Saturday, August 6, 2011

እንድምን ከረሙ?

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና! ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም።


እንድምን ከረሙ?

ለተወደዳችሁ የዚህ ገጽ ተከታታዮች፡ እንደምን ሰነበታችሁ? ሁላችንንም በአንድነትና በሰላም ጠብቆ ለዚህ ላደረሰን ለልዑል እግዜአብሔር አሁንም ከሁሉ በላይ ክብርና ምስጋና ይሁንልን። ፀጋ፣ፍቅሩ፣ በረከቱና ጥበቃው አሁንም አይለየን። በመካከላችን ያለውን ልዩነትን ሁሉ አጥፍቶ በመካከላችን መተሳሰብና አንድነትን ይሰጠን ዘንድ ፈቃዱ ይሁንልን። አሜን።

ባለፈው ጥሁፍ እንዳመለከትነው ሁሉ ፤ የሚጣፍ እንዳለን ነበር። እርሱን ለጊዜው በመዝለል በ08/06/2011 በዳላስ ደብረ ምህረት ካቴድራል ደብር ስለተጠራው የአባላት ስብሰባ ከሚካኤል ሠይፍ የተወረወረልንን በማስቀደም ይሆናል። ይህንን በግምባር ቀደም ተወካይ ያደረጉት ልዕል ሰገድ አበሻው የተባለውን ነው። ለስለስ ያለ የሚመስል ነገር ግን ተመራጭ በነበረበት ወቅት ሆነም ከዚያ በኃላ የስውር አመራሩን በቀደሙት ተመራጮ ላይ ጫና ያደረገና እንደለመደው በአሁኖቹም ላይ ሊያደርግ ያሰበውን ስውር አመራር ባለማግኘቱ በትግሬ ነጻ አውጪ ምንደኞች ቡድን በመደባለቅ ከነ ጌታቸው ትርፌ ፣ ከነ ኪዳኔ አለማየሁ፣ ከነ በትሩና ከመሳሰሉት ጋር በመሆን ቢችሉ አመራሩን ለመገልበጥ ካልቻሉ ደግሞ የተጀመረውን የደብሩን የመሻሻልና የእድገት አቅጣጫ መግታት ብለውም መቀልበስ መሆኑንን አስረድቶናል። እነዚህ የትግሬ ነጻ አውጪ ምንደኞች አመራሩ ደብሩን ለውጪው ሲኖዶስ ሊሰጥብን ነው እያሉ በሬ ወለደ እያወሩ መሆኑንና ቅስቀሳቸው ምናልባት ኮረም ያስሞላልናል በማለት ለሁከት የተነሱ መሆናቸውን ነው። በዚህ ስብሰባም አብዛኛው አባል እንደማይገኝና እንዳለፈው ሁሉ እንደሚበተን ከወዲሁ ግምት አምጥቷል። ማን ነው በደብሩ ውስጥ ከነዚህ ነገረኞች ጋር ተቀምጦ ስብሰባ የሚያደርግ። ሁሌም እነርሱ አመራሩን ካልያዙና እንደፈለጉት ካላደርጉ ሌላው እንደማያውቅና መጥፎ አድርገው መቀባት ምግባራቸው ነው። በነእርሱ መሪነትና አማካሪነት የመጣውን ውድቀት ባለፉት ጥቂት አመታት የሁሉም ግንዛቤ ነው። በተለይ ቆራቢ ነኝ እየተባለ በፀሎት እንደመጠንከር ፊት አውራሪ ሆኖ ሁከትን መቀስቀስ ስይጣናዊ ምግባር መሆኑንን መቼ ይሆን የሚረዱት በማለት ደምድሞልናል።

ገጻችን ከታዘበችው ውስጥም በኢትዮጵያ ካለው ሲኖዶስ ስር ካሉት ጳጳሳትና ከህን ደብሩ ደጋግሞ ጋብዞ በኛ ሥር ካልሆናችሁ ምንም አይነት ግልጋሎት አንሰጥም በማለት አሻፈረኝ ያለው ወገን ሂዱና አስተምሩ ሲል ኢየሱስ ለግልጋሎታችሁ ካሳ ከምትሰጡት ተቀበሉ የሚል በመጽሀፍ አላየንም። አንድ አይነት እምነት ያለውን ወገናቸውን አናገለግል ያሉትና ፖለቲከኛ የሆነ አቋም የወሰደ ሲኖዶስ ያስፈልጋልን? የሚለውን ጥያቄ ለአንባቢያን በመተው፤ እኛ እራሳችንን በዋቢነት አድርገን የምንሰጠው ነጥብ ቢኖር የተሰደደው ወገናችን ለከፈለው ሁሉ እሰከዛሬ ድረስ ሲኖዶሱም ሆነ ቤተ ክህነት እንኳን ሕይወታቸው ላለፉት ቀርቶ በሕወት ላለነውም ዝምታን በመምረጥ የወሰደው አቋም ከክርስትና መንገድ የወጣ ነው። ቤተክርስትያን ስንከፍትም እንኳን ሊባርኩ ወይንም ካህን ሊሰጡ አንድ ጧፍ ጀባ ያላሉ ዛሬ ግን በግልፅና በስውር ለዘረፋና ለቅሚያ የሚያደርጉት የዶላር ሩጫ ነው። በሀገር ውስጥ ያሉትንም እያደኸዩና እንዲዘጉ እያደረጉ የሚገኙ፤ ከእምነቱ ይልቅ ለፓለቲካ ያደሩ ለመሆናቸው በተግባር እያሳዩን ነው። ሌላው ያሳደጉት ተኩላቸው ደግሞ ማህበረ ቅዱሳን / ማቅ የሚሉት ከልትም ካጀማመሩ የሀሰት ካባ ለብሶ ቤተክህነቱን ሲያተራምስ፤ ዛሬ መሪያቸው በግልጽ እንዳስቀመጠው “አባሎቻቸው የኢሀዴግ አባላት መሆናቸውን“ ነው። ከላይ መሪያቸው የትግሬ ነጻ አውጪ ማለት ነው።

በኛ አስተሳሰብ አባላቱ የፈለገውን ሲኖዶስ የመምረጥም ሆነ ገለልተኛ የመሆን መብቱን እንጠብቃለን። ነገር ግን ለእምነቱ ሲባልና ለተተኪው የኢትዮጵያ ተወላጅ እንዲሁም እምነቱን ላልያዙ ለሌላው ወገኖች የሚጠቅሙና ብቃት ያላቸውን ካህናትን ያቀፈው በሰሜን አሜሪካ የሚገኘው ሲኖዶስ ነው። በተለያዩ ደብሮች ካየነው ልምድ በቂ እምነትና ስረዐትን የሚከተሉ ተከታዮችን እያሰፉ ያሉትን ፣ ለሚሰጡትም አገልግሎት ንጹህና ምንም አይነት ስውር ተለጣፊ ምክንያትን የሌላቸው ሆነው አግኝተናቸዋል። በሀገር ቤትም ሆነ በውጪ ከፍተኛ ትምህርት ያላቸው እነዚህ አገልጋዮች፤ ሰሜን አሜሪካን እንደሀገራችን ለምናየው ሁሉ እጅግ በጣም ተስማሚዎች መሆናቸውን ነው። በየትኛውም ጊዜ ለአገልግሎት ቢጠየቁ በቅርብ ሊገኙ የሚችሉ የተትረፈረፈ የሰው ሀይል ያላቸ ሆነው ነው የሚታዩት። ስለዚህ የትኛውንም ሲኖዶስ መከተል ወይንም ገለልተኝ መሆን መንግሥቱን አያወርሰንም፣ ነገር ግን እምነትና ምግባሩን መጠበቅ ነው ።  በመጀመሪያ የውስጥ የውጪ በማለት ለመከፋፈል ምክንያትን ከማዳነቅነት፤ ለተለያዩት አባቶች አንድነትና መግባባትን አጥብቀን መጸለይን ማዘውተርና የሀገር ቤቱም ሆነ የውጪው ተከታይ እንደሚመቸው እያመለከ እንጂ ለማንንም ተጽእኖ ማደር የለበትም በማለት ገጿ ታስገነዝባለች።

ይህን ጥሁፍ ከመለጠፋችን በፊት ዘግይቶ በደረሰን ዘገባ መሰረት፤ ሚስትና ባል በመሆን ላስጠሩት የአባላት ስብሰባ በቅዱስ ሚካኤል ደብር ዛሬም ኮረም ባለሞምላቱ መበተኑን ነበር። ነገር ግን እንወያይ በማለት ሰይፉ ይገዙ የተባለውን እንዲመራቸው አድርገው የመጨረሻ እስትንፋሳቸውን እየተነፈሱ መሆናቸውን ነው። ሰይፉ የተባለውም ግለሰብ በሁለት ቢላዋ ለመብላት እየተንቀሳቀሰ እንዳለ አስምሮበታል። በሌላ በኩል ደግሞ ኢዮኤል (ክፈተው) ነጋ የተባለውና ላለፉት ችግሮች መሪ ብቻ ሳይሆን አሁንም በከሳሽነት ከስብሰባ የተባረረው ሀይሉ (ቀዩ ሰይጣን) እጅጉና የትግሬ ነጻ አውጪ ቅጥረኛ ከሆኑት ጋር ደስታ በተባለው ምግቤት ሲዶልትና መመሪያ ሲቀበል ቆይቶ ወደስብሰባው ያመራው። እንግዲህ ይህቺ ጥለናት ለምንሄድ አለም ይህን ያህል በዕምነት ስፍራ መባላትና አፍራሽ መሆንን ከፈጣሪ እስኪያገኙትና እርሱ እስኪመክራቸው መታገሱ ሳያሻ አይቀርም። የታደለማ  ነገር ሳይሆን በፍልሰታ ዋዜማ ለሱባኤ ይዘጋጃል እንጂ የቤተክርስትያንን ሰላም ለማወክ አይሰበሰብም። ቆራቢ ነን የሚሉትስ ምን ይመልሱ?

ከዚህ ደግሞ ፈቀቅ ስንል ወደ መረዳጃ ማህበራችሁ ትንሽ የምንለው አለን። አንዳንድ ጊዜ ቃላትን ባለማወቅ ወይንም ከመሀል አንድን ቃላት ብቻ ወስዶ የራስን ትርጓሜን መስጠት አላግባብ እጅጉን ጎጂ ነው። ከጥቂት ሳምንት በፊት የዳላስ የኢትዮጵያ መረዳጃ ማህበር ሬዲዮ ስርጭት ካለንበት ሆነን በኢንተርኔት ስንከታታተል አቅራቢዎቹ ከሪዲዮ ጣቢያው ሀላፊ ጋር ያደርጉትን ስምተናል። ዲ መጋዘን የተባለውንም ቃኝተነዋል። የተጣፈው ስለሬዲዮ ጣቢያው ምግባር ሲሆን ከሚሸፍናቸው የህብረተሰብ ክፍሎቹ በማነጻፀር ዝቅ ብሎና አናሳ ከሆኑትና በከተማው ውስጥ በአስተዋጾ ደርጃ እውቅና ያላስመዘገቡትንም በምሳሌ አድርጎ ወገኖቻችንን ጠቀሰ እንጂ ሌላ አይደለም።

2ኛ/ በቅርቡ መረዳጃ ማህበሩ በጠራው ስብሰባ ላይ ይኽው ግለሰብ አንዲቷ እህት ተመራጭ ካሉት አረፍተ ነገር ውስጥ በእንግሊዘኛ ካሉት ውስጥ ብቻ አንድን ቃል በመውሰድ ሕዝቡን እንዲ ብላ ሰደበች ብሎ ያለውን በዲኤፍ ደብልዩ አማርኛ ገፅ በማንበብ ላደረግነው መከታታተል አሁንም ዳግም ስህተት አግኝተንበታል። ሴት እህታችን ያሉት “እኔ የምሰራውን የማላውቅ ደደብ መሰልኩህን “ የሚል ጥያቄን ያዘለ መልስን እንደነበር ነው። በዚሁም ወቅት ግለሰቡ በእታችን ላይ ያሳየው ሁለንተናዊ ባሕርይ ወደ አካል ግጭት የሚያስገባ እንደነበር ከስፍራው የደረሰን ዘገባ ያስረዳል።

እንግዲህ ዘውገ (ዝንጀሮ) በስውር የትግሬ ነጻ አውጪ ቅጥረኛና የሬዲዮ ተስፈኛ በነጻ ማገልገል ሲገባው፣ እርሱ ግን ለጥቅም ያደረ በመሆኑ በማስታወቂያ ስም ለሚገኘው ገቢ እንጂየነጻ አገልጋይ አለመሆኑን። መረዳጃው ግን እያስተባበር የአየር ሰዐቱን የሚሸፍንለት፣ በቂ እውቀትና ስልጠና የሌለው ነው። ለዚህም ነው እንዲገባው ሙያ አድርጎ እንዲይዘው ከፈለገ የእንግሊዝ ቋንቋን 101 መውሰድና በሙያው አንዳንድ የማሻሻያ እውቀቶችን ቢገበይ የሚሻል ። በሬዲዮም እየወጣ መዋሸቱን ያቁም።

ሌላው ለረዥም ጊዜ ሲካድ የቆየው የመረዳጃ ማህበር ተዘግቶ የነበረበትን በዚህ ስብሰባ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ኮለኔል ሊበን የተባለው የቀድሞ አመራር አመነ። የጴንጤ እምነት ተከታይ ነኝ የሚልና ሲክድ አመታትን ያስቆጠርው ሊበን የዕምነቱን ተከታዮችን አንገት አስደፊና አሳፋሪ ሆኖ ለትዝብት በቅቷል። ይህንንም ሊያምን የተገደደው በኛ ገጽ ቀደም ብለን ያወጣነውን ማስርጃና በስብሰባውም ላይ ወ/ሮ የሐረር (የኢትዮጵያ) ወርቅ ጋሻው የተባሉትና የከተማችሁ የሰብዐዊ መብት ተሟጋችና ቀስቃሽ ተገኝተው ለአመራሩ ካስረከቧቸው መርጃዎች አባሪ ሆኖ በመቅረቡ ነበር። እንግዲህ በዚህ ወቅት መረዳጃው ሕጋዊ ሰውነቱን አብክነውና ጊዜው ሲደርስ እራሳቸው ስሙን ወስደው በስማቸው ፈቃድ በማውጣት ለማካሄድና ወገኖቻችንን ለመዝረፍ ነበር። በተለይም ከትግሬ ነጻ አውጪ ጋር ባላቸው ንኪኪ ለጥቅም ብለው አሳልፈው ይሸጡትም ነበር። ሌላው የመረዳጃ ማህበሩ በስሩ ያለውንም የሬዲዮ አየር ሰአትም ለነዝንጀሮ በግላቸው ሊሰጣቸው ሲል ደርሰው ያስጣሉት እኒህ ወ/ሮ መሆናቸው ፀሀይ የሞቀው ሀቅ ነው። ነገር ግን አንድም ወቅት የራዲዮኑን ስርጭት አስቁመዋል የሚል ምንም መረጃ እስከዛሬ የለም። መረዳጃውንም ከሳለች የተባለውም አፈታሪክ ሆኗል።  ግለሰቧ ሀቀኛና እውነትን ዳሳሽ በመሆናቸውና እራሳቸውን ለጥቅም ያላስገዙ በመሆናቸው በግለስቧ ላይ ዛሪም መተናፈሻ ያጡ ሕመምተኞች እየተወራጩ ይታያሉ። በተለይም መረዳጃው ፈርሶ እያለ በሕግ ወጥ መንገድ ያካሄዱት ውሳኔና ምግባር ብሎም በሌለ ድርጅት ስም ገንዘብ መሰብሰብ ከሕግ የተጻረረ ነው። ያስጠይቃልም።

ምሳሌ፡ ባለፈው ፍልብ ፍሎብ ያልነውና ቃል የገባውንም ገንዘብ ለመረዳጃው ያላስገባ ነገር ግን አንዴ ለቀኩኝ ሌላ ጊዜ አማልዱኝ አስታርቁኝ ባይና እንደሚጠፈጥፈው ቂጣ የሚገለባበጠው ፣ አሁንም በቃሉ የማይረጋና የአመራሩ ሊቀመንበር የሆነው ብርሀን (ማክ) መኮንን ወይንም ፍልብ ፍሎብ በግለሰቧ ላይ ዛሪም መሰሪ ምግባርን በመረዳጃው ማህበር ውስጥ እየሰራ ለመሆኑ የሚደርሱን ዘገባዎች ያትታሉ። ይህ ግለሰብ መረዳጃ ማህበር አመራር እውቀት የሌለውና ለመማርም ያልፈቀደ ዝግ ግለሰብ ብቻ ሳይሆን አደገኛ መርዝ ነው። ሊቀ መንበር ለቀረቡት ሀሳቦች ግራ ቀኙን በስርዐት እንዲካሄድ አድርጎ ለድምጽ ያቀርባል። እኩል ድምጽ ቤመጣ የመጨረሻ ድምጽ ሰጪ በመሆን ለውሳኔ ያበቃል። ውሳኔው እንዲተገበር ለፈጻሚ ወገን መድረሱን ያረጋግጣል። ከዚህ ውጬ ወጥቶ አሉባልታን ይዞ መርጃን ሳይጨብጡ ሊሎች የእርሱን አመለካከት እንዲደግፉለት ተጽእኖ ማድረግ ተገቢ አይደለምና ችሎታ ባለው መተካት አለበት። ባጠቃላይ ፍልብ ፍሎብ እየሰራ ያለው ከትግሬ ነጻ አውጪ ተቀጣሪዎች የታዘዘውን እንጂ ለዲኤፍ ደብልዩ ወገኖቻችን የሚበጅ አይደለም። ከዚህ በፊትም ወገኖቻችንን ለመከፋፈል የሞከረው ሲከሽፍበት መልሱኝ ምን አመጣው።
በመሪነቱ ብቃት እንደሌውና ከጎዳና መውጣቱን ለምን አደረገው?    

ባለፈው ጠቅላላ ስብሰባም የትግሬ ነጻ አውጪ አድርባይ ብቻ ነበር ሲደመጥ የነበረ። ከሁሉም በላይ የእያንዳንዱን ግለሰብ መረጃና ማንነትን የያዘው ኤሌክትሮኒክስ መረጃን አላስረክብም ብሎ የያዘውና የመረዳጃ ማህበሩን ድህረ ገጽ ያለአግባብ እየጠለፈ ያለው ዳንኤል የተባለው ግለሰብ ሕገወጥ ምግባር ነው። ይህ ግለሰብ የያዘው መረጃ ለ3ኛ ወገን አስተላልፎ ሰጥቶት ይሆን? ወይንስ ወደፊት ያደርገው? በተለይም ለትግራይ ነጻ አውጪ! እንግዲህ በመረዳጃውም ሆነ በእድሩ እስከ መለያ ቁጥራችሁ የሞላችሁት ቅጽ ካለ ከአሁኑ እርምጃ መውሰድ የናንተው ሀላፊነት ነው።

የትግራይ ነጻ አውጪ ወኪል የሆኑት በዚህ ስብሰባ ላይ ከሚሰጣቸው መድረክ አልፈው እስከ አመራሩ መድረክ ድረስ በመዝለቅ ሥርዐት አልበኝነታቸውን ያሳዩበት ስብሰባ ነበር። ኣንግዲህ እነዚህ ናቸው በዕምነት ማዕከልም ሆነ በሶሻሉም የሕብረተሰቡ ጠንቅና መርዘኛ። ለዛሬ በአብነት ከዚህ በታች ያለው ምስል በደርግ ውታደርነት በሩሲያ ተማረ የሚባለውና በኃላም ለትግሪ ነጻ አውጪ አገልጋይ፤ ለጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ሚስት የሽርክና ባለቤትነት የመድህን ድርጅት ያለሕጋዊ ፈቃድ በዳላስ የሚሰራና ያለሕዝብ ምርጫ የመረዳጃ ማህበር አመራር ይዞ የነበር፤ የቅዱስ ሚካኤልን ደብር ለሚከሱ አጽራረ ቤተክርስትያን ኮሚቴ አቋቁሞ የሚመራና ደብሩን ለአዲስ አበባው ጌቶቹ ለመስጠት የሚንቀሳቀስ ግለሰብ ተፈራወርቅ የተባለው ከጉባኤው መሪዎች መድረክ ድረስ በመሄድ ሲፎክር የሚያሳየውን ነው።



ለዛሬው በዚህ እየቋጨን መልካም የፍልሰታ ጊዜን እየተመኘን በቸር መልሶ ያገናኘን።

እርሶስ ምን ይላሉ? 

No comments: