ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።
ምርጫው ተሰረዘ!
እንዴት ከርማችኃል? እኛ እግዚሀብሔር ይመስገን በእርሱ ፈቃድመልሶ በዚህ ጦመር ላገናኘን ምስጋና ለእርሱ ይሁን። አሜን።
ባለፈው ጥሁፋችን የፊታችን እሁድ የዳላስና ፎርትዋርዝ የኢትዮጵያን መረዳጃ ማህበር አባላት በወሰኑት መሰረት ታቅዶ የነበረው ጉባኤ በአንባገነኑ የቀድሞና የአገልግሎት ጊዜውን በ12/31/2010 የጨረሰው አመራር አሻፈረኝ ለምልዐተ ጉባኤው አልገዛም፣ ስብሰባውንም አላመቻችም፣ እኔ የምፈልገውንና የጥቅሜ አስከባሪ የሆኑትንና ከኔም ጋር አብረው ሲዘርፉና ሲያዘርፍ የነበሩትን የፈላጭ ቆራጭ ሥልጣን የሚሆን ትረስቲ አቋቁሜ ካልሆነ በስተቀር በማለት በትላንቱ ምሽት በነበረው ካስመራጭ ኮሚቴ ጋር ስብሰባ መገለጡ ከምንጮቻችን ያገኘነው መሆኑን ልንካፈላችሁ እንወዳለን። ባለፈው እሁድ በሕብረተሰቡ የሬዲዮ ፕሮግራም ላይ ሁለቱም ወገኖች ማለትም አስመራጭ ኮሚቲውና የቀድሞው የአመራሩ ሊቀ መንበር ከሰጡት ንግግር ማካፈላችን የሚታወስ ሲሆን አስመራጭ ኮሚቴው ከጉባኤው የተሰጠውን ኃላፊነትና በራዲዮ በገለጠው መሰረት ይወጣ ይሆናል የሚል ሙሉ እምነት ሊጣልበት እንዳልቻለና እርሱም እንደቦርዱ እድሜ በማራዘም፤ እራሱን አሉታ ውስጥ ከቶቷል።
በዚህ አጋጣሚ ለፊታችን እሁድ ታስቦ የነበረው ጉባኤና የምርጫ ሂደት መሰረዙን ስንገልጽ ሀዘናችን ጥልቅ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ የቀድሞ ተመራጮችና አጃቢዎቻቸው፣ በተለይም ሊቀመንበሩ ይልማ ፈለቀ በየቦታው እንደሚለው የያዘለት መስሎትም ይሆናል “ ምን ሰው አለ፤ ትራክ ታክሲና ሊሞ ነጂ ብቻ ነው፤ እኛ የሰጠነውን ሁሉ አሜን ብሎ የሚቀበል“ በማለት ደጋግሞ ሕብረተሰቡን ባጠቃላይ የሚያንቋሽሽ፣ ለመሪነት ያልተገባና ያልታረመ ሲሆን፤ እርሱም ቢሆን የሚተዳደረው በነዳጅ ማደያ ሱቅ ውስጥ ተቀጣሪ ሆኖ፤ የሌሎቻችሁን ሙያ፣ የትምህርት ደርጃም ሆነ ግንዛቤ ስላላችሁ ሰርቶ በማደር ከራሳችሁ አልፋችሁ ቤተሰብ የምታስተዳድሩ ብዙዎች እንዳላችሁ እሙን ነው። ሰርቶ አዳሪ ሁሉ በዚህ ሀገር የተከበረ ነው። እርሱና ቢጤዎቹ ምን ያህል ከማህበረሰቡ እንደዘረፉ በውል እስኪታወቅ ድረስ ጊዜ ገዙ እንጂ ከዕውነት እንደማያመልጡ ግልጥ ነው። እውነትነቱን ባናውቅም የዳላሱ አቶነሪ ጀነራል ቢሮ የጀመረውን ምርመራና ማስረጃ ስብሰባ አስመልክቶ ፋይሉን ኦስተን ወደአለው ዋና መስሪያ ቤት ማስተላለፉን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው መጠቆማቸውን ተረድተናል። ሌሎችም ግለሰቦች ተመሳሳይ እርምጃ ሊወስዱ በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ከምንጮቻችን ደርሶናል። እንግዲህ የተናቅከው፣ ትሰራልኛለህ ብለህ አላፊነት የስጠኸው፣ ድምጽህ ያልተከበረው፣ ምን ሰው አለና የተባልከው፣ ምናምን ታክሲ ነጂ የተባልከው፣ ሙያህ የተናቀው፣ ትምህርትህና ዕውቀትህ የረከሰው፣ ዲቪ የጣለው የተባልከው፣ጥሬና እንጭጭ የተባልከው፣ ከፋፍለው ስም የወጣልህ የዳላስና አካባቢው ወገናችን ወንድ አይል ሴት ለመብትህ መቆምና ጉዳዩ የራሴ ነው የምትል ሁሉ የጽዋው ቀማሽ አንተ ነህና፤ እስከ ዛሬ ባንተ ስም መነገዱና ጥቅም ማጋበሱን ስትደርስባቸውና ሀቀኛ የሆኑ ተቆርቋሪዎች ከማህል ብቅ ማለት ሲጀምሩ ለማኮላሸት የጀመሩትን ሴራ ሁሉ መገንዘብ የራስህ የባለጉዳዩ ነውና ፣ ፈረሱም ሆነ ሜዳው ይኸውልህ፤ ለራስህ መቆምና የሚጠበቅብህን ሚና መወጣት ያንተው ነው!
እርሶስ ምን ይላሉ?
No comments:
Post a Comment