Tuesday, August 31, 2010

ለሰጣችሁት አስተያየቶችና

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!


ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።




ማንኛውም በሕግ ሰውነት ያለው ሁሉ ሕጋዊ መብቱን በአግባቡ መጠቀም ሲገባው፣በተሰጠው መብቱ አልፎ ያለአግባብ ሲንቀሳቀስ ደግሞ ውጤቱ አሉታን ያመጣል። እንደምን ከርማችኃል? እኛም ሳይመቸን ቀርቶ ትንሽ የተራራቅን መሰልን። የብዙዎቻችሁንም ስሞታ ደርሶናል፣ ከመቼውም በላይ ትችትና ወቀሳን እንዲሁም ነቀፌታን ጨምሮ ከሁሉም አቅጣጫ ዘንቦብን ነው የከረመው፤ ለሰጣችሁት አስተያየቶችና ላደረጋችሁት ተሳትፎ ከልብ ምስጋናችንን እናቀርባለን።

የኛና የናንተ የሆነችው ይህችው ብቸኛ ገጽ ከየትኛውም ጎራ ሆነው የግላቸውን አስተያየት ለሚሰጡትና የኛን ሀሳብ የሚቃወሙትንም ያለ አድሎና ያለእርማት በገጻችን እንዳለ ስናወጣ መክረማችን የሚታወቅ ነው። እኛ በምናወጣው ገጽ ትችትና ነቀፌታ ያደረስንባቸው ግለሰቦችና ድርጅቶችን አሁንም ስራቸውን ከመንቀፍ ወደ ኃላ አንልም። የነሱንም ሕጋዊ መብት ሕጉ እስከአልገፈፈው ድረስ እኛም እንጠብቃለን። ቤተ ክርስትያናችሁን የከሰሱና የሚከሱ ሁሉ በሕግ በተሰጣቸው መብት ተንቀሳቅሰው እስካረጋገጡ ውጤቱን መቀበል እንደሚገባ ሁሉ፤ በገጻችን አስተያየት ሰጪዎችን አስመልክቶ እያገዋለልን ማር ማሩን ብቻ እንላስ ማለት የሚወዱትን፤ ለምን የወዳጆቻችን ስምና ቤተሰብ ወጣ፣ለምን በነ ተኩላውና (ተኮላ መኮንን) በነ ቀዳዳው ሙላው ( ሙሉጌታ ወራሽ) ወዘተ….. ላይ ብቻ አትጽፉም ለሚሉት፤ እያንዳንዳችን የመጣነው ከተቀራረበ ሀረግ በመሆኑ በዚሁ ገጽም ያገናኘን ይህን መሰረት አድርጎ ነው። የሌላው ጎራዎች ከኛ የሚለያቸው ተግባራቸው፤ ብሎም ማንነታቸው እንጂ መሰረተ አፈጣጠራቸውን እንገነዘባለን። ግለሰቡን አስመልክቶ ስለቀረበው የግለሰብ አስተያየት እኛን ብቻ መኮነኑ ሳይሆን ምንም ነገር ከፈጣሪያችን የተሸሸገ ስለማይኖር ሁሉንም እሱ በጥበቡ ወደ መልካም እንዲለውጠው ፀሎታችን ነው። ተደጋግሞም ከቤተ ክርስትያን አመራርና ደጋፊዎች አካባቢ እየተሰጠን ያለው ስም የኛ ደጋፊ መስለው የሚሰሩት የወያኔን ስራ ነው ፣ ወያኔዎች ናቸው ይህን ገጽ የያዙትና የሚጠቀሙበት የሚል ዘመቻቸውን በታላቁ ከፍተውብን ይገኛል። እኛ የማንንም ቆሻሻና የጎደፈ ነውርን ለማገልገል ሃሳቡም የለንም። ከማንም ወግነን ማንንም አንኮንንም። የቤተ ክርስትያኑን አመራርንም ጥንቃቄ በተሞላበት ከመቆንጠጥ ወደ ኃላ ብለን አናውቅም፣ በግልጽ ብዙ የማንለው ህልውናውን ለመጠበቅና የቤተ ክርስትያኑንን ቀጣይነት ለማቆየት ነው። ለግል ፍላጎታቸውን ወይንም የሰይጣን መሳሪያ በመሆን በሀይማኖታችንና በማንነታችን ላይ በየትኛውም የአለም ገጽ እጃቸውን የሚያነሱትን ሁሉ ከመታገል ወደ ኃላ አንልም። የናንተም የዳላሶቹ የዚሁ ትግላችን ሰለባዎች ናቸው።

ለምሳሌ የተኩላው ገጽ ባለፈው የቅዱስ ሚካኤል አባል ሳይሆን ተቆርቋሪ ለመምሰል የሀይማኖትና የስጋዊ አለም ሕግ መብት ልዩነቱ የቸገረው፣ እንደ እርሱ በሰይጣን ጎዳና እንደጓዘው የሱ ቢጤ ገጽ ቢያንስ ድቁና ሳይኖራቸው መጽሐፍ እየጠቀሱ የኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ ሀይማኖትን በሚፈልጉት ትርጓሜ ለመግለጽ እንደሚሹት፤ ስለ መጽሐፍ በመጥቀስ እኛ ተሳዳቢ ለማድረግ መሞከር፣ አንተና ቢጤዎችህ መጀመሪያ ተግባራችሁን በመረመራችሁ? የትኛው መጽሐፍ ቅዱስን ለማስረገጫ ዋቢ አድርጋችሁ ቤተ ክርስትያንን ለመክሰስ ያበቃችሁ? ፈጣሪ በደሙ በገዛት ቤተ ክርስትያን ላይ በጥላቻ የተነሳችሁት? ብዙ ማለት ይቻላል ግን ሰይጣን እስረኛ ባሪያው ስላደረጋችሁ የሱን ስለምታገለግሉ አዳዲስ ዲያቆናት ሲወጡም እንደሚያገረሽባችሁ በጥሑፋችሁ አስረገጣቹ ከዚያም አልፋችሁ ነገር ያሳመራችሁ መስሏችሁ እኛን እንዳልተቻችሁ ሁሉ እናንተው ስለቦርድና ልጆቻቸው ብትችሉም ድቁናቸውን ለማፍረስ ወይንም ለማርከስ በብዕር ወጋቹህ ፤ ብሎም ደብሩ አንዴ ራሱን ከስደተኛው ሲኖዶስ አራቀ አንዴ ተቀላቀለ እይላችሁ በሬ ወለደ ሆናችሁ! እሱ ካሰራችሁ ሰይጣን ያውጣችሁ ለንስሐ ያብቃችሁ።

እኛም የመጣውን የዐየር ለውጥ ምክንያት በማድረግ ከሜክሲኮ የባሕር ሰላጤ ወደ ደረቅ መሬት እየተንቀሳቀስን ባለንበት ወቅት ይቺን ለመጣፍ ላበቃን አምላክ ምስጋና ይግባውና ዳላስ የተውናቸው አንዳንድ ወዳጆቻችን በሚሰጠው አስተያየቶች ባለመደሰት የሚያውቁትን ለማካፈል እየንፈጉን ይገኛሉ። የምንፈልገውን ያህል ዘገባዎችን ያለማግኘት ደግሞ ቀጣይነታችንን ያሳሳዋልና የሚተካን ዳላስ በቀል የሆነ ግጽ እንዲወጣ ዛሬም ደግመን እንጠይቃለን? ባልፈው ሰንበትም የሚይ ፪ቱ የደብሩ ብጥብጥ ተዋናይ የነበረችው ክስ መክፈቷን መነገሩን ስንስማ አልተገርምንም! ዕምነት ሳይኖራቸው ቤተ ክርስትያን የሚሄዱት፣ ቤተ ክርስትያንን ሰላም የሚረብሹትን፣ ከሀይማኖት ውጬ በአለም ሕግ ለንዋይ ብለው ካሳ ለሚሹ፣ ራሳቸውን ታላቅና ከፈጣሪ ሕግ በላይ ያደረጉ፣ የሕይወታቸውና የነፍሳቸውን ቁልፍ በማን እጅ እንደሆነ የካዱ፣ ወዮ ለናንተ!

ይህችው አዲሷ ከሳሽ በኛ ግምት የሚጨበጥ ጉዳይ የላትም ነው የምንለው! ምክንያቱም እርሷ ደረሰብኝ የምትለው አስነዋሪው የሀሰት የፎክስ ቲቪ የምሽት ዘገባ ማግስት በዳላስ ካውንቲ ፍርድ ቤት በምስክርነት በቀረበችበት ለነ ተኩላው ክስ ዳኛው በወሰነው ላይ “ የቤተ ክርስትያን መግላጫ የጸሎቱ ክፍል ስለሆነ ማደናቀፍ አይፈቀድም “ ባለው መሰረት ተላልፋ ከዚህም በላይ የሕግ አስከባሪውን ትዕዛዝ በመቃወም ባለማክበሯ ፤ እርሳም በዕለቱ በሰጠችው ምስክርንርትየተረጋገጠ በመሆኑ ለሰራችው በንስሐ መመለስ እንጂ የማይሆን ሌላ ሐጢያት ባልጨመርሽ ነው! የልጆች ማሳደጊያሽን ለከንቱ ባልዋልሽ ነው የምንል። በሌላ በኩል አመራሩም ቢሆን ከጠበቆቹ የሚያገኘው ጥቅም እስከሌለው ድረስ የያዛቸውን የሕግ ባለሙያዎች ባዲስ መተካት አለበት። ምክንያቱም የክስ ክስ ባለመክፈት ቤተ ክርስትያኑን እያስጠቃ ያለው በአሁኑ ሰአት ይኸው አመራር ክፍል ነው። ጉዳዩ ለተከሳሽ የክስ ክስ በመክፈት የሚጀመር ክስ አስተዋጸኦ ከፍተኛ ነው፣ ወጪውም አነስተኛ ነው። አሁን የከሰሱት ጉዳዩ ሳያልቅ ማድረጉ በጉዳዩ ተጠቃሚ ብቻ ሳይሆን ለከሳሾችም ተጨማሪ የንዋይ ተጽእኖ ሲፈጥር ሌሎችም ቤተ ክርስትያኑ ጥንካሬውን በማየት ነገርን በተለየ መንገድ እንዲገነዘቡ ያስገድዳል። ስለዚህ ጉዳይ ተኩላው እንደልማዱ ይጥፍ እንደሆን ብለን ነበር? ምክንያቱም የአላማ አድነት ብቻ ሳይሆን እርሱ ለከፈተው ክስ እማኝ አርጎ ያቀረባት ወዳጁ፣ሃዋዝ በሚሉት ቀጣፊ ለፎክስ ዜና ዘጋቢ ከሌሎቹ ሀገርና ወገንን ብሎም ሀይማኖታችንን ያዋረዱ አብሮቻቸው የፈተፈቱትን ስለሚያውቅ እጁን ምን ያዘው ዛሬ?

በሌላ በኩል ውሽማውን ማስፈታት ያቃተው ሙላው ቀዳዳው ከህብረተሰቡ ተገልሎና ተሸማቆ እንደሚገኝ ካካባቢው የሚደርሱት ዘገባዎች ይገልጻሉ። እየለመነ ከሚጠጋቸውና ከእርሱ ጋር በትምህርትም ሆነ በኑሮ የማይጣጣማቸውን ግለሰቦች ጋር ለመታየት ለሕሊናው መጋራጃ ያገኘ እየመሰለው በኢትዮጵያ የምግብ መመገቢያዎች ቢያዘወትርም ፣ እነርሱም ስለ እርሱ ጠንቅቀው ስልሚያውቁ አሻንጉሊት አድርገውታል ፣ እርሱ ግን ለህሊናው ተመልካችን ያሞኘ ስለሚመስለውና ራሱንም ለራሱ ስለሚዋሽ ላደረበት የጤና
ቅውሰት (ኮሞፕለሲፍ ላየር) እርዳታ ማግኘት ተስኖታል። በባሕላችንም በግልጽ መናገር ስላልተለመደ ደፍሮ ቆማጣን ቆማጣ ማለት ከብልግና ስለሚቆጠር ይሁን ደፍሮ የሚናገረው ስለሌለ ይሁን ውሸቱ እየተናደ በመምጣቱ ግድቡን ሲጣስ በደራሹ የሚጠረጉት ቁጥር ሰውረን ማለት ብቻ ሆናል።

እየተንደፋደፈ ያለው የኮሚኒቲው ድርጅትም የመጨረሻ እስትንፋሱን ውጦ በወያኔ ሎሌና አጫፋሪዎች እየተመራ የሚገኘው የወያኔ ኢትዮጵያ ቀን የፊታችን የሳምንቱ መጨረሻ አደርጋለው ብሎ የማይፈነቅለው ድንጋይ የለም። ቃል የገቡትም ፊታቸውን ማዞር ብቻ ሳይሆን ለመነገድ ያቀዱትም ፊታቸውን ማዞራቸው የበለጠ ፍርሀት አሳድሮባቸዋል። በሬድዮ ፕሮግራማቸውም ያለፈፉትና ያልቀባጠሩት የለም። ያወጡትንም ለመመለስ በመኪና ማቆሚያ ከፍተኛ ኪራይ ለማስከፈል፣ የመግቢያ ክፍያ በማድረግ ለመካካስ ያቀዱ ሲሆን፣ በሌላ በኩል በእድሩ የታቀፉትም የኮሚኒቲው አባሎች የተለያዩ ጥያቄዎችን ማየት ጀምረዋል፣ እድሩ በተጀመረ አመት ውስጥ ተጨማሪ መዋጮ እንዲከፍሉ የበቁት አሁንም ያለ ፕላን የተዋቀረ በመሆኑ በኪሳራ የሚጠፋ መሆኑን በመገንዘብ እንደሚገልጹ ተሰምቷል። ያለ ውዴታቸው የኮሚኒቲ አባል የሆኑት እድረተኞች ገንዘባቸው በኮሚኒቲው መዘረፉ አንዱ ምክንያት እንደሆነም ይጠቁማሉ። እንግዲህ በነተፈራ ወርቅ ወደ ተጠነሰሰው የቀብር ኢንሹራስ ወይንም የሕይወት ዋስትና ሰለባ መንገዱን እየጠረገ መሆኑን አባላቱ እየተረዱት መምጣታቸውንም ተረድተናል። አጫፋሪዎቻቸውም በስልክ፣ በኢሜይል፣ በበራሪ ወረቀቶችና የሚያውቅትን ዘመድና ቤተሰብ ሁሉ እንዲገኙላቸው በመማጸን ላይ ይገኙ እንጂ ሕብረተሰቡ በቃኝ ብሎ እንደተፋቸው ይገኛል። ውይይት የማይሆንለትና እብሪተኛ ለኪሳራ እንዲሉ የእጃቸውን እያገኙ ነው። ለባንዳና የወያኔ ሎሌ አሻፈረኝ ብላችሁ ጥሪያችንን የተቀበላችሁ በደጋፊዎቻችንና በገጻችን ስም ከፍ ያለ የክብር ቦታን ሰጥተናችኃል! ትግሉም ይቀጥላል! ያድርባዮች ጎራም ተሰብሯል።


እርሶስ ምን ይላሉ?

2 comments:

Anonymous said...

ባቶ ፍቅረማሪያም ላይ በ ኢትዮጵያ ቀን ዝግጅት መክኒያት ስለመሰሪነታቸውን አስተያየት ያሰቀመጡትን ሰዎችን አስመልክቶ አንባቢያን እርማት ማድረግ ይኖርብናል። መክኒያቱም ብዙዎቻችን በተለይ ታክሲ ነጂዎች አካባቢና በስልክ ጭምር ሳናነብ የታመመልጅ ላይ እንዴት ይጻፋል በሚል ብዙ ብለናል። የግለሰቦች ስም ሁሉ እያነሳን በተለይ ላቭ ፊልድ የተከራክርን አለን። ከዛም መሃል የተጻፈውን ለማንበብ ወስነን ያነበብነው አስተያየት ሰጭዎቹ ለሰጡት የራሳችን አስተያየት አለን።

አሰተያየት ሰጪዎቹ እንደውም ምክር ነው ለአቶ ፍቅረማሪያም ያቀረቡላቸው። ከሚያደርጉት የክፋት ተግባር ተወግደው የልጃቸው ጉዳይ አንገብጋቢ ጉዳይ ስለሆነ ያለ የሌለ የአይምሮዋቸውን ልጃቸው ላይ እንዲያውሉት የሚመክር ነው። አስተያየት ሰጪዎቹ ለአቶ ፍቅረማሪያም ምክር ነው የሰጡዋቸው እንጂ ልጃቸውን አልሰደቡም በበሽተኛም ልጅ አልተሳለቁም። እንዴውም ለልጃቸው ጠቃሚ ነው አባት ከልጁ ጋር ያጋጠመውን ጊዜ ሁሉ በመጠቀም አብሮ መሆን ይኖርበታል ነው። ይሄም በዚህ በምንኖርባት በአሜሪካን አገር ባልና ሚስት ልጆቻቸው ሲታመሙ ከልጆቻቸው ካልጋ አጠገብ አይለዩም በሆስፒታልም ይሁን እቤት ውስጥም በመፈራረቅ በታቻለ መጥን ጊዜያቸውን የሚያሳልፉት ፍቅር ከሚያሳይዋቸው ልጆቻቸው ጋር ነው። አሰተያየት ሰጪዎቹ ከመዘገቡት የሚያሳየው በአይን በነብስ በቦታ ተገኝተው የአቶ ፈቅረማሪያምን ልጅ የጠየቁና በልጃቸው ላይ ያለው ሕመም የአቶ ፍቅረማሪያምን ሙሉ ትኩረት የሚጠይቅ መሆኑን የተረዱም ይመስላል። ምክራቸው ጥሩ እንጂ የሚያጣላ አይደለም።

ሌላው አስተያየት ሰጪዎቹ የሚሉት፡ አቶ ፍቅረ ማሪያም ለልጃቸው ቅድሚያ ሰጥተው የግል ፍላጎታቸውን ለማርካት ኪሚኒቲ የኢትዮጵያ ወን ወዘተ በሚል ማበጣበጡን ትተው ልጃቸውን ያላስቀደሙ፤ ኢትዮጵያን ካለው የኢትዮጵያ መንግስት እጂ ፈልቅቀው ለማውጣት የሚችሉ ሰው አይደሉም ነው።

በበኩላችን ከዛሬ ጀምረን ከነ ቤተሰባችን ልጆቻችን ጭምር ለአቶ ፍቅረማሪያም ልጅ ጠንነት እግዚአብሄር እንዲሰጥልን እንጸልያለን። ፈጽሞ እንዲምርላቸውም እነማጸናለን ።

Anonymous said...

ይድረስ ለDallaseotc
በዚህ ብሎግ ላይ አቶ ዮሴፍና አቶ ፍቅረማሪያምን አስመልክቶ የተጻፈውን አይተናል። ከእነዚህ ጽሁፉ ተጻፈብን ብለው ካሉት ሁለት ግለሰቦች አንደበትና ከወያኔ ደጋፊዎች የህንን ጽሁፍ የጻፈችው የሐረር ወርቅናት ማለታቸውን ሰምተናል። ነገር ግን ውነቱ ከዚህበፊት መረዋ ላይ እነ አቶ ተኮላ በጻፉትጽሁፍ ስለ አቶ ዮሴፍ ረታና ስለ ሌሎቹም የቦርድ አባላት ስለ አቶ አበበና አቶ ሙሉ አለም ጭምር የቅዱስ ሚካኤልን ቤተክርሲያን አድሚኒስትሬሽን ለመምራት የሚያስችል ችሎታና ትምህርት የላቸውም ብለው በሰፊው አትተውታል። ይህም ተጨባጭ አንድ ምስክር ነው። አቶ ዮሴፍም ባፋቸው ሙሉ መረዋ መታ ላይ ተኩላ ነው የጻፈብኝ አልተማረም ችሎታ የለውም ስለ ኮምፑተርም አያውቅም ብሉ እንዳላሉ አሁን ድግሞ የሐረር ወርቅ ብቻ ነች ይምትጽፍብኝ ብለው አፋቸውን ሞልተው ሲናገሩ መስማታችን በጣም አሳዝኖናል። የወያኔ ደጋፊዎች ይቺን እህታችንን ከትግል ጎዳና ለማስውጣት ያላደረጉት ነገር የለም ቀደም ሲል ይሄውም አቶ ተኩላን ይጨምራል። አሁንም የወያኔ ደጋፊዎች በተለመደው አሉባልታ ወሬያቸውን በየሄዱበት በተለመደው እየነዙባት ይገኛሉ። ይሄንንም ድርጊት የሚያካሂዱት ከኢትዮጵያ ሕዝብ ያጣሉዋትና ያለያይዋት መስልዋቸው ነው። ይቺ እህታችን ግን የወያኔ ደጋፊዎች ባሰራጩትና እያሰራጩ ባሉት ከትግሉ ጎዳና ፈቀቅ አያሰኛትም።

በበጎ የምናይሽ ኢትዮጵያውያን ወገኖችሽ አይዞሽ በርቺ እንላለን።