ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።
ተኩላና ብዕሩ በከፊል ይህንን ይመስላል። የእንቅቡ መንጣጣት በትላንትናው ምሽት በዳላስ ተሰብስበው ነበር። በጸለምት የደረሰው መበታተን በዳላስ ተደገመ። ዛሬ የሚረሽኑበት የትግራይ ጫካ የለ ። የገዳዮች ለምድ ሲከፈት እንዲህ ይጀምራል።
ምነው ዳግም ጦ ርነት?
ተኮላ መ ኮንን
02/28/1999
የሳባ ጉዞ ምላሽ ምንሊህን ይዞ ሲተም ፣
ከፖርቹጊስ የጦር አጋር ከአሌክሳንደርያ ሥ ጋወደም ።
ከቱርክ ከድርቡሽ ወረራ ከግራኝ መ ሐመ ድ ስግደት ፣
ከቴዎድሮስ መ ቅደላ ከዮሐንስ የአንገት ስልበት፣
በሮም የዘርዓይ ድረስ ጎራዴ የሰላቶ ደም እልበት።
ለጣሊያን ነፍጥ በጋሻ ምትሽ፣
ጀግናሽ ከግራ ቀኝ ሲመ ክትልሽ።
ድል በድል ሆኖ አድዋ ላይ እልል ተብሎ ሲፎከር፣
ምነው ምኒልህ ፈረሱ ባሕር አጠገብ አድሮ በነበር።
ውጫ ሌ የተሻረው ውል አድዋ መፍረሱ ቀርቶ፣
አዶሊስ ላይ በነበረ ግጫ ነቅሎ ቄጤ ማ አንጥፎ ውኃ ነክቶ።
ፈረንጅ በገባበት ሁሉ የተከለው ተንኮል ሴራ ፣
ለዓመታት እኛም ላይ ሊያደራ?
እንደቆላ ቁስል ሊነፈርቅ እንደነቀርሳ ሊያንሰራራ?
ከከፋሽማ ተገንጠ ይ ካልጣ መ ሽ ቤታችን ቤትሽ ባልን፣
ለትግሉ እንዳልደማ ን ለነሱ ትላንት እንዳልሞትን፣
ይቅር መቼስ ተብሎ የሆነ ያልሆነውን እንዳልቻልን፣
የሕዝቡን ቁጣ እንዳልገታን እሮሮውን እንዳልዋጥን፣
ሚስት እንደነጠ ቀ አጉራ ዘለል ጣውንትነት ሊከጅሉን?
በጥይት ሊለበልቡን ባውርፕላን ሊያቃጥሉን?
በሞርተር ሊጨ ፈጭፉን በታንካቸው ሊዳምጡ ን?
ተው ሲሏቸው ካልሰሙ አውራው ከሆነ ንጉሳቸው ፣
ሠላም ማለት አቅሯቸው ጦር ከሆነ ዳንኪራቸው ፣
ወንድሞቼ ምርጫ ም የለ ክንዳቸሁን አሳዩአቸው ።
የተወጠ ረን ፊኛ እፍታ መ ች ይጎዳዋል፣
እስትንፋስማ ጌጡ ነው ወደ ሰማይ ይወስደዋል ።
ሲነኩት ነው እንጅ በመ ርፌ በቢለዋ በጉጠ ቱ ፣
የማያምረው አወዳደቁ መ ሽመ ድመ ዱ አሟ ሟ ቱ።
ተዋቸው ሲባሉ ከነገሱ ይብቃ ሲሏቸው ካበጡ ፣
ምንም ልመ ና አያሻም ወንድሞ ች የጠመ ቁትን ይጠ ጡ ።
ሰሚ ካለ ግን ጦ ር ይብቃ በሏቸው ዘፈናቸውን ይቀይሩ፣
«አደየ ጀጋኑ» ይቅርና ስለፈቅር ይዘም ሩ፣
ስለሰላም ተወያዩ በሏቸው መ ሃይሙ ን ያስተምሩ።
ከእጅ ወዳፍ የሚ ኖረው ን ያንን ጭ ቁን አርሶአደር፣
ዛሬም ያላለፈለትን የከተማ ው ን ላብ አደር፣
በግዴታ ተሰባስቦ የተከማ ቸውን ወታደር።
ምን አለ ሀሁ ቢያስተምሩት ሀ ግእዝ ለ ግዕዝ ፣
የጦር ከበሮ ከመ ምታት የትም ክህት ክራር ከመ ጠ ረዝ ፥
ምን አለበት «አሶ» ላይ ቢረባረቡ ፣
ማዳበሪያ ለአርሶ አደሩ ቢያቀርቡ ፣
ሚግ እየገዙ በየሜዳው ከሚ ከስሩ።
ሰውን የሚጎዳው ፍቅር እንጂ ጠብማ መ ዝጊያ በር ነው ፣
ትእግስት ሰላም ያዋቂ ፥ ጡ ጫ ብትር የመ ሃይም ነው ።
መ ሪዎች ትላንት ነበሩ አልፈዋል፥ የዛሬዎቹም ያልፋሉ፣
ምንም ነገር ቢፈጠ ር ሕዝቦች ግን ይኖራሉ።
እናም ለማያልፈው ሕዝብ እትብቱን ለበጠ ሰ ሰው ፣
ሠላምን እንስጠ ው እንጂ ጠ ላትነትን አናውርሰው ።
ለምነን ለምነን እንቢ ካላችሁ ፣
ከእውነት ይልቅ የዳንዴ ውሸት ከጣማችሁ፣
ለሃገር ሳይሆን ለግለሰብ ከቆማችሁ፣
የአማባ ገነኑ ደንገጡ ሮች ኩርኩማችን ያውላችሁ።
ደህና ሰንብት አበጀ
ተፈጥሮም: የራሱን: ሂደት: እድግቱን: እየጠ በቀ፣
ያልታሰበ: እየፈጠ ረ: ገና: በጉዞ: ላይ: ያለውን: በድንገት: እየነጠ ቀ።
ያልተጠ ራበት: እየገባ: የማያውቀውን: ቤት: እየከፈተ፣
ዛሬ: ገና: ድል: መታ: ጀግናውን: ይዞ: ተካተተ።
ምንድነው: ሞት? ወንድሞች: መ ተንፈስ: ማቆም: ሕ ይወት: ማጣት!!!!!
ከመ ሃል: ጠ ፍቶ: መ ቅረት: መ ሰወር: ለዘላለም: መ ረሳሳት?
እንዲያ: ከሆነስ: አልሰመረም ፣
በጭ ራሽ; ግቡን: አልመታም ።
እጁን: ቢይዘው: ብቻውን: አግኝቶት: ከመንገድ: ላይ፣
ስሙ ንስ: አይቀብረውም: ታሪኩ: ሕያው: ነው ከሞት በላይ።
እናም: አንቀበልም: ሞትህን: የሞ ተስ: ታሪክ: ያልሰራ፣
እኛ: አናወራም: መ ቀበርህን: የሚ ቀበር: በተግባሩ: የማይኮራ።
በምግባሩ: የማይተማመን: ባደረገው: ሁሉ: የሚ ያፍር ፣
በተናገረው: የሚ ጸጸት: አንገቱን: የሚያቀረቅር፣
ያንተ: የሚያኮራ: ነው: አበጀ: በሕይወት: ሳለህ: ሳንናግር: በሞትህ: ሳልስት: እንመ ስክር።
ለሕዝብ: መ ቆምን: መ ርጠ ህ: የግል: ጥቅምህን: ኌላ: ብለህ፣
ከላብ: አደሩ: አብረህ: ከአርሶ: አደሩ: ተቀላቅለህ ፣
እንደሌላው: ሳትመ ጻደቅ: እንዲህ: እኮ: ነበርኩ: ብለህ፣
በአላማህ: ሳትዋዥ ቅ: በእምነትህ: ሳትደራደር፣
ባልመ ሰለህ: ፍርድ: ላይ: ባለመ ስማማትህ: ሳታፍር።
ም ነው? ዛሬ: ታዲያ: ጔድ: አበጀ: ገና: ድፍርሱ: ሳይጠራ፣
የተንከራተትክበት: ሜዳ: አቀበት: አንተን: መ ሰል: ሳያፈራ፣
ወገብህ: ገና: ሳይጠ ና: መንገድ: የጎዳው: እግርህ: ሳያገግም ፣
በሩጫ : ላይ: እንዳለህ: በድንገት: እንዲህ: ታዘግም ።
በሰላሙ ም: በትግሉም: ሁሌ: ታጥቀህ: እንዳልነበር፣
ዛሬ: ትጥቅህን: ትፈታው: መንገድ: ጥለኸ ው: ትቀበር።
እኔ: አላምንም: ይኸንን: ለሰውም: እንዳትነግሩ፤
ሞቷል: ሲባል: የኖረ: ሰው: አለ: ሲባል: ልትቀብሩ?
አብረን: ስንኖር: እስከ: ዛሬ: ያላወቅሁት: ቅር: ያሰኘኝ፤
ኢትዮጵያዊነትህን: እንጂ: አማራ: መ ሆንክን: ሳትነግረኝ።
ደህና: ሰንብት: ኮሎኔል: አለማ የሁ: እንዳለቃ: ሰላምታ: ልስጥህ፣
ደህና: ክረም: ጔድ: አበጀ: እንደታጋይ: ልሰናበትህ፣
ለታጋይ: አያለቅሱማ: ይላሉና: እኔም: አላለቅስልህ፣
እንደጔደኛ: ሆኜ: ግን: መ ጎዳቴን: ልግለጽልህ።
ተኮላ: መ ኮንን
November 10th 2000
ለብርሃኑ ነጋ
ተኮላ መኮንን
ዳላስ ቴክሳስ
05/15/2006
የልጅነት ዘመ ን አንደዋዛ ሳይጫ ወቱበት እያለፈ፤
ሰኞ ማ ክሰኞ ሳይባል አስፋልት ላይ፤ እድሜ እንደ ቀልድ እየከነፈ።
በጊዜው የነበረ የትግል ግዳጅ ወጣ ትነትን እየበላ፤
ለግላጋ ጣቱን ለቃታ ሰጥቶ ፦ ለስላሳ እግሩን በፈንገስ እያቀላ።
«መ ዝሙር ዘፈኑን ተክቶት» ኮረዳ ማየት ቀርቶ፣
ባክስት ባጎት በወንድም ምትክ፦ ጔድ መባል ተተክቶ፣
አባት እናት ተረስተው ፦ቤት ንብረት ባገር ተሞልቴ፤
ትምሕርት ቤት በገባር ጎጆ ፦ ህክምናው በአኩምፓቸር ተቀይሮ፤
በእንጀራ ምትክ በቆሎ ተበልቶ፦ሆድ በበለስ ተወጥሮ።
ለቅንጦት ሲባል ተልባ፦ ለጉዝጔዝ ሲባል ሃምሊ ተበልቶ፣
ካልጋ ወርዶ ካንሶላ ቁራጭ ላይ ተኝቶ፣
ባልጠና ወገብ ዝናር ታጥቆ፦ በልጅነት ጫንቃ ብረት አንግቶ።
ገና ከትግሉ ሲቀላቀል መስዋእትነቱን ተቀብ ሎ፣
ኑዛዜውን ለጔዶቹ ትግሉን ቀጥሉ ብቻ ብሎ ።
አገር ለራስ ቅንጦ ት ሳይሆን፦ ለሕዝብ እኩልነት መ ሆኑን አምኖ፤
ላብ አደሩን ነፃ ሊያወጣ ከአፈር ገፊው እኩል አፈር ዘግኖ፤
ከቤት ከቀየው እርቆ በዱር በገደል ፈንኖ።
ለዓላማ መሞት ክብር እንደሆነ ያመነ፦ እህት ወንድሙን ለትግሉ የገበረ፣
ካላመነበት የሚናገር፦ የተሰለፈበት ድርጅት ሲዛነፍ እንኴን፦
አንገቱን ያልሰበረ፣
ትግል ብሎ ህይወቱን እንዳልገፋ በትግሉ እንዳላደገ፤ ዛሬ ዘብ ጥያ ተወረወረ????
ሲሆን ምስጋና ምርቃት እውቅና ይገባው ነበረ።
ወጣቱ ታጋይ ብርሃኑ ነጋ እግሩ በእግረ ሙቅ ታሰረ፣
እጁ በፌሮ አበጠ ዓይኑ በጨለማ ታወረ።
እኔ እንደትላንቱ «ጔድ »አይደለሁ አቌምህን አልገመግም ፥
ካጠገብህ አልተሰለፍኩ ብሩሕ ጨረር ዛሬ አላልም ።
እኔ እንዳንተ «ልብ ም »የለኝ ሁሉን ነገር ትቼዋለሁ ፣
ታገሉ ብየም አልሰብክ ዳግም በስደት ተወጥሬአለሁ ፣
በግለኝነት ተሳስሬ በሕይወት እጣ ወድቄአለሁ፣
ያም ቢባል የቆረጡ ትን ግን አደንቃለሁ፣
ለክቡር ሥራቸው ም እሰግዳለሁ፣
ብርሃኑ ምንም ባቌምህ ባልስማማ ቆራጥንትህን ግን አወድሳለሁ ።
ዝም በል ወንድሜ
ትላንት ወንጀል የነበር ፥ዛሬ ገድል ሆኖ አይተናል፣
«አንጃ» ብ ለን ዛሬ አንጠራህ፦ ተጋዳይ መ ሆንክን አም ነናል፣
በገንዘብ አልታለልክ፦ ኖሮህም ስትፋለም አስተው ለናል።
ድሮስ መች ታማ ህ በድህነት፦ በወጣ ትነትህ እንጂ፣
ጔዶችህን ጠ ላት ሳይሆን ሲያስተኛቸው የወገን ፈንጂ፤
ድሮስ መች ታሰርክ በሙ ስና፥ ተናገረ ተቃወመ ብ ለው ፣
ድክመ ታቸው ን አወላግደው ፥ አላማ ቸው ን ደበላልቀው ፣
ነፍጠኛ አይሉህ ነገር ዛሬ፥ የትላንቶቹም አልቀናቸው ፣
እዉ ነት እየፈካ እንደመ ጣ እነዚህንም አይለቃቸው ፣
ተዋግተህ ጦርነት ያክትም ደም ማ ፍሰስ ይብቃ ባልካቸው ፣
ከትግራይ አባረው ህ መ ርካቶ ብ ትጠ ብቃቸው ፣
የመ ብ ት ነገር ብታነሳ በኩልነት ብትገጥማ ቸው ፣
ዲሞክራሲው ተረሳና እስራት ሆነ ምላሻቸው፣
አባይ ኢ ትዮጵያ ያሉበት እሬት ሆነ ምላሳቸው ፣
ሕ ዝ ብ ሆነ ፈራጁ ም ርጫ ሆነ ጠ ላታቸው ።
ብ ርሃኑ የትላንት ወጣ ት ብ ርሃኑ ያሁንም ታጋይ፣
በርታ እንጂI አንሞት እኛ፦ መፈታትህን ገና ሳናይ።
አንሞት አንሞት አንሞት
አትሞት ያመንክበትን ፈጽመህ ሕልምህን እውን ሳታደግ፤
አምልጠህ የለ ከድርጅት ግርፊያ እስራት እንኴን ከዚህ ከትላንቱ ፋሽስት ደርግ።
አትሞት እኛም አንሞት
የብርሀኑን መጸሀፍ ባናነብም ተመሳሳይ ታሪክ አለውና ያሳደዱህና ሊገድሉህ የነበሩት የቀድሞ የኢትዮጵያ አየር ወለድና ከድተው ከኢሕ አፓ ተቀላቅለው ገዳይ ቡድን (እስኳድ) የነበሩት ዳላስ እንደሚገኙ ከዚህ በላይ መረጃ የሚያስፈልገው አይመስለንም።
እርሶስ ምን ይላሉ?
No comments:
Post a Comment