Wednesday, January 12, 2011

ገጻችሁን መሰረተቢስ አታድርጉ!

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!

ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።


ገጻችሁን መሰረተቢስ አታድርጉ!

ብዙ ጊዜ ካሰብኩበት በኃላ በመወሰኔ የሚቀጥለውን ለመጻፍ ተነሳሁ። እናንተም ያለቅሬታ በብሎጋችሁ ላይ እንደምትለጥፉት እርግጠኛ በመሆን ነው። ካደረጋችሁት ጥሩ ከቆሻሻም ካስገባችሁት የናንተ ውሳኔ ነው። ነገርግን ለዛችሁን የባሰ ነው እያጠፋችሁ የምትሄዱ። የምትነኩትንም ወዳጅ ጠላታችሁን የለያችሁ አትመስሉኝምና ብሎጋችሁ ሲያደርግ የነበረውንና ያበረከተውን ሚና እያጨለማችሁትና እያጠባባችሁት ትገኛላችሁ።

እኔ እንደደረስኩበትና እንደተረዳውት የጨበጥኩት ግንዛቤ ቢኖር የዚህ ገጽ አዘጋጅ ምንም አይነት ስለ ኢሕ አፓ እውቀት የሌላችሁ ነገር ግን ግለሰብን ለመኮነን ስትሉ ድርጅቱን ያለአግባብ ወነጀላችሁ። ይህንን ለማለት ያበቃኝና የዚሁ ጽሁፍ መነሻ የሆነው አቶ ተኮላ መኮንን የተባለውን ግለሰብ አስመልክቶ የቀረበውን በማንበቤ ነው። እኔ አቶ ተኮላን ከልጅነቱ አውቀዋለው። በእርግጥ ከናንተ የሚያስማማኝ በትምህርቱ እንደናንተ የገፋ አይደለም። ነገር ግን እድሜው ደርሶ ወደ ውትድርና የገባው ወደ አየር ወለድ መሆኑንን አልክድም ነገር ግን በአየር ወለድ ውስጥ ሾፌር እንዳልነበርና ከዚያ ጋር የተያያዘው ዘገባ የተሳሳተ ነው። በአየር ወለድም የቆየበት አመት እርግጠኛ ባልሆንም 2 አመት የሞላው አይመስለኝም። ከዚያ ጦር ክዶ የሚለውን ቃል ባልስማማበትም በትክክል የተወሰኑ ባልደረቦቹ ጋር በመሆን ኢሕ አፓን ተቀላቅሎ መሰለፉ ሀቅ ነው።

የናንተ ምንጭ የሆነው/የሆነችው ግለሰብ ከእውነት የራቀ ዘገባ ነውና የሰጡት ይህንን እንዲታረም ስጠይቅ ሁላችንም የተለያየ አመራር ስር በኢሕ አፓ ማገልገላችንና የሚጠበቅብንን መስዋዕት መክፈላችን እሙን ቢሆንም አቶ ተኮላ በጋንታ አዛዥነት አላገለገለም። በእርግጥ በቦታውና በሰአቱ ባልኖርም በአንጃነት እርምጃ የተወሰደባቸው እንዳሉ የአደባባይ ሚስጥር ነው። እኔ በአይኔ አቶ ተኮላ ሲገድል ስላላየሁኝ የምንጫችሁን እውነተኛነት ማረጋገጡ ተገቢ ነው። በግል ጥላቻ ከሆነም ሀሰት ማድረግ ተገቢ አይደለም። በእርግጥ ሚስጥር እንዳይወጣ የተያዙ ነጥቦች ቢኖሩም ውሾን ያነሳ ውሾ ይሁን ተባብለን የተውነውን የእናንተ መቀስቀስ ይሆናልና መተው ይመረጣል። ጥቅምም አይኖረውም። በተረፈ አቶ ተኮላ ዛሬ ለወያኔ ያደረ ለመሆኑ የዘገባችሁት ላይ ብስማማም መብትና ነጻነት እንዳለው እንደምንስማማ እርግጠኛ ነኝ። በተረፈ በአቶ ተኮላ ላይ የተሳሳተና የተዛባ ዘገባ የሚሰጧችሁ ምንጮቻችሁ በቦታው የሌሉና ወደቀ ሲሉ ተሰበረ የሚሉ አይነቶች እንጂ ያላቸውን እውነታ ይዘው ቢሞግቱኝ ደስታዬ የላቀ ነው።

እናንተም እዚህ ውስጥ የገባችሁት በእውነት ለሀይማኖት ከሆነ ሆዴን ነክታችኃልና አቶ ተኮላን ይቅርታ ልትጠይቁት ይገባል። በእርግጥ እርሱም ቢሆን ሀይማኖት ያለው ከሆነ ከቤተ ክርስትያን ጋር ግጭቱን አቁሞ ቢበደልና ቢገፋም ለፈጣሪ ብሎ እንዲተውና የበደሉትን ሁሉ ይቅር እንዲል በዚህ አጋጣሚ በእግዚሀብሔር ስም እጠይቃለሁ። ለተሰጠኝም እድል አመሰግናለሁ።

ምቾት ከዳላስ


ከብሎግ አዘጋጅ

ከዚህ በላይ ያለውን የላኩልን አንባቢያችንን ጥሁፍ እንዳለ ስናቀርብ የተለያዩ ተመሳሳይ ጥሁፎችም ደርሰውናልና እንድ ሀገሩ አባባል’ we can not agree more’ እንደሚሉት እንደዚሁም አቅራቢ የነበረው ወንድማችን በዚህ ጉዳይ ላይ የነበረውን contact ለአስተያየት ልንገናኘው ሞክረን ባለመቻላችን ይህንን ለማውጣት ተገደናል። በእርግጥ የተዛባ ዘገባ ከሆነ ለአቶ ተኮላ ገጻችን ከልብ ይቅርታን ትጠይቃለች። እንደግመዋለን አሁንም ከልብ ይቅርታን እንጠይቃለን። ማንኛውንም ነቀፌታና ትችት በዚህ ጉዳይ ዙሪያ በአስተያየት መስጫችን ላይ እናስተናግዳለን። ይህ ገጽ የሁላችሁም ነውና አስተያየት ስጡበት ነገር ግን ከላይ ጠሀፊው እንዳሉት ከአቶ ተኮላ ጋር ልዪነታችን ሀይማኖታችንና ደብሩን መክሰሱ ዋናው ነጥብ ስለሆነ የጠሀፊውን ጥያቄ ይቀበላል እንላለን።


በሌላ በኩል በተጠየቅነው አስተያየት መሰረትና ከሚካኤል ሠይፍ ባገኘነው መርጃ ለደብሩ አዲስ አስተዳደር ምርጫ ያለፉት ተጠቋሚዎች ስም
1. ሙሉጌታ ው/ሚካኤል  በኛ አስተየት ብዙም መርጃ የለንም
2.ሰሎሞን ጋዲሳ                                ጥሩ ምርጫ
3.ኤልሳ በቀለ                                    መልካምና ጥሩ
4.አብርሃም አሰፋ                                  ?
5.ዮሴፍ ረታ                                     የእረፍት ጊዜ
6.ተስፉ በላቸው                                    ?
7.መሠለ ከልል                                  ጥሩ
8.አምሃ ገ/አማኑኤል                           መጥፎ ምርጫ


 በማለት እንደመድመዋለን።

እርሶስ ምን ይላሉ?

3 comments:

Anonymous said...

የዚህን ጸሀፊ አስተያየት በጽሞና ተመልክቸዋለሁ። አባባሉ ወጋም ጠቀም ነው። ወይ አለመነካካት፣ ከጀመሩትም ማቡካት አስፈላጊ ነው። ሁላችንም በወቅቱ የድርጅቱ አባላት በተለያየ መንገድ በተሳትፎዎቻችን ጠላትን ለማጥቃት ስንል በወሰድነው ተግባር በታሪክ ቦታ ተሰጥቶናል።

የቻይና ሕዝብ የውስጥ ጦርነቱ ገትቶ አንድ በመሆን የመጣበትን ጠላት መክቷል። እኛ ግን በሰማሊያ ጦርነት ከጠላት ወገንን፣ በሰሜን ከተገንጣይ ኃይል ጋር አበርን፣ ደርግ በጦርነት እንዲሸነፍ በኢኮኖሚና በፖለቲካው ላይ ደባ ፈጸምን፣ ለጦሩ በሚዘጋጅ ስንቅ ሁሉ ሳይቀር አሳፋሪና ዘግናኝ አሻጥር ሰራን።

ኸረ ለመሆኑ ሜዳ ገብቶ ከኢሕ አፓ ሠራዊት ተቀላቅሎ ቃታ አልሳብኩም የሚል ማን ነው? ቃታ የሳብነው በውጪ ጠላት ነው ወይስ በኛ የፖለቲካ አቋም ያልተስማማው የየትኛው ሀገር ዜጋ ነው? ሁላችንም ተጠያቂ ስለሆንን አይደለምን ውሳኔ ያሳለፍን? ለዚህም መልሱን ከምቾትም ሆነ ከሌሎቻችሁ እጠብቃለሁ? ቤተክርስትያናችንን ከአጽራረ ቤተክርስትያን እንጠብቅ። አሁንም በኮሚኒስትን የተለከፉና የቤተክርስትያናችንን አመራር ለመያዝ የሚጠብቁትን ጠንቅቀን እንለይ። በተረፈ የዚህ ብሎግ የጠቆማቸውን ተመራጮች እኔም እስማማበታሉ።

ፍጹም ነኝ ከዳላስ

Anonymous said...

ፍጹም፣ ጉዳዩን በትክክል የገለጽኸው አይመስለኝም። ምናልባት ሳታውቅ ከሆነ መልካም። ማን ያውራ የነበረ ማን ያርዳ የቀበረ ይባላል። ትክክለኛ አባባል ነው። ሆኖም ሐሳብህ መሰረት ያደረገው አንድም በኮሎኔል መንግስቱ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ተንተርሶ ነው። አልያም የባለጊዜወቹ የትግራይ ነጻ አውጭ ድርጅት የፖሊት ቢሮ አባልና የድርጅቱ እንደአባት የሚቆጠረው አንዳንድ ሰወች ጃፋታም ይሉታል የአቦይ ስብሐት ነጋን ጸረ ኢህአፓ ፕሮፓጋንዳ ተንተርሰህ ከሆነ የናንተ ስራ ብዙ ነው። መግቢያ መውጫችሁ ያው እንደ እርጎ ዝንብ ከዚህም ከዚያም ጥልቅ ማለት ስለምትወዱ ከዚህ የተሻለ ጊዜ ሊኖራችሁ አይችልም። ዛሬ ቤተክርስቲያን ከሰው የሚያምሱንም በነዚህ ፈልፈላወች ፋይናንስ አራጊነት አይዟችሁ የተባሉ ወንድሞቻችን ናቸው። በነገርህ ላይ እንዴው የጀርባ ነገር ከሌለህና ለማወቅ አስበህ ከሆነ ብዙ ሰወች በዙሪያ ገቡ አሉ መጠየቅ አይሻልም። ደግሞም የናንተን ድርጅት (ሕወሐት)ን ከሻብያ ጋር የተከላከለና መሪወቹ በሁለቱ ጠባቦች የተበሉበት ድርጅት ኢሕአፓ ነው። ሌላው ለቁም ነገር አንድ ልበልህ። እናንተ አዲስ አበባን ከመውረራችሁ ቀደም ብሎ፤ የኢሕአፓ መሪወች ሳይሸሹ በገቡት ቃል መሰረት በውጊያ ሲወድቁ፣ እንደነ ገለብ ዳፍላ፣ ሐይሌ አባይ አይነቶች እንዲሁም አበበ ደፍተራው፣ ይስሐቅ ደብረጺዮን፣ ተስፋየ ታደሰ እና ሌሎችም መሸሻ ሞልቶ ቢሻቸው በሱዳን ወይንም በሌላ ለታሪካዊ ዘመናዊ ደርቡሾችና፣ ለአሽከሮቻቸው የናንተው ድርጅት ወያኔ ወሻብያ ጋር ገጥመው በሱዳን ሜካናይዝድ ጦር የሚደገፈውን የገንጣይ ጦር ከምንም ሳይቆጥሩ ነው ያለፉት።፡መቸም በጀ አትሉምና ደግ አዲስ አበባ የነበረው ስልጣኑን ለናንተ አስረክቦ የፈረጠጠው ኮሎኔልም ቢሆን ቃሉን እንዳጠፈ የሚታወቅ ነው። የማይደርስ መስሏት በእንትን..... እንደሚባለው። አንድ ሰው እስኪከር ብሎ እንዳልፎከረ የቁርጥ ቀኗ ስትደርስ አይደለም ቴወድሮስና የኢሓፓ ታጋዮችን ሊመስል፤ እንዳንበሳ ባገሳበት፡ እንደ ድመት ጮሆ እንደሸሸ አይተናል። ለሁሉም ከመናገር በፊት መመርመር ብትችል መልካም ነው። እንዴው እነዚህን ፈልፈላወች ስለሸተተኝ እንጅ ነህ ማለቴ ባለመሆኑ የተሳሳተ ግምት ካንጸባረቅሁ፣ የከበረ ይቅርታህን እጠይቃለሁ።

Anonymous said...

ወንድሜ ሆይ በጽሁፍህ የምስማማበትና የማላስማማበት ነጥቦች እንደተጠበቁ ሆኖ፤ ትውልድ ሀገራችንን አሁን የሚመሩት ከአብራኳ ያወጣቻቸውና ሀገርን ለመምራት መብት ያላቸው ናቸው። በዚህ ወደድንም ጠላን እንስማማለን። ከዚሀም ለጥቆ በትረ መንግሥቱን በዲሞክራሲያ መንገድ አልጨበጡም፣ በዚህም እንስማማለን። ሥልጣናቸውንም በአግባቡ አልተጠቀሙበትም፣ እራሳቸውም ያረቀቁትን ሕገመንግሥትንም ጥሰዋል፣ በዚህም እንስማማለን። የሕዝቡን ድምጽ አፍነው መብቱንም ረግጠው በኃይል ይመሩታል፣ በዚህም እንስማማለን።ሌላም ብዙ የምንስማማበት ሀቅ እያለን ለምን የሌለ ሰጣ ገባ አባባለን?

ብዙዎቻችን በዚህ ሀገር ከሰፈርን ጀምሮ ከልጅ አልፈን የልጅ ልጅ አፈራን። በዚያው ደረጃ የድሮው ወጣትነት አልፎ ህሊናችን ተሰብስቦ እንኳን ስንጽፍ አይደል ስናስብም ብስለታችን ይገመገማል። ዛሬ እንደድሮው ጥሬ ቆርጥሜ የወንዝ ውኃ ጠጥቼ ተራራና ሸሎቆውን፣ ሜዳና ገደሉን ዘልዬ የማልወጣውን አልሞክርም። ነገር ግን ጉልበቴንም አጥፌ አልቀመጥም። ዛሬም ለእኩልነትና ለፍትህ እታገላለሁ። ዘመን እንደምንቆጥረው ሁሉ የትግሉም ስልት ከአመት ወደ አመት እየተለዋወጠ መሆኑን ልንረዳ ይገባናል። በሚሰጡን ማንኛውም የዲሞክራቲክ መንገዶች ሁሉ በጥበብ መታገል ይገባናል። በእስር በመዳረግና በጀብደኝነት ያለ ጥበብ መስዋዕትነት ጊዜው እያለፈበት መጥቷል። ለዚህም ነው grass root movement የሚያስፈልገው።

በዚህ ከተስማማህ የኔ ወንድም ብታጣ ለራስህ የብዕር ስም ሰጥተህ ባገኘነው በዚህ መድረክ ተማምረን ለሌላውም ትምህርት እንሁን። ስለድርጅታችን የምለው አለኝና አንተም ሆንክ ሌላው ምላሽ እንደሰጠኝ እመለስበታለሁ።

ፍጹም ነኝ ከዳላስ