የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና! ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም።
ፍልፕ ፍሎፕ / flip-flop
የጎረፉልን መጣጥፎች ብዙ ናቸውና እኛም ሆን በማለት ያደፈጥነው ብዕራችን የምትጨምቀው ቀለም ደርቆ ሳይሆን በተቀጣጠለው እሳት ላይ በዚህ በጋ የድርቆሽ ሣር ላለመጨመር አሊያም እንደ ቀያችን አዋራው እስኪከስም ለሰላም ፣ ለፍቅርና ለአንድነት ባለን ቅንነት በመሆኑና ጦመሯ የተደባየውን ለመለይት ወጀቡን ስታመዛዝን መሆኑን ለመጠቆም በቅድሚያ ትዳዳለች። የተወደዳችሁ የገጻችን ተከታታቶች እንደምን ከርማችኃል? በሰላምና በጤና ጠብቆ ለጠዋት ማታ ጸሎታችን ምላሽ እያደረገና እንባችንን እያበሰ ላለለውና ለፈጠረን ልዑል እግዜብሔር አሁንም ክብር ምስጋና ይሁን! ወደፊትም እስከመጨረሻው ይሁንልን። አሜን።
ከሁሉ በፊት ያሳሰበን ሁለት ነጥብ ልንጋራችሁና ከጸሎታችሁ እንድታስገቡት የሚያስፈልግ ማሳሰቢያ ነው።
1. በአሁኑ ወቅት በትውልድ አገራችን ላይ እንዲሁም በአካባቢው አጎራባቾችን ጨምሮ የደረሰው የአየር መዛባት ከፍተኛ የሆነ የረአብ አደጋ መድረሱን የሁላችንም ግንዛቤ ነው። ምንም አይነት ምክንያትና ሰበብ ሳንይዝ የተቻለንን መርዳት ለየትኛውም ዕምነት ተከታይ የሚጠበቅበት ብቻ ሳይሆን ሰብዐዊነትም ጭምር ነው። አማኝ የሆነም ሆነ የሆነች ሁሉ ከእርዳታ ጋር ፈጣሪንም በፀሎት መጠየቅ ይገባል።
2. በሀገራችን አሜሪካን ምክር ቤት የተፋጠጡበት የእዳ ጭመራ ውዝግብን በመግባባት በቶሎ ይቋጩት ዘንድ ማሳሰብና መፀለይ ይገባናል። ምክንያቱም አሁን ያለው ምጣኔ ሀብት ቀውሱ አለምን እያናጋና ብዙዎችን ከኑሮ ሕይወታቸው ዛሬም እያናጋው ያለበት ወቅት ላይ ይኼው ሲጨመርበት ወደ ባሰ ጎዳና ይገፋዋልና የየትኛውም የፓለቲካ ፓርቲ ደጋፊና አባል የሆናችሁ ሁሉ ለምክር ቤቱ ተወካዮቻችሁ ማሳሰብ ተገቢ ነው በማለት ገጻችን ያሳሰባትን አበይት ትኩረት ታካፍላለች።
የኛን ገጽ ለማንበብ የምትናፍቁ ከልብ የምትውዷት ወዳጆችዋ ብቻ ሳትሆኑ በኛ ዝምታም ግራ የሚገባቸውና ቀልባቸውን የሳበቻቸው ውስጥ ቅድሚያ የምንሰጣቸው በገጻችን ስማቸው የተጠቀሱት ሁሉ በምጎሳም ሆነ በነቀፊታ ሱስ ሆናባቸው እንዳለች ፀሀይ የሞቀው እውነታ ነው። ነቀፊታችን የሚመራቸው ሁሉ በገጿ ላይ ከመፋጨት ይልቅ ወደ ቅንነትና ወደ በጎ መስመር ገብተውልን ለማየት ለፈጣሪያችን የዘወትር ፀሎት ከማቅረብ አልቦዘንም። ሁላችሁም በዚህ ብትተባበርሩ ገፃችን ደስታዋ የላቀ ነው። ሌላው ወገን ደግሞ የድርጅት ሱሰኞችን ገጻችን በሰፊው አፍርታለች። በአውሮፓና በአሜሪካ ተቀማጭነትን ይዘውና እንዲሁም በኤትዮጵያ ውስጥም ያሰረጉት የትግሬ ነፃ አውጪ ምንደኞች ፣ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ ከሊቀ ጳጳሱ ጀምሮ እንዲሁም የማህበረ ቅዱሳን የተባለው የከልት ቡድን በሀገር ቤትና በውጪ ያሉትን ፣ ብሎም የአጽራረ ቤተ ክርስትያን ቡድን ሆነው ፤ አንዳንዶችም የሀሰትና ፍሬ አልባ ግብረሰናይ በማቅዋቋም የሚንቀሳቀሱትን ያካትታል።
ከላይ እንደጠቀስነው ብዙ አስተያየቶች ቢደርሱንም ሆነ ከዝህ በፊት የኮነንነው ምግባርም ገና ዳኛው ሳይፈርድ ነበር አካሄዱን የምናስተውል። በተለይ በአእምሮ ኹከት ምክንያት የምትቸገረው እህት ቀደምትነትና እንደእርሷ ለይቶ ለሕክምና ያልዳረጋቸው ነገር ግን የጤናው እውክታን በተለይ መልኩ እየተገበሩ ያሉት ከዳላሱ የቅዱስ ሚካኤል ጋር ያላጋቸው፤ ትሁትና ታጋሽ መልአክትነቱን ሊመክረን ደገመ እንጂ በእነርሱ እንደማይወድቅ አረጋገጠልን። ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤትም ደገመልን። በዚህ ላይ የምንለው ቢኖር የደብሩ ጠበቆች በቀጥታ ይግባኝ የተባለበት ጉዳይ ፍርዱን የሰጠው የበታች ችሎት ነጥብን ብቻ እንጂ ተጨማሪ አቤቱታን እንደማያይ እንዴት መረዳት ተሳናቸው። በወቅቱ አመራር ላይ የነበረው አስተዳደር መወሰን የነበረበትና የመጀመሪያ ክስ ሲደርሳቸው ፤ የክስ ክስን አስገብተው ቢሆን ኖሮ የታችኛው ችሎት ይወስን ነበርና ዛሬ ደብሩ አዲስ የኪሳራ ክስ ለመክፈት ወደ ሌላ ጎዳና ባልተመለከተ ነበር ብሎ ያስመዘገበን የሚካኤል ሠይፍ ከሚናለው ቡድን ተወካይ ነው።
2. ተወካዩም አያይዞ ካቀረበልን ውስጥ ፤ በተኩላውና ብጤዎቹ የተከፈተው ክስም የመጨረሻ ውስኔ ሊሰጥበት ሲጠበቅ ከሳሽ ክሱን አንስቻለሁና ጉዳዩ ይዘጋልኝ በማለት ያቀረበው መንገድ አደገኛ ስለሆነና ለሌሎችም በር የሚከፍት ስለሆነ በመመሪያ ተቀብሎ ነገር ግን ኪሳራዬ ይከፈለኝ የማለት መብቱን ማስጠበቅ አለበት። ይህ ካልሆነ የህግ አማካሪዎቹን ባስቸኳይ መለወጥ ካልሆነ ፤ አሁን ያለው አመራርን መለወጥ የግድ ይሆናል።
ሌላው ከዚህ ቀደም አስተዳደር ቦርዱ ለ2 ጌዜ የጠራው ስብሰባ አስፈላጊው ቁጥር ባለመሟላቱ መሰረዙ የታወቀ ነው። በወቅቱም በድጋሚ ጭምር የተገኙት አነዚያ ብቻ ናቸው በኦገስት 6 ስብሰባ ይጥራልን ብለው ባቀረቡት መሰረት ሲሆን አሁንም እነአርሱ ብቻ እንጂ ሌላ ክርስትያን ለነገርና ለክርክር አልፎም በእነርሱ ሊስሟጠጥ ብሎም ሊሰደብ የሚመጣ የለም። ካለእነርሱ ሀይማኖተኛ ለአሳር ፣ እንእርሱ ብቻ ለደብራችን እጣ ፈንታ አዋቂ ፣ ከዚህ ካሳለፍነው ፈተና የዶሉን እነእርሱ፣ ቆራቢም እነእርሱ፣ አስከሳሽና አካሻሽ እንእርሱ፣ ቅን አገልጋዮችን አዋኪና እንቅፋት እንእርሱ። ዛሬማ እኛ ብቻ የአሽከርካሪውን መቀመጫ ካልያዝን ሌላው መንዳት እንደማይችል ወይንም ማሽከርከ እንደማያውቅ ነው የሚያምኑ በማለት የሚካኤል ሠይፍ ተወካይ ደምድሞልናል።
ተኩላውና አጋሮቹ እንደገና ክርስትና ተነስተው ነው ወይስ የትግራይ ነጻ አውጪ አዲስ ብልሀት መመሪያ ተቀብለው ይሆን። በክርስትናው ከሆነ ደብሩን በግልጽና ባደባባይ የበደሉትን ምዕመን ጨምሮ ካሕን ይዘው መጠየቅ አሊያም ለሰይጣናዊው ምግባር ከሆነም ከፈጣሪ ያገኙታል። አሁንም በቁም እየተቀበሉት ነው። ለዚህም እንደሀገራችን አባባል ፍልፕ ፍሎፕ ያልነው’ በተለይ ተኩላው በወጣትነቱ ነበር ለትውልድ ሀገሩ ቃል ገብቶ መለዮ ያደረገ ክዶ ከኢሕአፓ የተቀላቀለ። አሜሪካ ከርሞ ኢሕአፓ ሆኜም አላውቅ ሲል በሌላ በኩል እዚያው ይልከሰከሳል። እኛ እስከምናውቅ በደብሩ መተዳደሪያ አርቃቂነት ከነግርማቸው አድማሴ ጋር ከአዲስ አበባ መመሪያ እየተቀበሉ የጣፉት በመውደቁ ያኮረፈና ልክፍቱ የተቀሰቀሰበት ትላንት ለመብቱ ነው ብሎ ከብጤዎቹ ጋር አብሮ የከሰሰውን ለምን እስከ ውሳኔ መጠበቅ አቃተው? ከታሪክ እንደምንረዳው ለመብታቸው የቆሙ እስከመጨረሻው መሰላል ይወጣሉ እንጂ እንደ እርሱና ቢጤዎቹ አያፈገፍጉም። ምናምንቴ ፍልፕ ፍሎፐር!
ሌላው ፍልፕ ፍሎፐር ደግሞ ብርሀን መኮንን aka ማክ መኮንን ነው። ሕዝብን መምራት እንደሚጠፈጥፈው ቂጣ መገለባበጥ መስሎት ይሆን የተጣለበትን ሀላፊነት ሸጦ ሲያበቃ በፈቃዱ ከለቀቀ በኃላ አማልዱኝ ብሎ ሰብስቦ መልሱኝ ማለት ምንድን ነው። ቂጣ መጠፍጠፍ ሌላ ሙያ ሕብረተሰብ መምራት ሌላ መሆኑን አላወቀምን? መረዳጃ ማህበር አመራር 101 ትምህርት የለውምን? አሁንስ በመልቀቂያ ወረቀቱ እንደተናዘዘው ሊተገብር ዘዴ ብሎ የያዘው ይኖር? ይህ ግለሰብ ባለፈው ሕብረተሰቡን ለመከፋፈል ዛሬም በሪዲዮኑ እየወጣ ያውካልን? ለማን እንደሚሰራማ በግልጽ በበተነው አይተነዋልና ለምን መለሱት? ብቻቸውን የቀሩ የእርሱ ቢጤዎች ካመራሩ ይኖሩ ይሆን? የእርሱ መመለስ ከጉዳቱ ጥቅሙ ምንድን ይሆን? የገባውንም የገንዘብ ቃል እስከ ዛሪ እንዳላስገባ ነው መረጃ የሚያሳየን ፣ እንግዲህ መጨረሻውን እዛው ለናንተ ዳላሶች እንተወዋለን።
በተለይም በዳላስ ስላለው አለም አቀፍ የምዕመን ማህበር ስለሚለውና የኢትዮጵያን ቀን በዳላስ አንባቢ እንዲያውቀው ገጿ ያዘጋጀችውን እንደ አመቺነቱ ወደፊት ታስነብባለች። ማህበረ ቅዱሳን aka ማቅ የተባለው ከልት እንደምህጻረ ቃሉ ማቅ እየለበሰ ነው። ቅንነትና ከልብ ያልሆነ ሁሉ ግዜ ይፍጅ እንጅ እውነቱ ገህድ ወጥቶ ፀሀይ እንደሚሞቅ የታወቀ ነው። በሰሜን አሜሪካ ያለው የነርቭ ሴንተራቸውም ሁኔታዎችን ለመቆጣጠር ከአቅሙ በላይ ሆኖበት ምናልባት ሌሎቹን ተሀድሶ ባለበት አንደበቱ ዛሬ ተሀድሶ ለእርሱ ወይንም አብሮ ወደ መቃብር ወራጅነቱን ከሚደርሱን ዘገባዎች ልንረዳ ችለናል። ይህም ከሚከተሉት የብዕር ጨመቃ ስራዎች የሚካተት ይሆናል። ለዛሬው ቸር ያሰማን በማለት ስንሰናበት መልካሙን ሁሉ እየተመኘንላችሁ ነው።
እርሶስ ምን ይላሉ?
No comments:
Post a Comment