Wednesday, May 4, 2011

ኮርት አለብኝ…….

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!

ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።


ኮርት አለብኝ…….

እንደምን ከርማችኃል? እኛ በፈጠረን በእግዚሀብሔር ችሮታ ለዚህ አብቅቶናልና ለቅዱስ ስሙ ክብርና ምስጋና ለዘላለም ይሁን። አሜን። ባለፈው እንዳስነበብናችሁ ሁሉ የዚህ ገፅ ዝግጅት አባል የሆነች እህታችን ከናንተ ዘንድ ከርማ ዛሬ ምሽቱን ስትለቅ፤ እንድትቆይ ካደረግንበት አንዱ ምክንያት የደብረምህርት ቅዱስ ሚካኤል በነጥሩአየር ተከሶ ከተፈረደለት በኃላ ከሳሾች የይግባኝ አቤቱታ በመጠየቃቸው፤ የይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የዛሬውን ችሎትን እንድትዘግብልን ነበር።

ከምሳ በኃላ የተጀመረው ችሎት በሁለቱም ወገን ከቀረቡት  መረጃዎች ሌላ ለእየአንዳንዶቻቸው የ15 ደቂቃ የቃል ክርክር ያሰሙ ሲሆን ፤ ይህንኑ ጉዳይ የሚያዩት ዳኞች ወደፊት ያላቸውን የሕግ ውሳኔ እንደሚሰጡበት በማስታወቅ ተፈጽሟል። ይግባኝ ባዩ የከሳሽ ነገረፈጅ ያለደንበኞቹ ብቻውን የቀረበና ስለጠቅላላው የደብሩና የከሳሾችን ጭብጡ አናሳ እንደነበር እህታችን ስትታዘብ፤ የከሳሾችን ወገን ሆነው ለትዝብት የመጡት መስፍን እኝ ብዬ የተባለውና እስስቱ ሰይጣን የሚሉት ሌላው ደብር ከሳሽ ፀሀይጽድቅ የተባሉት አጽራረ ቤተክርስትያንና ጸረ ክርስትያኖች ናቸው። እንደ እህታችን ዘገባ ከሆነ ከደብሩ በኩል እንደጠበቀችው የሰው ብዛት አለማየቷ እራሷን ለመደበቅ አዳድቷት እንደነበር አልሸሸገችም ምክንያቱም ማንንም ፈርታ ሳይሆን ለወደፊቱ አንዳንድ መረጃዎችን ለማግኘት እንዳትታወክ እንጂ። ቀደም ብላም ለሌላ ጉዳይ በአንዱ የዳወንታወን ሆቴል የቀጠሮዋ ሰአት እስኪደርስ በመኪና ማቆሚያ ገራዥ ውስጥ በትራንስፖርት ስራ ወደሚተዳደሩት ወገኖቻችን ጠጋ ብላ አቁማ በነበረበት ጊዜ፤ ከነበሩት ውስጥ አንዱ ተኩላው ነበር። እርሷም የሚላመጥ ባገኝ ብላ ጆሮዋን በመጣል  ያገኘችው ቢኖር “ኮርት አለብኝ….” ሲል ነበርና የትኛው መሆኑ ባይታወቅም እርሷ ከነበረችበት አልታየምና ከየትኛው እንደሆን ወደፊት የሚታወቅ ይሆናል። የዛሬውን የፍርድ ቤት ውሎ ማን እንደሚዘግብለት ባይታወቅም መስፍን እኝ ብዬ ABC አድርጌአልሁ የሚል ከሆነ እንግዲህ ሊታይ ነውና እስስቱ ፀህይጽድቅ ግን ምን እንደተባለ የማይገባው የትምህርት ድሀ ነውና። ከዚህ በፊትም የፍቅሩ ታደሠን ወንድም ብርሀነማርቆስ ታደሠ የሚሉትም ለናሙና ወይም ለቁጥር ከፍርድ ቤቱ ችሎት ተዶለ እንጂ ከተኩላው ያልተሻለና የእንግሊዘኛው ቋንቋ ችግር እንዳለበት በሚገባ አስጨብጦናል።

በተረፈ ስለነበትሩ ገ/እግዚሀብሔርና አለማየሁ ኪዳኔ ላይ ሀገር ወዳድ አስመስለው የጀመሩትና ያስጀመሩት የሀሰት ወሬ መንገዱን እንዳለያዘላቸው ደርባ ገልጻልናለችና በቸር እንሰንብት።

እርሶስ ምን ይላሉ?  

No comments: