ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።
የኢትዮጵያ ሕዝብ የልቡን የሚገልጽበት እድል ሲያገኝ የኢሕአፓን እውነተኛ ታሪክና መስዋእትነትን ይናገራል!
ከዚህ በላይ ያለውን ጥቅስ የወሰድነው ከአሲምባ ድኅረገጽ ሲሆን እኛ በጥያቄ ምልክት የምናልፈው ይሆናል፤ አንባቢዎቻችን ደግሞ የእራሳቸውን ግንዛቤ ይወስዳሉ እንላለን።ሃማ ቱማ የተባሉት የገጻችን ተከታታይ የታወቁ የኢሕአፓ ገጣሚና ቀንደኛ ዘካሪ ለኛ የሚጥፉት ይኖር ይሆን? ጥሁፋችንን አምነው ነው ዝምታን የመረጡት ወይስ ብዕራቸው ነጠፈ?
እኛ ተኩላው በገጹ ከሚያለቃቅስ እውነቱን ይዞ በብዕሩ ቢሟገት፣ ገጻችን እርሱንና ቢጤዎቹን ያለ አድሎ እንደምታስተናግድ ዛሬም መልሳ ታረጋግጣለች። በሀሳብ መለያየትና መሞገት አዋቂነት ነው። ሲነገረን የኖርነው ድርጅቱ ለሀሳብ ነጻነትና ለውይይት ያመቸ ነበር የተባልነው፣ ዛሬ ግን የተቃራኒ አቋም የሚጓዝ ጭፍንና ለሥልጣን ብቻ ያነጣጣረ ነው። ኢሕአፓ ሥልጣን ያዘ ማለት መንግሥቱ ኃ/ማሪያምን መመለስ ማለት ነው። ከላይ ወደጀመርነው ጥቅስ ስንመለስ በሀገር ውስጥ ያለውን ዘለን በምዕራቡ አለም ያለው ኢትዮጵያዊ ያለምንም ሥጋት ስለ ኢሕአፓ በስፋት እየደለቀው እንደሆነ ገጻችን የመረጃ ምሳሌ ነው። የእኛ ገጽ በሚገባ ማንነታችሁን አስቀምጦ ይገኛል።
በኮምኒዝም እምነትና አላማ በወጣትነት እድሜው ጭንቅላቱን በርዛችሁ፣ ከወላጆቹ ነጥላችሁ፣ ቡቃያ እድሜውን አበላሽታችሁ፣ ለሰቆቃ ዳርጋችሁ፣ በየአደባባዩ አስረግፋችሁ፣ ሌላውንም ከቄው አስኮብልላችሁ፣ ለናንተ ሎሌ አድርጋችሁ፣ ጋሻና መከታ ሽፋናችሁ ሆኖ እንዲሰዋ ያደረጋችሁ፣ እናንተ ምርጥ በልታችሁና ጠጥታችሁ እርሱንና እርሷን በጥሬ አውላችሁ ያሳደራችሁ፣ ያለፍላጎቷ የደፈራችሁ፣ ጥያቄ ያቀረበን አንጃ እያላችሁ መራራ ስቃይ ብሎም ሕይወቱን የቀጫችሁ፣ የጫካ ንጉሥ የነበራችሁ፣ ኸረ እናንተን ማን ብለን እንጥራችሁ? የትኛው ነው የናንተ ጀብዱ የሚወሳላችሁ? የትኛው ታሪክና መስዋዕት ነው የሚዘከርላችሁ? ኸረ እናንተን ምን ብለን ከምን እንጀምርላችሁ? ዛሬም የትላንት ኮሚኒስቶች የሀይማኖት ካባ ለባሾች፣ የፈጸማችሁት በደል ጸጽቶ በንስሀ ያልተመለሳችሁ፣ አሁንም ካለፈው ያልተማራችሁ፣ ዛሬም ለሥልጣን የቋመጣችሁ፣ በካህናት መካከል ሳይቀር ገብታችሁ የከፋፈላችሁ፣ ከደርግ ሸሽታችሁ በገዳም ተሰውራችሁ፣ የተቀበላችሁትን ክህነት ያላከበራችሁ፣ ዛሬም ለሥልጣን ጥመኛ ሀይማኖት ከፋፋይ ቂመኛ፣ሰርጎ ገብ ሸረኛ፣በምዕራቡም ሀገር በሽታኛ፣ ደብር በጥባጭ ሱሰኛ፣ እምነት የሌለው መጋኛ፣ ኸረ እናንተን ማን ብለን እንጥራችሁ? ምንስ ማዕጸን አወጣችሁ፣ ከአንድ ትውልድ አልፋችሁ አሁን ደግሞ ሁለተኛ ትውልድ እንዲጠፋ የቆማችሁ፣ የሀገር ጥፋት ነው ወይስ የትውልድ ነቀርሳ፣ መርግም ናችሁ ወይስ አበሳ? ኸረ ማን እንበላችሁ? ዘመንም ሆነ እድሜ ያለወጣችሁ፣ የሰው ሰቆቃ የመይሰማችሁ፣ ጨካኝና እርጉም የሆናችሁ፣ ኸረ ምን እንበላችሁ? እውነትና ሀቅ የማትቀበሉ እናንተ ማናችሁ? ጊዜም የማይሽረው ልክፍት የያዛችሁ፣ በሽታችሁን ሲነግሯችሁ የምትክዱ፣ የሀሰት ስም የምትለጥፉ፣ሴሬኛ ትውልድ አንገት የምታስደፉ፣ኸረ እናንተ እነማን ናችሁ? ማን ብለን እንጥራችሁ? ለቅጣትና ለመከራ የተፈጠራችሁ፣ አምላካችን ይቅር ይበላችሁ፣ ከአጽራረ ቤተክርስትያን ሕይወት ያውጣችሁ፣ መልካሙን ልቦና ይስጣችሁ፣ ለንስሀ ሞት ያብቃችሁ።
እርሶስ ምን ይላሉ?
2 comments:
ዳላስ ኢኦቲሲ ዛሬ ገና አንጀቴን ቅቤ አጠጣሽልኝ። ጎሽ። እኔ ግን ይሔ የሚመለከተው ኢሀፓ የነበሩትን ብቻ ሳይሆን ሙሉውን ያንን ትውልድ በተለይም አገር ቤት እያሉ በእርዮት አለም ልዩነትም ይሁን በዘመንተኝነት ወይም በሌላ ከቤተክርስትያን ጋር ሆድና ጀርባ ሆኖ ኖሮ ዛሬ በሀገረና በዘመነ የልብ ልብ የቤተክርስትያን ሊቅና አዛዥ የሆነውን ጨካኝ ጨዋ ሁላ ነው እላለው። ወደ እግዚአብሄር መመለስ ጥሩ ነው ገደብን ማወቅ ግን ለምህረት ነው። የተዋህዶ ልጅ ነኝ
We request your patience while fixing the security compromise on this page.
Thanks
Post a Comment