Tuesday, March 29, 2011

ቃል እንደገባነው

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!

ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።


ቃል እንደገባነው

ተወዳጅ የገጻችን ተከታታዮች እንዴት ናችሁ? በገባነው ቃል መሰረት የትግሬ ነጻ አውጪ ቅጥረኛ የሆነው የአዲስ አበባው መንግሥት ተወካዮች በከተማችሁ ላቀዱት የፕሮፓጋንድ ሥራ በ04/09/2011 ከቀኑ 2ፒ ኤም እስከ 6ፒ ኤም በዳላስ ፓርክ ዌይና በቤልት ላይን መንገድ በደቡብ ምዕራብ ዳርቻና በአድሰን ክፍለ ከተማ ውስጥ በሚገኘው በማርዮት ኮረም ሆቴል ውስጥ በሚገኘው ግራንድ ቦል ሩም አዳራሽ ውስጥ እንደሆነ ከሆቴሉ ለማረጋገጥ ችለናል። ይህ ቦታም የተያዘው በኤምባሲው ስም ለመሆኑ አብሮ የደረሰን ዘገባ ያስረዳል።

ቦታው የሚገኘው በ14901 Dallas Parkway
                      Dallas, Texas 75254
                      Tel. (972) 661-2800

ይህንንኑ አስመልክቶ በከተማችሁ የሚገኘውና የኛ ገጽ  ከሚደብራቸው ብሎጎች አንዱና የተቃዋሚ ልሳን አርጎ እራሱን የሚያቀርበው ብሎግ በገጹ ያወጣው የሚላመጥ ይኖረዋልና ጎራ እንድትሉና እንድትቃኙት እንጋብዛለን ። ለመግባት ይህንን መዛለያ ይጨቁኑ (ይጫኑ) http://www.ethiodallas.blogspot.com/
አልሆን ካለዎት እንዳለ ኮፒና ፓሴት በማድረግ ይጠቀሙ። በዚህ አጋጣሚ የዚህን ገፅ አቅራቢ በሀሳብ ልዩነት ቢኖረንም ለሚያደርገው ግልጋሎት እያመሰገንን ከብሔራዊ አጅንዳ በፊት የአካባቢ ሕብረተሰብ ባለው የመረዳጃ ማህበር ችግሮች ላይ ዝምታን በመምረጡ ትችታችን ታላቅና ባስቸኳይ መተግበር ያለበት በመሆኑ ሕዝባዊነት ከቄይ ይጀመር፣ ድምጡ ለታፈነበት መብቱ ለተረገጠበትና ለተቀማበት ቅድሚያ ይሰጠው እንላለን! አሊያ ለግል ጥቅምና ለሥልጣን ከሚያልሙት፣ መብትን ከሚረግጡት መፈረጅን ያመጣልና ይተግበር እንላለን። የዳላስ ወገናችን የጊዜው አንገብጋቢ ጥያቄ በጥቂት እብሪተኞች እየተፈጸመ ያለው ችላ የማይባል የነዚሁ የትግሬ ነጻ አውጪ ተቀጣሪዎች ተግባር ነውና ትግሉና ጽዳቱ ከቄይ መጀመር የግድ ነው እያልን ጥርያችንን በዚህ ገጻችን እናሻግራለንና መልሱን ለመተግባር እግዚሀብሔር ይጨመርልን እንላለን።

ተመሳሳይ ጥያቄና ጥሪያችን እንደዚሁ ለhttp://www.dfwethiopiancommunity.blogspot.com/
አዘጋጅ ወይዘሮ እያቀረብን ፤ በገጾ የጀመሩትን መውጋት ብቻ ሳይሆን ከዚህ በፊት እንደሚያደርጉት ባደባባይ መውጣትና በየስብስቡ ይገኙልን ዘንድ በትህትና  እንድንጠይቆት ተደጋግሞ በቀረበልን ጥያቄ መሰረት ነው። ባደረግነው ጥናት ያካበቱት ልምድና ያበረከቱትን አስተዋጾ አይናችን ስለገባ ይበርቱና መረዳጃ ማህበሩን ወግ እንዲይዝ የበኩሎን አጉሊ አስተዋጾን ያደርጉ ዘንድ የክብር ጥሪያችንን እናቀርባለን? የእርሶን ቢጤ እህቶቻችንን እግዚሀብሔር ያበርክትልን፣ ያበረታታልን። ካልጫ ሱሪ ቆራጥ ቀሚስ ይበልጣልና ትምህርት ለሁላችንም እንደምትሆኑ ተስፋችን የላቀ ነው።

እርሶስ ምን ይላሉ?

1 comment:

Anonymous said...

I am tired and hate you guys. Does Negusie (yederge militia) telling me not to participate the meeting. I am not a member of EPRDF, but I support the development strategic, I am open not close.