Tuesday, September 7, 2010

ከማያዳምጥ ጋር መወያየት ትርፉ የራስን ቃል መልሶ ማዳመጥ ብቻ ነው። ቁጥር ፵፩

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!


ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።



ከማያዳምጥ ጋር መወያየት ትርፉ የራስን ቃል መልሶ ማዳመጥ ብቻ ነው። ቁጥር ፵፩

መልካም አባባል ነበር ነገሩ እንዳመልካች ጣት ሆነና ተሙሾ አልቆ ደቆ ፵ው ወጥቶለት በ፵፩ኛው ቀኑ የተረዳው የነተኩላው ገጽን ለእረፍት በወጣንበት ወቅት ትንፋሽ ያገኘ መስሎት ከመቃብር የንስሐ ጩኸት ካነበነበው ነበር። እንደምን ሰንብታችኃል? በፈጣሪ ጸጋና ቸርነት መልሰን ለመገናኘት በመብቃታችን ለልዑል እግዚሐብሔር ምስግና ይሁን‘።

ወግና ሙያ ለብቻ መሆኑን ያልተረዳው የነ ጋሼ ተኮላ (ተኩላው) ገጽ የቻለውን ተንፈራገጠ እንጂ የመቃብር ውስጥ ጩኸት ከምንም እንደማያወጣው መገንዘብ ከተሳነው ዛሬ አይደለም፣ ባሕሪው ሆኖ አብሮት ኖሮታልና። የቅርቡ ጊዜ ምሳሌ ብንጠቅስ ያለውቀቱ ገብቶ የቅዱስ ሚካኤል ደብር መተዳደሪያ ደንብ የማሻሺያ ሀሳብ እንዲያያዘጋጁ ተብሎ የተሰየመ ኮሚቴ ውስጥ ገብቶ፣ አብረውትም የተሰየሙት ከእጅ አይሻል ዶማ ሆነው ፤ ማሻሻያ የሚለውን ትርጉም ገብቷቸው ይሁን ወይም ሌላ ተልኮ በወቅቱ ይዘው ፤ ያቀረቡት ከተጣለባቸው ኃላፊነት ውጪ ወጥተው ሕጉን በመለወጣቸው ነበር። ምዕመናኑ የቀረበለትን አዲስ ሕግ በሙሉ በመቃወሙ በደረሰባቸው ኪሳራ መቀበል ተስኖቸው በአደባባይ ዛሬም ቤተክርስትያናን እየወጉ ያሉት። የዚሁ ኪሳራ ሰለባዎች የሆኑትና አሁንም በግምባር ቀደምትነት ደብሩን የሚወጉት የዚሁ የፈረሰ ኮሚቴ ውስጥ የነበሩት መሆናቸው ሁሉም የሚያውቀው ሀቅ ነው። እኔ ያልኩት እንጂ ልዑል እግዚሀብሔር የፈቀደው አይደለም፤ ወይንም የሀይማኖቱ ጥልቅ እውቀት ያላቸውንና በሚገባ በስደተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ አማኒያን በምዕራቡ አለም በገለልተኝነት እየተቋቋሙ ያሉትን ቤተክርስትያን በቂ ግንዛቤ ያለውን ጥናቶችን ማካሄድ ሲገባ፤ በዘፈቀደ ወይንም በሌላ ተጽዕኖ ሆኖ፤ አሊያም ግርማቸው የሚሉት የዚሁ ኮሚቴ አባል ከአዲስ አበባ በሚሰጠው አመራር የተቀነባበረ ሕግ ፤ ከመድረሱ መፍረሱን እንደ ግል ጥቃት አድርጎ መውሰድ አንዱ ነው። ስለ ህግና መብት መቀባጠር የማይሰለቸው ተኩላው እስረኛው ሁኖ የሚያመልከው የሰይጣኑን ብቻ ሆናል። ይህንኑ የተጠናወተው የመንፈሳዊውና የአለም ኑሮና ህግ ተምታቶበት ያንቧርቃል።

እኛን ተሳዳቢ ሌላም ብትለን ከቆምንለት የማናወላውልና ለማንም የማንወግን፤ እውነትና ቀጥተኛ መንገድ ይዘን የምንነጉድ ለመሆናችን እየተገለጸልህ ስለመጣ ፤ ቀድሞ እንደምታስበው አፍንጫህ ስር ተቀምጠን ፤ የቦርዱ ልሳን፤ አንዳንዴም ቦርዱ፤ ወይም ያንተ ስራ ከሚተባበሩ ጥቂት ቆራቢ ነን ብለው የጠረጠሩትን ሁሉ ማሉልኝ ያሏቸውን ወይንም ገጻችን አንቦ የተነፈሰውን ሁሉ የዚህ ገጽ አዘጋጅ አለምሆኑን አንተና ቢጤዎችህ በሚገባ እየተረዳችሁ በመምጣታችሁና ፤ ፈተና ስለሆንባችሁ የኛን ገጽ ወዳጆችን እንዳያነባት ምልጃ ጀመራችሁ። ባደባባይ አታንቡ ፣ አትረዱ ፣ የራሳችሁንም አቋም አትወስኑ፣ እኔ ብቻ ነኝ የማውቅላችሁ (እንደከሸፈው የመተዳደሪያ ደንብ) ፣ ወዘተ……. ከሆነ ያቺ እንደ አቡነዘሰማያት የምትደጋግማት የአለም መብት ጥያቄህን የትኛው ጉያህ ልትደብቃት? አንተ የገጻችን ወድጅና እድምተኛ እንደሆንክ ሁሉ እነርሱም ካንተ ያላነሰ መብት ገጻችን የሰጠቻቸው መሆኑን እንዴት አይገባህም? ልክ በ ፵ኛህ የአደባባይ ሞተ ገጽህ ማግስት እንደጠቀስከው ሆነብህና እንግዲህ እረፈው። እኛ ለቦርዱም፣ ለካህናቱም፣ ለዳቢሎሱም (አንተንና ቢጤዎችህን ለርሱ ያደራችሁትን) ሁሉ እንደ ፍጡራን እኩል ስናያችሁ በተግባራችሁ ግን እንለያችኃለን።

ጋሼ ተኩላው በብጥብጡ በወርድክ ነበር ግን ፈቅዶ እድሉን ቢሰጥህም ከታች ሁነህ የምትወጋ ፍጡር፤ አንተ ትላንት እቃወመዋለው የምትለውን ወያኔ ዛሬ ደጋፊ ሆነህ ደብሩን የእጅ መንሻ ለማድረግ መራራጥህ ቤተክርስትያኑ ለድርድር እንደማይቀርብ በተረዳኸው። የአንተን ወያኔ ደጋፊነት መግባትህን የግል መብትህ መሆኑን ባለፈው ጥቂት ወራት የተሳተፍካቸው ስብሰባዎች ያስረግጣሉ። በመጀመሪያ አባል ባልሆንክበትና ባቋቋሚነትም ስምህ በሌለብት ከሳሽ ፣ በሁለተኛ በማያገባህ ገብተህ ስደትኛ ሲኖዲስ ምናምን እያልክ መዘላበድ የራስህን ጎራ በግልጽ እያስበላህ መጣህ! እንግዲህ የወያኔ ሎሌ መሆን የጥቅል ውል አለበትና ኃይምኖቱም የዚሁ ሰለባ መሆኑ ሀቅ ነው፣ አንተም እያራመድከው ነው። እኛ ግን ካንተ የምንለየው ፤ ማንኛውም ከሀገር ውጪ በግሉ የሚከፍተውና እያስተዳደረው ያለውን ደብር መብቱ ይጠበቅለት፣ የራሱን መብት ራሱ ያቋቋመውና የሚያስተዳድረው ምዕመን ይወስን ነው። አንተና ያንተ ቢጤ ቅጥረኛ መቋመሪያ አይሁን ነው። የዚህ ሂደት ተሳታፊ ለመሆንም የተቀመጠውን መብትና ግዴታ መወጣት እንደሚያስፈልግ የጨለመብህ። አንተ ለኑሮ ውድነት መደጎሚያ እንደምትጠይቅ ሁሉ ደብሩም ካለው ሁኔታ ጋር አመዛዝኖ በቀን አንድ ብር በወር ድምሩና አባላት ክፈሉ በማለቱ አንተ በድሮ በሬ ሂደህ ለምን ከአምስት ብር በላይ እከፍላለሁ ብለህ ያኮርፍክና የወጣህ (ሊያው የትንሽ ጊዜ አባል) ትልቅ አያርጉህ ሕጻን። በተለያየ ቀን የዘባረከውን ስታውሳ ዛሬም እዛው አልንህ። ትላንት የድሮውን ሕግ ተቃውመህ አሻሻይ ኮሚቴ ዛሬ ደግሞ የተሻሻለውን ተቃውመህ በድሮው የምትል፣ አንተና ቢጤዎችህ የቤተ ክርስትያኑን ገንዘብ የዘርፉትን (ከፈጣሪ የሰረቁትን) በሱ ገንዘብ አንተና ቢጤውችህን ማን ወኪል አደረጋችሁ፣ ያው የለከፋችሁ የቤትክርስትያን ጠላትነታችሁ በሽታ የሌባ ጓደኛ አደረጋችሁ እንጂ። ባለፈው የመጽሀፍ ቅዱስ አንባቢ ብሎም ፈቺ ለመሆን ዳዴ ለማለት ቢያቅታችሁም፤ የድቁርና ስራችሁ እንደቀጠለ ለመሆኑና ላለፈው ስህተታችሁ የማትማሩ፣ ማስተዋል የጎደላችሁ ፣ ለመንፈሱ ማደሪያ የማትሆኑ ቀፎ ጭንቅላት የተሸከማችሁ መሆናችሁንና ስለሀይማኖቱ የእንጭጭ ስንኳ እውቀት የሌላችሁ በአስሩ ቃላት የተጻፈውን የማታውቁ ፣ “አትስረቅ“ የሚለውን ህግ ለተላለፉት ያውም የቤተ እግዚሀብሔርን ገንዘብ ሰረቁ የተባሉትን ዋሻ የሆናችሁና ከነሱ የወገናችሁ መሆናችሁን ዛሬም ደግማችሁ ያስረገጣችሁ የሰይጣን ማደሪያዎችና የሁላችን ማፈሪያዎች።

ሌላው ደግሞ ከላይ ስሙን ያነሳነው ግርማቸው አድማሴን ብዙ ከርሱ የቀረቡ ቢመክሩት አልሰማ ያለና ፤ እንደሰማነው ትምህርትን የሚችለውን ያህል የገረፈ የተባለለት፣ ልዑል እግዚሀብሔር ሳይሆን እኔ ያልኩት የሚል እልህ የተጠናውተው ያላዋቂ ሳሚ ሆኖ ከሰይጣን ወግኖ የወዳጆቹና የቤተሰቦቹ መሸማቀቂያ ሆኖ ሰንብቷል። በዚህ የቤተክርስትያን ጉዳይ ተመሳሳስይ ሁኔታ ውስጥ የገቡትና የተሸካካሩ ብዙ ናቸው። ሀይማኖታዊ እምነትንና የልብን ፍላጎት ነጥሎ አለማውቅ ውጤቱ ከዚህ የተለየ አይሆንም።

እኛን መቃረን ያልሰለቸው ኮሚኒቲውን አስመልክቶ ጥሩ በአል እንደነበር ሊቀባ ሞክራል። በስፍራው ከተገኙት እንደ ተረዳነው የቅዳሜው ከምን ጊዜውም በጣም ያነሰ እንደነበር ስንረዳ ከቀዳዳው (ሙላው) የተጋባበትን ተኩላው ሀሰትን እውነት ብሎ ዘግባል። በርግጥ በእሁዱ ጥርያችንያልደረሳቸውና የነሱንም በቤትሰብና ወዳጅ ልመናና ውትወታ ከእደረተኛው ቁጥር አካባቢ የሚቃረብ ጎብኚ እንደጣለላቸው ለመረዳት በቅተናል። ከሁሉም በላይ ጥሪያችንን ተቀብላችሁ እራሳችሁንን ከወያኔ ቀን በአል ላራቃችሁ ሁሉ ከፍተኛ አድናቆትና ክብር እናቀርባለን፣ በቆራጥና በንጹህ የኢትዮጵያ ውዳጆችና ተቆርቃሪ ሁሉ ስላደረጋችሁት ተሳትፎ ምስጋናችን ይድረሳችሁ።

ከዚህ ሌላ ቦርዱ ያለፉትን አመታት በተደረገው የሂሳብ ማጣሪያ መሰረት በኃላፊነት መጠየቅ ያለባቸውን ምን አደረሰው? ያለፈው አመትን በተመለከተ የሂሳብ ማጣርያ መቼ ነው? ለህጻናት አስተማሪ ተገኘ የተባለው ወሬ የት ገባ? ክሶችን በተመለከተ ምን እየተሰራ ነው? ይኼን በተመለክተ አስተዳደር ቦርዱ ምላሽ ሊሰጥ ይገባዋል እንላለን።


እርሶስ ምን ይላሉ?

4 comments:

Anonymous said...

Hello you the Blogger.

I have the chance to visit the Senbete Blogg and the name listed in regard a member of our community. I have lived in Dallas over 30 years. Most of the name is very known for me, when I analyzed those individual back ground and the work they contributed to our beloved Church and Community, there is none to back their accomplishment. In fact all of them are obstacle for our unity and progress here in Dallas aria. This individual ring is lead by Teferawork and Betru, Kedane and like Germachew, Tekola etc. have been fallers. I think you need to take time and write their bad work. Thanks,

Anonymous said...

Hi Dallas eotc blogger,

You are become more loveable among our community for your work. I and my friends decide to join your blogg as exciting our share of responsibility as not only a member of our communality as a follower of same Faith. We are appreciative for the work you doing from far away, for the LOVE and CARE for us. We also immersed for accommodating all negativity against your own Bloogg. This is the way to go and continue same.

Anonymous said...

Your blogg is very informative and yours only out there very balanced. You seem genuine and not take side either way put you in rank. Keep the path.

Anonymous said...

የተወደዳችሁ ዳላሶች,


እንደምን ክርማችኃል? እኛ እንደምናችቃፍሁ ሁሉ አትጥፉብን, ቸሩ ፈጣሪ ይጠብቃችሁ. እነዚህ ወሮበሎችን በህብረት ማጥፋት ስላለብን የሁላችንም ግዴታ መሆኑን ላንባቢያን ላሳስብ እወዳለሁ. ሁላችንም ነቅተተን የነሱን ተንኮል ማክሸፍ ግዴታችን ነው.