታግስልን፣ የተቀበሉትን ወሥጋ ደም በውስጣቸው ይሰራና ያንተን መንገድ እንዲጠብቁ ያድርግልን ፣ ምሕረትንም ፈጣሪ ይስጥልን። አሜን።

ትላንት የተጀመረው ታላቅ ጉባኤ፣ ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅ ልዩ የሆነና ተሳታፊዎቹ ሁሉ የተባረኩበትና ትልቅ ትምህርትን ያገኙበት መሆኑን ምንጫችን ሲጠቁመን፣ በተለይም ቅን ስለመሆን፣ በእምነት ስለመቆምና ማንኛውንም አይነት ፈተና እርሱን ይዞ መወጣት እንደሚቻል ነው። ይኸውም ባለፉት ጥቂት አመታት ደብራችሁ በወጀብ ውስጥ ማለፉንና ዛሬ የደረሳችሁበት አስመልክቶ በእምነት፣ በጾምና በጸሎት ፈጣሪን ይዛችሁ በመጽናታችሁ  መወጣታችሁንና ትላንት ብቻ ሳይሆን ዛሬም ለሚያውኳችሁ እንዴት ሁኔታዎችን እንደምታስተናግዱ መሆኑን ያጫበጠ እንደነበር ነው። ይህ ጉባኤ እስከ እሁድ ምሽት እንደሚቀጥልና ቀዳሚት ጠዋትም በታላቅ ሥርዐት የቅዱስ ሚካኤል በዐለ ንግሥ እንደሚደረግ አብሮን የደረሰን ዜና መሆኑን እንገልጻለን። የዚህ ጉባኤ የተሳታፊው ቁጥር ከተጠበቀው በላይ መሆኑንና ምንም አይነት የተጋነነነ ማስታወቂያ ያልተደረገለት በመሆኑ ሌሎች በጉባኤ ስም ከሚያዘጋጁት ለምን የተለየ እንደሆነ መልሱን ለአንባቢያን እንተዋለን።

ከዚሁ ወጣ ስንል ደግሞ ካካባቢያችሁ ከደረሰን የመረዳጃ ማህበር ምንጮቻችን መካከል፤ ሰሞኑንን ከቅዱስ ሚካኤል ደብር ቦርድ ደብዳቤ ያስገቡት ግለሰቦች ለመረዳጃው ማህበርም እንዳስገቡ ነው። አዲስ የተመረጡትንም አመራሮችን ለማዋከብ ሆነ ብለው ስራ እንዳይሰሩና በቅርቡ ሊካሄድ የታቀደውን የኢትዮጵያ ቀን ለማደናቀፍ እንደሆነ የሚታወቅ ነው። ሌላው ያናደዳቸውና ጥቅማቸው የተነካባቸው በመህበሩ ስም የተቀጠረችና በወር ከ2600 ዶላር ያላነሰ እየተከፈላት ነገር ግን ቤሮውን ለሚጋሩት ግለሰቦች ስልክ በመመለስና የነርሱን ስራ በመስራት እንጂ ለመረዳጃው የምታበረክተው ባለመኖሩ ፣ አመራሩ ጉዳዩን በጽሞና በመመርመር የስራ ሰአቷን በመቀነሱ ጥቅማቸው የተነካ አስተባብረው ማወክ መጀመራቸውን ነው። ባይገርማችሁ ይህ ገጽ በዚህ ጉዳይ ዙሪያ ቀደም ብሎ መጣፉ  አይዘነጋም። መረዳጃው በአቅሙ መሰረት መጓዝ ይገባዋል። ካለበት ቦታ በደባልነት የሚከፍለው ኪራይ የናጠጠ ነውና በውብ ሕንጻ ላይ በ200 ዎች ዶላር ያማረ ቢሮ ሊከራይ እንደሚችልና በፈቃደኛ (volunteers) ሰራተኛ ቢሮውን ማሟላትንም በቅርቡ ያደርጋል የሚል እምነት አለን። እነዚህ የሚንጫጩት የጥቅም ተጋሪዎችና በጡረታ ውስጥ ተቀምጠው የሚሰሩት የጠፋቸው ግብዞች መሆናቸውን ገጻችን በሚገባ የሚረዳው ነው። ቅንነት የሚባለው ቃል በእርግጡ ቢረዱ ኖሮ ኃይላቸውንና እውቀታቸውን አዋህደው ለሀይማኖታቸው፣ ለወገኖቻቸውና ለተተኪው ትውልድ የአቅማቸውን ቅን ሥራን ባደረጉና  ለምሳሌነት በበቁ። ያለፈውን በዚህ ገትተው ዛሬ ቅንነትን ታላብሰው ከወገኖቻቸው ተቀላቅለው ቅን በማድረግ የተሻለና የከበረን ስም ይላበሱ በማለት ገጻችን ጥሪውን ያቀርባል?

ይህንን ጥሪ ንቆና ማን አለብኝ ብሎ በዕብሪት ታውሮ በፈረሰ መረዳጃ ማህበር ስም እንዳለፈው ንጹሀን ኮንኖ የሚኖርበት ዘመን ማለፉን ዛሬም ካልተረዱት፣ እስከ ዛሬ አብረን ኖረናልና እኔ ጣቴን በእነ እከሌ ላይ አላነሳም ወይንም የእነ እከሌን ስም ጠርቼ አልኮንንም እየተባለ የተኖረበት የሀሰት ሕይወት ዛሬ አክትሟል። ወገኖቻችን ንቃተ ህሊና ዛሬ ጎልብቷልና እንደ ትላንትናው አይቶ አላየሁም፣ ስምቶ አልሰማሁም፣ ሰላም ልኑር፣ የሚባልበት ወቅት አርጅቶ ግልጽ ውይይት መጃመሩንና ላሉብን ድክመቶች ሁሉ እንዴት ማስተናገድ እንደሚቻል ዛሬ ወገናችን እየተረዳው መምጣቱን በገሀድ እያሳየው ነው። ባለፈው የዳላስ ሚካኤል የአባላት ስብሰባን ያልተገኘው ምዕመን በቃልና በስልክ የተማጸኑትን ችላ በማለትና የእነርሱን ማንነት በመረዳቱ እራሱን ገልሏል። ዛሬ ደግሞ አፉን ከፍቶ በተግባር ሊያስወግዳቸው ተዘጋጅቶ እንደጠበቃቸው በተረዱት በማለት ለዛሬው በዚህ ስንቋጭ በዐላችሁና ግባኤችሁን እግዜብሔር ይባርክላችሁ እንላለን።

ከዚህ በታች ወደ አስቀመጥነው የአባ ሰላማ ገጽ በWEDNESDAY, JUNE 8, 2011
እትሙ ያስቀመጠው የሚላመጥ አለውና ውድ አንባቢያን ጎራ ብላችሁ በማንበብ ያራሳችሁን ግብዛቤ እንድትወስዱ እንጋብዛለን ። ገጹ ለመግባት የሚቀጥለውን ይጫኑ ወይንም ኮፒና ፓሴትን በማድረግ ይጠቀሙ።
http://www.abaselama.org/2011/06/read-pdf_4347.html#more

እርሶስ እንደኛ እንባዎ ታብሷል?

እርሶስ ምን ይላሉ?

2 comments:

Anonymous said...

don't you say any thing about Luele kale Akalu who was spreading his non-Ethiopian Orthodox Church teaching on the so called yesosit ken gubae? He has been caught teaching yekihidet timihirt and suspended from preaching and any kind of service in the church. He has been asked to be under Likawint Abatoch kititil and learn his mistakes and set up to finish his nisha, but he refused it and fled to USA. The reason is he just wanted to stay Menafik. He is not Orthodox. Thanks for Bordochachin yesirachihun yistachihu.

Anonymous said...

ይህን ጽሑፍ የምታነቡ ሁሉ እኛንም ለመታዘብ ከፈለጋችሁ በአካባቢያችሁ የሚገኝን የማህበረ ቅዱሳን አባል "ጌታ ኢየሱስ‚ "የናዝሬቱ ኢየሱስ‚ "ኢየሱስ አዳኝ ነው‚ የሚሉትን የከበረና ምሥጢራዊ ስም በማንሳት መንፈሱ ምን ያህል እንደሚረበሽና እንደሚቆጣ መመልከት ትችላላችሁ የማህበረ ቅዱሳን አባል መሆኑንና አለመሆኑን እንኳ በዚህ ስም አጠራር ለይቶ ማወቅ ይችላል። ሆኖም ግን መንፈሱ ጌታችን መድኃኒታችን የሚለውን አጠራር በመዘርዘር ለማጭበርበር ይሞክራል። መንፈሱ ጋታችን መድሃኒታችን ማለት ከቻለ የናዝሬቱ ኢየሱስ ሲባል ለምን ይደነግጣል? ይህ ነው እንቆቅልሹ!
ታዲያ ማህብረ ቅዱሳን የናዝሬቱ ኢየሱስ ሲባል የሚደነግጥ ከሆነ የተቋቋመበት ዋና አላማ ምንድን ነው?
የመጀመሪያው የማህብረ ቅዱሳን አላማ የሥጋ ዘመዶቹ የሆኑትን የተክለሃይማኖት ተከታዮችና የዘራ ያዕቆብን የተበላሸ ታሪክ ለመሸፋፈን ነው። ወንጌል እንዲሰበክና እውነቱ እንዲወጣ አይፈልጉም፤ ተክለሃይማኖት ተከታዮችና ዘራያዕቆብ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን እና ሕዝብ ላይ የፈጸሙት ተንኮል እንዲገለጥባቸው አይፈልጉም። ለዚህም አላማቸው ወንጌል እንሰብካለን እያሉ በወንጌል ስም የተክለሃይማኖትን ገድልና ተረት በመስበክ ሕዝቡ የተሳሳተ ወንጌል እየሰማ እንዲደነዝዝ ያደርጋሉ።
ሁለተኛው ደግሞ በተክለ ሃይማኖት ስም የተሰወረውን አላማቸውን ማሥፈጸምና መንበሩን መውረስ ነው። ለዚህም የተለያዩ መነኮሳትን በመመልመል ለጵጵስና እያቀረቡ የሲኖዶሱን አባላት በማብዛት መንበረ ፓትርያርኩን መቆጣጠር ነው። ይህን የማህበረ ቅዱሳን ፍላጎት ያወቁ መነኮሳትም የተክለ ሃይማኖትን ሥእል ከትራሳቸው በማድረግ፣ ደብረ ሊባኖስ ሄዶ በመመንኮስ፣ ስለ ተክለ ሃይማኖት በማስተማር፣ የተክለዬ ታማኝ ወዳጅ መሆናቸውን በማሳየት ጵጵስናን ለመሾም ደጅ እየጠኑ ነው።
ለምሳሌ፦ በተክለ ሃይማኖት ስም የሥጋ ሥራ እየሠሩ ያሉትን ወገኖች ለማስደስትና የማህበረ ቅዱሳን ታማኝ ወዳጅ ለመሆን ጥረት ከሚያደርጉት አባት መካከል አንዱ ተክለ ሃይማኖትን እና ገብረ መንፈስ ቅዱስን ወደ አሜሬካ በመውሰድ የዲሲ እና የአትላንታ ታቦቶች አድርገው ወዳጅነትን አትርፈዋል።
የትግሬዎችንና የቡልጋዎችን ወዳጅነት ለማትረፍ ያሰቡት የዳላሱ ቄስ---- ደግሞ አቡነ አረጋዊንና ተክለ ሃይማኖትን ደራርበው ታቦት አድርገዋል። ሁሉም የሰውን ወዳጅ ለማብዛት እንጂ የሃይማኖት ሥራ ለመሥራት የሚፈልግ የለም። በአዲስ አበባ ከተመሠረቱት ወደ መቶ ሃምሳ ከሚጠጉት አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ በኢየሱስ ስም የተሰሩት ሁለት ብቻ ሲሆኑ በአሜሪካ ግን አንድ ብቻ የኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን አለ [በውጩ ሲኖዶስ ሥር]። ኢየሱስ የሚለውን የተጸውዖ [ዋና መጠሪያ] ስም የፈሩ አንዳድ ምእመናን ግን መድኃኔ ዓለም የሚለውን የግብር ስም [የሥራ ስም] በማንሳት ቤተ ክርስቲያን መሥርተዋል። ይህም ተመስገን ነው። የማህበረ ቅዱሳን መንፈስ ያለባቸው አቡነ ... ወደ አሜሪካ ከሄዱ ጀምሮ ብዙ አብያተ ክርስቲያናትን የከፈቱ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ ጥቂቶቹ ተክለ ሃይማኖት [ዲሲ]፣ ገ/መንፈስ ቅዱስ [አትላንታ]፣ ራጉኤል [ዲሲ]፣ ገብርኤል [ኬንታኪ] ወዘተ ናቸው። ኢየሱስን ግን ረስተውታል ከዘላለሙ ፍርድ በመስቀል ሞቶ ያዳናቸው እውነተኛ ወዳጅ ግን እርሱ ነበር። እነሱ ግን አንድ ቤተ ክርስቲያን እንኳ በስሙ ለመትከል ፈቃደኛ አይደሉም "ለወፎች መጠለያ ለቀበሮዎች ጉድጓድ አላቸው የሰው ልጅ ግን ራሱን የሚያስጠጋበት እንኳ የለውም‚ በማለት ጌታ አስቀድሞ ባይናገር እጅግ ይገርመን ነበር። ዛሬ ኢየሱስ የሚለውን ስም ደፍሮ ለማንሳት ትልቅ እምነትን ይጠይቃል፤ ኢየሱስ የሚለውን ስም ከቤተ ክርስቲያን እያስወጡ ወደ አሜሪካ እንኳ የዘው የሚሮጡት አቡዬን እና ተክልዬን ነው ድሮስ ወደ አሜሪካ እየተሄደ ያለው በዘመድ አይደል! ኢየሱስማ ምን ዘመድ አለው? እንኳንስ ወደ አሜሪካ የሚወስደው በኢትዮጵያም እነዳንኤል ክብረትና ዘመድኩን እያሳደዱት ነው።
ወደ ተነሳንበት ርእስ እንመለስና የተክለ ሃይማኖት ጠበቃ ነን ያሉ በማህበረ ቅዱሳን አሰልጣኝነት በሥውር የተደራጁ ወንበዴዎች አገልጋዮችን መደብደብ ጀምረዋል። ቀሲስ አሸናፊ ገብረ ማርያምን፣ ዘማሪ ዳግማዊን፣ ዘማሪ ምርትነሽን የድንጋይ ናዳ በማውረድ በመርካቶ ተክለ ሃይማኖት ደብድበዋቸዋል። ይህ ቡድን የማህበረ ቅዱሳን "አማራጭ ኃይል‚ ተብሎ በሥውር የተደራጀው ጉዳት ለማድረስ የተዘጋጀው ቡድን አካል ነው።
ባሁኑ የኢትዮጵያ ትውልድ ከሃያ አምስተኛ ኪሩብነት እየወረዱ የመጡትን አባት ተክለሃይማኖትን በዚያው በኪሩብነታቸው ለማቆየት ሲባል በቡድን ተደራጅቶ መደባደብ ዋና የማህበረ ቅዱሳን አማራጭ ሆኗል። ታዋቂው ደራሲ በውቀቱ ስዩም "እግር የሌለው ባለ ክንፍ‚ በሚል ያቀረበው ጽሑፍ ተክለ ሃይማኖትን ጥያቄ ላይ የጣላቸው ሲሆን ትንሽ ዱላ መቅመሱ ተሰምቷል። "አለባብሰው ቢያርሱ በአረም ይመለሱ‚ እንደተባለው ሃያ አምስተኛ ኪሩብ ብናደርጋችውም፤ ስድስት ክንፍ ብናወጣላቸውም፣ ቃል ኪዳናቸውን ብናበዛውም፣ ቤተ ክርስቲያን እየሰራን ብንሰብክላቸውም፣ ብንዘምርላቸውም፣ ከትውልዱ እንደማዕበል እየፈሰሱ ያሉ ጥያቄዎችን ማቆም ግን አልተቻለም። ምክንያቱም ጻድቁን "ሰይጣንን ገርዘው የቤተ ክርስቲያን አገልጋይ አድርገውታል‚ የሚለው ትምህርት ጥያቄ ላይ ጥሏቸዋል። ቅዱስ ጳውሎስ በገላትያ 5፥ 6 ላይ "መገረዝም ሆነ አለመገረዝ አይጠቅምም‚ ብሎ አስተምሮ እያለ ሰይጣንን መግረዝ ለምን አስፈለገ? በውነቱ ይህ የሐዋርያትን እምነት ከሚከተል ሰው ይጠበቃልን? እንዲህ ዓይነቱን ማፈሪያ ታሪክ በማረም ፈንታ በርሳቸው ምክንያት ባልተገረዙ የቤተ ክርስቲያን ወንበዴዎች ተጠግቶ፣ ደም ለማፍሰስ መጣደፉ ግን አግባብ አይደለም።
እኛን የሚያስፈራን ግን ማህበረ ቅዱሳን እነምርትነሽን መደብደብ እንዳማራጭ የሚወስደው ከሆነ ዱላው ነገ ወደ ማህበረ ቅዱሳን አባላት ፊቱን ማዞሩ የማይቀር መሆኑ ነው። እናም የቤተ ክርስቲያን የርስ በርስ ጦርነት ከመነሳቱ በፊት የመጨረሻ እልባት ይደረግለት ስንል እንማጸናለን። መንግሥትም ቢሆን እንዲህ ዓይነቱ መከፋፈል ለፖለቲካ ይጥቅመኛል ብሎ እንዳያስብ፤ ይህ ከሁሉም የከፋ ኋላ ቀርነት ነው ድህነትን እየተዋጋን እንዳለን ሁሉ ኋላ ቀርነትንም መዋጋት አለብን እምነት በሕሊና እንጂ በጉልበት አይሆንም፤ በጉልበት እንዲያምን የተደረገ ሰው እስላም እንጂ ክርስቲያን ሊሆን አይችልምና ማህበረ ቅዱሳን ወንበዴዎችን በማደራጀት የከፈተውን ጦርነት እንደገና ቁጭ ብሎ ያስብበት።
ዘማርያኑም ማስተዋልና ትግሥት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል በደም ፍላት መንፈሳዊ ሥራ አይሰራም በእግዚአብሔር ፊት በጾምና በጸሎት በመውደቅ እንጂ።አንዳዶቻችሁ ግን ወዘሮ እጅጋየሁን መጠጋታችሁን አልወደድነውም። እርሷን ተዋትና እግአዚአብሔርን ተጠጉ፤ በፖሊስና በዘመድ ኃይል ፍርድን ለማግኘት አትሞክሩ። ይህ የወንጌል ሕይወት ነው ብለን አናምንም። በናንተ ላይም ጥያቄ አለን ወንጌል ሰላማዊ ስለሆነ እየወደቅን ብዙዎችን ከወደቁበት እናነሳለን እንጂ ደካማዎችን በጉልበት እየጣልን ለመቆም አንሞክር። ይህን ከናንተ ያርቀው አሜን!

Source http://dejesemay.org/