Monday, August 2, 2010

አጭር ዜና

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!

ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።


አጭር ዜና

በኦገስት ሁለት ከዳላሱ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ሬዲዮ ባንሰማም ሁለት አበይት ሁኔታዎች እንደተፈጠሩ ሹክ ያሉንን ምንጮቻችንን ከማመስገን ወደ ኃላ አንልም። እናንተም ብዕሮቻችሁ አይንጠፉ ! ሰላም ለሁላችሁ ይሁን።

በጠዋቱ ነው አሉ በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስትያን ውስጥ በተሰገሰጉ የማህበረ ቅዱሳን አመራርና ጭፍሮቻቸው በተቀነባበር መንገድ ከቅዱስ ሚካኤል በቅሌት የተባረረው የጳውሎስ ካድሬ ሲደልል ከሂስተን መዳኒዓለም ቤተ ክርስትያም ከሴት ምዕመናን ጋር (አስነዋሪ ለመግለፅ) ምንክስናውን ባቃለለው ፣ እንደዚሁም የቡድኑ ተወካይ የሆነውን ዲያቆን ለማውኃድ በዚሁም ክምችት ውስጥ የተጠራቀሙት በሙሉ ከሚካኤል ሰይፍ የሸወዱ የመሰላቸው ፤ ባለ ቪዲዮው መስፍን ኢሀአባው ይህንኑ ጋብቻ ቪዲዮ ቀራጭ የተሳተፉበት ትእይንት መስታወሉ አልደነቀንም።አስቀድመን በመረዳታችን ከማሳሰብ ወደ ኃላ አላልንም። ሲሆን ትልቁን ደብር ካልሆነም ትንንሹን የመስበር አላማቸው ከማንም የተሰወረ አይደለምና። እንግዲህ እኛ የብዙሀኑ ፍላጎት ይሆን ባናውቅ፣ ከዚሁ ቤተ ክርስትያን ጋር ብዙም የጠለቀ እውቀቱ ስለሌለን የተቀረውን ከአባሎቻቸው እስክንሰማ በዚሁ መቋጨቱን እንመርጣለን።

ሌላው ማምሻውን የቅዱስ ሚካኤል ደብር ተቆርቋሪ ነን ብለው ራሳቸውን የሚጠሩ በጣት የሚቆጠሩ ግለሰቦች ከከሳሽና አጫፈሪዎቻቸው ቡድን ጋር ሁለተኛ ዙር ንግግር የጀመሩ መሆናቸውን ስንሰማ፣ እነዚህ ግለሰቦች እነማን ናቸው የሚለውን ለማወቅ ጥረናል። ግለሰቦቹ የራሳቸውን የግል ፍላጎት ተከትለው ከቀድሞ ወዳጆቻቸው ጋር የነበራቸውን ወዳጅነታቸውን ለማደስ እንጂ አሊያም ለወሬ ካልሆነ በቀር ከዚህ በፊትም ሆነ ወደፊት የሚያስመዘግቡት ፋይዳ የላቸውም።

የቦርዱም ሆነ የምዕመኑ አቋም የተለወጠ ወይም የሚለወጥ ምንም አዲስ ነገር የለም ፤ ውዥንብርም የለም። አባላቱም መብትና ግዳጃቸውን በሚገባ ተርድተው በመተዳደሪያው ሕግ መሰረት እየተገበሩት ይገኛል። አባል መሆን ለሚሹ ሁሉ የተዘጋጀ መድረክ አለው። አባል ያልሆንም የጋራም ሆነ የግል መንፈሳዊ ፍላጎቱን ለማርካት የተዘጋጀ መድረክ አስቀምጧል። ለከሳሾቹም እንደዚሁ ፤ ነገር ግን እነሱን በተመለከተ ምንም አይነት ድርድር ውስጥ ማንም እንደማይገባ (አክቲቭ ኬዝ) ተቀምጦ እያለ ምን ለማድረግ ወይስ ወዴት ለመወገን ነው። ከዚህ በፊት ደጋግመን እንዳስገነዘብነው ሁሉ ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ወይንም ፈቃድ ፤ የሁለቱም ወገን የሕግ ተወካዮች ወይም አማካሪዎች ውጪ መንቀሳቀስ በዚህ በምንኖርበት ታላቅ ሀገር ተቀባይነትና አግባብ ከሌለው ተግባር እንዲቆጠቡ ከዚሁ እንጠቁማለን። ከዚሁ ጋር በማያያዝ ከሳሾች ምንም የሕግ ነጥብ እንደሌላቸው እየታወቀ ይህንኑ መሰረት ያደረገ ክርክር ይዞ በፍርድ ቤት መጨረሱ አማራጭ የሌለውና ብቸኛ መንገድ ነው። መቃብር ጉድጓድ ውስጥ ለተኛ የቀረው አንድ ደረጃ ብቻ ነውና የምን ማስታመም?

በዚሁ ዕለትም ተኩላው የወንድሙ አጥንት ይውቀሰው ይሁን ሌላ በገጹ መረበሹን በግልጽ አስቀምጦቷል። ለዚህም ማገገሚያ ያገኘ መስሎት የኩይ ሰይጣን ምግባሩ ተካፋይ የሆኑትንና እንደሱ ሕመም ላይ መሆናቸውን ያወጉትን ጠቃቅሶ ሲዳክር ከሌላም ቦታ መነካካቱን አልተወም። አሁንም መስሚያህንና ማመዛዘኛህን የዘጋብህ ሰይጣን አብሮህ ስላደገ ማስተዋል አቃተህ እንጂ እግዚሐብሄርን ያመነና የተጠመቀ ሁሉ በእግዚሐብሄር ቤት መንገዱ አንድ ነው። አንተ እንደምትለው የአለም ፖለቲካ መብት ወይም ሥልጣን አይደለም ፣ አንተ እንደምታወጋው ሆኖም አያውቅ ወደፊትም አይሆንም ። ‘እኔ መንገድም ሕይወትም ነኝ’ ብሎ ተጽፋልና የቀዳዳው ጠበቃ፣ የቀዩ ሰይጣን ሳንቲም ፣ የከሸፈበት መተዳደሪያ ደንብ አርቃቂውና እንዳንተው ያሳበደው የግርማቸው ምክር ፣ ወዘተ…… እውነተኛ ክርስትያን ከሀይማኖቱ ጋር አይጣላም አይካሰስም፤ ለዚያ ቤተክርስትያን ያደረገውም ሆነ የሰጠው ሁሉ እንዲቆጠርለት በዕምነት ያደርጋል። የሰጠውን እንዲመለስለት አይጠይቅም ። በሚያመልክበት ቦታ ከእምነቱ ተጽራሪ ቢያጋጥመው እንኳን በሰላም በፍቅር የሀይማኖቱን ትምህርትና ስርዐት በተከተለ መንፈስ እንዲስተካከል ማድረግ በጸሎትና በጾም ጨምሮ መማለልን ይጨምራል ፤ ከዚህ ሁሉ ጥረት በኃላ ያንን ደብር ጥሎ ቢሄድ ለኛ መልካም ይመስለናል። አንተና ቢጤዎችህ እንደምትገብሩት ወደ ዐለም ፍርድ ቤት ሁሉን የፈጠረን ጌታን በፍጡራኑ ዳግመኛ እንዲዳኝ ማቅረብ ከፍ ያለ ስህተት ብቻ ሳይሆን ፍርዱ ለትውልድ ጭምር እንዳይተላለፍ ከዚሁ መመርመር ያሻል።

ተኩላውና ቢጤዎቹ እንግዲህ ከሰው አይምሰላችሁ እርሱ በደሙ የዋጃትን ቤተ ክርስትያንና ከሱ መንፈስ ጋር ስለሆነ የምትዋጉት ይህንኑ ተገልጾላችሁ በንስሐ ተመለሱ የምንለው! በዚህ በኩል ሥራችሁን ስንጸየፍ በናንተ መጥፋት ክርስትያን ሁሉ ማዘኑ አልቀረም ።

እርሶስ ምን ይላሉ?

5 comments:

Anonymous said...

ትክክል ጉዳዩ ማለቅ ያለበት አሁንም ቢሆን ያለምንም ቅድመሁኔታ ከሳሾች (በእርግጥም የወያኔ ደጅ ጠኝወችና የ አ.ል.ማ አባላት)ክሱን ሲያቆሙ ነው። ሆኖም ስለዚህ ዜና በበቂ ከማወቅ በፊት ብዙ አጉራ ዘለል ነገር ባይባል መልካም ነው እላለሁ።

ከምስጋና ጋር

Anonymous said...

I'm so sad about the article. What kind of fingers wrote and what a mind (waste) think and read all this .....

Those who don't know how to say 'please', they have no mercy to humanity.

Let’s work in our life, and not to regret when we 'die'.


for ET, LA, MK,

Anonymous said...

አዬ ጉድ፤ አዬ ጉድ፤ይኸ ወያኔ ብሎ ነገር፤ እንዳለ የተጠናወተው የሃሳውያን ቡድን እንዲህ እርቃኑን ይቅር? እናንተዬ! ጉድ አየን እኮ ዘንድሮ። በአማኝ ነኝ ተብየነቱ የሚካኤልን ስእለት ሲቦጠቡጥ፤ በየጋለሞታው ቤት እንደፈለገው ሲዘራ፤ ፎቅ ሲሰራ፤ ሲሸቅጥ፤ ጋዝ ስቴሽን ሲገዛ ኖረ። በግል ህይወቱ ደግሞ እነእንቶኔን ጋዝ ስቴሽን ላጋዛህ/ሽ በማለት በእንዶድ ያላጠቡት ሰው በዚህ ከተማ አይገኝም።ለመሆኑ ቀዩ ሰይጣንና ከሱዳን ገባ የሚባለው ቀዳዳ ኪስ አውላቂ ከነግብረአበሮቻቸው ያልዘረፉት የዳላስ ላብ አደር ይኖር ይሆን። አልፎ ተርፎ ዘመዱን ከኢትዮጵያ ለማስመጣት የተጨነቀ ወላጅ ወይም ዘመድ ሲገኝ በነፍስ ወከፍ ስድስት ሺህ ብር እየተገሸለጠ ሲራቆት ኖርዋል። ታዲያ እንዲህ ያሉ ያራዳ ጩሉሌዎች ናቸው ዛሬ ለክርስትና ሃይማኖት ተቆርቋሪ መስለው እንደተባለው አይናቸውን በጥሪ ጨው አጥበው ሰላም፤ ፍቅር፤ ወንድማማችነት፤ እህትማማችነት፤ አብረን በልተን፤ አብረን ጠጥተን እንዴት በአንድ በተረገመ ዶክተርና ከአፍ በወደቀ ጥሬ እንበታተናለን እንደድሮአችን እንፋቀር እንጂ የሚባባሉት። አልሰሜን ግባ በልው እንዲሉ፤ ለማያውቃችሁ ታጠኑ። እኛንማ ገንዘባችንን ንብረታችንን ጨርሳችሁ ስጋችንን በልታችሁ አጥንታችንን ግጣችሁናል። ከናንተ መሰል የሌባና የወንጀለኛ የተኩላ ጥርቅም ጋር ንግግር፤ ድርድር፤ የሰላም ውይይት ለምን አስፈለገን? ከኛ ምን ልታገኙ? ሚካኤልን እንደሁ ተመልሳችሁ መዝረፍ የምታልሙት ሱሚ ነው። ከሚካኤል ጋር ተነጋገሩ አዋዩት መልሱን ሳይውል ሳያድር ስእለቱን በልታችኋልና በሰይፉ ያሳውቃችኋል። ለመሆኑ በተባለው ስብሰባ እነ የቀድሞ ቦርድ አባላት ነበሩ እየተባለ የሚወራው እውነት ይሆን? አዬ ጉድ “እንደሰራ አይገድል እንዲሉ” ሳይቸግራቸው በሀሰት ምለው ሲገዘቱ ኖረው “አይነጋ መስሏት በቋት….” ሆነና ሚካኤል ሂሳቡን ሊተሳሰብ ጀመረአ!! ትናንት ሲደልልን ካላባረርኩ እያለ ሲያጓራ የነበረው ጸሃፊ ዛሬ አዲሱ ቦርድ “እንዴት ቄስ ያባርራል” አለ ቢሉ ተዉ ግድ የላችሁም እጉድ ዘመን ደረስን እነዚህ የቤተክርስቲያን ጠላቶች ጨርቃቸውን ጥለው ብታዩ አይናችሁን ሸፍኑ የሚልም አልታጣም። ለምን? እግዚአብሔርን ስልካዱ ክፍያቸውን አልነፈጋቸውምና። በከንፈራቸው ስሙን ጠሩ በልባቸው ግን ሸፈቱ። እምነት ካለን እውነትን ከያዝን ለሁሉ እንደስራው የሚከፍለው አምላክ ለሁላችንም እንደየስራችን እንዲከፍለን የዘወትር ጸሎታችን ሊሆን ይገባል።

Anonymous said...

Article from the Dallas Morning News August 4, 2010 on Ethiopian Yeharerwerk Gashaw. የወያኔና የጭፍረኛቹ እመቤት በዳላስ ፎርት ወርዝ የሆኑትና የቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል በጋርላንድ ከወያኔ እጅ እንዳይገባ ወያኔንና ቅጥረኞቹን የታገሉትና አፈር ድቤ ያስገብዋቸው ያሸነፉአቸው ጀግኒት የሐረርወርቅ እነሆ የኮንግረስ ሚኪሊላንድ መታሰቢያ እናት አባት የሌላቸው ሕጻናት መኖሪያ የነበርውን አዲስ አበባ ውስጥ የወያኔ ጭፍራ ሽፍታ በቦምብ መቶታል። Program will remember a Mickey Leland for humanitarian work የሚለውን ዳላስ ሞርኒንግ ንውስ ገብታችሁ ተመልከቱ።
ሚካኤል እንክዋን ወይዘሮ የሐረወርቅን ያንተ አደረካቸው ሊጠብቁህ እንጂ ሊያፈርሱህ አልመጡም እንደሌሎቹ ሴቶችና።


Program will remember a Mickey Leland for humanitarian work

12:00 AM CDT on Wednesday, August 4, 2010

The late U.S. Rep. Mickey Leland did not turn away and forget the starving masses in Ethiopia and other parts of Africa.

Now, nearly two decades after his death in a plane crash during a mission trip to Africa, an Ethiopian-born woman in Dallas is determined that the world not forget his ultimate sacrifice or people of her homeland.

Yaharerwerk Gashaw , an international humanitarian and former model who lives in Dallas, will lead a commemorative program honoring Leland at 2 p.m. Friday in the Dallas City Hall sixth-floor Flag Room.

Fifteen other Americans and Ethiopians also died in the Aug. 7, 1989, crash on a stormy day while taking famine relief to Ethiopian and Sudanese refugees.

Through the Mickey Leland Global Day on World Poverty and Peace, Gashaw hopes to perpetuate Leland's memory and inspire others to follow his legacy of helping the world's suffering people.

Gashaw has traveled extensively in Africa on diplomatic missions meeting African leaders, including Nelson Mandela. She said Leland is her hero and wants to make his commemoration an annual event in Texas, other parts of the United States and Africa.

She founded and supported an Ethiopian children's home in Leland's honor a year after his death.

Rebels bombed the home four years later, killing one child and injuring more than 50 others. But such incidents seem only to enhance her determination to move forward, and this year's commemoration is part of her crusade.

ደሳለኝ ጋርላንድ

Anonymous said...

about the saint George Church and the visitor bishop news is true, but the content did not have any substance . it is a defamatory words towards the innocent monk of the church.