Monday, May 30, 2011

ይድረስ ለአቶ አብርሃ በላይ/ኢትዮሚዲያ ገጽ

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!

ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።


ይድረስ ለአቶ አብርሃ በላይ/ኢትዮሚዲያ ገጽ

የተወደዳችሁ የገጻችን ታዳሚዎች እንኳን በሰላም ለሰማዕታት (ሜሞርያል) ቀን ሁላችንም ጠብቆ ለዚህ ላደረሰ ለልዑል እግዚሀብሔር ክብር ምስጋና ይሁን። በዚህ ሰማዕታት ቀን መጠለያ ብቻ ሳይሆን መመኪያና መኩሪያችን ፣ እኩልነትና ነጻነት የሞላበት ሀገራችን እንዲሆን በራቸውን ከፍተው በሙሉ ልብ ተቀብለው እንድንቀላቀላቸው ፈቃድ ላደረጉልንና ይኸው እንዲተገበር ውድ ሕይወታቸውን የከፈሉትና በመክፈል ላይ ላሉት የአሜሪካን የሲቭልና የጦር ኃይል አባላትን በመዘከር የምናስታውስበትና የምናመሰግንበት ዕለት በመሆኑ ይህንን ሀገር እግዚሀብሄር ይጠብቅልን። የትውልድ ሀገራችንን ኢትዮጵያንና ሕዝቧንም ያስብልን።

ሰሞኑን ከሀገር ወደ ሀገር በመዘዋወር በከፍተኛ ትምህርት እየተመረቁ ለሚገኙት ወጣቶች ልጆቻችንና የወዳጅና የዘመዶቻችንን ልጆች ተጠምደን ብንሰነብትም ለዚህ መሳካት የወጣቶቹ፣ የቤተሰቦቻቸውና በተቋማቱ ላሉት ሁሉ ላበረከቱት መሳካት፤ ሁሉንም እንኳን ደስ አላችሁ ስንል፤ ተተኪ በመሆን ከ2ኛ ደረጃ ለወጡትና ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ለሚገቡት፣ ከመጀመሪያ ዲግሪ አልፈው ወደ ድህረ ምረቃም ሆነ ለፒ ኤች ትምህርታቸው ለሚያቀኑት ሁሉ መልካም ምኞታችንን እየገለጽን ልዑል እግዚሀብሔር ያሳካላችሁ እንላለን።

የዳላስ ቅዱስ ሚካኤል ደብር አጠቃላይ የአባላት ስብሰባ አስፈላጊው ቁጥር ባለሞሙላቱ ሳይኬድ ቀርቶ ለ2 ሳምንት ለ05/28/2011 መቀጥሩን ሰምተናል። የ2ኛውም ጥሪ ለምን ምልዐተ ጉባኤው እንዳልሞላ ከሚካኤል ሠይፍ የደረሰን የተገኙት ወደ 40 ቀጥር ያላቸው ደብሩን አዋኪያን ስለሆኑ ከነእርሱ ጋር መቀመጥን አለማሻታቸውን ሲሆን ሁሉንም ለሚካኤል ፈቃድ መተዋቸውን ነበር። ታላቁ የቅዱስ ሚካኤልና የተዳበሉት ታቦቶችን ጨምሮ የሚሰሩትን ያልተገነዘቡ እነዚህ ጥቂት ግለሰቦችም ዛሬም ማስታወሉን እንዲሰጣቸውና ከታቦት ጋር የሚደርጉት ግጭት እንጂ ከግለሰብ እንዳልሆነ ሊረዱት ይገባል። የነዚሁ ቡድን ገፅ የሆነው ከስብሰባ ስለታገዱት አባሪዎቻቸውና ከሳሾች ቢያለቅስም ቦርዱ የተመረጠበትንና የሚተዳደርበትን መተዳደሪያ ደንብ አክባሪነቱን በማረጋገጥ ከሳሾቹን ለየ ፣ በሕጉ መሰረት 2ኛ ስብሰባውንም ጠራ። ሌላው ሥርዐቱን ለመናድ ካልሆነ በስተቀር ከንቱ ጩኸት እንለዋለን። ሌላው የኛን ገጽ ለማፈን በሚደረገው የሕግ ጎዳና ከጠንሳሽነቱ ጀምሮ አባሪ መሆኑንም ከለጠፈው ስንረዳ የመጻፍ መብታችንን ከሚያደናቅፉ በመሰለፉ በደብሩ ውስጥ መብት ተነካ የሚለውን የሀሰት ለቅሶውን አጋለጠ እንለዋለን። በሌላ በኩል እኛ ተከሰስን ብለን ለጥፈን አናውቅም ነገር ግን በሕግ ልሳናችንን ለመግታት በትግሬ ነጻ አውጪ ቅጥረኛና ምናምንቴዎች በተለያየ መልኩ እየተፈተንን ቢሆንም የመናገርና የመጻፍ መብታችንን መቀማት እንደማይቻል የሀገራችን ኮንስትቲይሽን በግልጽ አስቀምጦታል።

በዚህ 2 የደብሩ ስብሰባዎች መካከል የጠ/ሚ መለስ አምቼ ከቤ/ክ ከ60 በላይ የሚሆኑ ወንበሮችን ተከራይቶ ሲያጓጉዝ በየመንገዱ ሲያንጠባጥበው የታዘቡ የደብሩ አባላትም መኖራቸውን ሲደርሰን ፣ ወንበሩን የተከራዩት ለምን እንደሆነና የት ቦታ እንዳጓጓዙት በመስማታችን አዝነናል። ቦርዱም የኛን የተጋራ ይመስል ከዚህ በኃላ ማንም ይሁን ምን አሁን ለመከራየት ከተመዘገቡት ውጭ ወደፊት ላለማከራየት ወስኗል የሚል ከሚካኤል ሠይፍ አብሮ የደረሰን መሆኑንን ስንገልጽ ሰንከፎው እስኪወልቅ የመጣውን መቀበል የግድ መሆኑን ከዚሁ መገንዘብ ያሻል። ሰሞኑን በፍቅረማሪያም የተደረገው ቅስቀሳ አልመስራቱን ቀጥሎም በቀድሞው ሊቀመንበር ኢዮኤል የአዋኪያን ቡድን አባል እየተካሄደ ያለውን የፊርማ ስብሰባም ስንሰማ መቼ ነው እርሱ በሕዝብ ድምፅ ያመነው? በርሱ ጊዜ ስንት አይነት የምዕመናን ቅሬታ ሲጎርፍ ከምንጣፍ ስር ሲቀርብ አልነበረምን? የሕዝብንስ አደራ በግል ጥቅሙ መነካት ነው ወይንም ለምን በቁልፍ ሰበብ?

ለዛሬው ጥሁፋችን መንደርደሪያ የሆነን በአቶ አብርሃ በላይ የኢትዮ ሚዲያ ድህረ ገጽ በቅርቡ ስለዳላስ ነዋሪ ግለሰቦች ያስነበበንን በእማኝነት አድርገን ለምን እኛ ሀቅ ከጨበጥነውና በአጋጣሚዎች ሁሉ ካስነበብነው ጭብጥ የወጣ ዘገባ ለምንና እንዴት የመሰለውን ለማስረገጥና ወገኖቻችን የራሳቸውን ግንዛቤ ይስሉ ዘንድ ነው። አቶ አብርሃን በአይነ ስጋ ባናውቀውም የትግሬ ነፃ አውጪ ጎራ የነበረና ሀገር አብሮ ያስቆራረጠ ለመሆኑ የአደባባይ ሚስጥር ነው። ከነእርሱም ተፋታው ብሎ በአሜሪካ ተቀምጦ በከፈተው ድህረ ገጽ ጥሩና ድንቅዬ ሥራዎቹን አቅርቦልናል ፣ ለዚህም እናመሰግነዋለን። በሌላ በኩል ደግሞ ከግል ጥቅም ጋር በተሳሰረ የሕዝብንና የሀገር አንድነት በሚጻረር ስነ ባሕሪን ተላብሶ እያደማ ይንቀሳቀሳል። ለዚህም እኩይ ምግባር የተሰለፉለትንም ባገኘው አጋጣሚ ይዘክራል። የሚቋቋሙትም ጥሁፎች ሲደርሱትም ያፍናል። ሰሞኑንም 2 የዳላስ ነዋሪ ስለሆኑ ግለሰቦች የለጠፈውንና ቀብቶ የካናቸውን ገጻችን ከአለመስማማት አልፋ በጽኑ ትኮንን ዘንድ አብቅቷታል። ተካሄደ የተባለው የኢሳት መዋጮ 25 ሺህ ዶላር አስገባን ያሉት ግለስቦች ከዚህ በፊት ለዳላስ የኢትዮጵያ መርዳጃ ማህበር እጅግ ብዙ ሺህ የሆነ ዶላር አስገኘን ብለው በሪዲዮን የደሰኮሩትን ያስታውሰናል። እስከ ዛሬ ሳንቲም አልታየም። ወራዳና ዋሾ ራከርድ ያላቸው ብለን ብቻ አናልፈውም!

1. በትሩ ገብረእግዚሐብሄር ማለት ቀደም ሲል ገፃችን ከቴኔሲ ፍርድ ቤት በእርሱና በባለቤቱ ስም የተሰራውን ማጭበርበር አስመልክቶ ሁላችንንም የኢትዮጵያ ተወላጆች አንገት ያስደፋውን ምግባር መለጠፏን ብቻ ሳይሆን የተለያየ የግብረሰናይ ድርጅት ስም እየመሰረተ መተዳደሪያው ያደረገና በሰፈረበት ሀገርና ከተማ ሁሉ ምግባሩ አስነዋሪ ብቻ የማይባል ሕግን የተላለፈ ጭምር ነው። ሰሞኑን ሕይወታቸው ያለፈውና የበትሩ ሰለባ ከሆኑት አንዷን ግለሰብ ማንሳትም ተገቢ ነው። ስማቸው ወ/ሮ አልማዝ የተባሉ በአዲስ አበባ የባናቱ ምግብ ቤት ባለቤትና ልጆቻቸውን ብቻቸውን የሚያሳድጉትን ሴት ለንግድ ማካሄጃ ብሎ ተማጽኖ አንድና ብቸኛ መኖሪያቸውን በማስያዝ ትልቅ ገንዘብ በመበደር ኢትዮጵያን ለቆ ወጣ። ከዚያም ወደ ሌላ አፍሪካ ሀገር ተመሳሳይ ድርጊት ፈጽሟልም ይባላል መረጃው ባይደርሰንም። ነገር ግን የወ/ሮ አልማዝ በዚህ ውስልትና በተፈጸመባቸውና በደረሰባቸው ኪሳራ ምክንያት የደረሰባቸው የጤና መታወክ ለብዙ አመታት ሲሰቃዩ ቆይተውና ልጆቻቸውና የልጅ ልጆቻቸውን ጨምሮ የገፈቱ ቀማሽ አድርጓቸዋል። እንግዲህ አለም አቀፍ አጭበርባሪና ለወገኖቹም ርህራሄ የሌለው ለግል ጥቅሙ ብቻ የቆመ ለትግ ሬ ነጻ አውጪ የስውር አርበኛቸው በዳላስም በ2 ቤላዋ የሚበላውን መኮፈስ ለአብርሃ ማንነት ጥያቄ ምልክት ነው።

2. ስለ ዘውገ ቃኘውም ቢሆን ብዙ ብለናል። በቅርቡም ስለ አባይ ግድብ ከትግሪ ነጻ አውጪ ተልከው ዳላስ ከገቡት ቡድን ጋር አብሮ የከረመና እራት የተቋደሰ መሆኑንን በዳላስ ነዋሪ የተረጋገጠ ነው። ከሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ እስፖርት ተቋምም በየአመቱ የሚደረግለት የነጻ ጥቅም በመቅረቱ ወያኔ ያዘው ብሎ ስም ማጥፈት ዘመቻና እንዲፈርስ ከሚያውኩት ጋር መዳበሉ ለሁላችንም ግልጽ ነው። እርሱና የትግራይ ተውላጅ የሆነው የሬዲዮን ባልደረባው ስጦታው የተባለው በዳላስ የኮሚኒቲ ሬዲዮ ለትግሬ ነጻ አውጪ መሳሪያነታቸው እሙን ነው። ያለሙያ ብቃት የቆሙና ስደተኛውን መጠቀሚያ ያደረጉ መሆናቸውን እየታወቀ ያለ ነው። ከዚህ በታች ያለው እሮሮ ለአብርሃና ብጤዎቹ ድህረገጽ ተልኮ ያፈኑትን እነሆ አቅርበነዋል።

     





እንግዲህ ወደ ኃላ ያሉትን የለጠፍናቸውንም በመገንዘብ አቶ አብርሃ እርሶስ ምን ይላሉ? የሚለውን የተለመደውን ጥያቄያችንን እየተውን አንባቢያን በጥንድና በቡድን የሚተገበረውንና ወገኖች ላይ የሚካሄደውን ግምጋሜ ላይ አድርሶ ፍሬ ያስጨብጥ ዘንድ ያለንን ወርውረናል።

ለአንደኛ አመታችን ለደረሱን ግምገማዎች ተሳታፊዎቻችንን ሁሉ ከልብ እናመሰግናለን። ላበረታታችሁንና ለደገፋችሁን ፣ ያላችሁን መረጃዎች ላልነፈጋችሁን ፣ ሂስ ለሰነዘራችሁብን ና ለተቃወማችሁን ሁሉ ምስጋናችን የላቀ ነው። ወቀሳችንና ትችታችንን ተቀብላችሁ ለተመለሳችሁ አክብሮታችንን ስንገልጽ ላልተከፈተላቸውና በጨለማ ላሉት ወይንም ትቅማቸው የቀረባቸውና እልህ ይዞ ያለቀቃቸው፣ ስማችን ተነካ ብለው አምረረው እኛን ከመተንኮል ላላሰለሱት ጭምርና በሀይማኖትም ግዝት የጣሉብን ጨምሮ ለሁላችንም የምናስተውልበትን ህሊና ሰጥቶ መተቻቸትንና መነቃቀፍን ለመሻሻልና ለበጎ ምግባር አድርገን በመውሰድ በቅን ጎኑ በማየት የቀረ ሕይወታችንን ለጋራ ደህንነትና መደጋገፍ በማዋል በመካከላችን የሚሽሎከለኩትን አዋኪያን የራሳችንን ወገኖችን በራሳችን በመተናነጽ ለተተኪዎቻችን የተሻለ ለመከወን ልዑል እግዚሐብሄር መንፈሳችንን ያንጽልን።
አሜን።

እርሶስ ምን ይላሉ?      

No comments: