ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።
የተወደዳችሁ የገጻችን ተከታታዮች እንድምን አላችሁ? በእርሱ ፈቃድና ፀጋ መልሰን በዚህ ጦመራችን ላገናኘን ለልዑል እግዚሀብሔር ክብርና ምስጋና ይሁን። አሜን።
ባሳለፍነው የአመቱ መጀመርያ ዕለተ ሰንበት በደብራችሁ ለሚደረገው የአመራር አዲስ ተጠቋሚ መጠናቀቁን ከሚካኤል ሠይፍ ተወካይ ቢደርሰንም የተጠቋሚዎች ሥም ወደፊት ይወጣል። እኛም አስተያየታችን ወደፊት ይታከልበታል። ቅዱስ ሚካኤል የሚበጁትን ይምረጥ።
ምሽቱንም እንዳለፈው የምጣዱ ሳለ የእንቅቡ ተንጣጣ ያልናቸው የኢሕ አፓ አባላት መልሰው ተሰብስበው እንደነበር ቢገለጽልንም፤ እውነትን ከመደበቅና ለመሸፋፈን ከመራሯጥ በገሀድ ከወገኖቻቸው ጋር ተቀምጠው በመወያየት በወቅቱ በመካከላቸው በአንጃነት ለተገደሉት ወገኖቻችን ቤተሰቦችና ለተቀሩትም በምክንያት ላለፉት ጭምር የልጆቻቸውን ማለፍ በማስታወቅና እልባት እንዲያደርጉ መንገድ መፈለጉ አማራጭ የሌለው ለሁለቱም ወገን የሚጠቅም እንጂ ገዳዮችን ………መፍትሄ አያመጣም እንላለን። እርቅና
ለአማኝም ንስሀ የሚገባ ነው።
በሰንበቱ የዳላስ መረዳጃ ሬዲዮ እንደ አዲስ አበባው መብራት ብልጭና ድርግም እያለ ያስተላለፈውን ቅጂ ከዳላስ ወዳጃችን ደርሶናል። የመቆራረጡ ችግር የሙያ ብቃት የጎደላቸውና ራሳቸውን ለማሻሻል የማይቃጡ ግለሰቦች መሆናቸውን አስመስክሯል። በተለይም ለረዥም ጊዜ ስርጭቱን አንቀው የያዙት ግለሰቦች የግል ፍላጎትንና ማን አለብኝነት ትምክህት በገሀድ እያስመዘገቡ መቆየታቸውን ዛሬም እየደገሙት ይገኛል። የበላይ ታዛቢም ሆነ ተቆጣጣሪ የሌለው እንዲሁም አላማውን የሳተ መሆኑን በሚገባ አረጋግጧል። ይህን ለማለት ያነሳሳን ኢትዮጵያ ውስጥ ተወልዶ፣ አድጎና ተምሮባት፣ አለም ያየበትን ሀገር ክዶ በመኮብለል አልፎ ሲወጋት የኖረውን ግለሰብና ግባተ መሬቱንም አስመራ ላይ ያደረገውን ሲያወድስበት ተደምጦበታል። እኛ ሟቹ ለዳላስ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አበረከተ ብለን ምሳሌነቱን የሚያስመዘግብ ነጥብ ስላጣን የሬዲዮናችሁ ዝከራ ጥያቄን ማን ይመልስ? ወይንም ለኮሚኒቲው የሚጠቅም መልዕክት ጠፍቶ ነውን? በማለት ይህ አይነቱ በኢትዮጵያ ተወላጆች ላይ የሚደረግ ንቀትና መብት ዘረፋ ብቻ ሳይሆን በኮሚኒቲው ሀብት የሚደገፈውን የራዲዮ ስርጭት ለንግድና ለትርፍነት ብሎም ለጠላት መሳሪያነት እየተቸበቸበበት ይገኛል። ባለፈው የመረዳጃ ማህበር የኢትዮጵያ ቀን አሰያየም አስመልክቶ በአመራሩ ላይ ላቀረብነው ዘገባ ጥፋቱን አምኖም ሆነ ክዶ አልያም ለምን ያን አቋም እንደወሰደ ምላሽን ከመስጠት ማፈግፈግ ማንነቱን እንዲሁም የትግሬ ነጻ አውጪ ቅጥረኛነቱ አረጋገጠ። ዛሬም በራዲዮ ስርጭቱ ደግሞ አስረገጠ። ይህ አጠቃላይ አመራር የቅጥረኛ ስራው የወጣቶችን መደራጀት በመዳፉ ለመጨበጥ ቢከሽፍበት፣ ድርጅቱን ለማጥፋት በግልጽና በስውር እልቀመሳፍርት እንቅፋትና ፈተና አሁንም እየደነቀረባቸው ቢሆንም፤ ድርጅታቸው ከቅዱስ ሚካኤል ደብር ጋር በመተባበር በ2011 ሊጀምሩ ያቀዱትን tutorial program እንዳይሳካ፤ በመካከላቸው መከፋፈል እንዲፈጠርና እንዲበተን ጥረቱ የከሸፈበትን አመራር ፈጽመን መለወጥ ለነገ የማይባልና የማይዘለል ግዴታን መወጣት የዛሬ ግዴታ ነው። የመረዳጃ ማህበሩም ሆነ የሬዲዮው ስርጭት የናንተውና ለናንተው በናንተው እንጂ በከሀዲና በአጭበርባሪ ቅጥረኞች መነጠቅ የለበትም።
ስለታክሲ አሽከርካሪዎች የቀረበው ዘገባ የሚገባውን ያህል ያልተዘገበ ነው። ምክንያቱም አሽከርካሪዎቹንም ወክለው ከተደመጡት ውስጥ ሱራፌል የተባለው ግለሰብ የለየለት የትግሬ ነጻ አውጪ ቅጥረኛ ነው። ከዚህ በፊት በወዘሮ የሐረር(የኢትዮጵያ) ወርቅ ጋሻው ላይ የመረዳጃ ማህበራችሁን ወክለው ተመርጠናል በማለት “የካንጋሩ ኮርት“ ፍርድ ቤት አርክቴክተር ውስጥ አንዱ የነበረ፣ ይህንኑ ፍርድም በዚሁ የሬዲዮ ስርጭት ሪዞልሽን ብሎ የተረከ፣ በቅርቡም ከ60 ሺህ ዶላር በላይ ከእነዚሁ አሽከርካሪዎች የተሰበሰበ ገንዘብ ምዝበራ ተጠያቂ የሆነ። ይህን የዘመን መለወጫ ሥራ ማቆም አርክቴክት የሆነችውንና የተዘጋባቸውን የብረት መዝጊያ ያስከፈተችላቸውን ወይዘሮ የሐረርን አንዴም በሬዲዮ ምስጋና ከመጥቀስ ይልቅ የሬዲዮ ዝግጅቱን ብቻ የሚያወድስ ሲሆን ፤ መንገሻ የተባለውም ተጠሪ አንድም አላለም።
ግለሰቧ ያላትን ችሎታ ዛሬም ደግማ ብቃቷን ያስመዘገበችውን እህት ጊዜዋን፣ ዕውቀቷን ያለአንዳች ክፍያ የሰጠችውንና ጠበቃቸው ያቃተውን የከወነች የአደባባይ ጀግናን ለአገልግሎቷ እውቅና መንፈግ የሚቀጥለውን የትግል ደረጃ የእርሷን መሪነት እንዳያሳጣት እያሳሰብን አስቸኳይ እርምጃና ማስተካከያ ከተረጂ ወገኖቻችን ይጠበቃል እንላለን። ከዚህ ቀደም ሲኮንናትና ሲፈርድባት የቆየውና በተልኮ ዳላስ የገባው ሱራፌል የተባለውን የጥፋት መልክተኛ፣ የረባ ትምህርት የሌለው ከወይዘሮዋ ማራቅና በትምህርት፣ በዕድሜ፣ በእውቀት፤ እዚህም ሀገር ለራዥም ጊዜው በመቆየት social culture and good English language skill ያካበተና ያለውን ነባራዊ ችግር አጉልቶ የማስረዳትና ጥሩ communicator በመሆን ያለባችሁን ችግር አስወጋጅ አምባሳደራችሁ መሆን የሚችል መሆን ይገባዋል። ለወይዘሮ ሐረርም የምትመካበትና በdisposes ያለ arsenal በመሆን ያለማችሁትን በቅርቡ ድልን ያጎናጽፍላችኃል።
የአካባቢን ብክለት በተመለከተ ባለሙያዎች ብንሆንም የታክሲ መኪና አሽከርካሪዎችን ባለ 4 ነጥብ አቀራረብ ጠለቅ ያለ ድርድርን የሚጠይቅ ሆኖ፣ ሕግ አውጪውም ሆነ አስፈጻሚ ወገን በመረጃ የተደገፈና በብሔራዊ ደርጃ ተቀባይነት ያለው መሆን ይገባዋል ። CNG compressed natural gas vehicle ከ200 ማይል እርቀት በላይ የማይጓዙ፣ ውስን የመቅጃ ጣቢያዎችና አብዛኛዎቹ ጋዙን የመልቀቅ ችግር፣ እንዲሁም ሕግ አውጪው ክፍል እራሱ የራሱ የሆኑትን በሙሉ ለውጣልን? ግለስቦቹ Owner operator በመሆናቸውና ከአንድ በላይ ስለማችሉ አቅም ጉዳይ ጋር በተያያዘ ከመንግሥት የሚያገኙት ሪቤት መጠን እንዲሁም መኪናውን ያመረተው ፋብሪካ Warranty be voided case of tampering እና ማን ሀላፊነትን ይወስዳል? አሁን የጋዝ መኪናዎች እድሜ ለአምስት አመት ከሆነ መስፈርቱን ለሚያሟሉ የአገልግሎት ዘመን ዕድሜ፣ የአካባቢን ብከላን ለመቀነስ በእህት ከተሞች ልምድ መውሰድ፣ ይህን የመሳሰሉትን ጥያቄዎችን ከድርድሩ ውስጥ ለማስገባት መሞከር ተገቢ ነው።
ሌላው ያስደመጡን ቢኖር ስንጥፍበት የነበረው በመረዳጃ ማህበሩ ጥገኛ የሆነው የእድር ሊቀ መንበር ተብዮው ያቀረበው ትምህርት አይሉት ልመና ነበር። እስከ አሁን 80 ሺህ ከፍያለሁ የሚለው እድር ከተጀመረ እስካሁን ይሁን ያለፈው አመት ብቻ አላብራራም። እስካሁንም ጥንካሬውን ለመገምገም በባንክ ምን ያህል ጥሬ ገንዝብ እንዳለውና የአባላቱንም ቁጥር ያላካተተ አሀዝ ጥርጣሬን ያመጣል እንላለን። በኛ መረጃ ግን 400 አካባቢ ደርሶ የነበረው የአባላት ቁጥር ክፉኛ አዘቅዝቆ ይገኛል። ቢወተወቱም መስራች አባሎችን ጨምሮ እምቢኝ ብለዋል። ጥያቄዎቻቸውም አይስተናገዱም። አንዳንዶች እንደሚሉት በትግራይ ነጻ አውጪ ቅጥረኞች አመራር፣ ለኮሚኒቲው የሚከፈለው 40 ዶላር ጥያቄ፣ ኮሚኒቲው እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን በእኩልነት አለማስተናገድ፣ በአመራር አካባቢ ያለግለስብ ሚሽት መቀጠር፣ ሌላም ሌላም ተጨምሮበት መሆኑን የሚደርሱን አስተያየቶች ይጠቁማሉ።
እርሶስ ምን ይላሉ?
No comments:
Post a Comment