Thursday, April 14, 2011

ዝንባም ዳይስፖራ!

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!

ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።


ዝንባም ዳይስፖራ!


አቤቱ የሠራዊት ሁሉ ጌታ የሆንኽ ፈጣሪያችን ሆይ፣ ሁሉን ቻይና ታጋሽ መድሐኒተ ዓለም ይህንን ጊዜ ፈቃድህ አድርገህ በርቀት ከሚገኙ ወገኖቻችን ዘንድ በዚህ ጦመር ዳግም ስላመቻቸህልን ለታላቁና ገናናው ሥምህ ክብርና ምስጋና ይሁንልህ። አሜን። የጀመርነውና ለመጨረስም ላቃረብኸን ፣ በዐለ ፆሙንም ጨርሰን ለትንሣኤ በዐል በሰላም ታደርሰን ዘንድ ፈቃድህ ይብዛልን። የተያዘውንና የቀረበውን ፆምና ፀሎታችንን ተቀበለን? ለሁላችንም ምሕረትና ሰላምን ስጠን? በዐለ ትንሣኤን ባርክልን? አሜን። 

እኛ በሥራ ምኸንያት ከናንተ ብንርቅም፣ የኛም ጋደኞች በሥራ ግዳጅ እርቀውን፣ ሕይወታቸውም በአደገኛ አካባቢ ቢሆንም ዘወትር ባለን ፍቅር በኢ-ሚይል ወይንም ቻት ግንኙነታችን ስንችልም በድምፅ  ለመለዋወጥ በመቻላችን ለታላቁ ጌታ ለእግዚሀብሔር ክብር ምስጋና ይሁን። የእርሱ ጥበቃና ከለላ ለእነዚህ ወንድሞች አይለይ። በዚህ አብይ ፆም በፍጡም በዚህ ጦመር ላለመውጣት ወስነን ነበር። ግዜውን በፆምና በጸሎት ለወንድሞቻችን ለመስጠት የወሰንበት ነበር። ባለፈው የመጨረሻ ጥሁፋችንም የተለየናችሁ ከትንሣኤ በኃላ ለመገናኘት ነበር። ዛሬ ብቅ ብንልም ከደረሱን ዘገባዎችና በእጃችንም ካለው ጨምረን ለማስታወስ ብቻ እንጂ ፤ በፆመ እማማት ምንም ሆነ ምን እንደማታገኙን ለማስረገጥ መሆኑን ከወዲሁ ልንጋራ እንፈልጋለን።

የዳላሱ ቅዱስ ሚካኤል ደብር ካሉት የሚካኤል ሠይፍ ወዳጆቻችን ያተረፍነው ለጆራችን ቢኖር በአዲሱ ዲያቆን አማካኝነት የሚካኤል ወዳጆች ለትንሣኤ በዐል በጋራ ያበረከቱትን አዲስ ሻንድለር መብራት ለማየት መጓጓታቸውን ነው። እኛም ሰምተን እንደዳዳነው እናንተም የበረከቱ ተካፋይ ለመሆን ስትሉ የሚገባችሁን እንድታደርጉ በዚህ አጋጣሚ እያካፈልን ፤ አንዳንድ በሬ ወለደ ባዮች ደብሩ ከነ እከሌ ሲኖዶስ ተደባለቀ የሚሉት የፍርድ ቤቱ ጉዳያቸው ኪሳራ ላይ የጣላቸው የአጽራረ ቤተክርስትያን መሆኑን የሚካኤል ሠይፍ ተወካይ አካፍሎናል።  በሌላ በኩልም ለትንሣኤ ክብረ በዐል ዝግጅቱ እየተጧጧፈ መሆኑንና የፊታችን ሰንበት የሚከበረውን የሆሳህና በዐል ሁላችሁም በአንድነት በመሆን እንደምታደምቁት እርግጠኞች ነን። ያማረ በዐል ያድርግላችሁ። እንዚያም አርፋጅ፣ ለነገር ብቻ የሚመጡትና በአዳራሹ ብቻ እየተቀመጡ ነገር የሚሸርቡት፣ ፈጣሪ ልቦናቸውን ለውጦ የምሕረትን መንገድ ያሳያቸው እንጂ፣ የፍርድ ቤቱ ጉዳይ ሲያልቅ የማይታረሙ ከሆነ ወይ ቦታቸውን ይፈልጉ አሊያም የቤተክርስትያኑ አገልግሎት አልቆ ወደአዳራሹ ለሕዝበ ክርስትያኑ እስኪከፈት ድረስ ይታገዱ፤ አዳራሹ ለአጽራረ ቤተክርስትያን መዶለቻና ለበረከቱ በማለት በነጻ የሚያገለግሉትን እህትና ወንድሞችን መተቺያ ስፍራ አይደለምና። በግለስቦች መልካም ፈቃድና ጉልበት ከፀሎቱ መጨረሻ በአዳራሹ ለምዕመናን የሚቀርበው ሻይም ሆነ ምግብ ሁሉ ወጪ አለውና ከማዕዱ ተሳታፊ  በእህቶች በተቀመጠው ትናንሽ ሳጥኖች የተቻላችሁን የገንዘብ ድጎማ ብታደርጉላቸው ከበረከቱ ታሳታፊዎች ትሆናላችሁ።

ቀደም ሲል ከአዲስ ከሳሽ ተራ የገባው የአጽራረ ቤተክርስትያን ቡድን  ያቀፋቸው የአንዳንዶች ስም ለመያዝ ያቀድነው ከደብሩ አመራር ጋር ስህተታቸውን በመገንዘብ ይቅርታ እየጠየቁ ያሉትንና ለመመለስ ያመለከቱ መኖራቸውን ከምንጮቻችን ስለደረሰን ነው። ከዚህ በፊትም በገነት ከበደ በተባለችው ላይ ቀደም ታሪኳን ከኢትዮጵያ ውስጥ አዲስ አበባም ሆነ ድሬዳዋ ብሎም የጂቡቲ ሕይወቷም ከዚያም የአሜሪካን ጨምሮ የደረሱን አሳዛኝ ዘገባዎችን ወደፊት የምንጋራችሁ ሲሆን፤ ግደይ ከምትባል እህታችን ጋር ስትጋራው የነበረውን ባለትዳር አፍሪካዊ በወኪሎቻችን በኩል እያፈላለግነው ስለሆነ የምታውቁ ትጋሩን ዘንድ እንጠይቃለን። ይህች ያጎረሷትን ሁሉ ነካሽ ከምትሰራበት የፓርኪንግ ሌብነት ብትፈናቀል በዚህ በተንቋቋ እድሜዋ የሥራ እድል በጠበበት በማለት እንጂ የጸሀይ ጽድቅ እድል እጅ ከፍንጅ እንዳይጥልባት ስርቆቱ፣ በተለይም በኛ ገጽ በጣሙን መመታትሽ ደርሶናል በሴት የመጨክን ሳይሆን የእጅሽን ትንሹን ብቻ ነው የሰጠሽ እንጂ አሁን አንቺ የምታሚያቸው ሁሉ በነገር የሉበትም፣ እንደ እድሜሽና እንደቆርቆሮ መንቋቋቱንና መጮኹን አቁመሽ የሰይጣን መሳሪያ ከመሆን ታቅበሽ፤ ከደብር መካሰስሽን በማቆም በንስሀ እንድትመለሽ እናሳስብሻለን።

የትግራይ ነጻ አውጪ አባልና በሕይወት የሌለው ክንፈ የተባለው ከድርጅቱ ያምታታውን ንዋይ ውስጥ በአሜሪካን መሸሸጉ የሚታወቅ ነው። ይኸንኑ ገንዘብ በመከታተል ላይ የሚገኘው ድርጅታቸው የዳላስ ነዋሪ ወደሆነውና ሙሉጌታ ወራሽ aka ቀዳዳው ዘንድ እንደነበር በሚገባ ያረጋገጡ ለመሆናቸው ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸው ደርሶናል። ብዛቱ ለጊዜው በአኃዝ ባይታወቅም በርካታነቱ እሙን ነው። ድርጅቱም ጥንቃቄ በመላበት ሁኔታ ዘገባውን እያጠናቀቀ ሲሆን በምን አይነት ሕጋዊ መንገድ ማስመለስ እንደሚችሉ መላ እየተነበዩ ነው። ከሟቹ የአደራ ገንዘብ የበላውና ሟቹ የአንድ ቀዬ ና የትግራይ ዘር ብቻ ሳይሆን ጠለቅ ያለ ቤተሰብነትንም አፍርተዋል። የቀዳዳውን አባት ተኩሰው ከገደሉት የትግራይ ነጻ አውጪ ተዋጊ ቡድን በሥፍራው ከነበሩት ውስጥ አጁ አለበት ብቻ ሳይሆን ገዳዩም ክንፈ ነው የሚሉም አሉ። ቀዳዳውም ዳላስ ላይ አባላቸው ለመምሰልና ወያኔ ነኝ እያለ ሀሰታዊ መፎለሉን እንዲያቆም ከኢሀዴግ ማስጠንቀቂያ እንደደረሰውና ተኮማሽሾ እንዳለ አብሮን የደረሰን ዘገባ አክሎበታል። እንደዚሁም ውሸቱ የሰላቻቸውና በትምህርትም ሆነ በኑሮ ከማይመጥናቸው የማለዳ የቁርስ ተቃማሾቹ ከሆኑት የሲቲ ካፌ ደንበኞች አካባቢ፣ ፊት ስለነሱትና የትግሬውም ድርጅት ብላክ ማርኬት ዶላር ንግዱን ስለደረሱበት አንገቱን ደፍቶ መራቁን መርጦቷል። እንደዚሁም የተሰለፈበትም የአጽራረ ቤተክርስትያን ጎራም በቀዳዳነቱ እያገሸሹት መሆኑንም ዘጋቢያችን አካፍሎናል።
  
ከዚህ ወጣ ስንል ደግሞ የምንለው ቢኖር እንድንተችበት ከብዙዎቻችሁ ስለተጠየቅን ያጠናከርነውን ነው። ለምን የትግሬ ነጻ አውጪ ድርጅት የተለመደው ተቃውሞ አላገኘውም የሚለውና በዚያ ዙሪያ ያለውን ነው። አንዳንዶች እራሳቸውን እንደሚዋሹት ሳይሆን በዳላስ ከተማ ለሚገኙት ወገኖቻችን ሕብረተሰቡን አስመልክቶ ከሚዘገቡት ውስጥ ብዙ አንባቢን ካተረፈውና ከማንም ሳይወግን የተቻለውን ያህል ሲያስገነዝብና ቢሳሳትም ይቅርታን ከመጠየቅ የማያፈገፍገው ጦመራችን ሲያስረግጥ የቆየውን በገሀድ ውጤትን ያስመዘገበበት አጋጣሚ ስለነበር ነው። እንደዚሁም ለግል ጥቅም ብቻ በጎብኝዎቻቸው ቁጥር ብዛት በማስታወቂያ ገቢ ለሚተዳደርት ነባር ድህረ ገጾች ምን አጀንዳ እንዳነገቡ አንባቢያን በመረዳታቸውና ዘወትር ለገጾቻቸው ተሳታፊ የሆኑትን በትምህርታቸው የገፉም ሆነ ምንም የሌላቸው በጥንድና በተናጠል የሚያራምዱትን ምግባር የተረዱና ፀረ ሰላምና አንድነት መሆናቸውና ባለው የፖለቲካ መዛባት አጋጣሚ ተጠቃሚዎች ማንነት በመረዳት ለልፈፋቸው ቦታን በመንፈግ የሰጡት ምላሸ አንዱ ገፅታ ነው። እነዚሁ ኢሕአፓ እንደዚሁም የትግሬ ነጻ አውጪ ወይንም የሌላ ቡድን አባል አሊያም ቡችላ የነበሩና ዘመናቸው የረፈደባቸው በሕይወት በሌለ ድርጅት ስም የሚንቀሳቀሱ መሆናቸውን በመረዳቱም ጭምር ነው።  

እኛ የትግሬ ነጻ አውጪ ድርጅትንና እርሱ የወለዳቸውን ሁሉ የምንኮንነውና የምንታገላቸው የተለያዩ ነጥቦች አሉን። የሰሯቸው ጥሩ ስራዎች አሉ የሚሉን ቢኖሩ እጅጉን ከኛ ይለያሉ። አንድ ትውልድ ሙሉ ዘመን ሲያስተዳድሩ፤ የጤናና የማሕበራዊ ችግሮችን ያልቀረፉ፣ የሀገሪቱን የእድገት ጎዳና አንቀው የያዙ፣ በዘርና በጎሳ ነጣጥለው በመግዛት ነቀርሳ የተከሉ፣ የትምህርትን እድገት ላራሳቸው ብሔር ቅድሚያ የሰጡ፣ የዲሞክራሲ ጎዳናዎችን የዘጉ፣ ተቃዋሚዎቻቸውን ሁሉ በተለያየ መንገድ እያጠፉ ያሉ፣ የንግዱን ተቋም በሙሉ በቁጥጥራቸው ሥር ያዋሉ፣ ለነሱ ብቻ ያጎበደደ ወይንም የነሱ ብቻ ብሄር ለሆነ ለይተው ዕድል የሚሰጡ፣ ወዘተ…..ማለት ይቻላል። ቀደም ሲል ኮሚኒስትና ለመገንጠል የቆመ ድርጅት እንደመሆኑ ሁሉ፤ ለኢትዮጵያና ለሕዝቧ አንዴም ቅንነት ያልነበረውና ወታደራዊውን መንግሥት በሕዝብ አመጽ ሲወድቅ የተደራጁ እነርሱ ብቻ በመሆናቸው በምዕራባዊያን ምርቃት የምኒሊክን ቤተመንግሥት ለመያዝ በበቁ ማግሥት አገርን ያስገነጠሉ። አንድ የትውልድ ሙሉ ዘመን ጨብጠው ዛሬም ሀገሪቱ በአለም ደርጃ የመጨርሻዋ ድሀና ኃላ ቀር አድርገው የያዙ፤ ብዙ እድገትና የተሻለ ለውጥን ማስመዝገብ በቻሉ ነበርነገር ግን ሁል ጊዜ ስለ አባይ ወንዝ እንዘፍናለን የሚያደርሰውንም ጉዳት እናወራለን፤ ከዘመን ወደዘመን ፣ ከመሪ ወደ አዲስ ስንል አሁን በሰሜን አፍሪካና በዓረቡ ዓለም በተጀመረው የለውጥ እንቅስቃሴ ሀሳብ ማጨናገፊያ የሚሉ ቢኖሩም ፤ ግድቡን ከልባችን የምንደግፈውና እንዲተገበር በጎ አመለካከት አለን። ይህንኑም የሚጋሩን እጅግ ብዙ ሲሆኑ ችግር ያለበት ዝምባሙ ዳይስፖራ ብቻ ነው። ምቀኝነትና ጥላቻ፣ ደም መፋሰስና ሁካታ መተዳደሪያው የሆነ  እርሱ ነው። ተቃውሞ ሰልፍ የወጣ እርሱ ነው። በምዕራቡ ሀገር ድሕረ ገጽ ከፍቶ በማስታወቂያ መተዳደሪያው ያደረገ እርሱ ነው። ልብ ካላችሁ በከተማችሁ በያለበት የፖለቲካም ሆነ የማህበረሰቡ ጉዳዮች አካባቢ ብቅ ጥልቅ የሚያበዙት እነማን ናቸው እነርሱ አይደሉምን? በህብረተሰቡ መረዳጃና ሬዲዮኑን ይዘው እየከፋፈሉ ተጠቃሚ እነርሱ አይደሉምን? በናንተው ስም ከተለያዩ ድርጅቶች እርዳታን እየጠየቁ ለግላቸው የሚያውሉ እነርሱ አይደሉምን? ባለፈው በናንተ ራዲዮ አብሬው ነበርኩኝ ያለው ዘጋቢና ታሰረ የተባለው ሽማግሌ እነማን ናቸው? በትሩ የተባለ በዚያን ሰሞን የታሰረ የፖሊስ መዝገብ የለም የማይመስል ነገር ግን ለማስመሰል። ጋዜጠኛ ነኝ እያለ በሌለው የሙያ ብቃት መለኪያም ሆነ መረጃ እራሱን የሚጠራው ዘውገስ ቢሆን አትገቡም ከተባሉ በኃላ ከተቋዋሚው ተለይተው ለምን በየጓሮው አስካሄዳቸው? ተደብቀው ለመግባት? እነዚህ በ2 ቢላዋ የሚበሉ አይደለምን? በምሽት ከኢትዮጵያ መንግሥት ከተላከው ልዑካን ጋር እራት አብሮ ሲበላ አልነበረምን ለምንስ በራዲዮው አልዘገበም?

ኸዚሁ እራት ከተሳተፉት ውስጥ ፈተና ውድቆ በሌላ ባለፈ ስም የኢትዮጵያ ባሕር ሀይል የቀደመ ተቀጣሪ፤ ዳላስም ከመጣ በኃላ በመረዳጃ ማህበር ውስጥ በተመራጭነት ሲያጨማልቅ የነበረ፣ ለትግራይ ነጻ አውጪ ቡችላ የሆነና በሬዲዮ አካባቢ ያሰማሩት፣ አሁን ደግሞ በቂ ድምጽ ሳያገኝ አጭበርብረው አስርገው ለአስመራጭነት በመረዳጃው ማህበር የዶሉትና ግርማ ንጉሴ ወይንም ግርማ ታደሰ ተብሎ የሚጠራው ይገኙበታል። ይህ ቡችላቸው ቀደም ሲል ከየመን የመጡትን የቀድሞ የባሕር ሀይል ሠራዊት አባላትን ለመከፋፈል ባደረግው እንቅስቃሴ መጋለጡ የሚታወቅና ትምህርት የሌለው በመሆኑና በጋብቻ ከጸረ ኢትዮጵያን ጎራ የሰመጠ በስውር የሚንቀሳቀስ ጠላት ነው። ፀረ ሕዝብና አንድነት የሆኑት ሌሎቹ ውሮዎች ደግሞ እንደነ ደጀኔ፣ ሰሎሞን አባተ፣ መንግሥቱ ሙሴ፣ ሌንጮ ወይንም መሀመድ፣አበበ ንጋቱና ሊሎች አበበዎች ወዘተ……እያለ ይሄዳል። እነዚህ ሀቀኛ ታጋይ መሳይ ነገር ግን ባደባባይ ተቃዋሚ መሳይ ለሕዝብ አንድነትና እድገት ነቀርሳ መሆናቸውንና ይህንኑ መተዳደሪያ እንዳደረጉት በተመሳሳይ ገጽና በኛም ሲመዘገብ ቆይቷል። ዝምባሙ ዲያስፖራ እንጂ የገባውማ በነሱ እንደማይመራ እየለየለት ነው። የነርሱ ዘመን አበቃ። ካፍንጫቸው ስር ያለውን የመረዳጃ ማህበርን ከሀቀኞችና ለህብረተሰቡ የሚጠቅሙትን አርቀው ፤ ዛሬ በግላጭ ለትግራይ ነጻ አውጪ እያስረከቡ ለመሆናቸው እያስመዘገቡ ያለው ሂደት ምላሽ ነውና ተጨማሪ ማብራሪያ እንደማትሹ በመተማመን ነው። አሁንም እነዚህ የሕዝብ ሾተሌዎችን ከመረዳጃ ማህበራችሁ ለማጥፋት በነቂስ በመውጣት በቅርቡ በሚደረገው ምርጫ በመሳተፍ ማህበራችሁን አጥሩ! የኤትዮጵያ ተወላጅነታችሁ ብቻ ምርጫውን ለመሳተፍ በቂ ነውና ምንም አይነት ቅድሚያ ምዝገባም ሆነ ክፍያ የሚጠይቅ መተዳደሪያ ሕግ የለውምና። ኸዚህ ያልጠቀስናቸው ቅጥረኛና አባሪዎቻቸው ስም አለንና እንደአስፈላጊነቱ  ወደፊት እንጋራችኃለን። በዳላስና አካባቢ ያለው የኢትዮጵያ ተወላጅ ትላንት በሀሰት የመሩትንና በዚያም የተጠቀሙበትን አጥርቶ እየለየ ለትውልድ ሀገሩም ሆነ ለሚኖርበት እንዲሁም ለወገኑ የሚበጀውን አገናዝቦ በወሰደው አቋም የተጨበጠው ዕውነታ ውጤት ነው። እነዚህ ጥቂት የሀሰት ታጋዮችና ሽብር ቀማሪዎች ከዝንባም ዳይስፖራ ጋር የተሰለፉበት ተቃውሞ የተመዘገበበት ጎራቸውን ክፉኛ መቶባቸዋል። ዝንምባሞችም ከዚህ ተምረው ራሳቸውን እንደሚያጠሩ ጥርጥር የለንም።

መልካም የትንሣኤ በዐል እንዲሆንላችሁ እንመኛለን!


እርሶስ ምን ይላሉ?   

2 comments:

Dagnachew said...

በጣም ጋጠወጥና ነውር የሆነ ርዕስ አመራረጥ ሲሆን አንዳችም ፍሬ የሌለበት በጥላቻ ላይ የተሞላ በማስረጃ ያልተደገፈ ህብረተሰቡን ከፋፋይ መርዘኛ አሉቧልታ ነው:: በእግዚአብሄር ስም ተጀምሮ በ መርዘኛ ጥላቻ ያለቀው ስም አጥፊነት አሳዛኝ ነው:: ሁሉንም ከሶ ሁሉንም ጠልቶ ለመከፋፈል መሞከር ከሀገር ቤት ህዝብን በመከፋፈል አራቁቶ የሚመራ የመርዘኛው የወያኔ ስራ ነው:: ጸሀፊው ወያኔ ካልሆነ ራሱን ደብቆ
ይህን አስከፊ የእፉኝት መርዝ በህብረተሰቡ መካከል ሲረጭ ባልኖረ::

Selam Dallas said...

ከላይ ለሰጡት አስተያየት ለወገናችን ምስጋናችን የላቀ ነው፣ ትዝብቶንም አይሸሽጉን። የእርሶን አስተያየት ተጋሪ ብጤዎች እንዳሉ ስለሚገባን አስተያየቶን ለጥፈነዋል፤ አክለንም ስሜቶን ሳንነካ መልስ ልንሰጥዎ ይገባልና ከነብጤዎ እንደሚቀበሉን ተስፋ ቢኖረንም ምሬቱን የሚችል ልቦናና ማስተዋልን እንመኝሎታለን።

ትክክል ያገኙት ቢኖር የአምላክን ስም ጠርተን ስንጀምር ትንሣኤውንም በዐል መደምደሚያችን ማድረጋችንን ስተውታልና ከልቦ አላነበቡትም አሊያም በቁጭት ላይ ሆነው ብዕሮትን ያሾሉት ለማለት ያዳዳናልና የኃላ ማርሽ አስገብተው በጥንቃቄ በመዘወር ይቃኙ እንላለን። ሀይማኖቶ ምን እንደሆነ ባናውቅም እኛ ግን በእርግጡ ከመኮነንም አልፈን የዘለቅን ቢያስመስለንም ሀይማኖት ያለው ሁሉ የሀይማኖት ቤቱን መንከባከብና በጾም በጸሎትም መትጋት አለበት የሚል እምነት እንጂ ደብር ከሳሽና አፍራሽን እንዲሁም አጽራረ ቤተክርስትያንን ለምን ዘገባችሁባቸው የሚል ቅንቅን የፈሰሰቦትና ወሮ ያስጨነቆት ካልሆነ በቀር ብዕሮን ለእዚህ ልቦና መትፊያ ማድረግ ባልተገባዎ ፤ ለእንርሱም ባልቆሙና የለጥፍነውን ለመኮነን ባልዳዱ። ለዚህ ደጋፊነቶ ንስሀን መዳኒት ያድርጉ።

ጠሀፊው ከዳላስ ከሆኑ የዘገብነውን ሁሉ እየኖሩትና ከላዮ ያለውን ዝንብም ተስማምቶት ያሉ ከሆነ ይመቾት ነው፣ ነገር ግን ማንም የእርሶን ዝንብ የሚነካ የለምና በእርሱ ሀሳብ አይግባዎት። በሽታ ሲሆኑ ውጤቱን ያገኙታልና። ሌላው ዝንቡን ካመጡት ወይንም ከሚያራቡት መኃል ከሆኑንም መርዘኛ መሆኖን አውቀውም እድሜ ለማራዘምና የእርሶን ድሎት ብቻ የሚታዮት ፣ ተሰናክለው የሚያሰናክሉ ከሆኑ ለዚህም የራቀ ቢመስልም ገፈቱን በቅርቡ ቀምሰው እስኪያጣጥሙ የኖሩ የሚመስሎ ግለኛ መሆኖን የብዕሮ ጫፍ የተፋው ነው።

በሌላ በኩል ወያኔ ብለው ተንፍሰዋል። ወያኔ የሚለውን ቃል ትርጉሙ ምን እንደሆነ ቢያስተምሩን ደግ ነበር። ነገር ግን እርሶም ያገኙት አልመሰለንምና ሁለታችንም በዚህ የምሑር እርዳታ የምንሻ አስመስሎናል። ይሁን እንጂ የትውል ሀገራችንን የሚመራውን የትግራይ ነጻ አውጪ የተከለውን መንግሥት ሎሌዎችን በተመለከተ የለጠፍነውን ከሆነ እንደ ብዕር አጣጣሎ እርሶ ከኛ ብዙ የቀረቡና የጨበጡት መረጃ ያለ አስመስሎታልና ከጨበጡት ጀባ ቢሉን ደስ ባለን። የእርሶን ወይስ የወዳጆን ስም መትረነው ከሆነ አሊያም እርሶም እንደነርሱ ያደሩ ከሆነ መከላኪያዎን ቢያቀርቡ ከማስተናገድ ወደኃላ አንልምና ይሞክሩን።

ከሚላመጠው ሳይሆን የኛን ማንነትም ለማወቅ የተቸገሩበት ምን እንደሆነ ባናውቅም በላኩት ስማችንና አድራሻ አስ
መልክቶ ምላሽ ስናደርግ ፤ እርሶና ቢጤዎቾ ግን ለራሳችሁ ራሳችሁን መጠየቅን በውል ስታችሁታል። ሲጠይቁ መጠየቅንም ማወቅ መልካም ነውና የእርሶን ሙሉ ስምና አድራሻን ሸሸጉ? አርያነት ከራስ ይጀምር ሲባል ካልሰሙ አሁንም ከዝንባሙ መደብ ያስቆጥሮታልና ለኛ የሰደዱት ግን በስማችንና በአድራሻችን ስለቀረበ ማስተናገዳችንን በተግባር ዋቢ አድርገሎት በሀሳቡ ይስማሙ ይሆን? የእርሶ ነውና መልካም ትንሣኤን እየተመኘን ቅን ልቦና እንዲሰጦት ከውዲሁ ፍላጎታችን ነው።