ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።
ይድረስ ለኢሕአፓና ለሎሌዎቹ
ከሁሉ በላይ ፈቃዱ ሆኖ ለታላቁ የጥምቀት በዐል ሁላችንን ጠብቆ በሰላም ላደረሰን ለልዑል እግዚሀብሔር ክብር ምስጋና ይሁን። አሜን። እንኳን በሰላም አደረሳችሁ።
ባለፈው ‘እናንተን ምን እንበላችሁ?’ በሚል እርእስ ላቀረብነው ጥሁፋችን በአለም ደረጃውን የጠበቀ አቅርቦት መሆኑንና በየትኛውም ወገን የቆሙት በሙሉ የግላቸውን ግንዛቤ ወስደዋል። በእርግጥ በድርጅቱ ሥር ለታቀፉት ወይንም ዳይሀርድ ከሆኑት ጎራ ቅሬታን ብናስመዘግብም፤ ከትግሬ ነጻ አውጪ ቅጥረኞች ጎራ ልባቸውን ለጊዜው አሞቀው እንጂ እነርሱም የሰው ልጅ በልተው ለዚህ መድረሳቸው መረጃ እኛን መጠየቅ ማለት ከሌላ ፕላኔት የወረደ ብቻ ስለሆነ ባንድ እንመትራቸዋለን።
ከጥቂቶች በስተቀር አብዛኛው ቃታ የሳበ የኢሕአፓ ጀሌ ሁሉ ባለሁለት ስም መጠሪያ ያለውና እስከ ሁለት ፓስፓርትም የያዘ እንዳለ የሚታወቅ ነው። በትግሬ ነጻ አውጪ ውስጥ ይህ ድርጊት ተመሳሳይነት አለው።የዳላሱ ወንድሞቻችን በethiodallas ገጽ ላይ በብዕር ስም ሳሙኤል ሽፈራው የተባሉት “ኢሕአፓን ለቀቅ“ ብለው ያጣፉትን በትህትና ተቀብለን በማፈግፈግ ላይ እያለን በፓርቲያቸው ልሳን በሆነው አሲምባ.ኦርግ ላይ እንደዚሁም በቢጤዎቹ ድኅረ ገጽ በተመሳሳይ ያስነበቡን እርእስ “ የቀድሞው ፕሬዝዳንት መንሥቱ ኃ/ማርያምን “ አስመልክቶ በኪዳኔ አለማየሁ የቀረበውን ማስተናገዱ ፍጹም ስህተት ነው። ይሀው ጠሀፊ በብሄራዊ ደርጃ ሊያስተዋውቃቸው የሚቃጣውን የግለሰቦችን ስም ማንነትና ምንነት የዳላስና የቴኔሲ ወገኖቻችን የተፏቸው መሆናቸው እሙን ነው። እነዚህ በትግሬ ነጻ አውጪ ቅጥረኝነት የሚተዳደሩ ግለስቦችን ከቀይ ምንጣፍ እኩል ያነጠፈላቸው ለምን እንደሆነ ለናንተው ዳላስ ላይ ላላችሁትና የፓርቲያችሁ ክንፍ ለሆናችሁት ስንተው መልሱን ለአንባቢዎቻችን እንደምታቀርቡ በመተማመን ነው። ድኅረ ገጾችም ባስቸኳይ ያነሱታል የሚልም እምነት አለን። በተለይም የመንግሥቱን ፊርማ ተብሎ የቀረበው በኛ በኩል እውነተኛነቱን ለመቀበል አዳግቶናልና ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ይተቹበት እያልን በጥያቄ እናልፈዋለን። ምንአልባትም ኮለኔሉ ወይንም በዚህ አካባቢ ያሉ ሊመልሱ ይችላሉ። እኛ ከማስረጃው እውነተኛነት እንጂ ድርጊቱ አልተፈጸመም ብለን እንዳልሆነ ከዚሁ ለማስጨበጥ እንወዳለን።
ባለፈው በገጻችን ላይ“ከምቾት“ ለቀረበውና እኛም ለወሰድነው እርምጃ ለልቡ ሙቀት የተሰማው የመሰለው ባንዳ ምቾትን ጥሩ በሰራለት መልሶ ሊነክሰው ሞክሯልና እንግዲህ ባንድ ቀዬ ያደጋችሁ ከሆነና አብራችሁ ጓዴ ተባብላችሁ መሳሪያ በደርግ ላይ ያነሳችሁና የኢሕአፓ ሠራዊት የነበራችሁ ስለሆነ ክንብንባችሁን አውርዱት ነው የምንል። አሁንም ከጊዮርጊስ ያመለጠህ የተባልከው ምቾትም ካልሆንክ አንተ ማነህ? ወይ ከተኩላው ወይ ካንዳችሁ አንድ በሉን እያልን ለዛሬው በዚህ እንሰናበታለን።
እርሶስ ምን ይላሉ?
1 comment:
ለ ጓደኛችን ለ ሉልሰገድ አበሻው።
በተአምር እናምናለን! አንተም እመን!
ሰሞኑን በመረዋ ብሎግ እንዳነበብነው የምርጫ ማስቆም ፔቲሽን፤ ምርጫውን ለማስቆም (Petition) አስገብተን የቅዱስ ሚካኤል ቦርድ አልተቀበለንም በማለት ክስ ለመመስረት የሄዱት አቶ ፍቅረማርያምና ሉሉ ያሰቡት ሳይሳካ ክሱም ሳይመዘገብ ተጣልተው
መለያየታቸውን ሰምተናል። የህንን አለመስማማት የፈጠረው አምላክ ሉሉን ሳያውቅ ሊገባበት ከነበረውን አዘቅት ከአፋፉ ላይ ለማዳን መሆኑንም እናምናለን። ሉሉን አንድበግ እየመራ አዚህ አዘቅት ላይ ያስገባው ፍቅረማርያም፤ ድሮውንም የቤተክርስቲያን ደጋፊ መስሎ ሰርጎ እንዲገባና እንዲያተራምስ በጌታው በሻለቃ ተፈራዎርቅ ተእዛዝ መሆኑን የምናውቅ ሁሉ ብንነግረው አልሰማም ብሎ ነው። ከጓደኞቹም ጋር እንዲጣላ ሲያደርገውም ተው ተመለስ ብለን ነበር። ካሁን ቀደም ስለ ልጁም የጻፉት ሰዎች በሻለቃው እንደተላከ ስላወቁ መሆኑን መዘንጋት የለበትም ነበር፤ የተጻፈውም ሁሉንም ለማስጠንቀቅ እና እንዲጠራጠሩ ለማድረግ ነበር እንጅ!። ሉሉ ግን ይህን እውነተኛ
ተግባሩን እንዳያይ አይኑን እንዲሸፍን ሲያደርገው ማወቅ ነበረበት። ያደረገውም የተንኮል ስራ ሲጋለጥና የሚያሳፍር ደረጃ ሲደርስ አብሮት እንዲዘምት ሲገፋፋም ስናይ በጣም አዝነን ነበር።
ይሄ ሁሉ አልበቃ ብሎ በውሸት ላይ የተመሰረተ ፔቲሽን፤
1 ፊርማ አስመስሎ በመፈረም
2 ተደጋጋሚ ስም በማስገባት
3 ግራ የገባውና ግልጽ ያልሆነ፤ (የምንስማማ ይመስለናል፤ጥርጥር የፍለንም፤ ክሱ ሳያልቅ) የሚል ከ አንድ አዋቂ የማይጠበቅ ግልጽ ያልሆነ ፔቲሽን አስገብቻለሁ ብሎ መክሰስ የሚያመጣው ጣጣ ለከሳሹ ወይስ ለተከሳሹ?
ሉሉ! አሁንም ወደ ጓደኞችህና ወደ ቤተክርስቲያንህ ተመለስ። ክሱን የምትመሰርተው አንተ እንኳ ባትሆንም ያቀረብከው አንተ ስለሆንክ፤
1 ፊርማ አስመስለህ በመፈረም
2 ተደጋጋሚ ስም በማስገባትህ
3 የፈረሙልህን ምእመን በማሳሳትህ (የቤተክርስቲያኑን የቦርድ ምርጫ ለማስቆም)
መሆኑን ሳታስረዳ ክስ ቢመሰረት ኖሮ፤ ልትፈጽመው የነበረውን የወንጀል እንደገና ጠበቃ ጠይቅና ከምን ጉድ እንዳዳነህ ተረዳ እንልሃለን።
ከዚህም ሁሉ በላይ ዘለአለም በሄድክበት ሁሉ ቤተክርስቲያን የከሰሰ እየተባልክ እንደነ ጥሩ አየር ሲጠነቆልብህ ከመኖር የዳንህ መሆንህን አትርሳ።
ለመሆኑ የከሰሱ ሁሉ ምን ያተረፉ መሰለህ ?። ምንም ጥፋት ሳላደርግ ቄስ ለምን አባረራችሁ ስላልኩ በፓሊስ አስወጡኝ ስለዚህ ገንዘብ ይከፈለኝ ብላ የከሰሰችው ሴት ክስሽ ተገቢ አይደለም ቤተክርስቲያኑንም የሚያስከሥሥ ጉዳይ አይደለም ተብሎ ክሷ እንደተወረወረባት አልሰማህም ይሆን?
ተኮላና ጸሃይ ጽድቅም ክስ እንደሌላቸው መፈረዱን ሲያውቁ፤ ጊዜ ለማራዘም በሌለንበት ተፈረደብን ለማለት በቀጠሮው ቀን ጠፉ።
ጥሩ አየርም ብትሆን አንዴ የተፈረደውን ፍርድ ለመገልበጥ ምን እድል ያላት ይመስልሃል?።
ፍቅረማርያምና ጓደኞቹ ክሱ ሁሉ አስከ (February) አጋማሽ ስለሚያልቅ ከማለቁ በፊት እንፍጨርጨር ብለው አንተን የድሮ ጓደኛችንን ሊያሳስቱ መሞከራቸው ነው።
ሚካኤል ግን ድሮ የሰራህለትን ውለታ ሳይረሳ ከዚህ ሁሉ ጉድ አድኖሃልና ወደ ቤተክርስቲያኑ ደረስ ብለህ ማረኝ ብትል ጌታ መሃሪ ነውና ይምርሃል።
እኛም ደስ ይለናል።
ተአምር ይሉሃል ይሄ ነው።
ሁላችንንም መልካም ተግባር እንዲዳርገን ለአምላካችን እንጸልይ፤
አሜን!
Post a Comment