Saturday, August 27, 2011

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!

ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም።


የተወደደዳችሁ የዚህ ገጽ ተከታታዮች በያላችሁበት፡  እንኳን በሰላምና በጤና ለቡሄ በአል አደረሳችሁ! የፍልሰታን ፆም በሰላም ለመፍታት አበቃችሁ! ልዑል እግዜብሔርም ያቀረብነውን ፆም፣ ፀሎት፣ ምህላና ሱባኤን ይቀበልልን። ፈቃዱም ሆኖ መልሰን በዚች ገጽ ዳግም ለመገናኘት ስለፈቀደልን ለክቡር ስሙ የማያልቅ ክብርና ምስጋና ይሁንልን። በአንድ ቤተ ክርስትያን ስር በአባቶች እንዲሁም በወንድማሞችና እህትማሞች መካከል ፍቅርና አንድነትን ይስጥልን። በትውልድ ሀገር ኢትዮጵያና በአካባቢው ያለውን የአየር መዛባትንና የፈጠረውን የረሀብ ችግር ያስወግድልን። በዚህ በምንኖርበት ሀገረ አሜሪካ በምስራቀ የባሕረ ሰላጤ እየደረሰ ያለውን ሄርኬን አይረን ፈጣሪ ጥበቃና ከለላውን ያድርግልንን፣ መአቱን ይመልስልን። ወገኖቻችንን ለሚያስተዳድሩ ሁሉ ቅን ልቦናንና ፈሪያ እግዜብሔርን ይስጥልን፣ ይታደግልን። የምንኖርበትንም ሀገር እርሱ ይጠብቅልን። የኛንም ሕይወትና ኑሮ ባርኮ ቅን መንፈስን ይስጠን። አሜን።

ለተሳትፎ መጣጥፎቻችሁና ተሳትፎዎቻችሁ ሁሉ ልባዊ ምስጋና ይድረሳችሁ በማለት የፍልሰታን ጾም ምክንያት በማድረግ ገጿ አፈግፍጋ መክረሟን በቅድሚያ ታስገነዝባለች። ነገር ግን ከመስመር የወጡና እራሳቸውን የቤተክርስትያን ብቸኛ ልጅና ተቆርቋሪ አርገው በመቀባት የቆሙት ወንድሞችና እህቶች ሀሰታዊና ከክርስትናው መንገድ የተጻረረ መጣጥፍ በገጾቻቸው መለጠፋቸው የሚታወቅ ነው። ችግሮች እንኳን ቢኖሩ በፍልሰታ ወቅት ወደ ፈጣሪ ልመናና ፀሎት እንጂ ባገልጋዮች ላይ የሚያቀርቡት መስመር ዘለልና ነቀፈታዊ የሀሰት መጣጥፍ ኢ ክርስትያናዊ መሆናቸውን ዳግም አረጋገጠ እንጂ ያመጣው ውጤት የለም። እነዚህ ጥቂት ግለሰቦች ደብር በጥባጮች በመሆን መሰሪነትን የሚመሩ ናቸው። ንጹሀንን በማሳሳት ደብር እንዲከሱ ማድረግና አንድነትን ለመናድ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ሁሌም እንደከሸፈባቸው ነው። ከለቀቁት ደብር ውጪ ሆነው የሚያካሂዱት በዕምነት ላልጠነከሩት ምክንያት እንዳይሆኑ ያሳስባል ወይንም ወደ ሌላ ዕምነት እንዲነጉዱ መንገድን ያመቻቻል። ስለዚህም ምግባር በአጽራረ ቤተክርስትያንነት ያስፈርጃቸዋል። ምሳሌ በማድረግም ከምንጠቅሰው ውስጥ የዳላሱን ቅዱስ ሚካኤል ደብር በአባልነት ካሉ ተባባሪዎቿቿው አማካኝነት በፍልሰታ መጀመሪያ ዋዜማ ያስጠሩት የአባላት ጠቅላል ስብሰባ ኮረም አልሞላም በማለት ቢሰረዝም ፤ እንደ ክርስታዊነት ለጾም መዘጋጀት በተገባ ነበር። ከነዚህ ተሰብሳቢዎች መካከል ከደብሩ አባላትነታቸውን ያለቀቁ ነገር ግን ወደ ሌላ ቤተክርስትያን የተቀላቀሉና የአዋኪና የከሳሽ ቡድን ደጋፊዎችና ተባባሪዎች ናቸው። ቤተክርስትያን ማለት ምን ማለት እንደሆነና ዕምነትስ ምን እንደሆነ ፈጣሪ ይምከራቸው በማለት ገጿ ታሰምራለች።

የሚካኤል ሠይፍ ተወካይም ተመሳሳይ ያለው አመለካከት ቢሆንም በቅርቡ የተጠራውን ጠቅላላ ስብሰባ በጥቂት እባጮች የተመራ መሆኑን አልሸሸገም ። ከጠራቸው ስሞችም ውስጥ ዛሬም በነበትሩ ገ/እግዜአብሔር ፣ ኪዳኔ አለማየሁ፣ ጌታቸው ትርፌና እነኤዮኤል(ክፈተው) ነጋ በመሳሰሉት ነው። እኛም እንደምንረዳው፤ በትሩና ኪዳኔ ማንኛውንም ድርጅት ቀርበው በመንጠቅና በመዘበር፣ በማፈራረስና ለትግሬ ነጻ አውጪ በማሳለፍ የታወቁ ናቸው። ጌታቸው ትርፌ የተባለና ትምህርት የሌለው ጎንደር የተወለደና በዘሩ ኤርትራዊ፣ አማርኛና ትግርኛ በመቻሉ ብቻ የስደተኛ ረዴት ድርጅት የተቀጠረና፤ ሳቦታጅ በማድረግ ከእርሱ ያልተባበሩትን ሌሎች ኢትዮጵያዊያንን እንዲባረሩ የሚያደርግ፣ በሚስቱ የመለሰ ሚስት አክስት በመሆኗ ደብሩን ለትግሪ መንግሥት ተመሪ ለመስጠት የሚሯሯጥና በቅርቡም በደብሩ ውስጥ በመስተንግዶ ኮሚቴ የሚያገለግሉትን እንዲተዉ ሳቦታጅ ስለሚሰራባቸውና ቦርዱም እርምጃ ስላልወሰደ፤ በተለይም ቦርዱን ወክሎ የመሰተንግዶ ኮሚቴን የሚመራው ሊቀ መንበሩ የጊታቸው ቤተኛ በምሆኑ ጨምሮና እርምጃ መውሰድ ስላልተቻለ በመልቀቃቸው፤ የደብሩ አስተዳደር ያላወቀውንና ያልተቀበለውን ፤ የመረዳጃ ማህበሩ ቦርድ አባልና አንዴ ለቅቄ አለሁ በማለት በሀሰት ነገር ግን መርዳጃውን ከሚያፈርሱት የነበትሩ ሎሌ፣ በትምህርት ያላገኘውን የዶክተርነት ማዕረግ የሚሞካሽበት አምሀ የተባለውን ቢጤ አፍራሹን ለአጋርነት ያስገባና ለወደፊትም የቦርድ ምርጫ የሚያዘጋጀው ሎሌው፤ ነገረ ስራው ሁሉ አጽራረ ቤተክርስትያን እንጂ ከቆረበ ኦርቶዶክስ የማይጠበቅ። ክፈተው / ኤዮኤልም ቤሆን ለረዥም ጊዜ የደብሩ ተመራጭ ሆኖ ላደረሰው ምዝበራና በደል ገና ለገና እጠየቃለሁ በማለት ዛሬ ደብሩን ከሚከሱና ከሚያፈርሱ ወገን ግምባር ቀደምት ቦታን የያዘና ፣ ተመረጭ በነበርበት አጋጣሚ ከሚያውቀው በመነሳት የደብሩን ስስ ጎኖችና ሰነዶችን በማካፈል የሚጎዳና በግልጽ ከምዕመናን ጠቅላላ ስብሰባ ላይ የተጣለበትን የተመራጭ ሀላፊነት ጥሎ የለቀቀ ፤ ለምንም የማይሆን ማፈሪያ ነው። በእርሱም ጌዜ የቦርዱ ጠሀፊ የነበረው ሀይሉ የተባለውና የኔጊታቸው ዘመድም እስከ ዛሬ በእጁ ያለውን የደብሩን ሰነድ አላስረክብም ብሎ የያዘ ነውና ገጻችን በሕግ መጠየቅ አለበት ነው የምትለው።
   
‘ቅዱስ ሲኖዶስ የብፁህ አቡነ ዜና ማርቆስን ውግዘት አንስቶ ሥርዐተ ቀብራቸው በኢትዮጵያ እንዲፈፀም ፣ አስከሬናቸውም ለጵጵስናቸው በሚገባ ክብር ፣ አበው ጳጳሳት በሚያርፉበት በመ/ፀ/ቅ/ሥላሴ ቤተ ክርስትያን እንዲያርፍ ወስኗል።‘ይህ መግለጫ መንበሩን በኢትዮጵያ ያደረገው ሲኖዶስ የብፁነታቸውን ማረፍ አስመልክቶ የሰጠውን ፤ ገጻችን እርሶስ ምን ይላሉ? በሚለው ከተወረወረልን ያገኘነውን አርፍደን ብናካፍላችሁም ነገሩ አስቂኝ ነው። ምክንያቱም በቤተ ክርስትያን የውስጥ አስተዳደር ምክንያት የተነጠለ የክርስትና መብቱም አብሮ የሚገፈፍበት አልፎም ወደ ትውልድ ሀገሩ በሕይወት ብቻ ሳይሆን ኮርብሱም ወደ ትውልድ ሀገሩ እንዳይመለስ የሚያግድ የቤተክርስትያኒቱ ሆነ የሀገሪቱም ሕገ መንግሥት መኖሩን ገጻችን ስለማታውቅና የጠየቅናቸውም የሕጉ ባለሙያዎች ጨምሮ እንደማያውቁት ሲሆን አለ የምትሉ ጀባ በሉን። ሲኖዶሱ ሕግን ጥሶ የቀደሙትን ጳጳስ በአካል ሳይመረምር በላያቸው ላይ አዲስ መሾሙ ያመጣው ውዝግብ በአባቶች መካከል መከፋፈልን ብቻ ሳይሆን በምዕራቡ አለም ላለነው የቤተክርስትያኒቷ ልጆችም በትውልድ ሀገር አጽማችንን ለማሳረፍ የአዲስ አበባውን ሲኖዶስ ፈቃድ ሊያስፈልገን ይሆን? ብፁእነታቸው በሕይወት ለምን ተወግዘው ፣ ሲያርፍ ለምንስ ውግዘቱ ተነሳ ለሚለው ጥያቄ የእርሶ መልስ ምን ይሆን? ገጻችን በሕይወት የተወገዙበትንና ሲያልፉ የተነሳላቸውን ምክንያት ውግዘቱም ሆነ ሽረቱ በራሱ ለራሱ መልስ ነው። ውግዘቱ ሀቅን ለመሸፈንና ለማሳደድ እንዲመች ሲሆን፣ ሽረቱ ደግሞ አሁን በምድር በሕይወት የሉምና እውነታቸውን ይዘው ስላለፉ ፤ በዕምነታቸውም ተሰደው በመፅናታቸው ፤ በመንግሥቱ ፊት በፈጸምነው በደል እንዳያሳቅቁን ብለው ይሆን?

ጳጳስ መሰደድ አዲስ ነገር አይደለም። ከግብጦችም ተምረናል። በቅርቡም በትረ ሥልጣኑን እመራለው የሚሉት ሊቀ ጳጳስ ዘ ኢትዮጵያ አባ ጳውሎስ በዚሁ በምዕራቡ አለም በዲሲና ካልፎርኒያ የፖለቲካ ስደተኛ ሆነው አገልግሎት ሰጥተውናል። በእጃቸው መባረክ ብቻ ሳይሆን ወዳጅነትንም በወቅቱ አትርፈናል። ዛሬ ደግሞ ተለያይተናል ነገር ግን እኛም ሆን እርሳቸው የቤተክርስትያኒቱ ልጆችነታችን እሙን ነው። ምንም ሁላችንም ዜግነታችንን ብንለውጥም ቀደም ባለው ታሪካችን ከግብጥ ሊቀ ጳጳስ ይሾምልን እንደነበር ማስመር እንወዳለን።

 ባለው የቤተክርስትያኒቱ ሕግ መጣስ ምክንያት የአባቶች መለያየት ፤ ዛሬ ተሰደው በሰሜን አሜሪካ የሚገኙት አባቶች የተጣለባቸውን የአባትነት ግዴታ በተቀናጀ መልኩ በሚገባ እንዲወጡ በማሰብ የራሳቸውን ጉባኤ በማድረግ ሲኖዶስ መስርተው ምዕመኑን በማገልገልና በትውልድ ሀገር ላሉትም ቤተክርስትያንና አገልጋዮች ጨምረው በፀሎት እየተጉ ይገኛሉ። ሕግ አይጣስ ፣ አንድ ዕምነትና ሀይማኖት ፀንቶ ይኑር፣ ስህተት ይታረም ከማለት ውጪ ቤተ ክርስትያኗ እንድትከፋፈል ፈፅመው እንደማይፈልጉ ዘወትር በግልጽ በአፅኖ ይመሰክራሉ። አንዳንድ አካባቢ እንደምናስተውለው አንዳንድ ከፋፋይ ግለሰቦችን በመከተል የተሳሳተ መስመር ላይ የሚከተሉትን ወገኖቻችንን ስናይና በዚህ ዙርያ ሁከትና መከፋፈልን በምዕራቡ ሀገር ቤተክርስትያን የሚያስፋፉ ታዝበናል፣ ስለእነርሱም ዘወትር እንጸልያለን።

ማን ነው የትኛውን? የውጪውን ወይንም የሀገር ቤቱን አንዱን ብቻ ሲኖዶስ በመከተል የእግዜብሔርን መንግሥት የሚወረሰው ብሎ የሚነግረን? ማንም እንደሌለና መዳንም ሆነ መንግሥቱን መውረስ የሚቻል በኢየሱስ ክርስቶስ አምኖ፣ በእርሱ ስም ተጠምቆ፣ ስጋ ወደሙን ተቀብሎና በቅዱስ መፅሀፍ እንደተጣፈው ሲኖር ብቻ መሆኑ የታመነ እንጂ በሲኖዶስ የሚተካ አይደለም። በዚህ ወይንም በዚያ ሲኖዶስ መመራት ሳይሆን፣ ወይንም የአንደኛው ወገን የሆነውን አገልጋይ ግልጋሎትን መሻት አይደለም። አንዳንዶች በመጣጥፋቸው ወገናዊነትን ያሳያሉ። የሌላውንም አባላትንና አገልጋዮችን ሲኮንኑ ይስተዋላሉ። የቤተክርስትያኒቱንም ልጅነታቸውን ለመቀማት ያዳዳቸዋል። እነርሱ የክርስትና ልጅነታቸውንም ለመቀማት ይችሉ ይመስል የማይቀቡት የላቸውም። ሀይማኖቱ እንዳይሰፋና በዕምነታቸው የቀጨጩትን እንዲጠፉ ፣ ዕምነቱን ለመቀበል የሚዳዱትንም እንዲሸሹ ፣ በተለይም በምዕራቡ አህጉር ለተወለዱትና ለሚወለዱትም የመሸሻ ምክንያት እየሆኑ ይታያሉ። እውቅ መምህራን እንዳያስተምሩ እንከን ይፈጥራሉ። ወይ እነርሱ አውቀው አያስተምሩም። ለማወቅም የማይፈልጉ ዝጎችና ቤተክርስትያኒቷን ጎጂ ምግባርን ብቻ ያካሂዳሉ። እነርሱ አመራሩን ካልጨበጡና ካልመዘበሩ ሌላው ቤተክርስትያን አይመስላቸውም። ለምሳሌ የዳላሱን ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ደብርን ብንወስድ፡ ለብዙ አመታት ማህበረ ቅዱሳን / ማቅ የተባለው የቤተክርስትያናችን በቀል ቡድን ተሰሚነትን አግኝቶና አመራሩን ተቆጣጥሮ የእርሱን ወገንና አባላቱ የሆኑትን መምህራንን ብቻ ሲያስመጣ ነበር። ምዕመኑ በተለያየ ወቅት ሌላም መምህር ከዚህ ቡድን ውጪ ቢጠይቅ ፣ አልፎም ፊርማ አሰባስቦ ቢያቀርብም ሰሚ አጥቶ ነበር።
በቅርቡ ደግሞ አንድ የሀገር ቤቱን ሲኖዶስ ተከታይ መምህር ለ3 ጊዜ ሌላም እንደዚሁ መጥተው ቃሉን ሲያስተምሩ ምንም አይነት ተቃውሞ ከማቅና ከመሰሎቹ አልተሰማም። በቅርቡ ደግሞ ከሰሜን አሜሪካው ሲኖዶስ በተገኘ መምህር ሊያፏጩ ይዳዳሉ። ገጻችን የምትል ሁሉም የቤተክርስትያን ልጆችና ለአገልግሎት የበቁ ስለሆነ ምዕመኑ ከማንኛውም ወገን የሚገኙትን አገልጋዮች በእኩል የሚያይና የሚገመግም መሆኑን መረዳት እንዴት ተሳናቸው? መንፈሳዊ ቅናት ቢሆን እንኳ ለአባቶች አንድነት አጥብቆ መፀለይና አንድ ወጥ አመራር የሚመጣበትን መተለምና መሳተፍ ከቅንነት አልፎ ዋጋን ከፈጣሪ የሚያስገኝ መሆኑን እንዴት መለየት ያዳግታል። የሚያውካቸው ከሆነ ደግሞ ይህ ከቅዱስ መንፈስ ውጪ ነውና ሁላችንም ለተሳሳቱት መፀለይ ይገባናል። የአባቶች ልዩነት የፈጠረውን ዋና ምክንያት የሆነውን ቀነኖ በመገንዘብ አንድነትን እንዲፈጥሩ ምዕመናን የሚገባውን ጾምና ፀሎት ከማድረግ አልፎ በመካከሉ ልዩነት እንዳይኖርና አባቶችም አንድ እንዲሆኑ የተቻለውን ሁሉ በማድረግ ማሳሰብ ይጠበቅበታል።

በሌላ በኩል ለምሳሌ እንደ ዳላሱ ቅዱስ ሚካኤል ገለልተኛ የሚባለው አይነት አካሄድ እስከ መቼ ድረስ ይዘለቃል? ቀደም ሲል ብፁእ አቡነ ይስሐቅ (ፈጣሪ ለነፍሳቸው ማደሪያ ይስጥልንና) ነገሩ በቶሎ የሚቋጭ መስሏቸው ይሁን ወይም ሌላ በገለልተኛነት መቆየትን መርጠው ነበር። ከማለፋቸው በፊት የወደፊቱን እጣ ያስቀመጡትን ገጻችን ባታውቅም የአባት አስፈላጊነቱ እሙን ነውና በተመሳሳይ መስመር ያሉትም ጊዜው ከማለፉና ችግር ከመባባሱ በፊት መቋጫ ከወዲሁ ማጤን ይገባል። ገፃችን ካላት ግንዛቤ ልታካፍል የምትወደው ቢኖር እንደሚከተለው ነው። ገለልተኛ የሆኑ ሁሉ አመራሮቹ ያለምንም ወገንተኛነት ከሁለቱም ሲኖዶሶች ምሁራንን እየጋበዙ ስለቤተክርስትያናችን ሕግና ስርዐት ፣ በሁለቱም ሲኖዶሶች ላይ ጥልቅ ግንዛቤን በማድረግና በተረጋጋ መንፈስ እርስ በእርስ በመመካከር በአባሎቻቸው ምዕመናን በጎ ፈቃድ ላይ የተመሰረተና መንፈሳዊ የሆነ ምላሽ እንዲሰጡ ነው። የዳላሱን ቅዱስ ሚካኤልን በተመለከተ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ይህች ገጽ ነቀፊታ፣ ማበረተቻና የግሏን አስተያየት ስትወረውር መቆየቷ የሚታወስ ነው። ነገር ግን የትኛውን ሲኖዶስ ይከተል የሚል አቋም ወስዳ አታውቅም። ውሳኔው ሁሉ የደብሩ አባላት ብቻ እንጂ የማህበረ ቅዱሳን /ማቅ ወይንም የውጪ ጥቅማ ጥቅም ፈላጊዎች አሊያም የወገኑ ድብቅ አላማ ያላቸው ጫና መሆን የለበትም። ለዚሁ ምእመኑ የራሱን ግንዛቤ እንዳይጨብጥና የጠለቀ ዕውቀትን እንዳይኖረው በተቀጠሩና በተጋበዙ መምህራን ላይ በማያገባቸውና ከመንፈሳዊ መንገድ ውጪ የቀደምት ሁከታቸው፣ ክስ ከሳሽና አስተባባሪነታቸው አልፎ ወሳኝ ከሳሽና  ዳኛ እንዲሁም ፍርድ አስፈፃሚ ሆነው ዛሬም ሰይጣናዊ ከፋፋይ ምግባር ላይ  ይታያሉ። እግዜብሔር ምህረትን ይስጣቸው ፣ ልቦናቸውንም ለውጦ ቀና መንገዱንም ያስይዛቸው። እነርሱም ዋሻ ያደረገውና በቅርቡ የተከፈተው እንዲሁም በአዲስ አበባ ሥር ያለው የዳላሱ ተክላይማኖት አቡነ አረጋዊ ቢሆንም በመከፈቱ ገጻችን አልተቃወመችም እንደውም ምርጫ ለምዕመኑ በዛ እንጂ፤ እዛ በካሕንነት ከሚያገለግለው አንዱ ከፈጣሪ የተቀበለውን የጠባቂነትን ሀላፊነት ከፑልፒት ላይ ‘ባትሪዬን ጨርሻለሁ “ ብሎ ሲኮበልል፣ ብሎም ከሚካኤል አጥር ስር ሆኖ ኢ ክርስትያንዊ ምግባርን ሲያከናውንና መጥፎ መጣጥፍን በብሎግ ሲለቅ የነበረው መቼ ንስሀ ወስዶ ነው ከዚያ የሚቀድስም ሆነ የሚያስተምር። ሌላውም ጎጠኛ ብቻ ሳይሆን ሚሽቱ ስትማግጥና ማህተሟን ስታፈርስ በቤተ ክርስትያኗ ህግ መሰረት ፈትቶ መመንኮስ እንጂ አብሮ መኖር የማይገባው በመሆኑ ፤ ከነሱ የመንፈሳዊ አመራር ምን ይጠበቃል? ለዚህም ነው ዛሬ ኢ ክርስትና መዶለቻና መጠንሰሻ ጎራ በማድረግ በምዕመናን ላይ በሚያደርሱት ከፈጣሪ የሚያገኙትን ዋጋ ከፋዩ እርሱ ነውና ለእርሱ እንተወው።

ከዚህ ፈቀቅ ብለን ደግሞ በዚያው በዳላስ ወገኖቻችን መካከል ያለውን ወቅታዊ ሁኔታን ስንቃኝ፤ የመረዳጃው ማህበር በቅርቡ ከመረጣቸው አመራርና ካቀፈው 9 የቦርድ አባላት ውስጥ 6 የሚሆኑት በፈቃዳቸው ከሀላፊነት መልቀቃቸው በሕግ አመለካከት አመራሩ ፈርሷል። ለመረጣቸው ሕዝብ መልሶ ለማስረከብና ሕጋዊ በሆነ ምንገድ ሀላፊነትን ለማስተላለፍ ያልቻሉበት ወይንም ያሰጋቸው መክንያት ምን እንደሆነ እስካሁን በግልጽ የቀረበ ሁኔታን በእጃችን እስካሁን የገባ ስለሌለ ለመተቸት ቢያስቸግረንም፣ ሀላፊነትን ጥሎ መኮብለል ከክህደት እንዳይቆጠርባቸው መላ መፈለጉንና ለዚህ ያበቃቸውን ለመረጣቸው ማሳወቅ የግድ ሆኖ ለሕይወታቸው የሚያሰጋ ሁኔታም ካላቸው ፤ ለሕግ ማሳወቅና አስፈላጊውን ጥበቃ እንዲደረግላቸው የመጠየቅ መብታቸውን እንዲገነዘቡ ገጻችን ታስገነዝባለች።ከዚህ ጋር
በማያያዝ ማንኛውም የድርጅቱ እንቅስቃሴ አብሮ በዚህ ሀገር ህጋዊ አባባል ድስስት ያደርጋል። ባስቸኳይ አጠቃላይ ስብሰባ መጥራት የግድ ነው። እንደምንሰማው ከሆነ ሸሪኮቻቸውን በጣት በመጥራት ያዋቀሩት አመራር ሕጋዊ ስላልሆነ በሕግ ያስጠይቃል።

በእርግጥም በመረዳጃው ማህበር ውስጥና በሥሩ ባቀፋቸው ድርጅቶች ውስጥ ከሕግ ተጻራሪ የሆኑ የተለያዩ ፍሮድ ይሉታል በሀገሩ እንደሚካሄዱ በየጊዜው የሚደርሱን መረጃዎችን ዋቢ በማድረግ ዘግበናል።  ገጿ ባለባት ወገናዊ ሀላፊነት ገሀድ ላለማውጣትና እርስ በእርስ በመተራረም እንዲያልፍ ስትጥር ቆይታ ነበር። አሁን ግን ከማንኛውም ጊዜ በበለጠ መልኩ የሕዝቡን ጥሪትና መብት ብቻ ሳይሆን ሕገወጥ ምግባሩ በከፋ ሁኔታ ቀጥሎ በመታየቱ እንዳመቺነቱ መርጃዎቹን ለመልቀቅ ተገዳለች። ከሚመለከታቸውም የሕግ አስከባሪ ክፍሎችም ጋር ለመተባበርና ጉዳዩ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንዲጠራና አጥፊና ተባባሪ ሆነው በሚገኙት ላይም ለሚወሰደው እርምጃ ምንም አይነት ቅሪታን በማንኛውም መንገድ በማንም ዘንድ እንደማትጸርስ በማመን ነው። በተለይም በመረዳጃው ማህበር አማካኝነት በኢትዮጵያ ቀን ዝግጅት ቀደም ባለውና አሁንም በሚሽቀዳደሙበት ትርዒት ከጀርባ ያለው ጉድ የሰፋ ነውና፤ ንጹአን ወገንን እናገልግል ብላችሁ የምትሳተፉ ውድ ወንድሞችና እህቶች ልታጤኑትና ልታስተውሉት የሚገባ ከጀርባ ያለውን ጉድ በቀላሉ የምትገነዘቡት ስለማይሆን ቀደም ሲል የጣጣፍናቸውን መመርመሩና የጎደሉትን የመስመር ነጥቦችን (ዶቶችን) ማገናኘት ብልህነት ብቻ ሳይሆን በሕግ አብሮ ከተጠያቂነትን ያድናል ብላ ገጿ ታሳስባለች።  በአማርኛ “ለብልህ ………ምን አይሉ“ እንደሚሉ።

ሌላው የመረዳጃው አካል ነኝ ባዩና ሀሰተኛው እድር ተብዬው መረዳጃ ማህበሩን የሕገወጥ ምግባር መሸፈኛ ብቻ ሳይሆን ፤ ከሥሩ መሆኑ ቀርቶ ዛሬ እንደሚታየው ከበላይ ተቆጣጣሪ ሆኖ ብዙ ምዝበራና የወንጀል ፋብሪካ ሆኖ ነው ያገኘነው። እራሱን እንዲያጠራና እርምት እንዲያደርግ የተደጋገመ የዚች ገጽ ትችትና ማሳሰቢያ ጥረት ሁሉ ተቀባይ ባለማግኘቱና የተደጋገም ክህደትን ሳይቀርና ኩነናን በሚቆጣጠሩት የወገን ሬዲዮ ስርጭት ሁሉ ሰንዝረውባታል። ይሁንና ዛሬ ባደባባይ የማይክዱትን ወንጀል የመልቀቅ ወቅቱ ስለሆነ በእጃችን ካሉን መርጃዎች አንዱን ብቻ ጀባ እንላችኃለንና ግንዛቤው የናንተ ሲሆን ፣ እንደለመዱት ክህደት የወንጀለኞች ነው። ገቢያቸውን መደበቅ የሚፈልጉና የታክስ ግዴታቸውን ላለሟሟላት ነገር ግን ለጥቅም የመጀመሪያ ለመሆን የሚቸኩሉ ግለሰቦች ግን በጥሬ ገንዘብ ለዚህ እድር አባልነት የከፈሉበትን ደረስኝ እንኳን በመረጃነት የያዙ ስለማይኖሩ ለምዝበራ ያመቹ ናቸው። በቼክ ከከፈሉትም አንዳንዶች ለመረጃ በተባባሪዎቻችን ቢጠየቁም ፈቃደኛ ሆነው እንዳልተገኙ ከዳላስ ምንጮቻችን ብንጋራም፤ መረዳጃውም ሆነ እድሩ የባንክ ሂሳብ ቁጥራቸው የሚገኘው ከባንክ ኦፍ አሜሪካ ብቻ ነው። ወደ ሂሳቡ የሚገቡት ቼኮች ሁሉ ከጀርባቸው የባለ ሂሳቡ የባንክ ሂሳብ ቁጥሩና ስሙ ማህተም ኢንዶርስ ወይንም በእጅ ተሞልቶበት እንደሚገባ የባንክ የተለመደ አሰራር ነው። በእጃችን የገቡት ግን ከዚህ ተጻራሪና በሌላ ባንክ ውስጥ በሕገወጥ መንግድ በሶስተኛ ወገን በጥሬ ገንዘብ የተወሰደ ስርቆትን ያሳያል። ከዚህ በታች ያለውም መረጃ ቀጥታ ከባንክ የተገኘና፤ ጉዳዩ የሚመለከተው ባንኩም የራሱን የውስጥ ምርመራ በማካሄድ ከቻለ በጥሬ ገንዘብ የወሰደውን ማንነቱን እንዲገልጽ ካልሆነም የውስጥ ተባባሪ ካለ አስፈላጊውን እንዲፈጽም፣ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ያለውን ማንኛውንም ሪከርድ የኤሊክትሮኒክ መርጃዎችና የሰው ምስሎችንም ሁሉ የጨመረ መርረጃዎችን እንዲያቀርብ ሕጋዊ ጥያቄ ሰሞኑን ደርሶታል የሚል ፍንጭ ለምርመራው ቅርበት ያላቸው ምንጮቻችን ያዳዳቸውን እያካፈልን ጀባ ባልናችሁ በሚቀጥለው መረጃ ላይ የባለቤቱንና የሂሳቡን ቁጥር በማጥቆር ማንነታቸውን ለመደበቅ ግዴታ ስላለብን መሆኑን አስቀድመን ማሳወቅ እንፈልጋለን።

       
በመጀመሪያ መረባረብ መርዳጃ ማህበሩን መልሶ ማቋቋም ሲገባ ለኢትዮጵያ ቀን በዐል ብሎ መሯሯጥ እራሱን የቻለ ጥያቄና ለዝርፊያ ጥድፊያ አስመስሎታል። ከዚህ በላይ የተለጠፈውም ቺክ ይህንንኑ ያስረግጣል።

እርሶስ ምን ይላሉ?

2 comments:

Anonymous said...

To the blogger:

.... can you please look up to the sky before you set your mind to write what in your mind.
I know it's hard to look to 'brothers and sisters', 'fathers and elders' and to those who live with you in this earth temporarly, but look up to sky where the half or full moon passes through cloud.
Just not to look who you want to be write for or/about first, but for the moment -- just for seconds ------ just for blinks ---
yes, it's hard...

yes, we all die one day, but I want you to try on your heart. Even on closed eye.

yes, I want you to pray not to die before your heads up and open your eye to see the sky ...

your little brother.

Anonymous said...

The Health of our Church is in Jeopardy!!
In recent days our Church has started Delivering Good
service for which we thank our Savior and the people who are
behind this good service, (like the Priests the Deacons and
the Board of Directors who run the day today affairs). To
those of us who want this good service to continue! It is
about time to think ahead and to prepare in advance what
need to be done before the next election of Board Members
which I believe is due in a couple of Months.
We need to start looking for candidates who will keep the
present trend to replace the out going members.
In my opinion; re electing any present serving member to
run another term is contrary to the beliefs and doctrine of
a good governance of any organization especially when it
comes to serving a non profit organization with out any
compensation.
Re electing a member to serve another term without any
compensation and consuming his time and energy is harmful to
the individual’s well being as well as his pocket.
The term of service should also be reduced to two years
maximum to reduce the fatigue and the unintended consequence
that will follow a long term service.
When an individual is serving a long term service, he
develops an unhealthy attachment to the organization, in
this case to the Church and thinks that the Church belongs
to him only and that the others are there to take away his
authority and turn around what he thinks he has achieved.
He becomes obsessed and starts attacking his colleagues
instead of working with them. To give you an example, this
individual thinks that the others should not touch the
church computer or document because they will start learning
his trade trick or start deleting documents. He has become
paranoid, suspecting everyone except himself. He thinks that
he is the only one standing for the church and its property.
The others are traitors and should not have been elected to
the board. (He had forgotten that the church property
belongs not only to the Board members but also to any
individual who participate as members. Everything that is in
the church belongs to any paying members and any document
should be open to them. I think he had forgotten that this
church is a community property and not a private
individual’s property)
This unhealthy attitude was developed because he has stayed
longer than the others and thinks that by holding everybody
in the dark his chance of being re elected will be
guaranteed.
However if he was genuine and was serving in good faith and
his term was limited, I believe his attitude would have been,
“I am only here for two years, while I am here; I will
develop a good relationship with the others and when I am
gone I would always be remembered for my good deeds and not
for my crooked ideas” for it says “I expect to pass through life but once.