Sunday, March 20, 2011

የዳላሱ አስመራጭና መራጭ መብትና ሥልጣን

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና! 

ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።


አቤቱ የሠራዊት አምላክ ሁሉን የፈጠርክ አንተ ነህና ልዑል እግዚሀብሔር ሆይ ድክመታችንን አትቁጠርብን፣ በደላችንንም ሁሉ አስተስርይልን፣ የጀመርነውን ጾምና ጸሎት ተቀበልልን፣ ለትንሣኤ በዐል በሰላም እንድንደርስ ፈቃድህ ይሁንልን። በዚህ ወቅት ምንም አይነት ጥሁፍ ለማድረግ ፈጽሞ አልፈቀድንም ነገር ግን ሁኔታዎች አስገዳጅ ሆነው በመገኘታቸው በዳላስ ለሚገኙ ወጎኖቻችን የማካፈል ግዴታ ስላለብን በሚል ስለሆነ ብቻ ከቅንነትና በእውነተኛ መቆርቆር ተደርጎ ከዚህ በታች ያለውን እንዲነበብልንና ግንዛቤን እንዲጨበጥልን እንጄ፤ በዚህ ጥሁፍ በጦምና በጸሎት ለምትገኙ ወጎኖቻችን እንቅፋት እንዳንሆን የጀመርነውን ጥሑፍ እርሱ ፈጣሪ ይምራን! አሜን።

የዳላሱ ቅዱስ ሚካኤል እጅጉን በሚደነቅ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝና ብዙውን ምዕመን እየተባረከበት እንደሚገኝ ከሚደርሱን ዘገባዎች በጣም ደስ እያለን ለዚህ ፈቃዱ ላደረገው ለልዑል ግዚሀብሔር አሁንም ክብር ምስጋና ይሁን። ወጣቱ ዲያቆን እያደረገ ላለው ሥራዎች እያደነቅን አባቶችም በተለያየው ስጦታዎቻቸው ምዕመኑን ማገልገል ብቻ ሳይሆን እየባረኩት ይገኛል። ያርፋጅ ቁጥጥር ባይኖርም ምዕመኑ በተቻለው ሁሉ ቀደም በማለት ከበረከቱ እንዳይጎልበት ለመጠቆም ያዳዳናል።

ዋንኛው የዛሬው መልዕክታችን ያነጣጠረው በዳላስና ፎርትዎርዝ የኢትዮጵያን መረዳጃ ማሕበርን አስመልክቶ በዛሬው የማሕበሩ የራዲዮን ስርጭት ላይ በእንግድነት የቀረበው የዚሁ መረዳጃ ማሕበር ሊቀ መንበር ሆኖ ሲሰራ የቆየውና የአገልግሎት ጊዜውን በDecember 31, 2010 የጨረሰውና 7 አባላቱ ለሚተካቸው አዲስ አባላት በ01/01/2011 ማስረከብ የሚገባቸው ፣ አንባገነን የማን አለብኝና በገሀድ የሕዝብን ድምጽና ውሳኔ አልቀበለም በማለት ሥልጣንም ሆነ ኃላፊነት በመተዳደሪያው ደንብ ሳይኖረው፤ የሕብረተሰቡን መብትና ሥልጣን በፍጹም በተቃረነና በሕግም አግባብነት በሌለው መልኩ፤ ሕዝቡ ተሰብስቦና መክሮ የወሰነበትን የአስመራጭ አባላትን መብትና ሥልጣን በመጋፋት ለ03/27/2011 የተመደበውን የአስመራጭ አባላት የሥራ ውጤት ለማደናቀፍ እንቅስቃሴ መጀመሩን በራዲዮኑ መግለጫ ሰጥቷል። በተቃጠለ የሥራ ፈቃድ እርሱና ግብረአበሮቹ ለምን ከሕዝብ ድምጥ በላይ ለመንቀሳቀስ አስፈለጋቸው? ምንስ የፈሩት ነገር አለ? ባለፈው አጥቃላይ ስብሰባ ለምን ያቀረቡት አጀንዳ ወደቀባቸው? የግል ጥቅማቸው ተነካባቸውን? ለምን ከአስመራጭ አባላት ጋር ያልተፈጠረውን ሀሰት በራዲዮ መግላጫ ለመስጠት አበቃው? ከእርሱ በኃላ ለምን ያስመራጭ አባላት በሬዲዮ ምንም የቀን ለውጥ እንዳልተደርገና ሥራቸውን ለማቅረብ  በ03/27/2011 ዝግጁ ነን ብለው በተወካያቸው በዚሁ የራዲዮ ሰአት ውስጥ ገለጹ? ወዘተ……. ብለን ጥያቄዎችን ለማስተናገድ የጉዳዩ ባለቤት ለሆናችሁት እየተውን፤ ከራዲዮ ክፍል ዝግጅት አስተናጋጆች የተሰጠውን ወገናዊና ጨለማዊ አቋም ሕብረተሰቡን ብቻ ሳይሆን ሁላችንም አሳዝኖናል። ሽማግሌ ብሎ አስተያየትስ ለምን አስፈለገ ወይንስ እንደርሱ ጸጉርን እየቀቡና በሕብረተሰቡ መኃል ገብቶ መርዘኛ መሆንን ነውን? አሊያም የትግሬ ነጻ አውጪ ቅጥረኝነቱን በገሀድ ገልጦም ላመኑበት ራዲዮኑን መጠቀም በግልጥ ማን ከልክሎት ነው? ሁሉም ቅጥረኛ ብቻ አይደለም እንዴ በግል ጥቅም የታወረ? ለምን ብዙ ታናግሩን፣ ወጣቱ በመረዳጃው ማሕበር ሥር እንዳይደራጅ ያደረገው አንዱና ዋናው ምክንያት ለተተኪው ቦታ አለመልቀቅ አንዱ ችግር ለመሆኑ ከዚህ በላይ የተጠቀሰው የተመረጠበት ዘመኑ አልቆና ተቃጥሎ ላለመልቀቅ የባጡን የሚቀባጥረውና በእነቶኔ የሚመራው እንደ ሙባረክ በአመጽ ካልወረድኩኝ የሚልና እርሱን የሚያሽሞነሙነው የራዲዮ ዝግጅት አቅራቢ አብሮ መክሰም የግድ ነው። 

ራዲዮውን ከነካን አይቀር ሊቢያ ካሉት የኢትዮጵያ ተወላጆች ጋር አወራን ብለው የዘገቡት ሀሰት ነው። ኢትዮጵያዊ ብቻ ሳይሆን ጥቁር ቀለም ያላቸው ሊቢያኖች ብዙ ናቸው። ወደ ሊቢያ የስልክ መስመር አግኝቼ አናገርኩኝ የተባለው ፍጡም ሀሰትና የሌለ ወሬ ነው። እንኳን ግለሰብ አይደለም ድርጅቶችና ኤምባሲዎች የመገናኛ እክል አለባቸው። ቀይ መስቀልም አለው። ከውጪ ይዘው የገቡ የውጪ ዜና ማሰራጫዎችና የተወሰኑ ሀገሮች ብቻ ናቸው። ውሸት ይቁም። በነርሱ ስም ገንዘብ አሰባስቦ መብላት፤ በሌላው ሰቆቃ መኖር ልምድ ያካበቱ መቼ ይሆን የሚታቀቡ? ሰሞኑን ከሰማነው አሳዛኝ ዜና የአንድ ወጣት አሟሟት ልባችን ቢነካም በዚሁ ዙርያ ለቀብሩ የሚያስፈልገው ዝግጅት ከተጠናቀቀ በኃላ ፤ በሟች ቤተሰብ ስም ገንዘብ እንዲሰባሰብ የተጫወቱት ግለስቦች ጥያቄው ጥያቄ ሆኗል። ስንቶቻችን የሚከራዩ ቪላዎች በሀገርቤት ይኖሩን? ጥሩ ጡረታ ያለን? ስንቶቻችን ነን ውድ የስፖርት መኪናዎችና አፓርትመንት ኮሌጅ ላሉ ልጆቻችን የምናደርግ? በአካባቢያችን ስንት ችግረኛ ወገኖች ከነልጆቻቸው ባዶ የምግብ ማቀዝቀዣ ያላቸው ወይንም የመብራት መክፈል ያቃታቸው? አሊያም የቤት ኪራይ መክፈል አቅቷቸው በመኪናቸው ውስጥ የሚያድሩ ወይንም መጠለያ የገቡ? እንዲያው በደፈና ቤት ይቁጠርው? ብለን እናልፈው ይሆን። ስለዚህ የራዲዮ ዝግጅት ግለስቦችም የግል ጥቅማቸውን ለመንከባከብ ሲሉ ለጊቶቻቸው ያደሩትና የነሱን አስነዋሪና ሕገወጥ እንዲሁም አምባገነን ተግባር ሲያወድሱና ሲያሞካሹ ማየት ከሌላው ሀገራት የወደቁትና በመውደቅ ላይ ያሉ አምባገነን መሪዎች ዜና አውታሮች የተገበሩትን ተመሳሳይ ሂደትን እየደገሙ እንጂ ለሕብረተሰቡ የቆሙና ለማንም ያልወገኑ አለመሆናቸውን በዚሁ ስርጭታቸው ደግመውና ደጋግመው የብዙኃኑ ድምጽና ውሳኔ ይረገጥ ይታፈን፣ እንደ መድሀኒት ወይንም እንደምግብ ጌዜው አልፎ የተቃጠለበትን expired ያደረገበትን ምግብ ወይንም መድሀኒትን ውሰዱ የሚለውን ዲስኩር አሁኑኑ መቆም አለበት። እነርሱ ከፈለጉ ለራሳቸው ያድርጉት ብለን ለማለት እንኳ የማንዳዳው ፣ ነቀርሳ ነውና እራሳችሁን በጥቅም አትደልሉ። ለቦታው ብቃት እንደሌላችሁ ሀቅ ቢሆንም ሕብረተሰቡን አታወናብዱ፣ ቦታውን አሁኑን ልቀቁ። በስውር የምታደርጉትን ሕገወጥ ተግባር ዛሬም በራዲዮ advocate በማድረግ የሕዝብን ድምጽና ውሳኔ ይሻር የሚለውን አጀንዳችሁን ይዛችሁ ጥፉ።

አምባገነን የሆኑትና ተርማቸው የተቃጠለው የመረዳጃው ማህበር አመራርና ሎሌ ባለፈው ጠቅላላ ስብሰባ ጥሪ ሊሳተፉ የመጡትን የህብረተሰቡን አባላት በመለያየት የማይፈልጓቸው ግለስቦችን ብቻ በመለየት በሌለ የማህበሩ መተዳደሪያ ህግ አባል አይደላችሁምና በምርጫ አትሳተፉም በማለት የመለሷቸው ግለስቦች ወደ ቴክሳስ ግዛት የሕግ አስከባሪ ኃላፊ ቤሮ መብታችንን ከሕግ ውጪ ተደፍሮብናል በማለት ያቀረቡት ቅሬታ ተቀባይነትን አግኝቶ ምርመራው የተከፈተ መሆኑን ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸው የደረሰን መሆኑን ስናውቅ፣ ይህ ጉዳይ በቶሎ ካልተቋጨ ብዙ የሚያነካካ አሊያም ድርጅቱን የሚያዘጋ ደርጃ ያደርሳል የሚል ግምት ቢኖረንም፤ በኛ አስተሳሰብ ድርጅቱ ብዙ የሆነ የብሔራዊና የክልል ሕጎችን በመተላለፍ የሚንቀሳቀስ ስለሆነ ባስቸኳይ ካልታረመ መዝጋቱ አይቀሬ ነው።

አስመራጭ ኮሚቴ የተባለውም ከውስጡ ካቀፋቸው የኮሚቴ አባላት ውስጥ ገለልተኛ ያልሆኑና ቀደም ሲል አመራሩን ጨብጠው ካጨማለቁትና አሁንም ለአንባገነኖችና ለድርጅት የወገኑትን ያቀፈ ነው። እንግዲህ ምን ያህል አዲስ ሀይል ሆኖ ዘመናዊ ትምህርትና ልምድ ያቀፉትን ከሁለቱም ጾታ ያሉትን ወጣቶችን ይዞ ይቀርብ ይሆን? እንደኛ ለረዥም ጊዜ በዚህ ሀገር የቆየውና የጠለቀ እውቀትና ትምህርት ያካበተው የጊዜውን ጥያቄ ማስተናገድ የተሳነውና ወግኖ ያለው ትውልድ ከመኃል መውጣትና ለተተኪው መልቀቅ ግዴታችን ነው። እረኛም ሆንክ ሞፈር የጨበጥክ ፣ ሚልሻም ሆንክ ወታደር፣ ቤሮክራትም ሆንክ ምሑር፣ ፖለቲከኛም ሆንክ ካድሬ፣ ነጋዴም ሆንክ ቱጃር፣ ሴትም ሆነ ወንድ፣ ወዘተ…….. የሩቅ ተመልካችም ሆነ ተሳታፊ የነበረ ሁሉ እርስ በራስ ስትባላና ስትተረማመስ ለዚህ በቃን። ዛሬም ደግሞ መመረጥ ከደማችሁ የተዋሀደውን የሙጥኝ መርዝ addiction የሆነባችሁ ሲሆን በባለሙያ ታይታችሁ አስፈላጊውን እርዳታ እንድትሹ ስንመክር፤ ጊዜው መሽቶባችሁ የተሸፈናችሁበት ተገልጦ ለጠበል እንዳታውኩ ይሁን።

እርሶስ ምን ይላሉ?    

1 comment:

Anonymous said...

wow