Thursday, May 12, 2011

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!

ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።


የተወደዳችሁ የገጻችን ተከታታዮች እንደምን ከርማችኃል? ፈቃዱ ሆኖ ዳግም እንድንገናኝ ለወደደ ለእርሱ በቅዱስ ስሙ በእግዚሀብሔር ቸርነት ነውና ስሙ የተወደደ፣ የተከበረና የተመሰገነ ይሁንልን። ያለእርሱ ፈቃድ ምንም ምን ሊሆን አይችልምና ዛሬ ወደፊትም ሆነ እስከዘላለሙ ለእርሱ ክብርና ምስጋና ይሁንልን! አሜን።

የፊታችን ቀዳሚት የዳላሱ ቅዱስ ሚካኤል ደብር በ2010 ላይ ማቅረብ የነበረበትን የ2009 አመታዊ ዘገባ በአባላት ስብሰባ ላይ ያቀርባል ተብሎ ይጠበቃል። አንዳንድ ከአጽራረ ቤተክርስትያን የወገኑ ጥቂት ግለስቦች የ2010 አመታዊ ዘገባ እንጂ የ09 አመትን እንደማይፈልጉ ምልክቶች ቢኖሩም፤ በቅደም ተከተል መሄድ ያለበትና ለጣት ለሚቆጠር ግለስቦች መስማት ብቻ የሚፈልጉበት አካሄድ እንደሌለ ሊታወቅ ይገባል። የ09 ዘገባ ኮረም ባልሞምላት ምክንያት ሲተላለፍ ቢዘገይም በተለይ የቀደመው የወጪ ሂሳብ መርማሪ ቀደም ብለው ከቀጠሩት ግለሰቦች ትእዛዝ ባለመውጣትና ገለልተኛ ዘገባ ማቅረብ ባለመቻሉ ፣ ሰራ የተባለውንና በእጁ ያለውንም ዘገባ ለማቅረብ ፈቃደኛ ባለመሆኑ፤ በመጨረሻው የአስተዳደር ቦርድ አዲስ የውጪ ገለልተኛ የሆነ ሂሳብ መርማሪ አወዳድሮ በመኮናተር የተሰራ ዘገባ መሆኑን የሚካኤል ሠይፍ ተወካይ ገልጾልናል። የ2010 የሂሳብ ምርመራን በተመለከተ በቅርቡ ተጠናቆ እንዳለቀ ወደፊት እንደሚገለጽ ለመረዳት ችለናል። ከ2011 ጀምሮ አዲስ የገባውና በሥራ ላይ የሚገኘው ሶፍትዌር ከዚህ በፊት የነበረውና ለቁጥጥር የማይመቸውን መዝገብ አያያዝን በማስተካከል አሎታን ያጠፋል በሚል መልክ አያይዞ አስጨብጦናል።

ይህ አመታዊ ስብሰባ በመከባበር ፣ በመተሳሰብና ሙሉ ክርስትያናዊ ስነ-ምግባር የሚዘከርበት እንዲሁም በቤተክርስትያን ቅጥር ግቢ የሚከወን በመሆኑ ስፍራውንም ጭምር ሊከበር የሚገባው ነው። በሌላ በኩል በቀደመው ጥሁፍ ላይ ካሕኑን አንስተን በተዘገበው ላይ የቀረበልንን እንጂ ፈጥረን እንዳልሆነ ታውቆ፤ በሰንበቱ ትምህርታቸው ላይ ያቀረቡት፤ መልዕክቱ ደርሶናል። እኛ ብቻ ሳንሆን የሚያገለግሉበት ደብር አብዛኛው ምዕመን ከኛ ጋር የሚስማማው ፈጣሪ በሰጦት ክህነት ብቻ ሳይሆን ባካበቱት ዕውቀትና የትምህርት አሰጣጦ ጭምር የምነወድዶና የምናከብርዎ መሆናችንና ባለን ፍቅርና አክብሮት ስለምንሳሳሎት ከአዋኪያን እጅ ይጠበቁ ዘንድ መጎሻሸማችን ወደፊትም የማይቀር ነውና በሰይጣናዊ መንገድ ያለን ተደርጎ እንዳይታይብንና ትችታችንን ሁሉ በፍቅር መንገድ እንዲያስተውሉልን እንጠይቃለን። እንደ እርሶ በክህነቱ የሌሉበትን ፣ አልፈውም በአጽራረ ቤተክርስትያን ጎራ ያሉትንና ከክርስትናዊ ሕይወት ውጪ በመሆን ለሚያውኩ ወንድሞችና እህቶችም ላይ የምናቀርበው ትችት ሁሉ ክርስትናም ሆነ አለማዊ ሕይወታቸውን እንዲመረምሩና አብረው በሰላምና በፍቅር ከወገኖቻቸው ጋር እንዲኖሩ እንጂ፤ ይኸውም ይሆን ዘንድ ዘወትር ለሁሉም በጸሎታችን እንለምንላቸዋለን።

በተረፈ የትግራይ ነጻ አውጪ ድርጅት በከተማችሁ ተክሎትና ለብዙ አመታት ከናንተ ጋር አብሮ የኖረው፣ ቀደም ሲል ኤርትርያን ጌቶቹ ሲያስገነጥሉ ያዳመቀ፣ ብዙም ሳይቆይ የቅዱስ ሚካኤልን ደብር ከኤርትራዊያን ጋር በማበር በተደረገው የነጠቃ ሙከራ ውስጥ አንዱ የነበረ፤ በቅርቡ ከሚካኤል ወጥቶ በተክላይማኖት ስም ቤተክርስትያን ከከፈተው ጋር አብሮ የቆየውና ሰሞኑን ለነ አባ ጳውሎስ እጅ መንሻ ያስገባው ታደሰ ፀሀይ ከከተማችሁ ለቆ ወደ ካሊፎርንያ ለተመሳሳይ ተግባር የተዛወረ መሆኑንን የደረሰን ዘገባ ያስረዳል። እንግዲህ ታደሰ ቢሄድም ሌሎች ታደሰዎችን ተክቶ ነውና መዘናጋት አስፈላጊ አይደለም።

ባለፈው በካቶሊክ ቻርቲ ውስጥ እየተካሄደ ያለውን ሕገወጥ ሰው ማስተላለፍ በተመለከተ በዚህ ገጽ መውጣቱ ይታወቃል። ከእጃችን ከገቡት ውስጥ የግለሰቦቹን ማንነት በመሸፈን ቅጅውን እንደሚከተለው ስናወጣ የሚያሳዝነን ነገር ቢኖር እውነተኛ የተባሉት ስደተኞች በስደት ላይ እየተሰቃዩ ባሉበትና እድላቸውን ለሌሎች በቀጥታ ከሞቀ ቤታቸው ተነስተው ከነቤተሰቦቻቸው በሀሰት በተገዛ መረጃ ወደ አሜርካን ሀገር እንዲገቡ መደረጉ ብቻ ሳይሆን፤ ሀላፊነቱን የወሰዱት ቤተሰቦችም የአቅም ጉዳይ ሕጉን ያልተከተለ፤ ከገቡም በኃላ ያለአግባብ ጥቅማ ትቅም ከታክስ ገቢ ከመንግሥት ማግኘትና በሕክምና  እንደዚሁም የምግብ እርዳታ እንዲያገኙ የካቶሊኩ መስሪያ ቤት ሰራተኞች ማድረጋቸው፤ አንደኛዋ ግለስብ ሕክምናቸውን ከጨረሱ በኃላ ወደ ሀገራቸው መመለሳቸው ፤ ከመንግሥት ወጪ ተደርጎ የተጓጓዙበት ወጪ አለመከፈሉ፤ ወዘተርፈ……. ለሚሉት ጥያቄዋች ከዚህ በታች የቀረቡትን መረጃዎች ሀሳብን በሚገባ ያንሸራሽሩና ጭብጥ ያሲይዛሉ የሚል እምነት አለን።










ከዚህ በፊትም የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አምቻ የደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ቦርድ አባል በነበረችበት ወቅት፤ ዝይን የተባለች ምዕመን ጋር ይህንኑ በካቶሊክ ቻሪቲ ውስጥ በሚካሄደው ሕገወጥ ሙስና ምክንያት መጋጨታቸውን በወቅቱ ከቤተክርስትያኑ የነበሩ እማኞች በሚገባ  የሚያስታውሱት ሁኔታ ነው። ከዚህ ውጭም አንዳንድ ግለሰቦች በቤተክርስትያኑ ስም በሀሰት ሰዎችን አስመጡ የተባሉ እንዳሉም ይነገራል። በተመረጡበት ወንበር አማካኝነት ያለአግባብና በሕግ ወጥ መንገድ ተጠቃሚ የሆኑ እራሳቸውና ተጠቃሚ ግለስቦች የሚያውቁት ሀቅ ነው በማለት በዚሁ ስናልፈው እልባት ለማግኘትና ሀሜቱን ለማቆም አሁን ያሉት ተመራጮች ምርመራ ቢያደርጉበት ይበጃል እንላለን።  

እንግዲህ መናገርም ሆነ መጣፍ በትውልድ ሀገራችን ቢነፈግ እነአምቼዎችና ገጻችን የጎነተለቻቸው ሁሉ ግምባር ፈጥረው ይህ ሀገራችን አሜሪካ የሰጠንን የመናገርና የመጻፍ መብታችንን ለማፈንና በሕገ መንግሥታችን ላይ የተደነገገውን ለመናድ የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም። እኛ እንደ እነርሱ ስለማናስብ ፤ እነርሱ በግል ፣ በቡድን ፣ በገጾቻቸውና በመሀበሮቻቸው ሁሉ ያልሞከሩት የለም።
በእምነታቸው ጸንተው የቆረቡ ከሆነ ፣ ነገርንም ሆነ ሁኔታዎችን በምን አይነት ክርስትያናዊ ስነ ምግባር መያዝ እንዳለባቸውና የመንፈስ አባቶችም ካሉዋቸው አይሸሽጓቸውም ለማለት ያስደፍረናል። እኛ የምንተቻቸውን ሁሉ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ናቸው፣ ሁሉንም እንወዳቸዋለን። ማንንም ሰው አንጠላም ፣ የነእርሱንም ክፉ ማየት አንፈልግም። ችግራቸውም ሆነ ደስታቸው የጋራችን ነው። በሀሳብና በድርጊት መለያየትና በዚያም ላይ በያዝነው የልዩነት አቋም መከራከርና መተቻቸት አግባብ ነው። ልዩነቶች እንደ ሁኔታው ሁሉ ይጎላሉም ሆነ ያንሳሉ። ሲሆን ደግሞ ልዩነቶች እንደተጠበቁ ሆነው ወይንም አሳንሶ በመያዝና በመቻቻልም መቀጠል ይቻላል።
ገና ለገና ስሜ ተነሳና ተተቸ ብሎ ጉሮ ወሸባ ማለት ደግሞ የሀሳብ አመዛዛኝነትን አድማስ ያጠባል እንጂ ለአዲስ ሀሳብና ግኝት አያጎለምስም። ለዚህም ነው ገጻችን በአንድ በኩል ሲተችና  ሲኮነን በሌላ በኩል ደግሞ ያገኘውን ሲቸር፣ ሲሳሳትም ይቅርታ ሲጠይቅ፣ ከሚወዱትም ሆነ ከሚኮንኑት ሀሳባቸውን እንደ አመቺነቱ ሲያስተናግድ አመትን ያስቆጠረው። በዚህ ሲጠላ በዚያ ከበሪታ ሲያገኝ ሁሉም የየራሱን ስሜት እንደ አሻው አፈራርቆበታል።

ነገር ግን አንድ ማስጨበጥ የምንወደው ነገር ቢኖር ሀይማኖታችንን እንወዳለን እናከብረዋለን። የሌላውንም ሀይማኖት እንጠብቃለን። ሁሉም በነጻነት ማምለክ አለበት እንላለን። የፈለገ የሀገር ቤቱን ሲኖዶስ፣ ያልፈለገ የውጪውን ወይንም ገለልተኛ ሆኖ በመረጠው የመጓዝ መብቱን እንጠብቃለን። ዳላስ በቆየንበት አጭር ጊዜ ስለ ቅዱስ ሚካኤል ደብር የሚበቃንን ያህል ባይሆንም የምንችለውን ያህል ጨብጠናል። ነገር ግን ሀይማኖት ቤት መሆኑ ቀርቶ ጎጠኝነት የሰፈነበት፣ ለግል ፍላጎት ብቻ ያደሩ ፤ ደብሩን በኃይል ከገለልተኝነት መንገዱ ለማውጣት የተነሱና በፖለቲካው የታወሩት፣ ወይንም የራሳቸውን ድርጅትና አላማ ብቻ በማራመድና ሲጠቀሙ ጥገታቸው የደረቀችባቸው (የነጠፈችባቸው)፣ ወዘተ……. በመሆን ሕብረት ፈጥረው የከፈቱትን ሴራ ስለተገነዘብን በኦርቶዶክስ ልጅነታችን በመቆርቆርና ለደብሩ ባለን ፍቅር ጭምር በምንችለው ሁሉ እርሱ በሰጠንና በፈቀደው መሰረት የአቅማችንን እየወረወርን ነው።

የቀደሙትን ብቻ ሳይሆን አሁንም ያሉትን የቦርድ ተመራጮችንም አልተውናቸውም አንተዋቸውም። ከኛ ጆሮ እንዳይደርስ በማለት በሚካኤል ሠይፍ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖና ቁጥጥር ያደርጉበታል። ለምን የኛን ገጽ ሁሉንም በእኩልና በገለልተኛነት ብትቀበልም ከደብሩ ጋር ያከረሩት ላይ ግን ጠንከር እንደምትል አትሸሽግም። ከግለስብና ድርጅት አልፎ በተከበሩት የሀገራችን መሪ ፕሬዝዳንት ብራክ ኦባማ ላይ ይህ ገጽ ባልተስማማበት ጉዳይ ትችትን ሰንዝሯል። ሁላችንም በእርሱ አምሳል ተፈጥረናልና እንደመልካችን ምግባራችን በመለያየቱ ከጥንት ጀምሮ የነበረ፣ አሁንም ያለና እየኖርነው ስለሆነ ሁላችንንም ፈጣሪ የቅን ልቦናን ከማስተዋል ጋር አክሎ ለተቀረው ጊዜአችን ሰላምና ፍቅሩን ሰጥቶን ለንስሀ ያብቃን። በመንግሥቱም ይሰብስበን። አሜን።

እርሶስ ምን ይላሉ?

1 comment:

Anonymous said...

የቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ወይስ የሚካኤል ግሮሰሪ?
የዳላስን ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የማልፈልጋቸው የቤተክርስቲያን አገልጋዮች ለማገልገል
ተመርጠውበታል በማልለት ቤተክርስቲያኑን በአጭበርባሪ ጠበቃ ከሰውና አራቁተው ህንጻውን
ለመረከብና ግሮሰሪ ለማድረግ ክስ የመሰረቱት የቤተክርስቲያን አባላት ከመረዋ ብሎግ
እንደተረዳነው ከቤተክርስቲያን አጠቃላይ ስብሰባ መባረራቸውን ስንሰማ የሚካኤል ቁጣ ቢዘገይ
ቤቱን አይጠብቅም ማለት አለመሆኑን እንደገና መረዳት ችለናል።
ድሮውንም ጓደኞቻቸውንና ዘመዶቻቸውን በማታለል እያራቆቱ ሃብት ያከማቹ ቤተክርስቲያን
እንረዳለን እያሉ በሰው ፊት ክብርን ለማግኘትና ለማስመሰል ለቤተክርስቲያን ያወጡትን ገንዘብ
የሚቆጥሩ ነጋዴዎች እውነት ለክርስቲያንነት ሳይሆን ያወጡትን ገንዘብ በመቶና በሽህ እጥፍ
ለመመለስና ለመዝረፍ የሚያደርጉት ሙከራ ነበር።
የክርስቲያናዊ ተግባር እንኳን ለቤተክርስቲያን የሰጠውን ለሰው ማሳወቅ ቀርቶ “በቀኝህ
የሰጠኅውን ግራህ አይወቅ ይል የለን?
የማቴወስ ወንጌል ቁጥር ፮ አንቀጽ ፩ እስከ ፬ አንብቡ።
ስም ለመጥቀስ አልፈልግም ምክንያቱም መረዋ ሁሉንም ገልጾታልና ያገራችን አባባል “ባለጌን
አንዴ ስደበው፤ እድሜ ልኩን ራሱ እንደተሰደበ ይኖራል” ይላል! አሁንም እንዚሁ ተባራሪዎች
በደብቅ በትቂት ሰዎች ፊት የሆነውን መዋረድ በብሎግ ለሁላችንም እያሰሙን ነው፤ እኔም
በተራየ መረዋ ባያወጣው ኖሮ አጥብቄ አልጠይቅም ነበር። ይባስ ብሎ የገዛ ጓደኛው ታዝቦት ብዙ
ብዙ ነገር የማላውቀውን ሁሉ ነግሮኛል። አንደኛው ከሰማሁት የገረመኝ! ብር የያዘበትን እጅ
በብረት ብትመታው ብሯ ጥብ አትለም፤ ነገር ግን ብሯ ሌላ ብር የምታመጣ ከሆነች ባስቸኳይ
ትወድቃለች አለኝ። ለዚህ ነው ለካ በየሄደበት ይሄን ቤተክርስቲያን አቋቁሜ እያለ የሚፎክረው።
ሌላዋም ተባራሪ ታድያ ለምንድነው ገንዘቤን የምትወስዱት ማለቷን ስሰማ ገንዘብ ለቤተክርስቲያን
እንጅ የተሰጠው ለአባራሪዎቹ ነው እያለች ታስባለች ማለት ነው ይሆን?
የመረዋ ማህበረ ቅዱሳን ደራሲ ፍርድቤት ቀርቦ የማህበረቅዱሳን ተከታይ መሆኑን ለመካድ የተነሳ
የከሳሾች ወገን ከሳሾቹ ሲያሸንፉ ስንት ሊከፍሉት ቃል ገብተውለት ይሆን?
አሁን ብዙ ገንዘብ ለቤተክርስቲያን አጥፍቷል ያልከው ግለሰብ በሚያሸንፍበት ጊዜ አንዲት ቤሳ
እንዳማያቀምስህ የታወቀ ነው በከንቱ አትከጅል!ምናልባት ቤቱን ተረክቦ ግሮሰሪ ሲያደርግ
በትርፍ ጊዜህ የእቃ መደርደር ስራ ይሰጥህ ይሆናል ብየ አምናለሁ፡
ብሎግ በማውጣትህ አዋረድካቸው ጉዳቸውን አወጣህባቸው እንጅ አልጠቀምካቸውም፤
የቤተክርስቲያኑ አስተማሪዎች ለሚመጣውና ለሚሰማው ምእመን ሁሉ እንዲያስተምሩ የምመኘው
ዋና ትምህርት ቢኖር የማቴወስ ወንጌልን አንቀጽ ፮ እያብራሩ ለምንሰማው ሁሉ እንዲያስተምሩን
ነው።
ቤተክርስቲያን የሁሉም እንጅ የንዳንድ ግለ ሰብ እንዳልሆነች የማወቅ ትምህርት የጎደለን
ይመስላል።
የሁላችንም ስለሆነች እንንከባከባት እንውደዳት ከዘራፊዎችና ከ አጭበርባሪዎች እንጠብቃት ዘንድ
አምላካችን ይርዳን!
አሜን!!!!