Friday, June 10, 2011

እንደ ኤሊዋ በጀርባ ወድቆ

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!

ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።


እንደ ኤሊዋ በጀርባ ወድቆ

Watch USCIS Director Alejandro Mayorkas and colleagues from U.S. Immigration and Customs Enforcement, Department of Justice, the Federal Trade Commission and the Texas Attorney General announce the launch of a multi-agency initiative to combat immigration services scams through enforcement, education and continued collaboration with federal, state and local government partners. To find out more go towww.uscis.gov/avoidscams

ይህ ከዚህ በላይ የተጠቀሰው አንዳንድ በወገኖቻችን ውስጥ ሲርመሰመሱ የኖሩትን የገዛ ጉዶቻችንን ለማሳሰብና ወገኖቻችንን ከሕግ ወጥ ድርጊት ተባባሪነት ስሀተት ለማገናዘቢያ ቢጠቅም በማለት ያለንን ለመወርወር ያህል ያዳዳንን በቅንነት እንጂ በሌላ መልኩ እንዳይወሰድባት ገጻችን ታበክራለች።

የተወደዳችሁ የገጻችን ተከታታዮችና ተሳታፊዎች እንደምን ከርማችኃል? እኛና እናንተን ዳግም በፈቃዱ በዚህች ገጽ እንድንገናኝ ለፈቀደ ለእርሱ ለልዑል እግዚአብሔር ፍጹም የከበረና ንጹህ የሆነ ታላቅ ክብር ምስጋና ይሁንልን። አሜን።

ጁን 21 መጥቶ ከዳላስ የወጣንበትን አንደኛ አመት ለማሰብ እየተዘጋጀን በዋዜማው ምሽት የመሰናበቻ ጥሁፍ ወርውረን እናከትማለን ብለን ከጅለን የነበረውን በናንተ ተሳትፎ ለዚህ በቅተናል። በወቅቱ በቦኒ ምንያት በቢፒ ከባሕር ወለል በታች የነዳጅና ጋዝ ማምረቻ ላይ በደረሰው ፣  በወቅቱ የ11 ሰራተኞች ሰለባ ፣ ከዚህም በላይ እሳቱን ለማጥፋት፣ የጋዝና የዘይት ፍሳሹን ለመግታትና በቁጥጥር ስር ለማድረግ፣ የተፈጠረውን የአካባቢ ብክለት ፈጽሞ ማጥፋት ባይቻልም በቁጥጥር ስር አድርጎ እራሱን እንዲያድስና ከአደጋነት ውጪ ሆኖ ለአካባቢው ሕይወት ተቀባይነት በሚኖረው ደረጃ ማድረስ፣ በእክሉ ምክንያት ሕይወታቸው የተዛበውን የአካባቢው ተጠቃሚዎችን በተመለከተ አስፈላጊውን እገዛ ማድረግ፣ ለአካባቢው አስፈላጊውን መልሶ ማቋቋም ማድረግ የመሳሰሉትን ተግባራት ወደ ኃላ ዞረን እየገመገምን የሚቀጥለውን ቀሪውን እቅድ መተግበሩ ላይ አካባቢው ይንቀሳቀሳል። እኛም እንጀራ ነውና በአጋርነት የሚጠበቅብንን እየወረወርን እንገኛለን።

እናንተም ከዳላስ ቅዱስ ሚካኤል ደብር ጋር ጸንታችሁ በመቆየት ለደብራችሁ የሚጠበቅባችሁን እያደረጋችሁ በመበርታት ለዚህ ላበቃችሁ ለእርሱ ክብር ምስጋና ይሁንልን። አሜን።  አሁንም ጽናቱን ሰጥቶ ለበረከቱ ያብቃችሁ። ለዚህ ላልታደሉትም መክሮና አስተምሮ ይመልሳቸው። አሁን ደብራችሁ ከመቼውም በላይ ስላምና ፍቅር እየነገሰበት ያለ ፣ ብዙዎች በመጸጸት እየተመለሱ መሆናቸውንና ለበረከቱም ለመሳተፍ እራሳቸውን እያዘጋጁ መሆናቸውን ከሚደርሱን መረጃዎች ብቻ ሳይሆን ራሳችሁን ዋቢ በማድረግ የምናስረግጣችሁ ቢኖር ፤ ላለፈው 2ጊዜ ተጠርቶ በነበረው አመታዊ የአባላት ስብሰባ ላይ ሳይሳተፍ የቀረው አባላት ቁጥር ‘ዝምታም መልስ ነው“ ፣ ከነማን ጋር ነው የምንሰበሰብ በማለት የሰጡትን ባለፈው አስነብበነዋል። ምንም እንኳን አብዛኛው አባላት ባሉት አመራሮች ሙሉ እምነት በመስጠቱ በሕጉ መሰረት እንዲፈጸም በማድረጉ ፣ የተገኙት ደግሞ በተቃራኒው ጎዳና የተሰለፉ ሆነው ቢገኙም በዚያ መልኩ ሳይፈረጁ ፈጣሪ ልቦናቸውን ይመልስልንና መልካሙን መንገድ ያሳይልን እንላለን። ዘግይቶ እንደደረሰን 10 የማይሞሉ ግለሰቦች አቤቱታ ለአስተዳደሩ ማስገባታቸውን ነው። እነዚህ ግለሰቦች ቅሬታቸው በሚገባ ተስተናግዶ መሰመር እንዲይዝላቸው ገጻችን ስትጠይቅ፣ አስተዳደሩም ሙሉ ጥያቄቸውን በሚገባ ተቀብሎ ያከሄደውን ስብሰባና ውሳኔ ለመላ ምዕመን ትምህርትን ይሰጥ ዘንድ በማስታወቂያ ሠሌዳ ላይ እንዳለ እንዲለጠፍ ገጻችን በትህትና ትጠይቃለች?

ከዚሁ ደብር ሳንርቅ ዳላስ በኖርንበት ወቅት አንደኛው የደብሩ ካሕን “ እኔ ካለ ቅዱስ ቁርባን አላጋባም ፣ ዝሙትን ማስፋፋት ነው“ ያሉንና በወቅቱ የእርሳቸውን ሀሳብ በአደባባይ ሲያስተጋቡ ከነበሩት ቀደምት ፊት አውራሪ ሰሞኑን ልጁን በእኚው ቄስ ነኝ በሚሉት ግለሰብ አማካኝነት ያለ ቅዱስ ቁርባን ጋብቻን በሌላ ስፍራ ሲሰጡ በወቅቱ ከተገኙት ወዳጆቻችን ደርሶናል። እኜህ አደራ የተሰጣቸውን ምዕመን ባትሪዬን ጨርሻለሁ ብለው ከቅዱስ ሚካኤል ዐውደ ምህረት ላይ ጥለው ሲኮበልሉ ወይ ገዳም ገብተውም ሆነ በጾምና በጸሎት ያለቀባቸውን ባትሪ ሞልተው በመመለስ በትነው የተውትን መንጋ ሰብሳቤ እረኛ ይወጣቸው ይሆናል አሊያም ቅስናቸውን ይፈቱ ይሆናል ብለን ነበር። 2ቱም ግምታችን አልሰራም። ነገር ግን በሚያዘጋጁት በየጥቂት ወራት ጉባኤም ያለቀው ባትሪያቸው ተሞልቶና ታድሶ ላገልግሎት የጠፉትን ይሰበስብና ይጠብቃል ስንል እንግዲህ አመት ሞልቶታል። ፈጣሪ ሁለተኛ ትላንት በቅዱስ ሚካኤል ደብር ውስጥ ያሰሙት የነበረውን አንደበት ዛሬም እንዲጠብቁና ከዳግም ስህተት ምህረትን ሰጥቶ ፣ በአባትነት ስህተት ሳይሆን የግል ስህተት ብሎ ቆጥሮ ለንስሀ ያብቃቸው። ሀይማኖታችንም ከማያምኑ ተሳላቂዎችና ከጠላቶቿ ይጠብቅልን። አሜን።

ከዚህ ፈቀቅ ብንልም ከሰሞኑ ከደረሱን ጀባ ብለን ብንለይ በማለት የሚቀጥለውን በመወርወር ለዛሬ መቋጫ ያደረግነው ብዙ ነገር አለ። አንዳንዶች ከእስር ቤት ወጥተው ዛሬም እየበረገጉ ያሉ እንዳሉ ነው። ሌሎችም በእስር ላይ ያሉና ቀጣዮችም በራቸው እየተንኳኳ ያሉ ይገኛሉ። በኢንሹራንስ ፍሮድ፣ በሞርጌጅና በኢምግሬሽን ሕገወጥ ጥቅም ላይ ተሰማርተው የነበሩት መካከል ከውጪና በማረፊያ ቤት ያሉት ምንም ያደባባይ ሚስጥር ቤሆንም የእያንዳንዳቸውን ማንነት ከመግለጽ ለጊዜው ብንቆጠብም ፤ የሕጉ ሥርዐት መስመሩን መያዝ ስላለበትና በዚያው መቋጨት ስለሚገባው ነው። ከዚሁ ጋር በጠረቤዛ ስር ያለ ሙያ ስራ ፈቃድ የንግድ መደብሮችን ሁሉ ሲደልሉና ሕገ ወጥ ጥቅም ያጋበሱትን ቀዳዶችንም ያካትታል። የዳላስና ፎርትዎርዝ የኢትዮጵያን መረዳጃ ማህበርም እድሩን በተመለከተ ተራ መዝገቡን እየጠበቀ መሆኑን ከሚደርሱን ጥቆማዎች ለመረዳት በቅተናል። ቀደም ሲል መረዳጃው ማህበር ፈርሶ በነበረበት ወቅት በስሙ ሕገወጥ ስብሰባና ውሳኔ ብሎም ገንዘብ ስብስብ ሁሉ ሲደረግ እንደነበር ስንቶቻችሁ ታውቁ ነበር? በዚህ ገፅ መረጃውን ለመለጠፍ የኮፒ መብት ስለሌለን የዲኤፍ ደብልዩ ኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ብሎግ የለጠፉትን በዚህ አድራሻ ገብታችሁ አንቡት። http://www.dfwethiopiancommunity.blogspot.com/
እንግዲህ በወቅቱ ሰብሳቢና አሰባሳቢ፣ ከሳሽና አስከሳሽ፣ ጁሪና ዳኛ የነበራችሁ፣ ገንዘብ ሰብሳቢና ተካፋይ ካላችሁ ህሊናችሁን አስተካክላችሁ የወሰዳችሁትን መልሳችሁ የበደላችሁትን ካሳም ሆነ ይቅርታ ተቀብላችሁ ወደ ቅን መንገድ ትገቡ ዘንድ ዛሬም አልመሸም። ሌሎችም በሳህን ከመቶ ዶላር በላይ እየተከፈለላችሁ በመረዳጃው ማህበር ገንዘብ በመጋበዝ የተመገባችሁና የተሳተፋችሁ ሁሉ ንስሀ መግቢያችሁ ዛሬ ነው። መረዳጃው ሲቋቋም ለተቸገሩት ውገኖቻችንን መርጃ እንጂ ለዝና ያለውን ጥሪት በጥቂት ግለስቦች ጥቅም ሲባል መማለያ አልነበረም። በተለይም 4 ግለሰቦች ሕብረተሰባችን አንቱ ያላቸውና በመረዳጃው ማህበር ስም በየጊዜው ገንዘብ ከቻርቲ ድርጅት እየተቀበሉ የሚካፈሉት እነማን እንደሆኑ ታውቁታላችሁ። ገጻችን የነዚህን ግለሰቦች ስም በየጊዜው ስትወቅስ ከርማለች ዛሬ ህሊናቸውን መርምረው የበደሉትን ወገኖቻቸውን ይቅርታ ቢጠይቁ ፣ እኛም ብዕራችንን በገታን። ጉዳቱ ተፈጽሟል። ከውጤቱ ጋርም እየኖራችሁ ነው። እንዳይደገም ማድረግ እንጂ፣ እንዚህ በጥቅም ታውረው ከስህተት የወደቁትንና በዕድሜ የገፉትን ለሰሩት በደል ሕግ ይዳኛቸው በማለት ለመረዳጃው ማሕበርም ሆነ ለተጠቃሚው ሕብረተሰብ የሚጨምረው ሳንቲም የለምና የራሳችን የቤተሰብ ጉዳይ በማድረግ በአስቸኳይ ይቅር ለእግዜአብሔር መባባሉን ገጻችን ስታሳስብ፤ ይህን ሳያደርጉ ቀርተው ጉዳዩን ሕግ ከጨበጠው የሚዳኘው ከክልል እስከ ብሔራዊ ደረጃ ባሉ የሕግ አንቀጽ መሆኑንና ውጤቱ ሁላችንንም አንገት የሚያስደፋ ይሆናል። ከዚያም አልፎ ወደፊት ለወገኖቻችን እርዳታን ለሚያደርጉ ግለሰቦችና ድርጅቶችም አሉታን ይፈጥራል በማለት ገጻችን ትሰጋለች።

ውድ ወገኖች፣ ዳላስ በነበርንበት ወቅትና ከወገን ለመደባለቅ በምናጠናበት ጊዜ ያየነው ቢኖር ብዙ ችግረኛ መኖሩንና መረዳጃው ማህበር አንድም ሲረዳ አለማስተዋላችንን እንጂ ወደ ቅዱስ ሚካኤል ደብር በማምጣት ግን ንዋይ ሲለመንላቸው ከነበሩት ውስጥ በአሀዝ ለመቀመር ቀርቶ አደረገ ተብሎ ለናሙና የሚበቃም አይደለም። አንዳንዶች በምግባራቸው ሲኮነኑና በተሰጣቸው አደራም ሆነ በቡድን ተደራጅተው ሳይመረጡ ፣ በወገኖቻችን ችግር መጠቀሚያና የኑሮ ምንጭ ማስገኛ በማድረግ ክቡር ስምን ከማስጠቀብ ይልቅ ለግል ጥቅም ሲባል በሌላው ወገን ላይ ጉዳትን ማድረግ ከሞራል ተጠያቂነት አልፎ የሕግንም ጥያቄ ያስከትላል። ከዚያ በላይ የኮሚኒቲውንም ንፁህ አባል የሆነውን ሁሉ አሉታን ያመጣበታል። ለዋቢነት ለመጥቀስም ባለፈው አመት በሜይ 2 ዕለተ ሰንበት በዳላስ ቅዱስ ሚካኤል ደብር ውስጥ ሁካታን የፈጠሩትና ይህንኑም ምስል ቀርጸው ያራቡትን ግለስቦች ጨምሮ የፈጸሙብን በደል ከሀይማኖት አልፎ ማንኛውንም የኢትዮጵያ ትውልድ ያለውንና ኢትዮጵያዊ እንዲሁም የኢትዮጵያዊያንን ወዳጆች ጭምር አንገት ያስደፋና አስነዋሪ ምግባር ነው። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ክርስትና ዶክተሪን ከየት ቦታ የዚህን አይነት ምግባር እንኳን ሊያስተምር አይደለም ፣ ድርጊቱን እውቅና የሚያሳይበትን ለማወቅ ባደረግነው ጥናት ወይንም ላቀረብነው ጥያቄ ከማንኛቸውም ምሁራን አባቶች ልንጨብጥ ባለመቻላችን ድርጊቱ በሚገባ መወገዝ ብቻ ሳይሆን አድራጊዎቹንም በመለየት ቤተክርስትያኗ መስመር የማሲያዝ ግዴታ አለባት።

ቀደም ሲል መረዳጃ ማህበሩን ከመሰርቱት መኃል ብቅብቅ ያሉ እንዳሉ ብንሰማም በ80ዎቹ ውስጥ እንደነበረው ወደ ቀድሞ የኢትዮጵያ ተወላጆች የነበራቸውን የክብር ስም ያስመልሳሉ የሚል እምነትን እያሳደረ ይገኛል። በትግል የወረደው የቀድሞ የመረዳጃው ማህበር አመራር አመጸኛነቱን በገሀድ ያስመሰከረው ላለመውረድ ያደረገው ስርዐት አልባነቱና በጉልበት የስራ ዘመኑን በማራዘም፣ መረጃዎችን ማጥፋትና አለ ሲባል የነበረውን ንዋይ አሟጦ መልቀቅን ነበር። በየትኛውም መልኩ በበቁ የውጪ መርማሪዎች የሂሳብ መዝገቡ ተመርምሮ የማያውቀው፣ ዛሬ ጉዱ እየወጣ ላደባባይ በመብቃት ላይ ነው። ባዶ መዝገብ የተረከበውም አዲሱ አመራር ለወገኖቹ ቅንነትን ለማድረግ ሲል የለመዱት የኢትዮጵያ ቀን ምንም ቀኑ ቢያልፍ ለማክበር በማቀድ የዝግጅት ኮሚቴ ለማቋቋም ባለፈው እሁድ ከሰአት በኃላ በጠራው ስብሰባ ላይ የታሰበው ኮሚቴ መመስረቱን አብሮ የደረሰን ዜና ነበር። በዚህ ስብሰባ ላይ ከተነሱት ጥያቄዎች ውስጥ ከ40 ሺህ በላይ ወገኖቻችን ይኖራሉ በተባለበት አካባቢ ለምን ከሺህ የማይደርስ ብቻ ነው በየአመቱ የሚሳተፈው የሚሉትና ተመሳሳይ ጥያቄዎች የተስተናገዱበት ነበር። ለብዙ አመታት ይህንኑ የሚያዘጋጁትና ሁሌም ከነርሱ እጅ ያልወጣው፤ አዲሶቹ ቦርድ ያው እኛ ባልናቸው ስለሆነ እኛኑ ነው የሚለምኑ ብለው እንደሆነ ይሁን ወይንም የሕጉ ጉዳይ አድቋቸው አልታወቀም አንዳንዶቹ በየግራጁዌሽን ግብዣ በመታየታቸው፣ አሊያም እንደ ጦር የሚፈሯቸውን የወ/ሮ የሐረር ወርቅ ጋሻውን ከብዙ አመት በኃላ መገኘትን አስበርግጎዋቸው የታወቀ ነገር የለም በጣት ከሚቆጠሩት አገልጋዮቻቸው ውጪ በሙሉ የተገኘው ጉዳዩ ያገባኛል ያለው ወገን ብቻ ነበር።

አዎን የወ/ሮዋ ብቅ ማለት ብቻ ሳይሆን የእርሳቸው የአዘጋጅ ኮሚቴ ኃላፊነቱን እንዲወስዱ የቀረበላቸው ጥያቄን በመቀበላቸው ገጻችን የተቃና የሥራ ጊዜ እንዲሆንላቸው መልካም ምኞቷን በዚህ አጋጣሚ ትገልፃለች። በዚህ ተቃራኒ ከላይ የጠቀስናቸውና የቦደኑት ጥቂት ግለሰቦች በዐሉ እንዳይሳካ ዘመቻ የጀመሩ መሆናቸውን ምንጮቻችን አልሸሸጉንም። ወገኖቻችንን ለመከፋፈል የማይቆፍሩትና ለመውጣት የማይሞክሩት ተራራ አይጠፋምና ጠንቅቆ ከወዲሁ መመርመር የሚበጅ ነው። እነዚህ ቡድኖች በተለያየ ወቅት በተለያየ ስምና ድርጅት የዳላስን ወገኖቻችንን መጠቀሚያ በማድረግ አመታትን አስቆጥረዋል።  ዘና ብለውም ይህንን ምግባራቸውን ሲከውኑ ክድርጅት አልፈው ተመሳሳይ ተግባር አጋጣሚን በመጠበቅ በደብር ላይ አነጣጥረው ተነሱ። በመጀመርያ ደብር ለመያዝ ማህበረ ቅዱሳንን መምታት፣ ቀጥሎ በምዕመን፣ በቀሳውስትና በቦርድ ተመራጮች መካከል ከፋፍሎ ማሸበር። በመረዳጃው ማህበርም ውስጥ በያዝነው አመራር በመጠቀም መከፋፈልን ማስፋትና በተለያዩ የፖለቲካ ድርጅት ስም ውስጥ በመካተት መረባችንን  ማስፋት በማለት ነበር የተጀመረው። ነገር ግን ክፉኛ የተቆጣው እውነተኛው ምዕመን አንድ በመሆን በፀሎትና በፆም በመታገዝ እንደ አመጣጣቸው እየመለሳቸው ይገኛል።

እንደ ኤሊዋ ሲንቀረፈፉ ያለሙትንም በሚሊዮን የሚቆጠረው ዶላር ከሚካኤል ደብር አጡት። በየፖለቲካና በግብረ ሰናይ ድርጅት ውስጥ ከየተሰገሰጉበት እየተፈነቀሉ ወጡ። ከሁልም በላይ ጠቅላይ መምሪያቸው የሆነውን  የመረዳጃ ማህበርን በትረስቲ በማዋቀር እድሜ ይፍታህ ምኞታቸውም ነጠፈና ከመረዳጃ ማህበሩም እየተመነቀሩ ይገኛሉ። እንግዲህ እንደ ኤሊዋ ጉዞ ዘና ብለው ባይዙት ኖሮ ዛሬ ያሰቡት ተሳክቶ ላገልግሎታቸውም የተገባላቸውን የ52ቱ ነጥብ ተሸላሚ ባደረጋቸው ነበር ። ነገር ግን በምን ጥፋቷ ድንጋይ እንዳለበሳት ባንጠይቅምና ምን በጀርባዋ እንዳጋለላት ባይነገረንም ፤ 4 እግሯ ብቻ በጀርባዋ ተንጋላ ብታወራጭ እንደወትሮ የትም መንቀሳቀስ እንዳልቻለች ነው የተረዳነው። አንገቷንም አውጥታ ለማየትም ማጅሯቷ ጭንቅላቷን መሸከም የቻለም ባለመሆኑና የሷም ቢጤዎች ከሩቁ ብቻ የሚያላዝኑ ሆነው መታየታቸውን በጣሙን እንድንመረምን የሚከጅለን። በወቅቱ ፈጥነው ፈጥመው በነበር ነበር። አሁን ግን የበደሉትን ይቅርታ የሚገባውን ሁሉ ጠይቀውና ከፈጣሪያቸው ታርቀው የተቀረ የዕድሜ ክፍላቸውን ለማጣጣም ያብቃቸው። እኛንም  ሆነ እናንተን እንደ ኤሊዋ በጀርባ ወድቆ ከመንጋለል እንዲሰውረን ፈቃዱ ለሁላችንም ይሁን። አሜን።

አቶ ኩባን ለዳላስ የሚያደርጉትን በጎ ስራ እያደነቅንላቸው ቡድናቸው ለደረሰበት ደርጃ ለእርሳቸው፣ ለቡድናቸውና ለደጋፊዎቻቸው እንኳን ደስ ያላችሁ! ለቀሪውም ግጥሚያ በለስ በናንተ ይሁን እያልን ለዛሬ GO MAVERICKS
GO እንላለን።

እርሶስ ምን ይላሉ?    



1 comment:

Anonymous said...

please try to get what is going to happen in Dallas yetifat tebabari kemehon yitebikachihu

http://www.eotc-mkidusan.org/site/index.php?option=com_content&task=view&id=683&Itemid=1