Tuesday, January 4, 2011

የህን መለክት እፊት ላይ እንዲለጥፉልን እንማጠናለን።

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!

ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።


Anonymous Anonymous said...

ጸሃይ ጽድቅ ተተባለ ግለሰብ ካሁን ቀደም በኢትዮጵያ ውስጥ የድሮው የደርጉ የግፍ ዝነኛ የነበረው የ አምሳለቃ ለገሰ አስፋው የግል አንጋች ወታደር የነበረ ብዙ ህጻን ልጃገረዶችን ክናታቸው ጉያ ውስጥ እየጠለፈ ለአለቃውና ለግብረ አበሮቹ ከማቅረብም ሌላ እናቶቻቸውን
በግድ “Rape” ያደርግ የነበር። ብዙ አቅመ አዳም ያልደረሱ ልጆች በመትረየስ የፈጀና ያስፈጀ የደርግ ወታደር እንዴት እንዳመለጠ ሳይታወቅ ወደ አሜሪካ መጥቶ አሁን የቅዱስ ሚካኤልን
ቤተክርስቲያን ከከሰሱት ውስጥ አንዱ መሆኑን የሚያውቁ፤ሰሞኑን በነበረው የሟችቱን ወ/ሮ ሃዘን ለመካፈል የተሰበሰቡትን ሃዘንተኞች ሳይፈራና ሳያከብር በወንድማችን በ አቶ አበበ ላይ የለመደውን አደጋ ላይ የመጣል ተንኮል በማናለብኝነት ለጓደኞቹ ለማህበር ቅዱስን ሲያስተምር ማምሸቱን ሰምተናል። በጣም የሚገርመው! ሃዘን ላይ የተቀመጡትን አዛኞች እንኳ ሳይፈራ አካኪ ዘራፍ ሲል አብረውት የነበሩት ማህበር ቅዱሳናት ሲያወድሱትና ሲያደፋፍሩት ማምሸታቸውን የተመለከቱ ሁሉ እየታዘቡ ምን ቤት ነው የመጣነው እያሉ ውልቅ ውልቅ እያሉ መሄዳቸው ታውቋል።
ይህ በብዙ ኢትዮጵያውያን ደም የታጠበ ፍርድ ሸንጎ እንደ አለቆቹ መቅረብ ሲገባው እንዴት አምልጦ አሜሪካ እንደገባና እየደጋገመም ወደ አዲስ አበባ ሲመላለስ በስልጣን ላይ ያለው መንግስት እንዴት እንዳልያዘው ባይገባንም! በኢትዮጵያዊነታችን የወንድሞቻችንን፣
የእህቶቻችንን፤ያባቶቻችንን፤ የናቶቻችንንና የጓደኞቻንን ደም በከንቱ ፈሶ እንዳይቀር ማድረግ መብታችን ስለሆነ! የዚህኑ የደርግ ወታደር ጸሃይ ጽድቅን ቢቻል የድሮ በዩኒፎርም ያለ ፎቶግራፍ ባይቻልም አሁን ያለ ፎቶግራፍ “ Name and Shame”
http://www.march4freedom.org/warcriminalsupporters/register.php በሚለው ብታወጡልን እኛም በበኩላችን ለሚታወቁት ጋዜጦች ሁሉ አባዝተን በዚሁ ግለሰብ (አናት፤ አባት፤ እህት፤ ወንድም፤ልጅ፤አጎት አክስት፤ ጎረቤት) የተገደለበት፤ ራፐ የተደረበበት፤ የታሰረበትን ሁሉ ፈልገን ወደ ፍርድ ሸንጎ ለማቅረብ እንዲቻለን እንድትተባበሩን ይህን መልእክት እናስተላልፋለን።
ሰሞኑንም አዲስ ብሎግ ከፍተን የሄን ግለ ሰብ ብቻ ሳይሆን ብዙ የሱ አይነት መታሰርና መገደልም ሲገባቸው አሁን ስልጣን ላይ ባለው የኢትዮጵያ መንግስት ወደ አሜሪካና አውሮፓ ሸሽተው እንዲኖሩ ዲ.ቪ እየገዛ የላካቸው ብዙ ስላሉ፤ እንሱን እየተከታተልን አንድ ምስክር እስካለን ድረስ በፍርድ ቤት የአሜሪካንም ሆነ የአውሮፓን ነዋሪነት አስፍቀን ቢቻል ማሳሰር ባይቻል ካገር ማባረር መብታችን መሆኑንና ለዚሁም የተቋቋመ ብዙ ድርጂት ስላለ የምንፈልገውን
እርዳታ ሁሉ በቀላሉ ማግኘት ስለምንችል፤ልትተባበሩን የምትፈልጉ ሁሉ በዙሁ በዳላስ ኢኦትሲ ብሎግ ድጋፋችሁንና አሳባችሁን ብትለግሱን በጣም ደስ ይለናል። ሰሞኑን እያከታተልን የደረስንበትን እናስታውቃችኋለን። የዳላስ ኢኦቲሲ ደራሲወችንም እባካችሁ የህን መለክት እፊት ላይ እንዲለጥፉልን እንማጠናለን።
ጥላቶቻችንና ተንኮል አሳቢዎች ሁሉ እንዲጠፉልንና ሚካኤል የሰይፍ ቁጣ እንዲያሳይልን
እንለምናለን።
አሚን።
January 3, 2011 8:12 AM

1 comment:

Anonymous said...

የአይጥ ምስክሯ ድንቢጥ!
ለአሲምባው ደመላሽ መልስ።
አሁን የምትለኝ አቶ ተኮላ ወደ አሲምባ የመጣው መንግስቱ ሃይለማርያምን ተቃውሞ ነው?
ሰው አንዳይስቅብህ። እኔ አቶ ተኮላ ጋር ቅራኔ የነበረኝ ቤተክርስቲያን ስለከሰሰ እንጅ ወታደር ስለነበረ አለነበረም።አንተም ቤተክርስቲያን የሚከስ የምትደግፍ ከሆነ ከከሳሾቹ ውስጥ አንተም አለህበት ማለት ነው። ልጠይቅህም የምፈልገው ቤተክርስቲያን መክሰስ ምን ለማትረፍ ነው?
የሃይማኖቱ ጥላቻ! ወይስ ከቤተክርስቲያኑ ካሳ ለመብላት?አሁን ወደ ዋናው ድንቢጥነት እንመለስና፡ አንተው የረዳህ መስሎህ አጋለጥከው። የአየር ወለድ ወታደሮች፤ በእድሜያቸው የገፉ በወታደርነት የሰለጠኑ እንደመሆናቸው መጠን እንኳን አንድ ወታደር ቀርቶ በስሜት የተገፋፋ መረን (Mob) የማይፈጽመውን መሳርያ ባልያዙ ገና ሙሉ አቅመ አዳም ባልደረሱ የአየር ሃይል ካዴቶች ላይ የፈጸሙት ድብደባና ባዶ ካምፕ በመትረየስና በታንክ መክበብ ሙያ መስሏቸው በጊዜው የነበረውን የእንዳልካቸው መኮንንን መንግስት ለመደገፍና ንቅናቄውን ለማፍረስ ያቀዱት ተግባር እንዳልሆነ ሲያውቁና እውነተኛው የኢትዮጵያ ወታደር ሲጥጋቸው የለበሱትን መለዮና ያደረጉትን ጫማ ሳይቀር ወርውረው የሴት ልብስና ለምድ ለብሰው ባዶ እግራቸውን ነፍሴ አውጭኝ ያሉ ናቸው። በዚያን ጊዜ መንግስቱ ሃይለ ማርያም የሚባልም ስም እንዳልነበረም አረጋግጥልሃለሁ። በዚያን
ሰአት ገዥውም ጃነሆይ ጠቅላይ ሚኒስተሩም እንዳልካቸው መኮንን ነበሩ። ንደዚህ ያለውን ሰው ነው እንደዝነኛ አድርገህ አሲምባ መጥቶ መንግስቱን ተዋጋ የምትለን። መንግስቱ ሃይለ ማርያም ህጻናትን አልገደለም ህጻናትን ያስፈጀ ኢህአፓ ነው። አትሳሳት መንግስቱ ሃይለ ማርያምን መደገፌ አይደለም እውነቱን ለመናገር ነው። የሃይሌ ፊዳን አቋም ተመቃዋሚ በማስመሰል እንድ የማይረባ ያልተማረ የቀበሌ ዘበኛ ገድላችሁ የሰፈሩን ህጻናት እንዲረሸኑ ማድረግ ተገቢ ነበረን? ወይስ ጠጅ ቤት ገብቶ መፎከርና መጥፋት ምን ለማትረፍ ነበር ድሃ ለማሳሰርና ለማሰቃየት ካልሆነ በስተቀር። ተኮላ እናንተ ጋ አሲምባ መምጣቱ ነፍሱን ለማዳን እንጅ መንግስቱን ለመቃወም ነበር እንዴ?።
እስቲ ምን ምን ተግባር ምን ጀብዱ የሚያሰኘው ነገር መስራቱን በሚቀጥለው ጽሁፍህ አብራራልን። እሱን የሚያክል ወታደር በእድሜም ሆነ ባሰለጣጠን ከማይወዳደሩት ህጻናት ስር ወድቆ በናንተ መመራቱ ውርደትን እንጅ ጀብዱነትን መስራት ከሆነ ይሁንልህ፤ በርታ ስሙን አጥፋለት።
በ እኔ አስተያየት አንድ ወታደር ለቆመበት እምነቱ መጋደልና ማሸነፍ አለበለዚያም መሞት እንጅ እንደናንተ ያሉ እንኳን ፖለቲካ ቀርቶ አቋም እንኳ የሌለው የኢትዮጵያን ህጻናት ማስጨረስና አገር ለማስከበር የዘመተው ወታደር ስንቅ ላይ ጠርሙስ ፈጭቶ የሚከት ደካማ ወጠጢወች ውስጥ መደበቅ አሳፋሪና ገመና አጋላጭ ነው።
እንደዚህ ያለ ግለ ሰብ ጋር መነጋገር ቀርቶ እውቀዋለሁ ማለት እንኳ አሳፋሪ ነው። የዚህ አይነቱ ግለ ሰብ እንኳን ቤተ ክርስቲያን መክሰስ ቀርቶ ሌላም ብዙ ነገር ቢያደርግ የሚያስገርም አይደለም።
በሌላው በኩል ክርስቲያን ለመምሰል ታላቁ ገታችንን መጥቀስህ ምና ይባላል። በተአምሩ ያማታምን ከሆነ ምን የሱን ስም አስጠራህ። አበበን ጌታ መላኩን በ ፓሊስ ምስል የላከለት መልካም አገልጋዩ ስለሆነ ነው። ለ እንዳንተ አይነቱ ቤተክርስቲያን ከሳሽና የሰው ሃጢአት በየ
ታክሲው ላይ በታኝ መልአኩን ልኮ ከመጥፎ ተግባርህ እንድትመለስ ከማድረግ ይልቅ ተገቢህን ይልክልሃል። መልእክቱንም ባይናችን አይተናል። አንተና ጓደኞችህ እነተኮላ አወን በእግዚብሄር
አታምኑም፤ አንዴ ማርክሲስት ሲመች ክርስቲያን በሊላ ጊዜ የትግራይ ነጻ አውጭ እያላችሁ ባልኖራችሁ ነበር። ቤተክርስቲያን መክሰስ ምን ለማትረፍ ነው? ቤተክርስቲያን መበጥበጥ፤ ቀሳውስት መሳደብን ምን አመጣው? ከቀሳውስት አልፎ ጳጳስ መሳደብ “ አገር ጥሎ የሸሸ
እያላችሁ “ መዝለፍ ማንን ለማስደሰት ነው?
እውነት አእምሮ ካለህ! አስበው ለምን መልአኩን ላከለት? ለምን መጥፎ ተግባር ከመፈጸም አዳነው? ለምን ያሰበውን በሚፈጽምበት ጊዜ ሊደርስበት ይችል ከነበረው አደጋ ሁሉ አዳነው?
መልሰህ መላልሰህ አስበው።
ዮናስን ለምን አሳ ነባሪ ላከለት? እግዚአብሄር ለሚወደውና ለሚያገለግለው ብዙ ክጥፋት መዳኛ መንገድ ይከፍትለታል።
ፖሊስዋ ባትላክለትኖሮ አንዷን (Drug addict) አግኝቶ ግብረ ስጋ ቢፈጽም፤
1፤- የአምላኩን ተእዛዝ አፈረሰ ማለት ነው ምክንያቱም ዝሙት አሰበ ከማለት ይልቅ ዝሙት ፈጸመ ማለት ነው።
2፤- ከዚሁ ዝሙት ጋር የሚመጣው ኤይድስ በሽታ ቢይዘው ምናልባት ያልተጠራጠረችውን ባለቤቱን የልጆቹን እናት በከለ ማለት ነው።
3፤- ይህን ዝሙት በሚፈጽምበት ጊዜ ሊደርሱ ከሚችሉ አደጋዎች አንዱ የሴተኛ አዳሪዋ በላቤት (Pimp) ሊዘርፈው ይችላል በዚያውም አኳያ ሊገድለው የችላል፤ባይገድለውም አንድ አካሉንም የማጣት አደጋ ሊገጥመው ይችላል። ከዚህ ሁሉ አደጋና ሃጢአት ውስጥ ከመግባቱ በፊት በቀላሉ ምናልባት በገንዘብ ክፍያና
በማስጠንቀቂያ ብቻ መመለስ ለ እንዳንት ላለው በሃጢአት ለተዋጠ ምንም አይመስለው ይሆናል። በእግዚአብሄር ማመንና እግዚብሔርን ማገልገል ግን ይህን አይነት ውጤት ያመጣልና አንተም ክስህን ትተህ አንዱ ጓደኛችሁ እንዳለው “እባካችሁ ሃጢአት በዛ” ብላችሁ ፊታችሁን ወደ አምላካችሁ አዙራችሁ ጸልዩና ምን አይነት መልካም ውጤት አንደምታገኙ ታያላችሁ።
በዛውም አገር ቤት ላስጨረሳችኋቸው ልጆች አምላክን ተንበርክካችሁ ይቅር በለን ብትሉ መሃሪው ፈጣሪያችን ይቀር ይላችኋልና።
አምላካችን ሆይ! ልቦናችንን ወደ ደጉ ተግባር ምራን! እነሱንም እባክህ የሚሰሩትን አያውቁምና ይቅር በላቸው እባክህ፤
አሜን!