Monday, January 24, 2011

አዲሱ ዘመቻ በራዲዮ

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!


ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።



አዲሱ ዘመቻ በራዲዮ

ፖለቲከኛም አይደለን ወይንም ተንታኝ ነገር ግን ነገርን ነገር አነሳውና ለዚህ ጥሁፍ በቃን። የተወደዳችሁ ተከታታዮቻችን እንደምን ከርማችኃል? ለልዑል እግዚሀብሔር አሁንም በቸርነቱ ጠብቆ መልሶ በዚህ ገጽ ለመገናኘት ፈቃዱ ለሆነው ለእርሱ አሁንም ክብር ምሥጋና ይሁንልን። ገናናው ስሙ ለዘለዓለም ይባረክልን። አሜን።

እኛ በገለልተኛነት በቀደምት ጥሁፎቻችን ኢሕአፓ የተባለውን የፖለቲካ ድርጅትን መተቸታችን የሚታወቅ ነው። ነገር ግን ቀደምት ታዳሚዎቻቸው ውስጥ ቀደምት የኮሚኒዝሙን ርዕዮተ ዓለም የሆነውን ቁሳዊ እምነትና አመለካከት የሻሩና ወደ መንፈሳዊነት ወይንም ሀሳባዊነት የተቀበሉ አያሌ አባሎችን ያቀፈ ድርጅት መሆኑና የአሰላለፍ ለውጥ ማድረጉ በሚገባ የተረጋገጠ ነው። ይህ ትውልደ ኢትዮጵያን አቅፎ የተነሳ ድርጅት ዛሬ የተለያዩ የሀይማኖት ተከታዮችን አቅፎ የያዘና በአለም ዙሪያ የተበተኑ ሺህዎች አባላት ያሉት ጎራ ነው። በትላንቱ የእሁድ ከሰአት በኃላ የዳላሱ የኢትዮጵያ መረዳጃ ማሕበር በአማርኛ ቋንቋ በሚያሰራጨው የሬዲዮ ፕሮግራም ስርጭቱ እንዳስደመጠው ከሆነ ኢሕአፓን ለዳላስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ደብር ቀደም ሲል አጽራረ ቤተ ክርስትያን በሆኑ ጥቂት ግለሰቦች ለፈጠሩት ሴራ በተጠያቂነት ሊያስቀምጠው ሲቀባው እንደነበር ከደረሰን ዘገባ ለመረዳት ችለናል።

በመሰረቱ በትግሬ ነጻ አውጪ ቡድን ተቀጣሪ የሆኑት ግለሰቦች ተይዞ የሚመራው የዳላስና ፎርት ዎርዝ የኢትዮጵያ መረዳጃ ማኅበር ማንነት ቀደም ሲል በተለያየ ጊዜ የተለያዩ ዘገባዎችን በአምዳችን ስናስነብባችሁ መክረማችን እሙን ነው። የዚህን መረዳጃ ማኅበር በወገኖቻችን ቸልተኝነትና የዋህነት አሊያም ድክመትም ሆነ አለማወቅ በሩንም ከፍተው ካስገቧቸው ውስጥ የኢሕአፓ አባላትንም ይጨምራል። ኢሕአፓና የትግሬ ነጻ አውጪ ድርጅት በአሁኑ ሰአት ከመገዳደል የማይመለሱ ለመጠፋፋት የቆሙ የራሳችን ወገኖች ናቸው (ልዩነታቸው ውስጥ በዝርዝር ሳንገባ)።

በሌላ በኩል የቅዱስ ሚካኤል ደብር አስተዳደርም ሆነ ምዕመን አንዴም ጣቱን በኢሕአፓ ላይ አልጠቆመም። በተለያየ ጊዜም እነዚሁ ተቀጣሪ የሆኑና ለትግሬ ነጻ አውጪ ያደሩ፣ አንዳንድ ከኢሕአፓ የከዱና አሁን ቅጥረኛ የሆኑ፣ ለይቶላቸው አጽራረ ቤተ ክርስትያን ጎራ የገቡ በመተባበር በደብሩ ላይ የከፈቱት ጥቃት በቅዱስ ሚካኤል ተራዳኢነት ፣ በቤተ ክርስትያን ልጆችና በምዕመናን ፀሎት በመክሸፉ፤ ባላቸውና በጨበጡት በትር መወናጨፋቸውን የሚያሳይ የዚሁ የሬዲዮ ስርጭቱ ያስደመጠው ነው። በሬዲዮ ስርጭት የሙያው ብቃትም ሆነ መረጃ የሌላቸውና የስርጭት ደንብና ሕግ በጣሰ፣ የመረዳጃ ማሕበሩን ሕግና ደንብ ባልተከተለ መልኩ የሀይማኖትና የፖለቲካ ድርጅቶችን ለማጋጨትና በሕብረተሰቡ መካከል የመከፋፈልንና የመጠላላትን ነቀርሳ ለመትከል የታቀደና ከደብሩ አካባቢ ያጡትን አጸፋ ለመውሰድ ቆርጠው መነሳታቸውን ያረጋገጠ ስርጭት ነበር።
የዳላስና አካባቢው ሕብረተሰብ ቸልተኝነትና ተሳትፎ ማጣት የፈጠረው ክፍተት ምክንያት ሆኖ፤ ዛሬ ተሰግስገውበት የሚገኙት የትግሬ ነጻ አውጪ ተቀጣሪዎች ባላቸው ተልዕኮ ቀሎ ያገኙትን ይህንን የመረዳጃ ማኅበርን መቆጣጠርን ነበር።  ከዚያ በኃላ የተለያዩ የግብረ-ሰናይ ድርጅቶችን ማቋቋምና በዚያ ስም በመታገዝ የህብረተሰቡን ስም በመጠቀም የተለያየ የገንዘብ ማግኛ ምንጭ ማድረግ ነው። አንዳንዶቹንም ቀድሞ ከነበሩበት ከተማ ሳይቀር እንዴት ሲያጭበረብሩ እንደነበር ከፍርድ ቤት መርጃ ጋር ማስነበባችን የሚታወስ ነው። ከዚህም አልፎ የሌለ የኮሚቴ ስም በመፍጠር በደብሩ ስምና በታቦቱ ሳይቀር እየቆመሩ ያሉ ግለሰቦች ናቸው። እንግዲህ ቅደም ብለው መረዳጃ ማህበሩን ከተቆጣጠሩ በኃላ ያመሩት ወደ ቅዱስ ሚካኤል ደብር ነበር። በዚያ ግን አልጋ በአልጋ ስላልገጠማቸው የተለያየ ስልት በማውጣት በደብሩ አስተዳደር ውስጥ ጣልቃ መግባትን፣ በፈጠራ ምዕመናኑን መከፋፈልን፣ ብለው ሁከት መፍጠርን፤ አጽራረ ቤተ ክርስትያን ቡድንን ማደራጀትን ብሎም መክሰስን አደረጉ። ይህ ሁላ ሴራቸው በተዋህዶ ልጆችና በደብሩ አመራር ከሸፈባቸው።

የተዋህዶ ልጆችም ተሰባስበው የነገሩን አመጣጥ ገመገሙ። በሕብረተሰቡም ውስጥ ያለውን የየግል ድርሻቸውን መረመሩ። መረዳጃ ማህበሩም የበለጠ መጠናከር እንዳለበት አመኑ። በዚህም ምክንያት መረዳጃ ማህበሩን ለማጠናከር እንቅስቃሴ ከጀመረው የወጣቶች ቡድን ጋር የጠለቀ ውይይትና መግባባት ላይ ደርሰው መንቀሳቀስ በጀመሩ ማግስት፤ የሬዲዮ ፕሮግራሙ አንዴም በደብሩ ውስጥ የነበረውን እክል ጆሮ ዳባ ብሎ እንዳልኖረ ዛሬ ተቆርቋሪ መስሎና አዲስ ካባ ለብሶ ብቅ በማለት በማር የተጠቀለለ መርዙን በራዲዮ ፕሮግራሙ በማሰራጨት በኢሕአፓና ወጣቱን ለመርዳት በቆሙ የተዋህዶ ልጆች መካከል ቅራኔን ለመፍጠርና እኔ በደብራችሁ ጉዳይ ውስጥ የለሁበትም ለማለት ከፋፋይ መርዙን ጀምሯል። ኢሕአፓንንም ዋና ተዋናይና የደብሩ ጠላት በማድረግ ኮንኖታል። ዘጋቢዎቹም ሆነ የበላዮቻቸው መጡብን በማለት ለተተኪው ትውልድም ላለመስተላለፍ ሲሉ የቀደም ፊውዳላዊ ሥርዐት ቢጤ የዕድሜ ልክ በትረ-ሥልጣን ጨብጦ ለመቆየት ሲሉ ትረስቲ ለመሆን የጀመሩትን የመተዳደሪያ ደንብ የብወዛ ጨዋታ ባለፈው ጥሁፋችን ማስነበባችን ይታወሳል። የዚሁ ዘመቻቸው አካል የሆነው ሌላው ተልዕኮ ኢሕአፓን ያለቦታው መኮነን ተገቢ አለመሆኑን ሁላችንም የምናውቀው ሀቅ ነው። ከዚህ ከፋፋይ ከሆነ መሰረተ-ቢስ ዘመቻ ባስቸካይ መገታት እንዳለበትና ሕብረተሰቡም ጠንከር ያለ ግንዛቤና እርምጃ ሊወስድበት ይገባል እንላለን።

እርሶስ ምን ይላሉ?

No comments: