Wednesday, March 23, 2011

የሚታኘከውን አትልቀቁ!

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!

ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።


የሚታኘከውን አትልቀቁ!

እንደምን ከርማችኃል? በእርሱ ፈቃድ ጠብቆ ለዚህ ላበቃን ለልዑል እግዚሀብሔር አሁንም ክብር ምስጋና ይሁን። ወዳጃችን ከዳላስ በስልክ ያበሰረንን ላልደረሳችሁ ልናካፍል በማለት ከቢሯችን ይችን ለመጣፍ ስለፈቀደልን ለእርሱ ምስጋና ይሁን! አሜን።

በዳላስና ፎርት ዎርዝ የኢትዮጵያን መረዳጃ ማህበር አመራር የተመራጠበት የአገልግሎት ዘመን በ12/31/2010 መቃጠሉ የሚታወቅ ነው። ተተኪዎቹን አስመርጦ በወቅቱ ላለመተካት የሚያደርገው ህገወጥ ተግባር አምባገነንነቱን አረጋግጦበታል። ባለፈው ጠቅላላ ስብሰባ በተወሰነው መሰረት የተመረጠው አስመራጭ ቡድን በተቀበለውና በተመደበለት ጌዜ ገደብ አክብሮ እጩ ተመራጮቹን የፊታችን እሁድ በ 03/27/2011 ከዚህ በፊት ጉባኤውን በተደረገበት የሆቴል አዳራሽ ውስጥ ከቀኑ በ4 ፒኤም እንደሚያቀርብ ምንጮቻችን ገልጸውልናል። አሁንም ይህን ግባኤ እንዲሰናከል የቀድሞው አመራር የማይሞክረው እንደሌለም ተገልጦልናል። ቦታው ደብል ትሪ ካምብል ከሚባለው ቁጥር 75 አውራ ጎድና እንዲሁም ካምብል መንገድ መጋጠሚያ ላይ፣ በደቡብ ምዕራብ ወገን የሚገኘው ነው። አምባገነን የቀድሞ አመራር በምስጋና መውረድን የሚሻ ሳይሆን ለመረጠው ማህበረሰብ አልገዛ ባይነትና በግል ጥቅም የታወረ ለመሆኑ የመንኮራኩር ጠበብት የሚያሻው አለመሆኑን በአረቡና በተለይም በአፍሪካ አህጉር ከምናየው መገንዘብ አዳጋች አይሆንምና ሁላችሁም በተባለው ቀን፣ ቦታን ሰአት በመገኘት ግዴታችሁን እንድትወጡ እያሳሰብን፤ ለማንኛውም የኢትዮጵያ ተወላጅና የሕብረተሰቡ አባል የነጻ መብት ነው። ምንም አይነት የአባልነት ግዴታም ሆነ ክፍያ የማይጠየቅበትና ለሁሉም የተሰጠ መብት መሆኑን መተዳደሪያው በግልጥ አስቀምጦታል

ከዚህ ወጣ ስንል ደግሞ ከዚህ በፊት እኛ ቤተክርስትያን አልከሰስንም እያሉ ነገር ግን ከጀርባ ሲያደራጁ የነበሩ ዛሬ በነበረው የፍርድ ቤት ጉዳይ ላይ በይፋ መቀላቀላቸውን አረጋገጡ። ከአሁን በኃላ ኃይሉ እጅጉ ቨርስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ደብረ ምህረት ካቴድራል ደብር በጋርላንድ ቴክሳ ብለን እንድንጠራው ከስፍራው የተገኙት ምንጮች ጠቁመውናል። እንግዲህ እንደዚህ እያለ አጽራረ ቤተክርስትያን ወይንም ቀደም ብለን ያልነው ቀዩ ሰይጣን መውጣቱና ባደባባይ መቆሙ ሁላችንን ቢያሳዝነንም በሌላው በኩል “የሚታኘከውን አትልቀቁ!” ወደ አልነው እርእሳችን ይመልሰናል። እስካሁን ድረስ በመልዕክተኞቻቸው አማካኝነት ደብሩን ሲያደሙ ነበር፣ ዛሬ የሚወስዱት መዳኒት መስራቱን አቆመ ወይንስ መውሰዱን ዝንግተው ይሁን ባይታወቅም ከነዚህ አዲስ ክስ ተቀላቃይ አጽራረ ቤተክርስትያን ውስጥ እንዲህ ጥሪት አለው የሚባል መግባቱ መልካም ነው። እንግዲህ ስንልና ስንወተውት እንደነበር አዲሱ የደብር አስተዳደር ተመራጮች ሳይውሉና ሳያድሩ ውሳኔ በማድረግ የክስ ክስ ባስቸኳይ መመስረት አለበት። ደብሩ በሕጉ ሂደት ምክንያት በንዋይ የሚያጠፋውን መተክያ አሁን መጥቷልና የሚታኘከውን አትልቀቁ እንላለን።

እንግዲህ ቸር ወሬ ያሰማን! ለበዐለ ትንሣኤው በሰላም ያድርሰን!

እርሶስ  ምን ይላሉ?  

No comments: