Tuesday, February 1, 2011

WHAT IS GOING ON?

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!

ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።


WHAT IS GOING ON?

የተወደዳችሁ የገጻችን አንባቢዎች እንደምን ከርማችኃል? ደግሞና ደጋግሞ በቸርነቱ ጠብቆና በሰላም ለዚህ ያቆየን ልዑል እግዚሀብሔር ክብር ምስጋና ለእርሱ ይሁን። አሜን። ዛሬ ቸርነቱ ለናንተ በተለይም ለዳላሶች ብቸኛና ታላቁ ደብራችሁ የደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ከአጽራረ ቤተክርስትያን ሴራ እጅ አውጥቶ በመላእኩ ተራዳኢነት በተዋህዶ ልጆች አመራሩ እንዲቆይ ፈቃዱን በመድገሙ አሁንም ክብር ምሥጋና ለእርሱ ይሁን። አሜን።

ደግመንና ደጋግመን የትግሬ ነጻ አውጪ ድርጅት በቅጥረኞቹ አማካኝነት ከሀገር ውጪ በሚገኙ ተወላጆች የሥልጣን ስጋት ይመጣብኛል በሚልና የሕዝብንና የሀገር አመራርን በሚገባ ከመተግበር ይልቅ ማሳደድ፣ ማፈንና አንድነትን ማወክን ዛሬ በሚገባ ሁሉም እየተረዳው መጥቷል። ለዚሁም በዋቢ ለመጥቀስ ካስፈለገ፤ ትላንት ከተቋሚው ጎራ ሰላማዊ ሰልፍ እስከ ክሮፎርድ ቴክሳስ ቡሽ ራንች ተቀላቅለው የተሰለፉ፣ ከቅዱስ ሚካኤል ደብር ላደግንበት ቀዬ ቤተክርስትያን እርዳታ ብለው ወስደው ለአባ ጳውሎስ እጅ መንሻና ለግል ጥቅማ ጥቅም መደለያ ከመንግሥት ያገኙና የወገኑ፣ ትላንት የደርግ ባለሟል በመሆን በወገኖቻችን ላይ ግፍ የፈጸሙ፣  ከቅዱስ ሚካኤል ለወሰዱት ገንዘብ ማወራርድ ሲያቅታቸው የዋለላቸውን ደብር በፍርድ ቤት የከሰሱ አጽራረ ቤተክርስትያንን ማንነት የሚገልጽ በተለይም በአሁኑ ሰአት በአጣብቂኝ ውስጥ ያለውና እንደ ሌሎቹ አምባ ገነን መሪዎች መታናፈሻ ለጨነቀው መንግሥት ምክር ሰጪ ሆነው የሚቀላምዱና ነባራዊ ሀቅ ያልተዋጠላቸውን ቅጥረኞች ዳላስ ላይ የሚዘጋጅና ኢትዮዳላስ በተባለ ብሎግ ላይ ማንነታቸውን በግልጽና በመርጃ አስደግፎ ስላቀረበው ምስጋናችን ከዚሁ ይድረሳቸው እያልን እኛም የሚቀጥለውን Link ለናንተም አቅርበነዋል።
http://www.waltainfo.com/index.php?option=com_content&task=view&id=25158&Itemid=52

  ከዚሁ አለፍ ስንል ደግሞ በዳላስ በታክሲ አሽከርካሪነት የሚተዳደሩት ወገኖቻችን በጀመሩት የስራ ማቆም ገጻችን ቢደግፋቸውም ገና ብዙ የሚቀራቸው ሥርዐት አለ። ከነዚሁ መካከል የተደራጀና የተቀናጀ አቀራረብ ዋናው ችግራቸው ሆኖ ሲታይ በውስጣቸው ያለውን ችግርም መፍታትና ለመሪነትም ሆነ ለተመሪነት የሚያስፈልገውን ልምድ ያካበቱና ብቃት ያላቸው መሆን ይገባል። በቅርቡ እየረዷቸው ያሉት የወ/ሮ የሐረርወርቅን ሥራ ለማወክ የተነሱ በሁለት ቢላ የሚበሉትን መለየቱ ጠቃሚ ነው እንላለን።

እንደ ሙባረክ አምባገነን ሆኖና ተርሙን የጨረሰው በትግሬ ነጻአውጪ ተቀጣሪ የሆነው የዲኤፍ ደብልዩ የኢትዮጵያ መረዳጃ ማህበር 7 አባላት በጉልበት የሚቀመጡት ለምንድን ነው? WHAT IS GOING ON? ለሚለው ጥያቄ መልሳቸው መቼ ይሆን የሚደርሰን? ከመተዳደሪያው ሕግ ውጪ እየተደረገ ያለው የአመራሩ እንቅስቃሴ በሚገባ እየዘገብን የያዝነው ስለሆነ ፤ ይህ ድርጊት ባስቸኳይ ካልተገታ በጉዳዩ Secretary of State of Texas and the IRS በጉዳዩ ጣልቃ እንዲገቡበትና አስፈላጊውን እርምጃ በሕገወጦቹ ላይ እንዲወስዱ ከማድረግ ወደኃላ እንደማንል እሙን ነው። በተለይም እድሩን አስመልክቶ በሬዲዮኑ እየተደሰኮረ ያለው ሀሰትና እውነት መውጫው እሩቅ አይደለም።

ለማጠቃለያ በዳላስ ለምትገኙ የተዋህዶ ልጆች በሙሉ አጽራረ ቤተክርስትያን በደብራችሁ ላይ ለተመሰረተው የሀሰት ክስ እልባት የሚያገኝበት የፍርድ ቤት ቀጠሮው በ2/07/11 እንደዚሁም በ2/10/11 ስለሚታይ በዚሁ እለት በመገኘት ድጋፍችሁን ለደብራችሁ እንድትሰጡ በዚህ አጋጣሚ ጥሪ እያቀረብን፣ የቅዱስ ሚካኤል ተራዳይነት አይለያችሁ! አዲስ ለተመረጡትም አመራር ጥበብና ዕውቀትን ይስጥልን! አጽራረ ቤተክርስትያንን ያስታግስልን! ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ደብርን ይጠብቅልንን! የተዋህዶ ልጆችን አንድነትና ጥንካሬን ይጠብቅልን! አሜን።

እርሶስ ምን ይላሉ?

No comments: