Tuesday, February 22, 2011

እራሳቸው ያቀጣጠሉት እሳት እራሳቸውን እየፈጃቸው......

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!

ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።


እራሳቸው ያቀጣጠሉት እሳት እራሳቸውን እየፈጃቸው ያሉትን አምባገነን መሪዎችን እያየን ከእነርሱ ትምህርት የሚወስዱ ይኖሩ ይሆን? 

እንደምን ከረማችሁ? ፈቃዱ ሆኖ በዚህ ጦመር ዳግም እንድንገናኝ ላደርገው ለልዑል እግዚሀብሔር ክብርና ምስጋና ይሁን። አሜን። ከላይ ያስቀመጥነውና ለዛሬው መነሻ ጥሁፋችን ያደረግነው በአለም ዙሪያ ለሚካሄደው ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ያለንን ትንተና ለመስጠት ሳይሆን፤ በጥቂት አምባገነኖች የሚደረገውን የሌላውን መብት ጥሰት አንዱ የሆነው ፣ ድንበር ተሻግሮ የሚደረገው ሕገወጥ ሴራ ነው። ይኸውም ገና ለገና ከሀገር ውጪ የሚገኙ ተወላጆች ጥላቻን ብሎም ሥልጣኔን ያሳጡኝ ይሆን በሚል በቅጥረኞች ወይንም በደጋፈዎቻቸው የሚደረገው ሁከት አንዱ ነው።

ለምሳሌ ከትውልድ ሀገራቸው እርቀው የሚገኙ የኢትዮጵያ ተወላጆች በትውልድ ሀገራቸው ውስጥ ያለውን የሶሻል ኢኮኖሚና የአስተዳደር መብትና ነጻነት በተመለከተ አዲስ ከሰፈሩበት ወይንም ለአዲስ አመለካከት በመጋለጣቸው ምክንያት አሊያም ባገኙት ነጻነት የተለያየ አመለካከት በመያዝ እራሳቸውን መግለጽ የተለመደ ነው። አንዳንዶች በመደራጀት የተቃውሞ ፖለቲካ እንቅስቃሴ እንደሚያደርጉ እሙን ነው። እነዚህን ተቅዋሚ ድርጅቶችን ለማብከን ሲባል የማይደረግ ጥረት የለም። ለዚህም ሲባል ከፖለቲካ ድርጅቶች ባሻገር ያነጣጠረው በሀይማኖትና በስቪክ ድርጅቶች ላይ ነው። ለዚህም በናንተ የዳላስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ደብር ለረዥም ጊዜ ባካበተው መንፈሳዊ ግልጋሎትና ባቀፈው የምዕመናን ቁጥር ብዛት የመጀመሪያው ሰለባቸው ለማድረግ ቅጥረኛዎቻቸውንና አድርባይ ደጋፊዎቻቸውን አስርገው ለማስገባትና ለመቆጣጠር ያደረጉት ጥረት በሀቀኛ የኦርቶዶክስ ልጆች ሲቀለበስባቸውና የፖለቲካ አሻጥራቸው ሲጋለጥ፤ መንፈሳዊና የሀይማኖቱን መስፈርት የማያሟላ፣ ደንቡንና ሕጉንም ጥሶ ፤ አንድዬና ብርቅዬ የሆነውን ደብራችሁንና የመረጣችኃቸውን ሀቀኛ የቤተክርስትያኗን ልጆች ጨምሮ በመክሰስና ባማስከሰስ ማንኛውንም መንፈሳዊና የሲቪክ ማህበራትን መቆጣጠር ካልሆነ ማዳከም ብሎም ማጥፋትን ስራዬ ብለው ከጀመሩ መክረማቸው ለሁላችንም የታወቀ ነው። ለማስረጃ ያህል ከዚህ ቀጥሎ በገጻቸው የለጠፉትን እንዳለ ግልባጩን ለናንተ አውጥተነዋል።

United St. Micheal Church Peace Resolution Seekers Committee 3rd General Meeting 1--23-2011, Report from PR
የተባበሩት የቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የሰላም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ                 UNITED ST. MICHAEL CHURCH PEACE RESOLUTION SEEKERS COMMITTEE
       Meleket4u@gmail.com

1-23-2011
                                          ጠቅላላ የምዕመናን ስብሰባ

የዛሬውን አጠቃላይ ስብሰባ በ15:15 ፒ ኤም ም/ሊቀመንበሩ አቶ ግርማቸው አድማሴ ስብሰባውን በቄስስ መስፍን ደምሴ ቡራኬ በመስጠት በአንድነት በፀሎት ከፍቱልን። በ 5 ፒ ኤም ስብሰባው ተዘግቷል።

ከተሰጡትም ገንቢ አስተያየቶችና መልዕክቶች መካከል፤
ሀ. የኮሚቴው ዋና ሥራ የሆነው የሕግ አገልግሎት ጉዳይን በተመለከት መሰረታዊ ጥያቄዎችና ዓላማዎች ግልፅና አጭር በሆነ መልክ ለምዕመናን መግለጫ እንዲሰጥ።
ለ. የመልአከ ሣህልን በሥራ ጉዳይ ምክንያት ወደ ሌላ ግዛት መሄዳቸውን አስመልክቶ በ 1-28-2011 በሚደረገው የሽኝት ዝግጅት ላይ ከዓርብ ጉባኤ ጋር በመቀናጀት አሰኛኘት እንዲደረግላቸው።
ሐ. በቅርቡ በሚካሄዱት የፍርድ ቤት ቀጠሮዎች 2-7-2011፣ በ3 ፒ ኤም እና 2-10-2011፣ በ9 ኤ ኤም ላይ መገኘት የሚችሉ ምዕመናን አንዲገኙ።
መ. “ቤተክርስቲያን ተከሷል” የሚባለው የተዛባ ውዥንብር የሚወገድበት ትክክለኛው የፍትሕ ጥረት ለምዕመናኑ በመግለፅ የሚረዱበት መንገድ እንዲፈጠር።
ሠ. በዓርብ ጉባኤ እየተዘጋጀ ባለው ሦስተኛ ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ ኮሚቴው ትብብሩን እንዲያደርግና መድረኩንም በመጠቀም ለሕዝቡ መልእክት እንዲያዘጋጅ።
ረ. የሕግ ጉዳዩን በተመለከተ ለሚያስፈልጉት የኃሳብና የገንዘብ ዕርዳታ ቅንጅትና ትብብር በመላ ምዕመናኑ የሚካሄድበትን።

ሕዝብ ግንኙነት ክፍል

Posted by .......***መለከት***MELEKET*** at 2:29 PM 0 comments


ከዚህ በላይ እንደተቀመጠው እነዚህ አጽራረ ቤተክርስትያን የመንፈሳዊ ጉዳዮችና ችግሮችም ቢኖሩ በመንፈሳዊ መንገድ እንጂ በአለም ፍርድ ቤት አይበየንም።
2. በዲፕሎማት ፓስፖርት መጥተው ያለምንም ውድድር ያስቀጥሯቸው ቄስ ፣ በተሰጣቸው መመሪያ መሰረት ምዕመናኑ ለመለያየትና የቤተክርስትያኑን አንድነት በማናጋት ችግር የፈጠሩትን ለመመለስ ያደረጉት በመክሸፉ፤
3. በፍርድ ቤት ክስ ውስጥ የሚጫውቱት ሚና፤
4. አመራሩን ለይቶ መክሰስ ቤተክርስትያኑን መክሰስ ማለት መሆኑን ፣ ተመራጮቹ የቤተክርስትያኑ ሥራ ሲሰሩ እንጂ በግል ሕይወታቸው እስካልሆነ ድረስ ቤተክርስትያኑ በሕግ መከላከያ ወጪያቸውን እየከፈለ ባለበት ሁኔታ፤ ቤተክርስትያን አልከሰስንም ብሎ ሸፍጥ እንጂ እንደነሱ ውዥንብር አለመሆኑ ለሁላችንም ግልጽ ስለሆነ ምናልባት ውዥንብር ውስጥ የተደፈቁት እነሱው ለመሆናቸው፤ 
5. በመንፈሳዊ ስብሰባ ስም ጸረ ኃይማኖትና አጽራረ ቤተክርስትያን ሴራ የሚያራምዱና ንጹኃኑን ወደ ኃጢያት የሚመሩ፤ 
6.እንደዚሁ ንጹኃን የሆኑትን ምዕመና በማጥመድ የገንዝብ ዕርዳታ እንዲሰጣቸው የሚከጅሉ፤ 


እንግዲህ ከዚህ በላይ ያለውን የሚያካሂዱና የሚያራምዱ እነማናቸው? አሁንስ ምን እያደረጉ ናቸው? ለሚለው ጥያቄ ከዚህ ቀደም ሲል በሰፊው የዘገብን ሲሆን አሁንም እንዚሁ ግለስቦች ናቸው የዳላስና ፎርትዎርዝ የኢትዮጵያ መረዳጃ ማህበርን አንቀው ለመያዝና በዚያ አማካኝነት ሕብረተሰቡ ተደራጅቶና ተረዳድቶ የተሻለ ደረጃ ላይ እንዳይደርስ እክል መሆን ዋነኛ ተልዕኮአቸው ያደረጉት። ስለዚህ እናንተ የዳላስና አካባቢው ነዋሪ የኢትዮጵያ ተወላጆች የሆናችሁ ይህንን ሴራ ከወዲሁ ተገንዝባችሁ በአንድነት በመቆም በ02/27/2011 በተጠራው የመረዳጃ ማህበር ጠቅላላ ስብሰባ ላይ በመገኘት፣ የነርሱን አጃንዳ ወደ ጎን በመተው፣ ጊዜውን የጨረሰውን ቦርድ የሚተካ አዲስ አስመራጭ ኮሚቴ ብቻ መስርታችሁ እንድትደመድሙ ጥሪያችን ነው። ይህ ካልተገበረና ሕብረተሰቡ ከተከፈለ አዲስ የመረዳጃ ማህበር መመስረቱ አይቀሬ ነው። ሕብረተሰቡ እንዳይጠናከርና እድገቱን እንዳያስመዘግብ ለረዥም ጊዜ ስውር ደባ ፈጣሪና ከጀርባ ተዋናይ የሆኑት፤ ዛሬ የትግራይ ነጻ አውጪ አሽቋላጮች ከተደበቁበትና በወገኖቻችን ስም ከሚጠቀሙበት የግብረሰናይ ድርጅት ማለትም እንደ ካቶሊክ ቻሪቲና እንደ ዳላስ ሲቲና ካውንቲ መንግስት ውስጥ እንደሚወጡ የታወቀ ነው። ለዚህም ሲሉ ነው በመረዳጃው ማህበር ውስጥ ትረስቲ በማዋቀር እራሳቸውን ወይንም ቢጤዎቻቸውን እያደላደሉ የሚገኙት። እኛም እስከዛሬ ምንም ከናንተ ያገኘነው ስለሌ አሁንም የረባ የሌላችሁና ሕብረተሰባችን ላይ የምትሰሩት በደል ይቁም የምንል።

እርሶስ ምን ይላሉ?

Sunday, February 20, 2011

በእውነት ለትውልድ ሀገራችንና ወገናችን እንስባለን?

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!

ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።


በእውነት ለትውልድ ሀገራችንና ወገናችን እንስባለን?


ዝምታ ወርቅ ነው ሲባል ነበር ያደግነው። ዛሬ ደግሞ ዝምታ ጎጂ ወይም ካለመናገር ደጅ አዝማችነት ይቀራል የሚለውንም አባባል ጨምሮ በየፈርጁ ከተጠቀምንበት መልካም ውጤት ለማየት ያበቃናል። እንደምን አላችሁልን? እናንተንም እንደኛ አቅፎና ደግፎ በፀጋና በምሕረቱ ተንከባክቦ ዳግመኛ በዚህ ገጽ ለመገናኘት ፈቃዱ ለሆነና ቀጣዩንም ዕድሜ ደግሞ ፈቃዱ ከኛ እንዲሆን፣ ይህንንም ዓብይ ጾም በሰላም አስጀምሮ በሰላም እንዲያስጨርሰን፤ የምናቀርብለትን ጾምና ጸሎት እንዲቀበለን፤ ይቅርታን ምሕረቱን እንዲያበዛልን፤ ልባችንና አንደበታችንን እንዲገዛልን፤ አውቀንም ሆነ ሳናውቅ፣ በድፍረትሆነ በስህተት ያሳዘነውም ሆነ የበደልነው ቢኖር ይቅር ይለን ዘንድ፤ እኛም የተቆጣንበት ወንድም ይሁን ሴት ከልባችን ይቅር እንል ዘንድ ልቦናችን ያስገዛልን፤ ሁላችንንም በስላምና በፍቅር አንድ አድርጎ ይጠብቅልን፤ አጽራረ ቤተክርስትያንን አስታግስልን፣ እያልን በታላቁና ገናና ስምህ እንማጸንህ ዘንድ ፈቃድህ ስለሆነ ለአንተ ክብር ምስጋና  ይሁንልን። አሜን።

አንድ ታዳሚያችን ከሰደደልን ጥሁፍ በመነሳት ባለፈው ዕለተ ሰንበት ከቅዳሴ በኃላ በስለት ስም ይነገርልኝ ብለው ለመጋቢው ካሕን ያቀረቡትን ጥሁፍና የካሕኑን መልስ የሰማው ምዕመንም በግለሰቡ ገፋፊነት  የተሞከረው ኾነ ተብሎ offensive language ያለቦታው ለመጠቀም በመሆኑና እራሱን የቻለ አጀንዳ ያለው በመሆኑ ከላይ እንዳስቀመጥነው፤ ዝምታ ወርቅ ነው የሚለውን እናሰምርበታለን። ይሁንና በዚህ የዐብይ ጾም ለሁላችንም ማስተዋልን ሰጥቶ፤ ጌታ በምሳሌ 50 መንጋዎች ውስጥ አንድ ቢጠፋበት ለፍለጋ 49ኙን ትቶ በመሄድ እንዳስተማርን ፤ እኛም ከልባችን የጠፋውን ፍልጋ በጾምና በጸሎት መትጋትና ስናገኝም እጆቻችንን ዘርግተን መቀበል እንዳለብን ገጻችን በጥያቄ ለሁላችንም ያስተላልፋል?

ከዚሁ በተጓዳኝ እራስን ወይንም ቅሬታን በመግለጽ የሚያመጣውን ውጤት በአለማችን ዙሪያ እየተካሄደ ያለውን ነውጥ ስንዳስስ ከግለሰብ አልፎ ሀገርና አህጉርን እያተራመሰ ነው። ችግሮችና ብሶቶች በዘመናዊውና ቴክኖሎጂ ወለድ በሆነው መንገድ ሁሉ መጠቀም የግድ ሆኖ ለአመታት ሙጥኝ ብለው የራሳቸውን ሀገርና ሕዝብ ሲበድሉ የኖሩ በሕዝብ ተቃውሞ የሥልጣናቸው ሁሉ ፍጻሜ ሲሆን፣ ጎራቸው እየታመሰ ያሉትም አምባገነኖች እንደዚሁ ቀናቸውን እየቆጠሩ ይገኛሉ። ከአረቡ ሀገራት ብዙም የማትርቀው የኛው ኢትዮጵያ መብት መርገጥ የጀመረችው ከንጉሣዊው ዘመነ መንግሥት ቢሆንም ባለፈው 40 አመታት ውስጥ ከዘመን ወደ ዘመን እየባሰበትና እየከፋ የመጣው የሕዝቦች ጥያቄን በሰላማዊ መንገድ ከመፍታት ይልቅ በኃይል መስበርን ሲተገበር በማየት እንዲሁም የዚሁ ሰለባ በመሆን ለስደት የተዳረግን ሁሉ የገፈቱ ቀማሾችና እማኞች ለመሆን አብቅቶናል።

ዛሬ እኛና እናንተ በዚህ ገጽ አማካኝነት እንደልባችን ሀሳባችንን ብቻ ሳይሆን ያለውንም ዕውነታ ለመለዋወጫ መጠቀሚያ መስመር በመሆን ስንጠቀም፤ ከዚሁ ጋር ዘመን ያመጣውን  ጥበብ በመጠቀም ብሎግ፣ ፌስቡክ፣ ቲውተርና ዩ ቲዩብ ጥቂቶች ናቸው።
አምባገነን መሪዎች ግን በእጃቸው ያለውን ይህን ጥበብ ከሕዝባቸው አንቀው የሥልጣን እድሜ ያራዘሙ የመሰላቸው ሁሉ ቀኑ እየመሸባቸው ይገኛል። ባለፈው አመት ለአለም ትዝብት የበቃውና አስቂኝ የሆነው የትውልድ ሀገራችንን ብሔራዊ ምርጫ ውጤትዛሬም እውነተኛና ሕዝባዊ ነው የሚሉ አይነ ደረቆች ካሉ እንደ አምባገነኖች አእምሮ ራሳቸውን wire ያደርጉ ወይንም የስነ ልቦና ችግር ያለባቸው ብቻ ናቸው። እነዚህም ለነዚህ ጓጉንቸር መሪዎች የቀረቡና የሥልጣን ሸሪኮች፣ የጥቅም ተካፍዮችና ቅጥረኞች ሲሆኑ ምንም አይነት የሞራል ግዴታን የማያውቁ ራሳቸውን ያሳወሩ ብቻ ናቸው።

አንዳንድ ፖለቲከኞች በሰሜን አፍሪካ ተጀምሮ በአረቡ አህጉር የተቀጣጠለው አብዮት ለኢትዮጵያም እንዲደርስ ቅስቀሳ ጀምረዋል። ነገር ግን አሁን በሥልጣን ላይ ያለው የለገሰ ዜናዊ አስተዳደር እዚህ ይደርሳል ተብሎ ያሰበ ማንም አልነበርም እቅድም የለም። በዚህ ወር 36 አመት ይሞላዋል የሚባለው ድርጅት በልደት በአል ስም ኬክ ሊቃመሱ ቀርቶ ፕላን ቁጥር 1, 2, 3, ወዘተ እያለ የሕዝብ አመጽን መግታት ካልቻለ የትኛው ሀገር ይቀበለኝ ይሆን? በማለት በሽብር ላይ መሆኑን የሚደርሱን ዘገባዎች ይጠቁሟሉ። ከጅምሩ እነ አባይ ጸሀይ የትግራይ ነጻ አውጪ ብለው ለጠባብና ለአንድ ጠቅላይ ግዛት የመገንጠል ነጻነት ብቻ ነበር። ያንን ካሟሉ በኃላ ፤ ከሌሎች ገንጣይ ቡድኖች ጋር ሆነው ሀገር ለመገነጣጠል ባደርጉት እንቅስቃሴ ትግል መዲናዋን ለመጨበጥና ራሳቸውንም ለማስቀመጥ ያበቁት። በለስ ቀንቷቸው በትረ መንግሥቱን ቢጨብጡም የነበረውን የወታደራዊ መዋቀር መበተንና የገቡትን የመጀመሪያውን ሀገርን የመገንጠል ኮንትራት እውነታ የፈጸሙት። ይህ በዚህ እንዳለ ወታደራዊ አመራሩም በአንድ ብሔር ቁጥጥር ሥር ወድቆ ፣ ጠበንጃ ያነሳውም ተቃዋሚ በዘርና በጎሳ ጠባብ አመለካከትና ከሌላው ብሔር ጋር ለመተባበር እምነት አልባ የሆነ፣ የተላያዩ በሀገር ውስጥ አለን የሚሉ ተቃዋሚ ሀይሎች እንደ ውጪዎቹ በወረቀት ላይ ብቻ የሰፈሩ ስሞች በሆኑበት ሰአት፤ ሕዝቡ ያንገሸገሸውን የትግሬ ነጻ አውጪ ተሳክቶለት በአመጽ ቢጥል የተዘጋጀ ተረካቢ ማነው? ሰላምና ፀጥታ መሰረታዊና ቅድሚያ የሚሰጠው ሲሆን፣ ተቃዋሚ ነን ወይንም ለውጥ እንፈልጋለን የሚሉ ወገኖች ሁሉ ምን ያህል ground work አጠናቀዋል? ምንስ ያህሉ የጸጥታ አስከባሪው ክፍል ተባባሪ ሊሆን ይችላል? ጊዜያዊ አመራሩንስ እነማን ይይዛሉ? በእርግጥስ ለሕዝቡ ያስረክባሉን? የመሳሰሉትን ጥያቄዎችን ከወዲሁ ማላመጥ ተገቢ ይመስለናል።


በሌላው በኩል የነዚሁ አንባገነን መሪዎች ተቀጣሪና አራማጅ የሆኑትን በቅርቡ በአለም ዙሪያ ለሰበካ የሚያሰራጨው የትግሬ ነጻ አውጪ እንደተጠበቀ ሆኖ አብረውን ከኛ ጋራ የሚኖሩ ሌሎቹ ቅጥረኞች በተሰጣቸው የሥራ ድልድል፤ የኛ የሆኑት ድርጅቶች ውስጥ ጠልቀው በመግባት ቁልፍ የሆኑትን ቦታዎችን መያዝ ነው። በራሱምግባር የማይተማመን መንግሥት በውጪ የሚገኙትን ተወላጆች በሙሉ ተቃዋሚ መስለው ስለሚታዩት፣ በፍራቻ ብቻ በተለያየ ጥቅማ ጥቅም በመደለል በነጻ የተሰጣቸው ጥቂት የሚባሉ አይደሉም። ለጥቅም ታውረው በአንድ ወቅት እሽቅድድም ከገቡት ውስጥ ከስረው የተመለሱት አያሌ ሲሆኑ፤ ለንዋይ ብለውም ህሊናቸውን ሸጠው በባንዳነት ያደሩም አሉ። ይህ ከፋፍለህ ግዛ መርህ በትውልድ ሀገራቸው ከእለት ወደ እለት ገፈት ቀማሽ የሆኑት ዜጎች ግን በገንዘባቸው እንኳ የተነፈጉት፣ ቅድሚያ ውጪ ለሚኖሩት ወይንም ለሥርዐቱ አንቋላጮች ብቻ በመደረጉ፣ ከመንግሥት ትብብር ለማግኘት እኛም ሀገር ለቀን መሰደድ አለብን ? እያሉ መጠየቅ ከተጀመረ አመታትን እያስቆጠረ ነው። 

በዳላስ ከተማም ቢሆን ቅጥረኞች መጀመርያ ያደረጉት የዳላስ ቅዱስ ሚካኤል ደብርን በመቆጣጠር በአማኒዎች መካከል ለትግሬ ነጻ አውጪ የስለላ ስራዎችን ማካሄድንና ተቃዋሚዎችን ማብከን፣ የሀሰት አሉባልታን መክፈት፣ ከህብረተሰቡ የሚገለሉበትን ማንኛውንም አይነት ዘመቻ ማካሄድና በሀገር ቤት ባሉ ዘመዶቻቸው ላይ ሽብርን መፍጠር ነው። ይኼንን ለማድረግ የጀመሩት ሳይሳካ ሲቀር፣ አጽራረ ቤተ ክርስትያን ከሆኑት ጎራ በመቀላቀልና በአንድ በኩል ደብሩንና አስተዳዳሪዎችን በመክሰስና በማስከሰስ ፣ በሌላ በኩል የሰላም ኮሜቴ በማለት በቅዠት ጎዳና ብቻቸውን በመቅረታቸው፤ ዛሬ በዳላስና ፎርትዎርዝ የኢትዮጵያን መረዳጃ ማህበርን ለመያዝ የመጨረሻ ትግላቸውን ከፍተዋል።


ባለፈው እንዳስነበብነው ሁሉ ለ30 አመት የመረዳጃ ማህበሩ በየጊዜው የሚለዋውጡት አመራሮች ለተለያየ የፖለቲካ ተግባር እንጂ ለህብረተሰቡ ይህን አደረኩኝ ብሎ የሰራው ጉልህ አስተዋጾ ለመጥቀስ የሚያዳዳን አንዳችም የለም። በተለይ በቅርቡ ወደ ከተማው የዘለቁና ይህንኑ ድርጅት ሽፋን በማድረግ የራሳቸውን ግብረሰናይ ድርጅት በመክፈት የመረዳጃ ማህበሩ የገቢ ምንጭና የህብረተሰቡን ስም ለራሳቸው መጠቀሚያ እያደርጉ መሆናቸውን ባለፈው ጥሁፋችን ያሰመርንበት ነጥብ ነው። በቅርቡም በማርች 5 ያዘጋጀው ዝግጅት ወጪው በሙሉ በስፖንሰሩ የተሸፈነ ሲሆን ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ከተባለ የቅዱስ ሚካኤል አዳራሽ ወይንም የሌላው በነጻ መጠቀም ሲቻልና መረዳጃው ማህበሩም ቢሆን በተጠቀመ ነበር ቀጥረናታል የተባለችውም የቢሮዋ ሰራተኛም ቢሆን ይህን የመሳሰለ ለሕብረተሰቡ ይጠቅማሉ የተባሉትን ዝግጅቶች ማመቻቸትና ስፖንሰሮችን ማቅረብም የስራዋ ድርሻ ውስጥ አንደኛው በመሆን ከፍ ያለ ገቢን መፍጥር መሆን ሲገባ፣ ለጩልሌዎቹ ይህንን በሕብረተሰቡ ስም እንዲተገብሩና የግል ጥቅም እንዲያገኙ የማህበሩን ስምና ማህተም እያመቻቹ የእውቅናና የትብብር ጥያቄ ደብዳቤ አዘጋጂ ባልተሆነ ነበር። አሁን ደግሞ የተሰገሰጉትና የምርጫ አገልግሎት ጊዜ የተቃጠለባቸው፤ የሕብረተሰቡ ንቃት ስላስፈራቸው፤ ባለፈው 2 አመት ከሰሩት አስነዋሪ ተግባር ላለመጠየቅ ሲሉ፣ ሕብረተሰቡ ባልመከረበት ፣ ባልሰጣቸውም ሥልጣን መተዳደሪያ ደንቡን በአንባገነንነት ለውጠው ትረስቲ አቋቁመናልና መርቁልን ብለው አይናቸውን በጥሬ ጨው አጥበውና አፍጠው እንዲሁም አግጠው መምጣታቸውን ባለፈው ጥሁፋችን እንዲሁ አስረግጠን ማቅረባችን እሙን ነው።

እንግዲህ ለእነርሱም እንደ ቀኝ እጅ የሚጠቀሙበትስ የሬዲዮ ፕሮግራም ተመሳሳይ የቅጥረኛ ተግባሩን ከማካሄድና የግለስቦች የግል መጠቀሚያ ከመሆን ወጥቶ መቼ ነው ለሕብረተሰባችን የሚጠቅም በሚሆን መልኩ ብቃት ባላቸው ሙያተኞችና በማህበሩ በቅርብ ክትትልና ቁጥጥር ሥር መዋል የሚችለው? አሁንማ ሠርጌን  ወይንም የጋብቻና የልደት በዐሌን በመረዳጃ ራዲዮ እንዲያበስርልኝ እከሌን ልጥራው፤ የሚዘግቡትን ስለማያውቁ ከኢንተርኔት ብቻ የከረመውን ዜና እንዳለ ኮፒ እያደረጉ ማቅረብን እንደ አገልግሎት የሚቆጥሩ፤ ወዘተ….. ብለን ድክመታቸውን ብቻ ሳይሆን ማይክ ስለያዙ ብቻ ለሕብረተሰቡ የሚበጀውን፣ አንድነቱንና ሕብረቱን በመጠቀም ከውስጡና ከውጪ የሚገኙትን ሙያተኞች በማስተባበር፤ ሕብረተሰቡ ትምህርት ያገኝበታል፣ እውቀቱን ያሻሽልበታል፣ በመተባበርና አንድ ሆኖ በመረዳዳት ኑሮውን ያሻሽልበታል፤ ከዚህ ሀገር ኑሮና ባሕል ጋር እንዴት ሊጣጣም ይችላል፤ ወዘተ በመሳሰሉት ነጥቦች ላይ በቂ ግንዛቤን ይጨብጥበታል የተባሉ ጊዜያዊ ሆነ ዘለቄታው ፕሮግራሞችን  በመንደፍ ማቅረብ ተገቢ ነው።


የሙያ አድማሶቻቸው የሰፉ ማለትም ከፍተኛ የትምህርትና የሙያ ብስለታቸውን አጣምረው የተቀመጡት የኢትዮጵያ ተወላጆችም ቢሆኑ እራሳቸውን በማዘጋጀት ለሕብረተሰባችን ሊሰጡት የሚችሉትን አስተዋጾ በቀላል የሚገመት አይድለምና ከየጓዳው በመውጣት ያለምንም ይሉኝታ የሚችሉትን ሁሉ እንዲያደርጉ እያስገነዘብን፤ አንዳንድ ጠባብና የግል ጥቅም ያሰከራቸው መንገዱን አስቸጋሪ ሊያደርጉባቸው እንደሚሞክሩ ያለፈው ተመኩሮዎች ቢያስረዱም፤ ፍላጎቱና ቅንነቱ እስካለ ድረስ “ይቻላል“ እንደተባለው ለውጤት እንደምትበቁ በመተማመን ነው። የኢትዮጵያ ተወላጅ ካልሆኑት ያላችሁም net work ቀላል ስላልሆነ የውጪዎችንም በየፈርጅ አሰባስቦ ጠቃሚ የሆኑና ሕብረተሰባችንን ሊያሳድጉ የሚችሉ ድንቅዬ ሥራዎችን በተግባር እንደምታውሉ እርግጠኞች ነን። 

እርሶስ ምን ይላሉ? 

Tuesday, February 15, 2011

የፈሩት ይደርሳል ፣ የጠሉት ይወርሳል እንዳይሉ?

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!

ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።


የፈሩት ይደርሳል ፣ የጠሉት ይወርሳል እንዳይሉ?

እኛ ሌላውን እንደምንጠይቅ ሁሉ የኛም መጠየቅ አይቀሬ ነውና የት ጠፋችሁ? ለምትሉን ሁሉ እኛ በጣሙን በእያለንበት በእርሱ በፈጣሪ ምሕረት፣ በረከትና ፀጋ እጅጉን ተጠብቀን ነው ያለን፤ እናንተንም እንዲሁ ጠብቆ ዳግም እንድንገናኝ ፈቃዱን ላደረገልን ልዑል እግዚሀብሔር አሁንም ክብር ምስጋና ለእርሱ ይሁን። እሜን።


የዳላሱም ታላቁ ደብር የቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል በተዋህዶ ልጆች እንክብካቤው ከመቼውም ይልቅ አምሮበትና ደምቆ አገልግሎቱን ለአማኒው እያበረከተ መሆኑን ከስፍራው የሚደርሰን ዘገባ ብቻ ሳይሆን እናንተው ከተገልጋዮቹ በላይ ዋቢ አንሻም። ቀድመው ከመራቅም አልፈው በስህተት ከአጽራረ ቤተክርስትያን ጎራ እስከ ኮሚቴ አባልነት የገቡ ሳይቀሩ ዛሬ ተጸጽተው ወደ ቤተክርስትያናቸው በመመለስ አባል ለመሆን በብዛት ማመልከቻ ከሚያስገቡት ውስጥ ይገኛሉ። የአበው አባቶችም ትምህርት ልብ የሚነካና ማንኛውም ጎራ የገባው ሁሉ ዛሬ ያ መካረሩና ጥላቻውን በመተው ወደ በጎውና ወደ ቃሉ እየተመለሰ ይገኛል። ጥቂት አክርረው ላሉትም የሁላችንም ጸሎት መሆን ይገባዋልና በዚህ ዐቢይ ፆም ወቅት ፈጣሪያችንን እንድንማለደው ገጻችን ጥሪውን ያቀርባል።

Sent: Mon, Feb 7, 2011 4:14 pm
Subject: Fwd: [AfricanUnityDFW] Dallas cabbies' protest is wrong tactic

---------- Forwarded message ----------
From: Anne Marie Weiss-Armush <AnneMarieWeiss@dfwinternational.org>
Date: Sun, Feb 6, 2011 at 2:26 PM
Subject: [AfricanUnityDFW] Dallas cabbies' protest is wrong tactic
To: AfricanUnityDFW@yahoogroups.com



Steve Blow: Dallas Cabbies took a wrong turn with protest tactics

By Steve Blow
sblow@dallasnews.com

Published 05 February 2011 10:24 PM

I hate their tactics, but I sympathize with their plight.

Small cab companies and independent drivers say Dallas slashed their income with a policy favoring taxis powered by compressed natural gas.

The drivers say only the big taxi companies can afford to convert vehicles to CNG.

“We are starving,” said group spokesman Al-fatih A. Ameen.

But my sympathy was badly eroded last week with a couple of protest moves by the group, the Association of Taxi Operators.

Some of the ATO drivers formed a slow-rolling blockade on Monday that crawled along LBJ and North Central freeways, jamming traffic.

Sure, foul up people’s drive. That’s a great way to win friends in Dallas, Texas.

Then, later that day, protesting taxi drivers completely blocked the entrance to Dallas Love Field.

And that’s when any feeling of sympathy I had for the taxi drivers switched instead to the poor, frustrated travelers hurrying to the airport.

Some were reduced to bailing out of cars on Mockingbird Lane and hustling on foot toward the distant terminal, suitcases bouncing along behind them.

When I talked to ATO spokesman Ameen, he was unapologetic. “We will do what we have to do,” he said.

Without condoning their actions, I suppose I do understand the frustration that led to them.

Ameen said the group had tried peaceful protests and marches. “Even the news people don’t show up for that,” he said. “If you take it a step further and make it drastic, then it’s ‘breaking news’ and all that.”

Yeah, reporters and editors certainly did take notice when it was the public affected by the controversy, not just small-time taxi drivers and their families.

The real rub here is that public officials really don’t care if the small operators are forced out of business.

In fact, they would secretly be pleased.

The public rationale for encouraging CNG-fueled taxis is reducing air pollution. And it’s a legitimate one.

CNG taxis are rewarded by jumping to the head of the line picking up passengers at Love Field. That’s a huge perk for drivers, who sometimes wait hours for a single fare.

Dallas/Fort Worth International Airport adopted a similar policy for CNG taxis in 2009, but the independent drivers filed a lawsuit that is still holding up implementation.

But the back story to this controversy is that public officials have long said the Dallas area has too many taxis. Drivers can’t make a decent living, and the quality of cabs and service suffers.

D/FW Airport spokesman David Magana said 2,000 cabdrivers have permits to serve the airport. “We really only need about 700,” he said.

Dallas has authorized 2,022 cab licenses, had 1,804 drivers actually licensed at last count and needs well under that.

Mayor Tom Leppert said the CNG policy isn’t a backdoor approach to thinning the herd.

But he said the ATO drivers have resisted all previous efforts to improve taxi service ­ something important to locals and visitors alike.

“This group, for years and years, has been one that objected to additional consumer protections, increased insurance requirements and quality improvements,” Leppert said.

He sure didn’t sound like a guy troubled by the protests. “We just live with it and go on,” he said.

And that’s an attitude many more may have after the blockades.

The drivers were already way out on a limb. Last week they started shaking it


__._,_.___
Reply to sender | Reply to group | Reply via web post | Start a New Topic
Messages in this topic (1)
Recent Activity: New Members 21
Visit Your Group

1. Please send your new articles, commentaries, and other messages to:  AfricanUnityDFW@yahoogroups.com.

2. The messages posted on this board are moderated to protect you from SPAM.

3.  Before you send your cultural event to this list, PLEASE POST IT on our calendar at www.dfwinternational.org.  Events that have been posted on the calendar WILL BE APPROVED for distribution through this yahoogroups.

4. You can view the archive of all past messages at http://groups.yahoo.com/group/AfricanUnityDFW

5. Our website:  www.dfwinternational.org

6. Mission of the AfricanUnityDFW: The DFW International African Unity Network promotes and links African organizations and communities, providing forums through which they may explore their shared heritage and interests, strengthening educational and economic development, and empowering them to make the American dream a reality.
Switch to: Text-Only, Daily Digest • Unsubscribe • Terms of Use

ከዚህ በላይ ያለውን ጥሁፍ ከነምንጩ ያቀረብነው በሁለት ምክንያት ነው።
1. ወገኖቻችንን ጨምሮ የተሳተፉበት ቅሬታን ማሰማት ትግል ላይ ህብረታቸውን ለማጥፋት በውስጣቸው የተሰገሰጉት አንዳንድ ቅጥረኛ ግለሰቦችና አመራሩን የጨበጡትን ጨምሮ የሚፈጽሙት ሴራዎችን አደባባይ እየወጣ በገሀድ ታይቷል።
ካቢዎች ጥቅማቸው ሲነካ ብቻ ሳይሆን በተመቻቸውም ወቅት ለከተማቸውም ሆነ ለፕሮፌሽናቸው መሻሻል ተሳትፎ ይጠበቅባቸዋል። ከከተማው የካቢ አስተዳደር ጋር እጅና ጓንት በመሆን ተደራጅተው መስራት ብቻ ሳይሆን የራሳቸውንም ተወካይ በአማካሪነት ከአስተዳደሩ ጋር እንዲሰራ ማድረግ ግድ ነው። የCNG  አውቶሞቢል ጉዳይ አይቀሬ መሆኑንና እንዴት ሊተገበር እንደሚችል አሁንም አስተዳደሩ በሩን ያልዘጋ በመሆኑ የተሻለ ስምምነት ይመጣል ብለን እናምናለን።

ለምሳሌ በዲሲ ካቢዎች ላይ መቁጠሪያ ሜትር ሲገባ ገቢያችን ተጎዳ በማለት ከፍተኛ ተቃውሞ ከካቢዎች ተነስቶ ነበር። አስተዳደሩ ጥያቄ ያቀረባችሁትን እንቀበላለን፣ የናንተን ጉዳት አንሻም ነገር ግን ያለፈውን 2 አመት የሞላችሁትን የገቢ ግብር ሰነድ አቅርቡልንና አይተን ይስተካከል ሲላቸው አቅራቢ በመጥፋቱ ጉዳዩ ተዘጋ።


እንግዲህ የዳላስም ካቢዎች በቀደመውም ሆነ በዛሬው ጥሁፋችን የምንጋራቸውን ነጥቦች ማጤንና ከፊታችሁ የተጋረደውን እንደዚሁም በውስጣችሁ ያለውንም ማስተካከል ይቻላልና አንድነታችሁንና ቤታችሁን አስተካክሉ ነው የምንል።

2. ከዚህ በላይ የተጣፈውን ሆነ አፍሪካን ዩኒቲ ዲፍደብልዩ የሚለው ማነው? በሕብረተሰባችሁ ውስጥስ ምን እያደረገ ነው? እንደዚህ አይነቱን ጸረ ሕብረት በአፍሪካዊያን መካከል ከማጉላት ይልቅ ከጎናቸው በመሰለፍ ደካማ ጎናቸውን በመደገፍና ለተሻለ ነገ የማዘጋጀት ግዴታውን መወጣት አሊያም ስሙን መለወጥ ይገባዋል እንላለን።

በተለይም በኢትዮጵያን ተወላጆች ስም የተለያየ የግብረሰናይ ስም እየከፈቱና የተለያዩ የንግድ ተቋማትን የኮሚኒቲ አውት ሪች ቢሮዎችን እያጭበረበሩ የሚጠቀሙ ግለሰቦች ቁጥራቸው እየጨመረ መጥቷልለምሳሌ የምዕመናን ጉባኤ በሚል ከየቤተክርስትያኑ በሺህ የሚቆጠር ዶላር የሚወስዱ ሲነቃባቸው በቅዱስ ሚካኤል ደብር ውስጥ ትረስቲ ለማቋቋምና life time ሥልጣን ለመጨበጥ ብሎም እንደግል ሀብት ለመያዝ ያደረጉት ሙከራ በተዋህዶ ልጆች በመክሸፉ ዛሬ ፊታቸውን ያዞሩትና የጥፋት ነደፋቸውን በDFW ኢትዮጵያን መረዳጃ ማሕበር ውስጥ እየፈተሉ ይገኛል።

ሌላው ምሳሌ ደግሞ፡-


Sent: Fri, Feb 4, 2011 12:24 pm
Subject: POSTPONED UNTIL March 5 - African Leadership Luncheon


(Mailing list information, including unsubscription instructions, is located at the end of this message.)
    


The mission of the African Leadership Council is to promote        unity,         cultural awareness,                 networking, cooperation and         economic         empowerment initiatives        in the African diaspora.

    DFW Int'l's AFRICAN LEADERSHIP LUNCHEON
      sponsored by State Farm
      POSTPONED UNTIL Saturday, March 5, 2011- stay tuned for details
      12 noon till 2pm
       Ibex Ethiopian Restaurant, 12255 Greenville Ave (Greenville and LBJ), Dallas, TX 75243
       $15 ticket includes lunch -  purchased in advance HERE or by credit card at 972-661-2764
      $20 at the door or on the day of the event

     PROGRAM: Herbert Austin, Regional Director of SBA - how to qualify for new funding   authorized by Congress for small business loans , also                Dallas Economic Development Office - new visa opportunities for businessmen   who have funds to invest in Dallas
      State Farm - business opportunities with State Farm
       Pfizer - how to obtain free medicines for your low-income community members
       DFW Int'l announcements - new Guides, African Film Festival, etc

Click HERE to join the African Unity DFW Yahoogroup, which promotes and links African   organizations and communities, providing forums through which they may explore   their shared heritage and interests, strengthening educational and economic   development, and empowering them to make the American dream a reality.

  The Executive Committee of the African Leadership Council consists of
         Betru Gebregziabher (Ethiopia)
         Baba Kwasi (Diaspora)
         Ahmed Yanouri  (Morocco)
         Evelyne Djamat-Dubois (Cote d'Iviore)
         Lawrence Dagdu (Ghana)
         Kesete Yohannes (Eritrea)
         Abi Badiru (Nigeria )
         Patrick Obinabu (Nigeria)
         Tekeste Woldezghi (Eritrea)
         Eyassu Gebremedhin (Eritrea)
         Florence Campbell (Sierra Leone)
         Kakra A. Tham (Ghana)
         Patrick Jackson (Sierra Leone)
         Yilma Feleke (Ethiopia)
          Peter Mwaniki (Kenya)
          Shelly Lambe (Cameroon)
         Hurai Betts (Gambia)

Where is the Association for Mutual Assistance for Ethiopian at DFW? እንግዲህ Sponsor የሆነው ተቋም የሚያደርገው አስተዋጾ በአይነትና በመጠን ይለያይ እንጂ በድጋፍ ሰጪው አማካኝነት ወጪዎቹ ይሸፈናል። ነገር ግን  ከላይ የተጠቀሰው ግብረሰናይ ድርጅት ማነው? ምንስ ያህል አመታዊ ገቢ አለው? እንደስሙ ለአፍሪካውያኑ በየአመቱ የሰጠው ግልጋሎት ምንድን ነው? ለምንስ እዚህ ምግቤት ለማዘጋጀት ታቀደ? ይህን የመሳሰሉትን ጥያቄዎችን መዳሰሱ ለግንዛቤ ይረዳል እንላለን። በተጨማሪ የአሜሪካን ዜግነት ይዘው በህግ ኢትዮጵያን አሜሪካን መባል ሲገባቸው ራሳቸውን ለምን ኢትዮጵያዊ ብቻ ያደርጋሉ? Sponsor የተባለውስ ተቋም ምን ያህል ለዚህ ዝግጅት ለግሷል?

የተወደዳችሁ አንባቢዎቻችን፥ ከስንዴ መኃል እንክርዳድ አይጠፋምና ደግ ሰርቶ መከበርና መመስገን አኩሪና አርያነትም ጭምር ሲሆን፣ ያለአግባብ የግል ጥቅምን ለማግኘት ሲሉ extra mile በመጓዝ
በሕግ ወጥ መንገድ የሚደረገው ሩጫ
በማምጣቱ ፍጥጫ
ተጀመረ አይን ያወጣ ግልምጫ።
ባለፈው እንዳስነበብነው እነዚህ ግለሰቦች በቅዱስ ሚካኤል ያጡትን ትረስቲ ሥልጣን ወደ መረዳጃው ማህበር በማዞር ራሳቸውንና ቢጤዎቻቸውን በማዋቀር ትረስቲ ፈጥረው ብቅ ለማለት እየተሯሯጡ ይገኛሉ። እነዚሁ በግምባርም ሆነ በስውር ደብር ለመያዝና ትረስቲ ለመሆን ይደረጉት ሴራ በመክሸፉ ዛሬ በግምባርና በስውር ከሳሽና አስከሳሽ የሆኑ ግለሰቦች ናቸው። በግምባር ከሳሽ ከሆኑትም መኃል በቅርቡ አዲስ አበባ ላይ በትግሬ ነጻ አውጪ ለተጠራው የDiaspora ስብሰባ ላይ የሰጡትን አስተያየት ባለፈው ጥሁፋችን ማቅረባችን የሚታወስ ሲሆን አብረው አዲስ አበባ ተሳትፈው ከተመለሱት ውስጥም የአጽራረ ቤተክርስትያን ቡድን መሪ፣ የቀድሞው የደርግ  መኮንን ነኝ ባይ፣ የትግራይ ነጻ አውጪ ቅጥረኛና የኒያላ ኢንሹራንስ ወኪል፤ ሾላካና የሚፈጠር የፖለቲካን ድርጅት ሁሉ በማብከን የታወቀውን ያካትታል።

ከአዲስ አበባም አዲስ የተቀበሉትን መመሪያም ተግባራዊ ለማድረግ ሌት ተቀን እየተጉ ያሉት እነዚህ በጣት የሚቆጠሩ ቅጥረኞችን መመከት የሁላችሁንም ትብብር ያሻል። የቀራቸውን የመጨረሻ ዝግጅታቸው የመረዳጃ ማህበሩን በትረስቲ ማዋቀር ነው። የዚሁን የአዲስ አበባ ላይ ስብስብ ካነሳን አይቀር በመላው አለም ሊበተን የተዘጋጀው የትግሬ ነጻ አውጪ ቅጥረኛ ቡድን ለሰበካ ለመንቀሳቀስ ዝግጅቱን አጠናቋል። ቀደም ሲል ቅሌት ምሱ ያደረገው ተመሳሳይ ቡድን በቅርቡ በሰሜን ዳላስ የቀመሰው አይነት ውርደት እንዳይገጥመው አጋዚ ጦሩን ማስከተልም ስላልቻለ፤ የመቺ ቡድንም መግዛትም ሆነ መቅጠር ስላቃተው የፖሊስ መስሪያቤቱም ወጪ ቀላል ስላልሆነና፤ የስሞኑ የሰሜን አፍሪካም ሆነ የአረቡ አብዮት ያደናገጠው መንግሥት ስልቱ ሁላ ጠፍቶበታል። የአሜሪካን መንግሥትም በአንባ ገነን መሪዎች ላይ እየወሰደ ያለው አቋም ጨምሮ በዳላስ ፖሊስ ላይ ያላቸው አመኔታም አናሳ በመሆ ለApril 3rd, 2011 የታቀደው ስብስባን አስመልክቶ ከምንጮቻችን የደረሰንን ፤ የዳላስም ሆነ የአዲስ አበባው የተልዕኮ ቡድን ማደራጃና መምሪያው ሊያስተባብልም ሆነ ሊያረጋግጥ አልፈቀደም። በኛ ሀሳብ ግን በዚያው ስሞን ሳይደረግ አይቀርም የሚል ግምት ስላለን ጉዳዩ የሚመለከታቸው የተሻለ መረጃም ሆነ ዝግጅት ከዚሁ ለማለት ያህል በዚህ እንቋጨዋለን።

December 31/2010 የሥራ ጊዜውን የጨረሰውና ከውስጡም 7 አባላቶቹ የአገልግሎት ዘመናቸውን የጨረሱ እንደ ግብጹ ሙባረክ ሙጥኝ ለማለት ምን አስፈለጋቸው? የሚለውና እኛንም ጨምሮ ሌሎችም ድህረ ገጾች ከሚደርሳቸው የሕብረተሰቡ ጥያቄ መሰረት እምቢኝ ቢሉም የማታ ማታ አይቀሬ ሆኖ የሚቀጥለውን ስብሰባ ዘግይተው ጠርተዋል።

On Feb 27th 2011 at 3:00 PM Ethiopian Community will hold a general meeting to elect MAAEC Board of Trustee members, to elect election committee members for the upcoming election of MAAEC Board members, to amend the MAAEC By-Law, and to approve the Ethiopian Community Cultural Center resolution approved by MAAEC. We encourage all community members to come to the meeting and voice your opinion. In addition , the election of MAAEC Board members will be March 27th at 3:00 PM.  The location of  the meeting place is Double Tree Hotel  at
1981 North Central Expressway

Richardson, TX 75080.

Thanks
MAAEC Board

--
MAAEC IN DFW
11420 E.Northwest HWY Suite #93
Dallas,TX 75218
214-321-9992
 በዚህ የተጠራው ስብሰባ ላይ እንዳቀረቡት አጀንዳ
1.ትረስቲ መምረጥ (ቅድሚያ አጀንዳ)
2.ቦርድ አስመራጮችን መምረጥ
3. ሕግ ማሻሻልና
4.የባሕል ማዕከል በተመለከተ ያወጣውን ውሳኔ ማፅደቅ የሚሉትን ያቀፈ ነው።

ምን ያህል ሀብትና ንብረት ያለው ብሎም የፈጸማቸውን ተግባራት ምን ያህል ታላቅና አኩሪ ምዕራፍ ለሕብረተሰቡ ቢያስጨብጥ ነው ትረስቲ የሚባል የዕድሜ ልክ ሥልጣን ለግለሰቦች ያስፈለገው? እነርሱስ እነማን ናቸው? የትስ ቦታ ነው ሕብረትሰቡ ተሰብስቦ በዚህ ጉዳይ መክሮ የወሰነው? ለምንስ የአገልግሎት ዘመን በጨረሱት አመራሮች ተዘጋጅቶ በግዴታ እንዲያልፍ ጫናው ለምን ዛሬ ሆነ? ሌላም ጥያቄ ያስከተለ አጸያፊና አስነዋሪ ተግባር ለምን ይሰራል? ለተተኪው ትውልድ ተረክቦ በትውልድ ሀረጉ አምኖና ኮርቶ ወደ ቀና አመለካከት እንዳይመለከት፣ የተሻለም አስተዋጾ ለህብረተስቡም እንዳያበረክት ማነቆ ለምን አስፈለገ? በቅርቡ ወጣቶች ተደራጅተው ለሕብረተሰቡ አገልግሎት እንዳያበረክቱ እንቅፋት የሆኑባቸውና በኛ ሥር ካልሆናችሁ በማለት ያስወገዷቸውን የጥቂት ወራት ትዝታዎቻችንን እንዴት እንዘነጋዋለን? የቅዱስ ሚካኤል ደብር ለነዚሁ ወጣቶች ለሚሰጡት tutorial service ቦታ በመፍቀዱና በመደገፉ ለምን የሀሰት አሉባልታን በወጣቱ ላይ የሚያሰራጩትን ለትረስቲ አዘጋጁ? ወዘተ……


2ኛው አጀንዳ የሕዝቡ ጥያቄ ስለሆነና ባለፈው አመት ማገባጃ ላይ መሰራት የነበረበት አሁንም የሕዝቡ ጫና ያለበት ስለሆነ በተንኮል ምንም ቢያዘገዩት፤ ዘመናቸው በላይ አንድ ቀንም መቆየት የማይገባቸው ሕገወጥና አምባ ገነን ሥራ ላይ ያሉትን 7 የቦርድ አባላትን የሚተካ የአስመራጭ ኮሚቴ ብቻ በዚያኑ የስብሰባ ዕለት መዋቀር ይገባዋል። ለዚህ ሥራም የሚመረጡት ንጹህ የኢትዮጵያ ተወላጆችና ከማንኛውም የፕለቲካና መሰል ተግባራት የታቀቡ መሆን ይገባቸዋል። እንዚህንም ብቁ ግለሰቦች እንዲመርጡ ሁሉም የዳላስና አካባቢው ነዋሪ የሆነና ጉዳዩ ይመለከተኛል የሚል በነቂስ ወጥቶ መሳተፍ የሚገባው መሆኑን እያስገነዘብን ጥሪያችንን እናቀርባለን?


3ኛው አጀንዳ ሕግን ማሻሻል የሚለውን ብንቀበለውም ወደፊት የሚመረጠው ቦርድ ሥራ ይሆናል። በቁጥር 1 አጀንዳ የቀረበውም መጀመርያ ሕጉ ተሻሽሎ ቀርቦ ሲጸድቅ የሚደረግ እንጂ መሰረታዊ ነጥብን ሳያሟላ ትረስቲ የሚባለው በምንና በየትኛው መተዳደሪያ ደንብ ለሚለው መልስ አልባ የህልም ሩጫና ቅዥት ይሆናል። ስለዚህ በሀሳብ ደረጃ ለሚቀጥለው ቦርድ እንዲያጠናው ማለፍ ያለበት ነው።

4ኛውና የመጨረሻው አጀንዳ ስለ ባሕል ማዕከል የወሰኑትን ለማጸደቅ ያቀርቡት ቢሆንም፤ ይህንን ጉዳይ በተመለከተ ቀደም ሲል የተቋቋመ ኮሚቴ ነበር። እርሱን በግልጽ ሳይፈርስ ወይንም በምትኩ ሌላ ሳይመረጥ በአንባ ገነንነት የተመሰረተው አዲሱ ኮሚቴ ስላለ የማንኛውን የሥራ ውጤትና የሀሳብ ውሳኔን ለማጸደቅ ይሆን? አዲሱ ኮሚቴስ ምን ከወነ? ቃል የተገባለትንስ እርዳታ አሰባስቦ ጨረሰ ወይንስ የወረቀት ላይ ብቻ ኮሚቴ ነው? ሕብረተሰቡስ ምን አይነት አመኔታን ጥሎበታል? እንግዲህ እንደ ሀሰት የግብረሰናይ ድርጅት አቋቁመው እንደሚያጭበረብሩት ግለሰቦችና ዛሬ ራሳቸውን እንደ ትረስቲ ለማድረግ እንደሚቃዡት ህልመኞችና ቅጥረኞች ሆነው ነውን? ወዘተረፈ….. በማለት ለአንባቢዎቻችን መልሱንና ዕውነታውን እንዲሹ እንተወዋለን።

መቼም ቁልቋሉ ይሁን ወይስ አጋሙ ወደ ሌላው ተጠግቶ እየደማ ወደ 30 አመት የተጠጋው የመረዳጃ ማህበር መቼ ነው ደሙ ቆሞ የሚታደገው የሚወጣለት? ይሉኝታ በሚል መጥፎ ጸባይ ተጀቡዶ፣ ሌላው የእርሱን ሥራ እንዲሰራለት የሚሻ፣ ለራሱ መብት መቆም የተሳነው፣ መስሎ ማደረና ወደ ነፈሰበት መዝመም ሥራና ፈሊጥ አድርጎ የያዘው፣ ለግል ጥቅሙ ብቻ የቆመው ደካማ፣ ወዘተ….. የሆነው ሁሉ እራሱን መመርመር ያለበት አሁን ነው። ሕብረተሰባችን በዚህ ሀገር ከሰፈረ ረጅም አመታትን እያስቆጠረ ቢሆንም አብሮ ለመስራትና ለማደግ ያልቻለበት ዋነኛው ምክንያት የዕምነት ማጣትና ጥርጣሬ፣ በሕግ አለመደራጀት፣ አስፈላጊውን ጥናትና የባለሙያዎችን እርዳታን አለመጠቀም፣ የጠባብነት አመለካከት የመሳሰሉት አበይት ምክንያቶች ናቸው። በእድር ስም በአመት ከ20ሺህ ዶላር በላይ የሚያስገባው መረዳጃ ማህበር ለምን አውሎት ይሆን? ብዙዎቹ ወደ እድር የገቡት ሕብረተሰባቸውን ለመርዳት እንጂ ያላቸው ሀብት ወይንም የመድህን ዋስትና በጣሙን የተሻለ ነው። ነገር ግን አብረዋቸው የኖሩት ሲለዩ በነሱ ምስል ልመናው እንዲያቆም ብለው እንጂ፤ ከዚያም አልፎ 40ው ዶላር ተሰባስቦ ለችግረኛ ወገኖቻችን ይውላል በማለት ነበር።


ነገር ግን በቅርቡ በተዋህዶ ልጆች የጸዳው የቅዱስ ሚካኤል ደብር አይነት ሀቀኛ የኢትዮጵያ ተወላጆች ሁሉ አንድ ላይ በመተባበር መረዳጃ ማህበራችሁን አሳልፋችሁ አትስጡ! አሁን ተይዞ የሚገኘው በከሀዲና ቅጥረኞች እጅ ስለሆነ እስከመጨረሻው እንዳታጡት ያላችሁ ጊዜ ዛሬ ነውና ታጥቃችሁ በመነሳት ወደራሳችሁ እጅ መልሱት በማለት የመጨረሻ ጥሪያችንን እናቀርባለን!

እርሶስ ምን ይላሉ?  

Tuesday, February 1, 2011

WHAT IS GOING ON?

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!

ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።


WHAT IS GOING ON?

የተወደዳችሁ የገጻችን አንባቢዎች እንደምን ከርማችኃል? ደግሞና ደጋግሞ በቸርነቱ ጠብቆና በሰላም ለዚህ ያቆየን ልዑል እግዚሀብሔር ክብር ምስጋና ለእርሱ ይሁን። አሜን። ዛሬ ቸርነቱ ለናንተ በተለይም ለዳላሶች ብቸኛና ታላቁ ደብራችሁ የደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ከአጽራረ ቤተክርስትያን ሴራ እጅ አውጥቶ በመላእኩ ተራዳኢነት በተዋህዶ ልጆች አመራሩ እንዲቆይ ፈቃዱን በመድገሙ አሁንም ክብር ምሥጋና ለእርሱ ይሁን። አሜን።

ደግመንና ደጋግመን የትግሬ ነጻ አውጪ ድርጅት በቅጥረኞቹ አማካኝነት ከሀገር ውጪ በሚገኙ ተወላጆች የሥልጣን ስጋት ይመጣብኛል በሚልና የሕዝብንና የሀገር አመራርን በሚገባ ከመተግበር ይልቅ ማሳደድ፣ ማፈንና አንድነትን ማወክን ዛሬ በሚገባ ሁሉም እየተረዳው መጥቷል። ለዚሁም በዋቢ ለመጥቀስ ካስፈለገ፤ ትላንት ከተቋሚው ጎራ ሰላማዊ ሰልፍ እስከ ክሮፎርድ ቴክሳስ ቡሽ ራንች ተቀላቅለው የተሰለፉ፣ ከቅዱስ ሚካኤል ደብር ላደግንበት ቀዬ ቤተክርስትያን እርዳታ ብለው ወስደው ለአባ ጳውሎስ እጅ መንሻና ለግል ጥቅማ ጥቅም መደለያ ከመንግሥት ያገኙና የወገኑ፣ ትላንት የደርግ ባለሟል በመሆን በወገኖቻችን ላይ ግፍ የፈጸሙ፣  ከቅዱስ ሚካኤል ለወሰዱት ገንዘብ ማወራርድ ሲያቅታቸው የዋለላቸውን ደብር በፍርድ ቤት የከሰሱ አጽራረ ቤተክርስትያንን ማንነት የሚገልጽ በተለይም በአሁኑ ሰአት በአጣብቂኝ ውስጥ ያለውና እንደ ሌሎቹ አምባ ገነን መሪዎች መታናፈሻ ለጨነቀው መንግሥት ምክር ሰጪ ሆነው የሚቀላምዱና ነባራዊ ሀቅ ያልተዋጠላቸውን ቅጥረኞች ዳላስ ላይ የሚዘጋጅና ኢትዮዳላስ በተባለ ብሎግ ላይ ማንነታቸውን በግልጽና በመርጃ አስደግፎ ስላቀረበው ምስጋናችን ከዚሁ ይድረሳቸው እያልን እኛም የሚቀጥለውን Link ለናንተም አቅርበነዋል።
http://www.waltainfo.com/index.php?option=com_content&task=view&id=25158&Itemid=52

  ከዚሁ አለፍ ስንል ደግሞ በዳላስ በታክሲ አሽከርካሪነት የሚተዳደሩት ወገኖቻችን በጀመሩት የስራ ማቆም ገጻችን ቢደግፋቸውም ገና ብዙ የሚቀራቸው ሥርዐት አለ። ከነዚሁ መካከል የተደራጀና የተቀናጀ አቀራረብ ዋናው ችግራቸው ሆኖ ሲታይ በውስጣቸው ያለውን ችግርም መፍታትና ለመሪነትም ሆነ ለተመሪነት የሚያስፈልገውን ልምድ ያካበቱና ብቃት ያላቸው መሆን ይገባል። በቅርቡ እየረዷቸው ያሉት የወ/ሮ የሐረርወርቅን ሥራ ለማወክ የተነሱ በሁለት ቢላ የሚበሉትን መለየቱ ጠቃሚ ነው እንላለን።

እንደ ሙባረክ አምባገነን ሆኖና ተርሙን የጨረሰው በትግሬ ነጻአውጪ ተቀጣሪ የሆነው የዲኤፍ ደብልዩ የኢትዮጵያ መረዳጃ ማህበር 7 አባላት በጉልበት የሚቀመጡት ለምንድን ነው? WHAT IS GOING ON? ለሚለው ጥያቄ መልሳቸው መቼ ይሆን የሚደርሰን? ከመተዳደሪያው ሕግ ውጪ እየተደረገ ያለው የአመራሩ እንቅስቃሴ በሚገባ እየዘገብን የያዝነው ስለሆነ ፤ ይህ ድርጊት ባስቸኳይ ካልተገታ በጉዳዩ Secretary of State of Texas and the IRS በጉዳዩ ጣልቃ እንዲገቡበትና አስፈላጊውን እርምጃ በሕገወጦቹ ላይ እንዲወስዱ ከማድረግ ወደኃላ እንደማንል እሙን ነው። በተለይም እድሩን አስመልክቶ በሬዲዮኑ እየተደሰኮረ ያለው ሀሰትና እውነት መውጫው እሩቅ አይደለም።

ለማጠቃለያ በዳላስ ለምትገኙ የተዋህዶ ልጆች በሙሉ አጽራረ ቤተክርስትያን በደብራችሁ ላይ ለተመሰረተው የሀሰት ክስ እልባት የሚያገኝበት የፍርድ ቤት ቀጠሮው በ2/07/11 እንደዚሁም በ2/10/11 ስለሚታይ በዚሁ እለት በመገኘት ድጋፍችሁን ለደብራችሁ እንድትሰጡ በዚህ አጋጣሚ ጥሪ እያቀረብን፣ የቅዱስ ሚካኤል ተራዳይነት አይለያችሁ! አዲስ ለተመረጡትም አመራር ጥበብና ዕውቀትን ይስጥልን! አጽራረ ቤተክርስትያንን ያስታግስልን! ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ደብርን ይጠብቅልንን! የተዋህዶ ልጆችን አንድነትና ጥንካሬን ይጠብቅልን! አሜን።

እርሶስ ምን ይላሉ?