Saturday, January 22, 2011

ዛሬም እንደትላንቱ

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!

ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።


ዛሬም እንደትላንቱ

መቼም የት ተደበቃችሁ? ምንስ አገኘኛችሁ? ምንድን ነው ድምጻችሁ የጠፋው? አበቃላችሁ? ወያኔ ሆኑ እንዴ? ለምንስ ከድርጅት ጋር ተላጋችሁ? ኢሕአፓን ለምን ነካችሁብን? ወዘተረፈ የተባለውን ሁሉ ከምንጮቻችን ሰማነው።

የተወደዳችሁ የገጻችን ተከታታዮች እንደምን ከርማችኃል? እንኳንም ለጥምቀቱ በአል በሰላም አደረሳችሁ? መልካም ፈቃዱ ሆኖ ደግሞ ላገናኘን ለልዑል እግዚሀብሔር ክብር ምስጋና ይሁን። አሜን። አሁንም ጸሎታችንን ተቀብሎ ለመለሰልን ፈጣሪ ክብር ምስጋና አሁንም ለእርሱ ይሁን። አሜን።

የከተማችሁም ፖለቲከኞች ገጻችን ላበረከተው አስተዋጾ አክብሮት ቢኖራቸውም ለማጥላላት ያልፈነቀሉት ድንጋይ እንዳልነበረ ያምናሉ። አሁንም ከሚፈሩት ጦመር የመጀመሪያው ብንሆንም፣ እኛ የማንም ጠላት ወይንም ማንንም አንጠላም። ሁላችንም የኢትዮጵያ ተወላጅ ብቻ ሳንሆን በእያንዳችን ልብ የየግላችንን አመለካከት ቀርጸንና ይዘን የምንጓዝ እንደ መልካችን የተለያየን ነን። ነገር ግን ግለኝነትና በተለይም በሌላው ላይ ተንሰራፍቶ እኔን ብቻ አንግሡኝ፣ እኔ ብቻ ነኝ የማውቅላችሁ፣ እኔ ካልመራሁ እናንተ አታውቁም የሚሉና ነባራዊ ሁኔታን የማይረዱ ፣ ከጊዜው ጋር ግንዛቤ ለመውሰድ ዝግ የሆነ አእምሮ ለተሸከሙና ከፊውዳላዊው ሥርዐት ባፈጀ ዕድሜ በምዕራቡ ሀገር ለመጨበጥ የሚያልሙ በትሩና ካምፓኒው ትላንት በቅዱስ ሚካኤል ደብር ውስጥ የተደረገውን ታሪካዊ ምርጫ የመገንዘብ ብቃቱ የጎደላቸው ፣ እራሳቸውን ለራሳቸው ብቻ ጠቁመው ለመመረጥ ያቃታቸው ፣ የምዕመኑን ለውጥ መፈለግ ሊረዱ የተሳናቸው ግለሰቦች ዛሬም እንደ ትላንቱ በመረዳጃ ማሕበራችሁ ላይ የመጨረሻ የሞት ሽረት እርምጃ ላይ ይገኛሉ።

የመረዳጃው ማሕበር አባልና ያለመረጃ የዶክተርነት ማዕረግ የተሰጠው የወዳጃችን ወዳጅ እንዳካፈለው ሰሞኑን ባካሄዱት ስብሰባ ገንዘብ ዘርፈው ለመሮጥ የጠነሰሱት በቅርቡ የገንዘብ መዋጮ (fund raising) ለማድረግ መወሰናቸውን ነው። በተጨማርም ሚሽቱ ከንቱ ከሚባለው ግርማቸው ጋር በመሆን በትሩና ካምፓኒውን የዕድሜ ልክ (life time) የሚጨብጡበትን ትረስቲ የሚባለውን ሕግ እያረቀቀች ለመሆኗ በኩራት አውግቶለታል። እንግዲህ 30 ቀን እንኳን እድሜ የሌለው የመረዳጃ ማሕበር ለምን አዲስ አመራር በመመረጫው ሰአት ይህንን 2 አበይት ተግባራትን ለመከወን አስፈለገ ለሚለው ጥያቄ የመንኮራኩር ጠበብት መሆን አስፈላጊ አይደለም። ያለ ውዴታ የግዴታ በእድሩ ምክንያት አባል እንዲሆኑ የተገደዱት አባላት ለማሳደስ የተደጋገመ ጥሪ ቢቀርብላቸውም እምቢተኝነታቸውን አጽንተው የቆዩት ዋነኛው ምክንያት ያለአግባብ እየተመዘበረ ያለውን ጠቅላላ ምዝበራን በሚገባ ስለደረሱበትና የጠቅላላው ስብሰባ ተጠርቶ መልክ እንዲይዝ ለማድረግ መሆኑን በሚገባ ያስረዳሉ። ለዚህም አጠቃላይ ስብሰባ ተደርጎ፣ ሪፖርትም ተሰምቶ፣ ገቢና ወጪው ታውቆ፣ አዲስ አመራር ተመርጦ ለማየትና ያለባቸውንም ውዝፍ በመክፈል መልሰው በአዲስ መንፈስ ለመሳተፍ እንደተዘጋጁ አስታውቀውናል። ነገር ግን በትሩና ካምፓኒው ያለባችሁን ውዝፍ ካልከፈላችሁ ድምጽ አታደርጉም በማለት ለዘረፉትና ላዘረፉት ገንዘብ ተጠያቂ እንዳይሆኑ መምከራቸውን ከዚሁ ዶክተር ተብዬው መደመጡን ምንጫችን አውግቶናል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ ለጽሕፈት ቤቱ ተቀጣሪ የሆነችው ግለሰብ ያላት ብቃትና ግልጋሎት፣ አቀጣጠሯንም ጨምሮ ይከፈላታል የተባለው ከ26 ሺ ዶላር በላይ መሆኑ ከፍተኛ ጥያቄ ነው። ለመሆኑ ድርጅቱ ይህን ያህል ከፍሎ የቀጠራት ሰራተኛ ከአባላት ውጪ ምን ያህል አዲስ የገንዘብን ምንጭ ፈጥራለች? ምን ያህሉንስ ገቢ አስደርጋለች? ምን ያህል የተቸገሩ ወገኖቻችንን ከችግር አውጥታለች? ስንቱንስ አስፈላጊ እርዳታን እንዲያገኝ አመቻችታለች? በመቶ እጅ ሲሰላ ስንት እጅ የሚሆነውን ነበር ካሰባሰበችው የውጪ እርዳታ ለእርሷ ደሞዝ የዋለው? ወዘተ የሚለውን ጥያቄ ይዞ የሚጠብቅ ተሰብሳቢ ይገኛል። እንግዲህ በትሩና ካምፓኔው እረፍት መውጣትን ካልከጀሉ፣ ለመጪው ስብሰባ እንቅፋትን ቢደረድሩ ውርድ ከራሳቸው እንጂ የተቀጣጠለውን ለውጥ ሊገቱት እንደማይችሉ አውቀውና ተቀብለው ራሳቸውንና የጥቅም አጋራቸውን ከሀዲዱ ባሻገር ያቆዩ ብለን ምክራችንን እንለግሳለን። ዛሬም እንደትላንቱ ሊቀጥል አይችልምና።

እርሶስ ምን ይላሉ?

No comments: