Thursday, May 5, 2011

ትኩስ ዜና!

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!

ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።


ትኩስ ዜና!

እንደምን አላችሁ? የሚቀጥለውን ዜና ያገኘነው ከእናንተ ከተማ ከርማ የተመለሰችው አባላችን አዲስ ከተዋወቀቻቸው ወዳጆቿ ትላንት ማታ የደረሳትን ዜና ነበር። እንደሚታወቀው ሁሉና ደጋግሞ እንደተዘገበው እጃቸውን ይሰጣሉ ወይንም በቁጥጥር ሥር ይውላሉ የተባሉትን በትላንት ማምሻ መፈጸሙን ነበር።

ይህንን ዜና ከመቋጨታችን በፊት፣ ይህንን ገጽና ሰንበቴ የተባለውን ብሎግ ማንነት ለማወቅና ለመቅላት ጉግልን መረጃ እንዲሰጣት የፍርድ ቤት ትእዛዝ ያወጣችውን ግለሰብ ነገ ከእርሷ ቤሮ ኮምፕዩተር ወይንም ባሏ ከሚሰራበት ካቶሊክ ቻሪቲ ኮምፒዩተር ብንዝግብባት ምን ልትሆን ይሆን? እኛን ጸጥ ለማሰኘት ለይታ የተነሳችው ከማን ጎራ መሆኗን ስላስረገጠች የነተኩላው አጋርነቷን ይፋ አደርገች እንጂ ምንም አዲስ ነገር የለም። ሜይ 2 ያለፈው አመት ከተደራጁት አሸባሪዎች ጀርባ ከባሏ ጋር በመሆን ከሽብሩ በኃላ ስብሰባ በአዳራሹ በማድረግ ሥርዐቱን ለመናድና በአዲስ ተዋቅሮ ከውጪ ለሚጠብቀው የአባ ጳውሎስ ለላከው ጳጳስ ነኝ ተብዪ ለማስረከብ አልነበርምን? ትምህርት የሌላትና የሌሎች መጠቀሚያ ሆና የምትነዳው የመለስ ዜናዊ አምቻ ገንዘቡን ከየት አምጥታ ጠበቃ ቀጠረች? ከጠ/ሚኒስትሩ ፣ ከመንግሥት ወይስ ካቶሊክ ቻርቲ ውስጥ በሚደረገው የሕግ ወጥ ሰው ማስተላለፍ ንግድ ገቢ ይሆን? ስንቱ በስደት ሀገር ሲንገላታ የከፈለ ግን ከአዲስ አበባ በ3ኛ ሀገር አማካኝነት በሳምንቱ ዳላስ የገቡትን ስም እንዘርዝርና ትረፈው ይሆን? አሁን የነካሽ ሳይኖር ለምን የባልሽን የጡረታ መብት ልታስጠፊ ከሆነ ደሳለኝ እጅ ያገኘነው እንደዚሁም አሁንም እየደረሰን ያለው ብዙ ጉድ አለና አታስጨክኝን!

ገና ወር ያልሞላው የታደስ ተክላይማኖት የተባለው ቤተክርስትያንና ማስተዳደር ያቃተው የርእሰ ደብር ጊዮርጊስ ቤተክርስትያን ሰሞኑን ሲታሽ በከረመው ስብሰባ በትላንቱ እለት ለጳጳስ ተብዪው የጳውሎስ ቅጥርኛ እንዲያስረክቡና በእርሱ እንዲተዳደሩ ትእዛዝ ተሰጠ። ምሽቱን በህመም አለ የተባለው ታደሰም በጎ ማደሩን ባናውቅም ገና ሀኒሙኑን እንዳላስጨረሱት ከስብሰባው ተካፋዮች እህታችን ዘግባዋለች። ለጊዜው ወደ ሯሌት ከሰው ቤት ያረፈውም ጳጳስ ተብዬ ሥልጣነ ጵጵስናውን መንበር ወደ ዳላስ ለማዞር የቤት ኪራይ እየተፈለገለትወይንም ከህንጻው ውስጥ ቤሮና መኖሪያ ያደርግ ይሆናል የሚል ነውና ዳላሶች ተጠንቀቁ እንላለን።

ከዳላስ ሚካኤል ሠይፍም የደረሰን ለዚሁ እርክብክብ ዳላስ ከገቡት ውስጥ 2ቱ ባለፈው በሚካኤል ደብር የዳግማይ ትንሣኤን ካስቀደሱ በኃል እንደ እንግዳ ከምዕመናኑ ጋር ትውውቅ ሲያደርጉ ያረፉትም ከአዲሱ ካህን ቤት ሳይሆን እንዳልቀረ ተገምቷል። እንዚህን ግለሰቦች አጅበው ከመጡት 3 ግለሰቦች መካከል 1ኛው አደግድጎ ከመግቢያው በር ላይ 2ቱ ከምዕመናን ተደባልቀው ሲሰልሉ እንደነበርና በረኛውም በመጨረሻ እንግዳ ተብዬዎችን መቀላቀሉን አብሮ የደረሰን ዘገባ አመልክቷል። ይኽንኑ መሰሪያን ከመቼውም በላይ በመተባበር ደብራችሁን እንድትጠብቁ እያሳሰብን የተባበረና እውነተኛ አማኝ ከፈጣሪው ጋር ያሸንፋል። እንግዲህ ፖለቲከኛና ነጻነት የሚሹ ኃይሎችና ድህረ ገጾች ከጎናችሁ በመሆን የተደቀነባችሁን ፈተና እንድትወጡ ጥሪያችን ዳላስ ላይ ሳይወሰን ለሁሉም ወገናችን ጭምር ነው።
 
ሰፋ ያለ ዝርዝር ወደፊት ይቀርብበታል። ቸር እንሰንብት!

እርሶስ ምን ይላሉ?

No comments: