Monday, January 10, 2011

የሰደዱት መልዕክት

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!

ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።



በቅድሚያ ሰላምታችን ይድረስዎ! በእውነት ሃማ ቱማ ቢሆኑም ባይሆኑም የሰደዱት መልዕክት ለጥያቄያችን መልስ አድርገን ተቀብለናል። እኛም ስለተሳትፎዎ እያመሰገንን መልዕክቶን እንዳለ በፊት ገጻችንም እነሆ እንለጥፋለንና ግንዛቤውንም ለአንባቢያን እንተዋለን።

ነገር ግን የሰጡትን መልስ በእርግጥ መልሰው አንብበውት ካልሆነ ደግመው ያነቡት ዘንድ እየጠቆምን ከአንድ የላይላይ አመራር የማይጠበቅ ቃላትን በኛ ላይ መሰንዘር እኛን ሳይሆን የሚመሩትን ኢሕ አፓ ድርጅትን ብቻ ሳይሆን በሕይወት የተረፉትንና አሁንም አምነው የሚከተሉትን የድርጅቶን አባላት አንገት የሚያስደፋ ቃላትን መምረጥዎ አሳፋሪ ብቻ ሳይሆን ከተራ ጎራ በታች ዝቅ ያደርገዋል። በሀሳብ መለያየት፣ መወያየትም ሆነ መሞገት ሲገባ ራስን በተራ ቃላት ማዋረድ ማንነትን ያስገምታልና የሂስ ኪኒን ካላቃሮት ቢውጡ መልካም ይመስለናል።

ኢሕ አፓ በጨቅላነቷ ባሀገር ቤት ያስነበበችንን በቀይ ቀለም የደመቀው ዲሞክራሲያ የተባለው በራሪ ወርቀትን ያስታወሰችን በምላሾ ጥሁፍ የጠቆሙትን ገጽ አንብበን ላላዩትም ለጥፈናል። ከዚህ ጥሁፍ ልንጠይቆ ከፈቀዱልን የማጭድ መዶሻ አርማችሁን ተነጥቃችሁ ነው? ወይንስ የ strategy ማፈግፈግ ይሆን? መቼስ ተጀመረ? የሚለውንና ለምንስ ለውጥ አስፈለገ? የሚለውን እንዲያስረዱን እየጠየቅን ምላሾን እንደሚከተለው ለጥፈናል።


Emama Ethiopia First has left a new comment on your post "ኸረ ማን እንበላችሁ?":

በባዶ ሜዳ መንጨርጨር፥
አላዋቂ ሳሚ ንፍጥ ይለቀልቃል።

ይህን ሊንክ ተከትለህ ብታነበው ትንሽ ትማራለህ፥ ያም ንፍጥ ብቻ ካልሞላህ http://www.ethiomedia.com/augur/democracia_no36.pdf 



ሰው የጁን ያገኛል የሚለውን አባባል እያየነውና ምስክር ያደረገን አምላክ አሁንም ምስጋና ይግባው።አሜን።በዳላስ እየተደረገ ያለው የአጽራረ ቤተ ክርስትያን እንቅስቃሴ ለትልቁም ለትንሹም እየደረሰ ስለሆነ አቤቱ ፈጣሪ በመሀሪነትህ ማረን ከቁጣህ ሰይፍ አድነን። እግዚኦ እግዚኦ እግዚኦ…..።

አንዳንዱ አውቆም ይሁን በስህተት የደብሩን መተዳደሪያ ሕግ ለማስለወጥ ፊርማ አሰባስበው አስገብተዋል። ሌላው ደግሞ ካቶሊኮች ናቸው ደብሩን የያዙት ስለዚህ እነሱን ለመክሰስ ገንዘብ አዋጡ ይላል። አንዳንዱም የፈለገው ስላልተጠቆመ ምርጫው እንዲለወጥ ይፈልጋል። እንግዲህ ሌላው ደግሞ ወደ ፈጣሪው ስለደብሩ ጸንቶ በመጸለይና ምላሹን እያገኘ ለመሆኑ ገጻችን በየወቅቱ እያስረገጠ ነው። ማየትና መረዳት ያቃታቸውና ዕምነተ ጎዶሎ የሆኑት ግን የፈጣሪን ሥልጣን እየተጋፉ የአለምንም ሕግ በመንፈስ ቅዱስ ላይ እየጫኑ እየፈተኑት ስለሆነ ልብ ያለው ልብ ይበል ወደ ፈጠረው አምላኩ በጊዜ ይመለስ እንላለን።

ከዚህ ደግሞ ወጣ ስንል ወደ መረዳጃው ማህበር ነው ጎራ የምንል። በድብቅ የተጀመረውና በትግሬ ነጻ አውጪ ወኪሎች ለቁማር የበቃው መረዳጃ ማህበር አዲስ መተዳደሪያ ሕግ እየተፈጠረለት ነው። ይኸውም ደብሩ ትረስቲ ያስፈልገዋል ብለው የከሸፈባቸው ይህንን ድርጅት ወደዚያ ለማሸጋገርና የትግሬ ነጻ አውጪ እጅ ስር እንዲቀር ለመተግበር ነው። ከአርክቴክቸሩ አንዱ ከንቱ የሆነው ግርማቸው ሲሆን ከዚህ በፊትም በደብሩ ተመሳሳይ ሙከራው የተጋለጠበትና የከሸፈበት ውርደታም ነው።

ሌላዋም ከዚህ በፊት በማህበር አደራጂነት ምንም ልምድ የሌላትና ድርጅቱን ለረዙሜ ማመቻቻ ለማድረግ የተነሳችው፣ ቀደም ሲል ተመራጭ ነኝ በሚለው ባሏ አማካኝነት ዘ ላየን ራይደር የተባለውን የወጣቶች ድርጅት እኔ ካልመራውት በማለት ከመረዳጃው ማህበር እንዲሸሹት ያደረገችው፣ ወዘተ… ትገኝበታለች።

ሰፊው የዳላስና አካባቢው የኢትዮጵያ ተወላጅ ሆይ! ይህንን ሴራ ዛሬውኑ ምላሽ ካልሰጠኸው ነገ የምትነካው ላይሆን ስለሚችል ጉዳይህ የማድረግ የአንተና  የአንተ ብቻ ነው።

ባለፈው እንዳስነበብናችሁ የእድሩም ጉዳይ ውኃ እየበላው ነውና ከከፈላችሁት ገንዘብ የተረፈውን ወይ በጊዜ መካፈል አሊያም በስማችሁ ለበጎ አድራጎት ለሚከውኑ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ብትዶሉት እርባና ይኖረዋልና ከዚሁ ትኩረትን ስጡት። ከኪሳራ ያልወጣና ሊወጣ ያልቻለ ማህበር ነው። ይህን እድር መደጎም ማለት የተቀደደ በርሜልን ውኃ ሲሞሉ መኖር ምርጫ የናንተው ነው እንላለን።

እርሶስ ምን ይላሉ?  

No comments: