Monday, January 10, 2011

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!

ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።


የአይጥ ምስክሯ ድንቢጥ!
ለአሲምባው ደመላሽ መልስ።
አሁን የምትለኝ አቶ ተኮላ ወደ አሲምባ የመጣው መንግስቱ ሃይለማርያምን ተቃውሞ ነው?
ሰው አንዳይስቅብህ። እኔ አቶ ተኮላ ጋር ቅራኔ የነበረኝ ቤተክርስቲያን ስለከሰሰ እንጅ ወታደር ስለነበረ አለነበረም።አንተም ቤተክርስቲያን የሚከስ የምትደግፍ ከሆነ ከከሳሾቹ ውስጥ አንተም አለህበት ማለት ነው። ልጠይቅህም የምፈልገው ቤተክርስቲያን መክሰስ ምን ለማትረፍ ነው?
የሃይማኖቱ ጥላቻ! ወይስ ከቤተክርስቲያኑ ካሳ ለመብላት?አሁን ወደ ዋናው ድንቢጥነት እንመለስና፡ አንተው የረዳህ መስሎህ አጋለጥከው። የአየር ወለድ ወታደሮች፤ በእድሜያቸው የገፉ በወታደርነት የሰለጠኑ እንደመሆናቸው መጠን እንኳን አንድ ወታደር ቀርቶ በስሜት የተገፋፋ መረን (Mob) የማይፈጽመውን መሳርያ ባልያዙ ገና ሙሉ አቅመ አዳም ባልደረሱ የአየር ሃይል ካዴቶች ላይ የፈጸሙት ድብደባና ባዶ ካምፕ በመትረየስና በታንክ መክበብ ሙያ መስሏቸው በጊዜው የነበረውን የእንዳልካቸው መኮንንን መንግስት ለመደገፍና ንቅናቄውን ለማፍረስ ያቀዱት ተግባር እንዳልሆነ ሲያውቁና እውነተኛው የኢትዮጵያ ወታደር ሲጥጋቸው የለበሱትን መለዮና ያደረጉትን ጫማ ሳይቀር ወርውረው የሴት ልብስና ለምድ ለብሰው ባዶ እግራቸውን ነፍሴ አውጭኝ ያሉ ናቸው። በዚያን ጊዜ መንግስቱ ሃይለ ማርያም የሚባልም ስም እንዳልነበረም አረጋግጥልሃለሁ። በዚያን ሰአት ገዥውም ጃነሆይ ጠቅላይ ሚኒስተሩም እንዳልካቸው መኮንን ነበሩ። ንደዚህ ያለውን ሰው ነው እንደዝነኛ አድርገህ አሲምባ መጥቶ መንግስቱን ተዋጋ የምትለን። መንግስቱ ሃይለ ማርያም ህጻናትን አልገደለም ህጻናትን ያስፈጀ ኢህአፓ ነው። አትሳሳት መንግስቱ ሃይለ ማርያምን መደገፌ አይደለም እውነቱን ለመናገር ነው። የሃይሌ ፊዳን አቋም ተመቃዋሚ በማስመሰል እንድ የማይረባ ያልተማረ የቀበሌ ዘበኛ ገድላችሁ የሰፈሩን ህጻናት እንዲረሸኑ ማድረግ ተገቢ ነበረን? ወይስ ጠጅ ቤት ገብቶ መፎከርና መጥፋት ምን ለማትረፍ ነበር ድሃ ለማሳሰርና ለማሰቃየት ካልሆነ በስተቀር። ተኮላ እናንተ ጋ አሲምባ መምጣቱ ነፍሱን ለማዳን እንጅ መንግስቱን ለመቃወም ነበር እንዴ?። እስቲ ምን ምን ተግባር ምን ጀብዱ የሚያሰኘው ነገር መስራቱን በሚቀጥለው ጽሁፍህ አብራራልን። እሱን የሚያክል ወታደር በእድሜም ሆነ ባሰለጣጠን ከማይወዳደሩት ህጻናት ስር ወድቆ በናንተ መመራቱ ውርደትን እንጅ ጀብዱነትን መስራት ከሆነ ይሁንልህ፤ በርታ ስሙን አጥፋለት። በ እኔ አስተያየት አንድ ወታደር ለቆመበት እምነቱ መጋደልና ማሸነፍ አለበለዚያም መሞት እንጅ እንደናንተ ያሉ እንኳን ፖለቲካ ቀርቶ አቋም እንኳ የሌለው የኢትዮጵያን ህጻናት ማስጨረስና አገር ለማስከበር የዘመተው ወታደር ስንቅ ላይ ጠርሙስ ፈጭቶ የሚከት ደካማ ወጠጢወች ውስጥ መደበቅ አሳፋሪና ገመና አጋላጭ ነው።
እንደዚህ ያለ ግለ ሰብ ጋር መነጋገር ቀርቶ እውቀዋለሁ ማለት እንኳ አሳፋሪ ነው። የዚህ አይነቱ ግለ ሰብ እንኳን ቤተ ክርስቲያን መክሰስ ቀርቶ ሌላም ብዙ ነገር ቢያደርግ የሚያስገርም አይደለም። በሌላው በኩል ክርስቲያን ለመምሰል ታላቁ ገታችንን መጥቀስህ ምና ይባላል። በተአምሩ ያማታምን ከሆነ ምን የሱን ስም አስጠራህ። አበበን ጌታ መላኩን በ ፓሊስ ምስል የላከለት መልካም አገልጋዩ ስለሆነ ነው። ለ እንዳንተ አይነቱ ቤተክርስቲያን ከሳሽና የሰው ሃጢአት በየ
ታክሲው ላይ በታኝ መልአኩን ልኮ ከመጥፎ ተግባርህ እንድትመለስ ከማድረግ ይልቅ ተገቢህን ይልክልሃል። መልእክቱንም ባይናችን አይተናል። አንተና ጓደኞችህ እነተኮላ አወን በእግዚብሄር አታምኑም፤ አንዴ ማርክሲስት ሲመች ክርስቲያን በሊላ ጊዜ የትግራይ ነጻ አውጭ እያላችሁ ባልኖራችሁ ነበር። ቤተክርስቲያን መክሰስ ምን ለማትረፍ ነው? ቤተክርስቲያን መበጥበጥ፤ ቀሳውስት መሳደብን ምን አመጣው? ከቀሳውስት አልፎ ጳጳስ መሳደብ “ አገር ጥሎ የሸሸ
እያላችሁ “ መዝለፍ ማንን ለማስደሰት ነው? እውነት አእምሮ ካለህ! አስበው ለምን መልአኩን ላከለት? ለምን መጥፎ ተግባር ከመፈጸም አዳነው? ለምን ያሰበውን በሚፈጽምበት ጊዜ ሊደርስበት ይችል ከነበረው አደጋ ሁሉ አዳነው?
መልሰህ መላልሰህ አስበው።

ዮናስን ለምን አሳ ነባሪ ላከለት? እግዚአብሄር ለሚወደውና ለሚያገለግለው ብዙ ክጥፋት መዳኛ መንገድ ይከፍትለታል።
ፖሊስዋ ባትላክለትኖሮ አንዷን (Drug addict) አግኝቶ ግብረ ስጋ ቢፈጽም፤
1፤- የአምላኩን ተእዛዝ አፈረሰ ማለት ነው ምክንያቱም ዝሙት አሰበ ከማለት ይልቅ ዝሙት ፈጸመ ማለት ነው።
2፤- ከዚሁ ዝሙት ጋር የሚመጣው ኤይድስ በሽታ ቢይዘው ምናልባት ያልተጠራጠረችውን ባለቤቱን የልጆቹን እናት በከለ ማለት ነው።
3፤- ይህን ዝሙት በሚፈጽምበት ጊዜ ሊደርሱ ከሚችሉ አደጋዎች አንዱ የሴተኛ አዳሪዋ በላቤት (Pimp) ሊዘርፈው ይችላል በዚያውም አኳያ ሊገድለው የችላል፤ባይገድለውም አንድ አካሉንም የማጣት አደጋ ሊገጥመው ይችላል። ከዚህ ሁሉ አደጋና ሃጢአት ውስጥ ከመግባቱ በፊት በቀላሉ ምናልባት በገንዘብ ክፍያና
በማስጠንቀቂያ ብቻ መመለስ ለ እንዳንት ላለው በሃጢአት ለተዋጠ ምንም አይመስለው ይሆናል። በእግዚአብሄር ማመንና እግዚብሔርን ማገልገል ግን ይህን አይነት ውጤት ያመጣልና አንተም ክስህን ትተህ አንዱ ጓደኛችሁ እንዳለው “እባካችሁ ሃጢአት በዛ” ብላችሁ ፊታችሁን ወደ አምላካችሁ አዙራችሁ ጸልዩና ምን አይነት መልካም ውጤት አንደምታገኙ ታያላችሁ።
በዛውም አገር ቤት ላስጨረሳችኋቸው ልጆች አምላክን ተንበርክካችሁ ይቅር በለን ብትሉ መሃሪው ፈጣሪያችን ይቀር ይላችኋልና።
አምላካችን ሆይ! ልቦናችንን ወደ ደጉ ተግባር ምራን! እነሱንም እባክህ የሚሰሩትን አያውቁምና ይቅር በላቸው እባክህ፤
አሜን!
January 8, 2011 10:27 AM
Delete

ከዚህ በላይ ያስነበቡን ተሳታፊያችንን ከልብ እያመሰገንን፣ ከመመካከላችን መስራችና ረዳት አዘጋጃችን የሆነው ወንድማችን ላልተወሰነ ጊዜ ለግዳጅ ስለተለየን በሔደበት ሁሉ ቸሩ ፈጣሪያችን መሪና ጠባቂ እንዲሁም ደጋፊ ሆኖ በድል እንዲመልሰው የዘወትር ጸሎታችን ነው። የተወደዳችሁ የገጻችን ታዳሚዎችም በጸሎታችሁ ታስቡት ዘንድ እንጠይቃለን?

Semper fi!!

1 comment:

Anonymous said...

The person who comment under የአይጥ ምስክሯ ድንቢጥ! is giving us too much information about Abebe, Last time I read on this blog that Abebe was giving a ride to a lady who he wanted to hire her for Enjera megager business. He might not but if he is using that reason to defend himself, Mister i think you are killing him. By the way, you amazed me with your MENDEFADEF to express how he have been saved bla, bla. How about if we put it this way, it is a message to every body KEMETEMTEM MEMAR YIQEDEM, LEMAGELGEL first of all BEQEDESENA LEMENOR MEWESEN YEGEBACHIHUAL SILEN MEHON ALEBET since every body knew about it, it's a message to every body Mister. Let's check our self like what we do, what we say with God's word.