Thursday, July 7, 2011

ማርገብ ወይስ ማራገብ?

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!

ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም።


ማርገብ ወይስ ማራገብ?

የተወደዳችሁና የምንነፋፈቅ የገጻችን ተከታታዮች እንደምን ከረማችሁ? በልዑል እግዜአብሔር ፈቃድ ደግመን ብዕራችንን እንድንጨምቅ ወደ እናንተም እንዲደርስ ለፈቀደው ለእርሱ ሁሉም ክብርና ምስጋና ይሁንልን። ስለገናናው ስሙ በፍጥረቱ ዘንድ ሁሉ ይወደስልን። አሜን።

ጌታችን አምላካችንና ፈጣሪያችን በባዕድ ምድር አምጥቶ የማያልቅ ቸርነቱንና በረከቱን አፈሰሰልን። እጅ ለእጅ ተያይዘን በአንድነት እንግዳ የሆነውንና ያልታወቅውን እምነታችንን ከሩቅ ውቅያኖስን አሻግረን በየከተምንበት ሁሉ በማዳረስ ከአንድ ቤተክርስትያን ቁጥር እያበለጥን በእርሱ ጸጋ መብቃታችንን በማስተዋል ፈቃዱን በመቸሩ ምስጋናችንን ከልብ ማድረግ ይገባናል። ጽድቅ ባለበት ሁሉ አጥህ እንደሚያደናቅፈን መዘንጋት አያስፈልግም። እጅ ለእጅ ተያይዘን የጀመርነውን አብቦ ለተተኪው የማስተላለፍ ደግሞ የግድ ነውና በዚህ ሳምንት ማገባደጃ ላይ እየተካሄደ ያለው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታይ አማኞች በአይነቱ ለመጀመሪያ ጊዜ በሰሜን አሜሪካን በቴክሳስ ግዛት በዳላስ ከተማ አካባቢ የሚገኘው የደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ደብር የጀመረው ከታዳጊ እስከ ወጣት የሚያካትተው መንፈሳዊ ጉባኤ ታላቅ ቦታ ይሰጠዋል። በተለይም ከአመት በፊት ይህ ደብር ከተወሳሰበ ፈተና ብቻ ሳይሆን ሕልውናው አደጋ ላይ እንደነበር ለማንም ግልጽ ነው። እነዚህ ጠላቶች በተለያየ መልኩ የከፈቱበትን ፈተና በእግዜአብሔር እገዛ ለዚህ ታላቅ ምዕራፍ ጎህ ቀዳጅ ሆኖ በመገኘቱ ደግሞ ደስ ሊለን ይገባል። እኝባችንን አብሶልናል ጸሎታችንንም ስምቶናልና። ለፈጣሪያችን ምስጋና ይሁንልን። አሜን።

ዛሬም እንደዚህ አሜህላ የሆኑ እህትና ወንድሞች ጨርሰው አልጠፉምና በጸሎታች በርትተን መጽናት ይገባናል። ፈጣሪም እንደዚ ያሉትን እጸጽ ከማራገብ አውጥቶ አርጋቢ ያድርግልን እንላለን። የተከፈተው የወጣቶች ጉባኤ ወጣቶቻችን የምንጠብቅባቸውን የተረካቢ ጎዳና ውስጥ እንዲሳተፉ ፈጣሪያችንን እንማለዳለን። አንድነትና ሕብረታችንን ይጠብቅልን። ቤተክርስትያናችንን ቅን አገልጋዮቿን ይጠብቅልን። ጉባኤውንም የታቀደውን ግብ ያድርስልን፡። አጽራረ ቤተክርስትያንን ያስታግስልን። አሜን።

ከዚህ ፈቀቅ ስንል ደግሞ የዳላስ መረዳጃ ማህበርን አስመልክቶ ባለፈው ያወጣነውን ትኩስ ዜና የከተማችሁ መነጋገሪያ እንደነበርና ግንዛቤን ያጫበጠ መሆኑን ከሚደርሱን አስተያየቶች ስላገኘነው፣ ስለተሳትፎዎቿችሁ ልባዊ ምስጋናችን ይድረሳችሁ። ቀደም ሲል የነበረው ሴራ ውስብስብ እንደነበር ከመኃላችሁ የተረዱት በጣት የሚቆጠሩ ቤሆንም ቀደም ብለው ፊት ለፊት የገጠሟቸውን ወይዘሮ ላይ የከፈቱት ዘመቻና የግለሰቧን ቆራጥነት ገጻችን ታደንቃለች። የተራዷቸውና የደገፏችውንም ምስጋና ይድረሳችሁ እያልን ድርጅቱ ባለቤቱ ለሆነው ወገኖቻችን ተመለሰ ለማለት የሚያስችለው ፈጽሞ ሲጠራ ብቻ ነው።

በተለይ ድርጅቱን ለማጥፋት ዘመቻው የተጀመረው ቀደም ሲል ነበር። ወደመረዳጅው ማህበር ዘልቀው በመግባት የተቆጣጠሩት ጥቂት ግለሰቦች በእድር ሽፋን የሕይወት ኢንሹራንስ ለመሸጥ ነበር። እነዚህ የኢንሹራንስ ደላላዎች የታያቸውና የታወሩት በግል ጥቅም ብቻ ስለነበር፣ አጋጣሚው ድርጅቱ ደካማ እንዲሁም ተቆርቋሪ የለውምና ፤
1. የመረዳጃ ማህበሩን ሕጋዊ ስምና ፈቃዱን በማብከን። ጊዜው ሲደርስ ደግሞ በእራሳቸው ስም የማውጣት ቁልፍ ዋነኛው ስልትና በስሙ ከተለያየ መንግሥታዊና ግላዊ ድርጅቶች በኢትዮጵያውያን ስም ገንዘብ ማግኘት ነበር። ምሳሌ አውራዎቹ የፈጠሯቸውን የግብረ-ሰናይ ስሞች ብዛትና ማን ማን እንደሆነ እኛና ሌሎች በገጾቻችን ያስነበብነውን ማየቱ ይጠቅማል። ለዚህም ነበር የዳላስና አካባቢውን የኢትዮጵያን መረዳጃ ማህበር ሕጋዊ ፈቃድ አብክነው የነበሩ።
2. መረዳጃ ማህበሩ በድህረ-ገጹ እንዳስቀመጠው እድሩ በስሩ እንዳለ ያደረገውን አስነብቦናል። ነገር ግን እድሩ የተቋቋመበት ጊዜ መረዳጃ ማህበሩ ሕጋዊ ሰውነት የሌለውና ፈርሶ እንደነበር ይታወቃል። አላማው መረዳጃ ማህበሩ ስሙ ከመከነ በኃላ በግለሰብ ስም ለመተካትና ማንም ሳያውቅ ለመበዝበዝ ሲሆን፤ ይህ ቢታወቅም አንዴ ሕጋዊ ሰውነትን ከያዘ ማስመለስ አይቻልምና። ይህን እስከለጠፍንበት ደቂቃ እድሩ ምንም አይነት ሕጋዊ ሰውነት የሌለው ነገር ግን በጠረፔዛ ስር የተደረገ ሕገ ወጥ እድር ነው። ይህንንም ጊዜዊ ከለላ ያስተናገደው የቀድሞ መረዳጃ ማህበር አመራር ሲሆን የአሁንስ ምን ይል ይሆን? ዋናው አላማ እድሩን በመረዳጃው ማህበር ለመተካት ወይንም መረዳጃ ማህበሩን ለማገት ሲሆን፣ በዚህም ኢንሹራንስ ደላሎችም በእድር ስም ነገር ግን ጃንጥላ የተባለውን መድህን በመግዛት ከሆነ የራሳቸውን መድህን መክፈት ካልሆነም መሀል ቤት ሆነው ወገኖቻችንን መዝረፍ ነው። ነገርን ነገር ያነሳዋል እንዲሉ፤ አሁን እድሩ እክል ላጋጠመው መክፈል ባይችል ተጠያቂው ማነው? ለሚለው ጥያቄ ማንም የለም ነው መልሱ።።

ምክንያቱም እድሩ ምንም ሕጋዊ ሰውነት የሌለውና ተጠያቂ የሚሆን ሕጋዊ ተወካይ የሌለው ነው።
መረዳጃው ማህበርም ቢሆን ህገ ወጥ ስራ ሲሰራና በተባባሪነት ስሙ ሲጠቀስ እንጅ በመተዳደርያ ደንቡ ላይ ያልተቀመጠ በመሆኑ አላውቅም ባይ ይሆናል። ከዚህ ጋር ተያይዞ ሂሳብ ደብተሩ በገለልተኛ አካል ተመርምሮ ያልተረጋገጠና ሀቀኛ ቁጥሩ የማይታወቅ መሆኑን በተግባር ያሳየ ነው። መረዳጃውም ቤሆን በሂሳብ አያያዙ ላይና ቁጥጥር የማያደርግለት መሆኑ ይታወቃል። እድሩ ስም እንጂ በራሱ ገለልተኛ ነው። ሕጋዊ ፈቃድም በምንም ጎኑ የለውምና። 500 በላይ አባል አለን የሚሉትና አመራሩን የያዙት ቢሆኑም እምነት የማይጣልባቸውና በወገኖቻችን ላይ ለሚደረገው ስውር ብዝበዛ ተጠቃሚዎች እንጂ ንጹሀን እንዳይደሉ እናሰምርበታለን።

ዘግይቶ እንደደረሰን ከሆነ ባለፈው ሳምንት ለወራት የመረዳጃ ማህበር ሊቀመንበር የሆነው ብርሀን aka ማክ መኮንን ለቦርዱ እንቅፋት በመሆኑ ቦርዱ በመረጃ በተደገፈና በአንድ ድምጽ ወስኖበት እንደነበር ነው ግን ከእነርሱ መግለጫ ስላልመጣ አልፈነው በእርሱ ፈቃድ እንደለቀቀ አድርጎ የበተነውን ያነበባችሁ ሁሉ ትገነዘባላችሁ እንላለን። በጥሁፉ ላይ ከጠቀሰው ስም አንዱ የበተነውን ኢ ሜይል እንደዚህ ይነበባል።


--- On Tue, 7/5/11, Daniel Gizaw wrote:

From: Daniel Gizaw
Subject: Emergency meeting
To:
Date: Tuesday, July 5, 2011, 10:14 AM

SELAM  All EDIR members,

You might have heard the Ethiopian Community Radio Ato Birhan  on Sunday the MAAEC chairman  calling an emergency meeting. When there is an impasse to resolve an issue or issues the by-law give the chairman authority to call an emerngency  meeting. The Board members division is a sign of unhealthy atmosphere which  take our community and EDIR backward.  Therefore, we can not stress enough that your participation on the meeting which is going to be held July 10th at Double tree Hotel located at Central and Campbell.

We highly encourage you  to pass this information to EDIR members that you know.

Thank you very much

The EDIR  secretary  

Daniel Gizaw

እንግዲህ ከጠሀፊው አጻጻፍ የስፔሊንግና የግራመር ጉድፉን ለእራሱ በመተው ( ሊያው ሚስቱስ ቢሆን የመረዳጃው ማህበር በጠሀፊነት ተቀጣሪ ተመሳሳይ ችግር ያላት ስለሆነች ባልና ሚስት ከአንድ ውኃ ብለን እንለፋት)። የጥሁፋችን መነሻ ያደረግነው ‘ማርገብ ወይስ ማራገብ’ ወደ አልነው እርእስ ቢወስደንም አንባቢ የራሱን ግምገማ ያድርግ እንላለን። እንደ ደረሰን አስተያየቶች እንግዲ አቶ ብርሀን  ለግለሰቡና ለሚስቱ በጣም የተነካ ባስመሰለው የስንብት ጥሁፉ ካዘነላቸው፤ በግሉ ከሚያስተዳድረው ንግድ ቤት በቂጣ ጠፍጣፊነት ወይንም በፒሳ አድራሽነት የተላላኪ ስራ ውስጥ ቢዶላቸው እንጂ እርሷ ለመረዳጃው ማህበር ሳይሆን አብዛኛውን ጊዜዋን የምታጠፋው ለቢሮው ተጋሪዎች በማገልገል ሲሆን እርሱም መረዳጃውን በእድርና በሕይወት ኢንሹራንስ ድርጅት ለመተካት ነው። ምናልባትም አቶ ብርሀንም የዚያ ራዕይ ተጋሪ ለመሆን አስቦ ይሆን? ስለነእነርሱ የአዞ እንባ የያዘው። የተመረጠው ለመረዳጃው ማህበር ጥቅምና ጥቅም ብቻ መሆኑን አላወቀውምን?

ይህ የተበተነውና ተጠራ የተባለው ስብሰባን በተመለከተ የሚመለከታችሁ ሁሉ በቀጥታ የመረዳጃ ማህበር ተመራጮቹን በማነጋገር መረዳት ይገባችኃል። ጠሪው የቀድሞው ሊቀመንበር በግሉ እንጂ መረዳጃው እንዳልሆነ ስላረጋገጥን ይህ ሕገወጥ ስብሰባና ወገኖቻችንን አንድነት የሚያናጋ ሰይጣናዊ ስብሰባ ነው። የመረዳጃውንም ማህበር እንዲፈታተን ጥቅማቸው የተነካ ግለሰቦች አብረው የሚደልቁት ከበሮ ነው እንላለን።  

በሚቀጥለው መጣጥፋችን እስክንገናኝ፤ ለሁላችንም ማስተዋልና ቅንነትን ይስጠን። ከመካከላችሁ አሜኸላ የሆኑባቸሁን ውንድሞችና እህቶች ፈጣሪ ልቦናቸውን ይመልስልን፤ ቸር ወሬ ያሰማን ፤ በቸር ያገናኘን። አሜን።

እርሶስ ምን ይላሉ?

No comments: