Tuesday, February 22, 2011

እራሳቸው ያቀጣጠሉት እሳት እራሳቸውን እየፈጃቸው......

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!

ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።


እራሳቸው ያቀጣጠሉት እሳት እራሳቸውን እየፈጃቸው ያሉትን አምባገነን መሪዎችን እያየን ከእነርሱ ትምህርት የሚወስዱ ይኖሩ ይሆን? 

እንደምን ከረማችሁ? ፈቃዱ ሆኖ በዚህ ጦመር ዳግም እንድንገናኝ ላደርገው ለልዑል እግዚሀብሔር ክብርና ምስጋና ይሁን። አሜን። ከላይ ያስቀመጥነውና ለዛሬው መነሻ ጥሁፋችን ያደረግነው በአለም ዙሪያ ለሚካሄደው ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ያለንን ትንተና ለመስጠት ሳይሆን፤ በጥቂት አምባገነኖች የሚደረገውን የሌላውን መብት ጥሰት አንዱ የሆነው ፣ ድንበር ተሻግሮ የሚደረገው ሕገወጥ ሴራ ነው። ይኸውም ገና ለገና ከሀገር ውጪ የሚገኙ ተወላጆች ጥላቻን ብሎም ሥልጣኔን ያሳጡኝ ይሆን በሚል በቅጥረኞች ወይንም በደጋፈዎቻቸው የሚደረገው ሁከት አንዱ ነው።

ለምሳሌ ከትውልድ ሀገራቸው እርቀው የሚገኙ የኢትዮጵያ ተወላጆች በትውልድ ሀገራቸው ውስጥ ያለውን የሶሻል ኢኮኖሚና የአስተዳደር መብትና ነጻነት በተመለከተ አዲስ ከሰፈሩበት ወይንም ለአዲስ አመለካከት በመጋለጣቸው ምክንያት አሊያም ባገኙት ነጻነት የተለያየ አመለካከት በመያዝ እራሳቸውን መግለጽ የተለመደ ነው። አንዳንዶች በመደራጀት የተቃውሞ ፖለቲካ እንቅስቃሴ እንደሚያደርጉ እሙን ነው። እነዚህን ተቅዋሚ ድርጅቶችን ለማብከን ሲባል የማይደረግ ጥረት የለም። ለዚህም ሲባል ከፖለቲካ ድርጅቶች ባሻገር ያነጣጠረው በሀይማኖትና በስቪክ ድርጅቶች ላይ ነው። ለዚህም በናንተ የዳላስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ደብር ለረዥም ጊዜ ባካበተው መንፈሳዊ ግልጋሎትና ባቀፈው የምዕመናን ቁጥር ብዛት የመጀመሪያው ሰለባቸው ለማድረግ ቅጥረኛዎቻቸውንና አድርባይ ደጋፊዎቻቸውን አስርገው ለማስገባትና ለመቆጣጠር ያደረጉት ጥረት በሀቀኛ የኦርቶዶክስ ልጆች ሲቀለበስባቸውና የፖለቲካ አሻጥራቸው ሲጋለጥ፤ መንፈሳዊና የሀይማኖቱን መስፈርት የማያሟላ፣ ደንቡንና ሕጉንም ጥሶ ፤ አንድዬና ብርቅዬ የሆነውን ደብራችሁንና የመረጣችኃቸውን ሀቀኛ የቤተክርስትያኗን ልጆች ጨምሮ በመክሰስና ባማስከሰስ ማንኛውንም መንፈሳዊና የሲቪክ ማህበራትን መቆጣጠር ካልሆነ ማዳከም ብሎም ማጥፋትን ስራዬ ብለው ከጀመሩ መክረማቸው ለሁላችንም የታወቀ ነው። ለማስረጃ ያህል ከዚህ ቀጥሎ በገጻቸው የለጠፉትን እንዳለ ግልባጩን ለናንተ አውጥተነዋል።

United St. Micheal Church Peace Resolution Seekers Committee 3rd General Meeting 1--23-2011, Report from PR
የተባበሩት የቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የሰላም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ                 UNITED ST. MICHAEL CHURCH PEACE RESOLUTION SEEKERS COMMITTEE
       Meleket4u@gmail.com

1-23-2011
                                          ጠቅላላ የምዕመናን ስብሰባ

የዛሬውን አጠቃላይ ስብሰባ በ15:15 ፒ ኤም ም/ሊቀመንበሩ አቶ ግርማቸው አድማሴ ስብሰባውን በቄስስ መስፍን ደምሴ ቡራኬ በመስጠት በአንድነት በፀሎት ከፍቱልን። በ 5 ፒ ኤም ስብሰባው ተዘግቷል።

ከተሰጡትም ገንቢ አስተያየቶችና መልዕክቶች መካከል፤
ሀ. የኮሚቴው ዋና ሥራ የሆነው የሕግ አገልግሎት ጉዳይን በተመለከት መሰረታዊ ጥያቄዎችና ዓላማዎች ግልፅና አጭር በሆነ መልክ ለምዕመናን መግለጫ እንዲሰጥ።
ለ. የመልአከ ሣህልን በሥራ ጉዳይ ምክንያት ወደ ሌላ ግዛት መሄዳቸውን አስመልክቶ በ 1-28-2011 በሚደረገው የሽኝት ዝግጅት ላይ ከዓርብ ጉባኤ ጋር በመቀናጀት አሰኛኘት እንዲደረግላቸው።
ሐ. በቅርቡ በሚካሄዱት የፍርድ ቤት ቀጠሮዎች 2-7-2011፣ በ3 ፒ ኤም እና 2-10-2011፣ በ9 ኤ ኤም ላይ መገኘት የሚችሉ ምዕመናን አንዲገኙ።
መ. “ቤተክርስቲያን ተከሷል” የሚባለው የተዛባ ውዥንብር የሚወገድበት ትክክለኛው የፍትሕ ጥረት ለምዕመናኑ በመግለፅ የሚረዱበት መንገድ እንዲፈጠር።
ሠ. በዓርብ ጉባኤ እየተዘጋጀ ባለው ሦስተኛ ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ ኮሚቴው ትብብሩን እንዲያደርግና መድረኩንም በመጠቀም ለሕዝቡ መልእክት እንዲያዘጋጅ።
ረ. የሕግ ጉዳዩን በተመለከተ ለሚያስፈልጉት የኃሳብና የገንዘብ ዕርዳታ ቅንጅትና ትብብር በመላ ምዕመናኑ የሚካሄድበትን።

ሕዝብ ግንኙነት ክፍል

Posted by .......***መለከት***MELEKET*** at 2:29 PM 0 comments


ከዚህ በላይ እንደተቀመጠው እነዚህ አጽራረ ቤተክርስትያን የመንፈሳዊ ጉዳዮችና ችግሮችም ቢኖሩ በመንፈሳዊ መንገድ እንጂ በአለም ፍርድ ቤት አይበየንም።
2. በዲፕሎማት ፓስፖርት መጥተው ያለምንም ውድድር ያስቀጥሯቸው ቄስ ፣ በተሰጣቸው መመሪያ መሰረት ምዕመናኑ ለመለያየትና የቤተክርስትያኑን አንድነት በማናጋት ችግር የፈጠሩትን ለመመለስ ያደረጉት በመክሸፉ፤
3. በፍርድ ቤት ክስ ውስጥ የሚጫውቱት ሚና፤
4. አመራሩን ለይቶ መክሰስ ቤተክርስትያኑን መክሰስ ማለት መሆኑን ፣ ተመራጮቹ የቤተክርስትያኑ ሥራ ሲሰሩ እንጂ በግል ሕይወታቸው እስካልሆነ ድረስ ቤተክርስትያኑ በሕግ መከላከያ ወጪያቸውን እየከፈለ ባለበት ሁኔታ፤ ቤተክርስትያን አልከሰስንም ብሎ ሸፍጥ እንጂ እንደነሱ ውዥንብር አለመሆኑ ለሁላችንም ግልጽ ስለሆነ ምናልባት ውዥንብር ውስጥ የተደፈቁት እነሱው ለመሆናቸው፤ 
5. በመንፈሳዊ ስብሰባ ስም ጸረ ኃይማኖትና አጽራረ ቤተክርስትያን ሴራ የሚያራምዱና ንጹኃኑን ወደ ኃጢያት የሚመሩ፤ 
6.እንደዚሁ ንጹኃን የሆኑትን ምዕመና በማጥመድ የገንዝብ ዕርዳታ እንዲሰጣቸው የሚከጅሉ፤ 


እንግዲህ ከዚህ በላይ ያለውን የሚያካሂዱና የሚያራምዱ እነማናቸው? አሁንስ ምን እያደረጉ ናቸው? ለሚለው ጥያቄ ከዚህ ቀደም ሲል በሰፊው የዘገብን ሲሆን አሁንም እንዚሁ ግለስቦች ናቸው የዳላስና ፎርትዎርዝ የኢትዮጵያ መረዳጃ ማህበርን አንቀው ለመያዝና በዚያ አማካኝነት ሕብረተሰቡ ተደራጅቶና ተረዳድቶ የተሻለ ደረጃ ላይ እንዳይደርስ እክል መሆን ዋነኛ ተልዕኮአቸው ያደረጉት። ስለዚህ እናንተ የዳላስና አካባቢው ነዋሪ የኢትዮጵያ ተወላጆች የሆናችሁ ይህንን ሴራ ከወዲሁ ተገንዝባችሁ በአንድነት በመቆም በ02/27/2011 በተጠራው የመረዳጃ ማህበር ጠቅላላ ስብሰባ ላይ በመገኘት፣ የነርሱን አጃንዳ ወደ ጎን በመተው፣ ጊዜውን የጨረሰውን ቦርድ የሚተካ አዲስ አስመራጭ ኮሚቴ ብቻ መስርታችሁ እንድትደመድሙ ጥሪያችን ነው። ይህ ካልተገበረና ሕብረተሰቡ ከተከፈለ አዲስ የመረዳጃ ማህበር መመስረቱ አይቀሬ ነው። ሕብረተሰቡ እንዳይጠናከርና እድገቱን እንዳያስመዘግብ ለረዥም ጊዜ ስውር ደባ ፈጣሪና ከጀርባ ተዋናይ የሆኑት፤ ዛሬ የትግራይ ነጻ አውጪ አሽቋላጮች ከተደበቁበትና በወገኖቻችን ስም ከሚጠቀሙበት የግብረሰናይ ድርጅት ማለትም እንደ ካቶሊክ ቻሪቲና እንደ ዳላስ ሲቲና ካውንቲ መንግስት ውስጥ እንደሚወጡ የታወቀ ነው። ለዚህም ሲሉ ነው በመረዳጃው ማህበር ውስጥ ትረስቲ በማዋቀር እራሳቸውን ወይንም ቢጤዎቻቸውን እያደላደሉ የሚገኙት። እኛም እስከዛሬ ምንም ከናንተ ያገኘነው ስለሌ አሁንም የረባ የሌላችሁና ሕብረተሰባችን ላይ የምትሰሩት በደል ይቁም የምንል።

እርሶስ ምን ይላሉ?

No comments: