Saturday, April 30, 2011

…..“ ሳምንት ይቆያሉ ብለው ያላሰቡን የቦርድ አባላት….’

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!

ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።

 …..“ ሳምንት ይቆያሉ ብለው ያላሰቡን የቦርድ አባላት….’


የተወደዳችሁ የገጻችን ተከታታዮች እንደምን ሰንብታችሁ? እንኳንም ለዳግማይ ትንሣኤ በሰላም አደረሳችሁ፤ ፈቃዱ ሆኖ ሁላችንንም ለዚህ ላደረሰን ለእግዚሀብሔር ታላቅ ክብርና ምስጋና ይሁን። አሜን። የዳላሱ ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ደብር ከምንግዜውም በላይ በታላቅ በዐል ትንሣኤን እንዳከበራችሁ ከጸሎተ ሀሙስ ጀምሮ ከከተማችሁ ገብታ ከናንተ ጋር የከረመችው የገጻችን እድምተኛ አካፍላናለች።

አሁንም እስከ ዳግማይ ተንሣይ እንደምትከርምና ሰፋ ያለ ዘገባ ደብሩንና ባጠቃላይ ወገኖቻችንን አስመልክቶ ወደፊት እንደምታካፍለን ተስፋችን የጎላ ነው። በተለይም በበዐሉ ላይ ከመቼውም ጌዜ የበለጠ ቁጥር ምዕመናን መሳተፉንና በአዲስ ልብሰ ተክህኖ ባጌጡ ካህናት የተካሄደው ግልጋሎት ከአዲሱ ዝርግፍ መብራት ጋር በጣም የደመቀ መሆኑንን ከህታችን ተረደተነዋል። አዲስም ሆኑ የቆዩት የወገኖቻችን የክርስትና እምነት ቦታዎች ሁሉ በጥሩ ሁኔታ መከበሩንም አልሸሸገችም።

በሌላ በኩል ደግሞ የቄስ ሽታ መሰናበትና በዚያው አካባቢ የተያያዘው ዘገባዋ ብዙ የሚላመጥ ስላለው እንደ አመቺነቱ ወደፊት የሚቀርብ ሲሆን፣ የዳላሱ ሚካኤል አስተዳደር ተመረጭ ጠሀፊና ሚስታቸው የሌላ(ዲቪ ጊዮርጊስ) ቤተክርስትያን ቦርድ አባልነት፣ ይኸው ቤተክርስትያን ከሌላው ጊዮርጊስ ጋር ውህደት፣ ወደ አባ ጳውሎስ ጎራ መግባት የመሳሰሉት ዘገባዎችን ከፊታችን አቆይተን ወደ መርዳጃው ማህበር በመዞር ከዚህ በፊት ተፈራወርቅና በትሩ የተመራውንና መረዳጃ ማህበር ፈቃዱን በማብከን በስማቸው ለማዞር ያደረጉትን ሴራ በወ/ሮ የሐረርወርቅ ጋሻው በመጋለጡ በሳቸው ላይ የተከፍተውን ዘመቻ የቅርብ ትዝታ መሆኑን ለሁላችሁም ግልጽ ነው። የወ/ሮዋ ጥቅም ፈልገው ሳይሆን አስቀድመው የደረሱበትና ሲወለድ ጀምሮ የተንከባከቡት ድርጅት ጭምር በመሆኑ ነው። አጋሮቻቸው እነ ዘውገ በወቅቱ እያወቁ በሌለ ድርጅት ስም እየጠሩ በራዲዮ የደሰኮሩት ዛሬ ምን ይበሉ?

የኢህአዴግ ልዑካን በመጡበት ጊዜ ከተቃዋሚዎች ተለይተው ዘውገና በትሩ ፊትና ኃላ ሁነው በጓሮ በር በተኮላ መኮንን aka ተኩላው አማካኝነት ለመግባት ሲሞክሩ በፖሊስ መጀመሪያ የተጋለጠውና ስለመታሰሩም ምንም መረጃ ያልተዘገበለት እንደ ታጋይ አድርጎ በሬዲዮ ያቀረበው፣ ሰሞኑንም እንደጀኔዎችና አበበዎች ለበትሩ ታጋይነት የጀመሩት ዘመቻ፤ የስብሰባው ምሽት አብረው ለምን ከልዑካኑ ጋር የእራት ምሽት አሳለፉ? አዲሱ መረዳጃ ማህበር አመራር ዘውገና ስጦታው የተባሉትን የኢህአዴግ የውስጥ ቅጥረኞችን ከራዲዮ፤ እነበትሩን ከሕንጻ ኮሚቴው ባስቸኳይ ማስወገድ አለበት።  

ሌላው ተኩላው ዘሬ በግላጭ ከሳሽነቱንና የመረዋ ቦላጊነቱን ባደባባይ አስቀመጠ። ሲጥፈው …..“ ሳምንት ይቆያሉ ብለው ያላሰቡን የቦርድ አባላት….’ ብሎ ። እራሱን እንደ ገለልተኛ አድርጎ ዋሽቶ መክረሙና በተለያየ የብዕር ስም መጠቀሙ እኛ ያልነውን አርጋገጠ። የጋንት 44 አባል በኃልም ጋንት 1 አባል በመሆን በተደረገው አፈና ፣ ሰቆቃዊ ምርመራና ግድያ በኢሕአፓ ውስጥ የፈጸመው ቡድን ነህ ስንለው፣ እኔ ኢሕአፓ አይደለሁም ሆኜም አላውቅ ያልክ በሕይወት አበጀ ቢመሰክር ምን ምድር ትዋጥህ? 10 ሳንቲም ለሚካኤል ለስኳር የማትል ገብትህ ዘኬ ስትዝቅ ምን አይነት ሆድና አእምሮ ይኖርህ? አባል ያልሆንክበትን ደብር በሀሰት ከሳሽነት ሲገርመን ያለስራህ ገብተህ ንብረት ቆጣሪነትህ ለምንድን ይሆን? ባንድ ወቅት የጌቶችህ ጌታ መለስ ዜናዊ መፍረስ ካለበት ደንበልም ይፈርሳል ያለው ገና ባዲስነቱ ነውና እንደ አስፈላጊነቱ ሁሉም ይሻሻላል። ከወደድከው ገራዥ ሴል ላይ ጠብቀህ መብራቱን መግዛት ትችላለህ። ቲቪውም ቢሆን ከዋናው ደህንነት መቆጣጠሪያ ቤሮው ውስጥ ከ10 በላይ አዲስ የተተከሉትን ምስል መቅራጫዎችን መመላከቻ ሆኖ እንደ አንተ አይነቱን አጽራረ ቤተክርስትያን የምታደርገውን ሁሉ ከውስጥም ሆነ ከውጭ ይመዘግባልና፣ የዛሬው የምላስህና የብዕርህ ሀሰት ነገ ደግሞ እጅ ከፍንጅ እንዳይሆንብህ እነ አባ ጳውሎስና ጌቶችህ የትግሪ ነጻ አውጪ ወደ ከፈቱት መካተቱ ይሻልሀል። ኸዚህ ደብር ሆኖ እንጂ አንተን ማየትም የሚፈቅድ ያለም አይመስልምና ከቀባሪህና ሊደግፍ ከሚችል ወገንህ ጋር ባትካረር መልካም ነበር። ለዋቢነት ወንድምህ መስፍንን እንዴት አድርገው አስከሬኑን እንደሸኙልህ መዘንጋት ከሌላው ክህደትህና ሀሰትህ ሁሉ ይከፋልና ልቦናህን ወደ ፈጣሪ መልሰህ አስገዛ።

በመጨረሻም ከሚካኤል ሠይፍ በተጥየቅነው መሰረት የፊታችን ሜይ 4 ቀን በነጥሩአየር ደብሩ ተከሶና ተፈርዶ የነበረውን ከሳሾች ይግባኝ ብለው የጠየቁትን በዚሁ እለት በይግባኝ ሰሚው ችሎት በመገኘት ለደብራችሁ ድጋፍ እንድታደርጉ ሲጠይቁ ዝርዝሩን ከደብሩ ታገኙታላችሁ ብለዋል። መልካም እድል ለደብሩ እየተመኘን አምላክ የተሳሳቱትን ወደ እውነተኛው መንገድ ይመልሳቸው፣ ሁላችንንም በምህረቱ ይጠብቀን። አሜን።

እርሶስ ምን ይላሉ?  

No comments: