Tuesday, September 14, 2010

የዳላሱ ቅዱስ ሚካኤል ጥሩ ነገር አይወድለትም ለሚሉ

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!


ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።



የዳላሱ ቅዱስ ሚካኤል ጥሩ ነገር አይወድለትም ለሚሉ

አዲሱን የዘመን መለወጫ ምክንያት በማድረግ በዕለቱ ምሽት አዳራሹ የሞላና የሞቀ የራት ምሽት ቀዳሚት መሰከረም ፩ ቀን አድርጓል። ከህፃናት እስከ አዋቂ የተሳተፉበት በየደረጃው የተዘጋጁት ትርዒቶች ታዳሚውን ያዝናኑና ያስተማሩ መሆናቸውን ከዳላስ የሚካኤል ሰይፍ እየተባለ የሚታወቀው ቡድን ካቀበለን ለመረዳት ችለናል። የተወደዳችሁ የገጻችን አንባቢያን እንደምን አላችሁልን? አዲሱ ዐመት ካለፈው የተሻለ የሰላም፣ የፍቅር፣ የጤንነት፣ የአንድነት ፣ የመቻቻልና የብልፅግና አመት እንዲሆንልን የልዑል እግዚሀብሔር ፈቃድ ይሁንልን። አሜን።

የበግ ለምድ የለበሱ ተኩላዎችም በምሽቱም ሆነ በሚቀጥለው ዕለተ ሰንበት የመጀመሪያው የዘመነ ሉቃስ ጸሎተ ቅዳሴ መቋጫ ላይ እንደ ልማዳቸው ብቅ ብቅ ያሉትና ከበጎቹ የተቀላቀሉትን እረኛው ጠንቅቆ የሚያውቃቸው ማፈሪያና ማዘኛ መሆናቸውን በዲሱም አመት የተጸናወታቸው ጸረ ቤተክርስትያናዊነትና እምነት ይለቃቸው ዘንድ የሁላችንም ጸሎት ነው። ምን ጊዜም ከነሱ በዕውቀትም ሆነ በተግባር ተሽሎ የተገኘ ሁሉ የሚያስፈራቸው እነዚሁ ግለሰቦች መርዝ እንደቀመሰ ውሻ ከመሆን ወደ ትክክለኛ ህሊና ፈጣሪ ይመልሳቸው እንላለን። በገጻችን የአስተያየት መስጫ ላይ ከምንለጥፋቸው ከነዚሁ ግለሰቦች አስተያየት እንደምንገነዘበው በአንድ ወቅት የአሁኑን የደብሩን ለቀ መንበር ላይ የሰጡትን አስተያየት ለምሳሌ ብንጠቅስ፤- ሊቀ መንበሩን ከነሱ ስላልወገነና የነሱን የርኩስ መንፈስ ስለተቃወመ፤ ከነርሱ የተሻለ አመለካከት ያለው ብቻ ሳይሆን በእምነቱም ሆነ ከደብሩ አመሰራረትት ጀምሮ ያበረከተውንና እያበረከተ ያለው አገልግሎት በአሀዝ የማይሰላና በዕውቀትም የማይመዘን ንጹህና ፈሪያ እግዚሀብሔር ያለበት ታላቅ ግለስብ፣ በትዳሩም ሆነ በኑሮው ልዑል ፈጣሪ የፈቀደውን ያላበሰው፤ የቻሉትን ያህል ቢቀቡትም እራሳቸውን ደግመው ዝቅ አደረጉ እንጂ አላማቸው አለመሳካቱን አውቀውታል። ይህ ግለሰብ ከአነስተኞቹና እንደ ተኩላ በመካከላችሁ ከሚሹለኮሎኩና በምግባራቸው ገጻችን ስማቸውን ስንኳ ለመጥቀስ ከምትጸየፋቸው ጋር በምንም መንፈስና ደረጃ ተመሳስሎ የማይመዛዘን መሆኑ የሚታወቅ ነው። ሌላው የተገነዘብነው ከነሱ የተሻለ አእምሮ ብስለትና እውቀት ካለው ጋር ተቀምጦ መስራት የተሳናቸው፣ ግለሰቦች ከቦርድ አመራር የተሰጣቸውን ሀላፊነት ጥለው ከሄዱት ውስጥ በኮሚኒትው የጋራ መረዳጃ የልማት ክፍል ውስጥ መግባትን በአሉታ እናልፈዋለን።

ስለ ኮሚኒቲውም ከነካን አይቀር ብዙ የምንለው አለን። የድርጅቱን መኖርና ለወደፊት በብቁ አመራር ጥሩ ደረጃ ደርሶ ከተመሳሳይ ድርጅቶች ጋር ለመነጻጸር እስኪበቃ ድረስ፣ የቀድሞ አመራሮች ካለችሎታ ወይንም ለግል ጥቅማ ጥቅም ሲሉ አጫጭተውት ነው የሚገኘው። እኛ ዳላስ በቆየንበት ጥቂት ጊዜ ለመዳሰስና ተሳትፎ ለማድረግ በሞከርንበት ወቅትም ሆነ በውይይታችን ከታዘብነው፤ የህብረተሰቡ ተሳትፎ በጣሙን ቢያሳዝነንም ምክንያቶችን ለማወቅ ጠለቅ ያለ በመረጃ የተደገፈ ጥናትን ይጠይቃል። ያለህብረተሰቡ ተሳትፎ ስንል ቢያንስ ሲሶውን ማቀፍና ማሳተፍ ካልቻለ የተፈለገውን አቅም ይዞ እድገትን በህብረተሰቡ ውስጥም ሆነ ከአቻዎች ማህበራት ለማነጻጸር አይቻለም። በመጀመሪያ ጥሩ ተመሪ መሆን ያልቻለ መሪ ሊሆን አይችልም። ፪ኛ/ ከፍተኛ እውቀትና ልምድ በሀገሩ ያካበቱና በተለያየ ከፍተኛ ሀላፊነት ግዳጃቸውን የተወጡና ውጤትንም ያስመዘገቡ። ፫ኛ/ አዲስ ሀሳብን የመቀበልና ሁል ጊዜም ለመማር የተዘጋጀ ፣ ህብረተሰቡን በሚገባ የሚረዳና ሊያስተባብር የሚችል፤ ከሀይማኖትና ከፖለቲካው ከራራ አስተሳሰብ የራቀና ጊዜውንና እውቀቱን ሊሰዋ እንጄ ለግል ጥቅሙ ማካበቻ የማያደርግ አመራርን ማስቀመጥ የግድ ነው። ለምሳሌ ለመጥቀስ የታሰበውን ማዕከል ኮሚቴ አባል ከሆኑት መካከል የብሔራዊ ባንኩ ተቀጣሪና ሌላው ቀደም ሲል በዘይት ክባንያ ውስጥ ተቀጣሪና ለቅዱስ ሚካኤል ደብር እድገትን ካስመዘገቡት ግለሰቦች አንዱ የሆነው ተሳተፎ ማግኘት ውጤት ሊያመጣ ሲችል፤ በአንጻሩ አመራሩ ባጠቃላይ የሰው ሀይል ይጎለዋል። የግድ ያሉት አመራሮች አእምሮቻቸውን በመክፈትና ወንበራቸውን ለማስረከብ በሩን እስከከፈቱ በዳላስ አካባቢ በቂ ቁጥር ያለውና ለቦታው ብቃት ያላቸው ኢትዮጵያውን፣ የኢትዮጵያ ተወላጅና ወዳጆች ሞልተዋል። አሁን ያለውም አመራር ከልብ የገንዘብና የሰው ሀይል በመጠቀም የአባላቱን ቁጥር ማሳደግ ግዴታው ሲሆን ፤ የራዲዮን አገልግሎቱን በሚገባ ተቆጣጥሮ ሊጠቀምበት ይገባል እንላለን።

ወደ እርዕሳችን ስንመለስ ደግሞ የቅዱስ ሚካኤል ደብር ደግሞ ደጋግሞ ልዑል እግዚሀብሔር እየባረከው ይገኛል። ለዚህም ሁላችንም ምስክሮች ነንና ምስጋን ለሱ ይሁን። ጥሩና ብቃት ያላቸውን ባለሙያዎችን የክርስትና አስተማሪዎችን ከጉያው ማቀፉ ብቻ ሳይሆን በየጊዜው እየተጋበዙ የሚቀርቡት አባቶችም በትምህርት እየባረኩት ነው። ለምሳሌ ያለፈውን እሁድ ያስተማሩት ሊቅ ቤተ ክርስትያኗ ከአብሯኳ ካፈራቻቸው ብርቅዬና አኩሪ ከሆኑት አንዱ ከእኩለ ሌሊት ጀምሮ የተሳተፉበት ድንቅ ማህሌትና ከቅዳሴው በኃላም የሰጡት ትምህርት የተሳተፉት ሁሉ በመደነቅ የተባረኩበት መሆኑን የደረሰን መረጃ ያስገነዝባል። እኝ አባት ያስተማሩትን የቤተክርስትያናችንን የቀናትን ቀመር ሲሆን ይህ ስሌት ለእምነቱ ተከታዮች ብቻ ሳይሆን ለሀገሪቱም ታሪክ፣ እድገትና አስተዳደር መሰረት ጭምር መሆኑን የተገነዝቡ ሁሉ የሚደነቁበት ነው። ከአገሪቱ ውጭም ያሉ ጠበብቶች ሁሉ ምንግዜም የሚያከብሩትና ከፍ ያለ ምርምርን ያካሂዱበት መሆኑን ብዙ መረጃዎች ይጠቁማሉ። ባትሪያችንን ጨረስን ለሚሉ አሊያም ሰዐታትና ኪዳን መቆም ብቃት የጎደላቸውን የስም ቄሶችን የሚሰሙና የሚከተሉ ቢኖሩ፤ አሊያም የደብራችሁን ውድቀት ለሚመኙና ለዚሁ እኩይ ተግባር ቀን ከሌት ለሚፈጉ ሁሉ እንግዲህ እረፉት። ትሩፍቱና በረከቱን በምግባራችሁ ሲነሳችሁ፤ የይቅርታ አምላክ ይጎብኛችሁ ነው የምንል።ክርስትያን የሆነና እምነቱን የተረዳ አማኒያን መሰማርት ከሌሌበት ምግባር መቆጠብ እምነቱ የሚያስገድደው ሲሆን እንደተገነዝብነው ከሆነ የበግ ለምድ የለበሱ ተኩላዎች በሰንበት ለጸሎት ወደ ደብሩ መጥተው ከመሳተፍ ይልቅ በአዳራሹ በመሰባሰብ ሳይባረክ ለእለቱ እንዲቀመስ የተዘጋጀውን ሲሳተፉና የማይገባ ውይይት ሲያደርጉ መታየት ከጀመሩ ሰንብተዋልና ድርጊታቸው ያለቦታውና ያለጊዜው መሆኑን ተረድተው እንዲቆጠቡ ልንገልጽ እንወዳለን። አዳራሹም የቤተክርስትያኑ አካል ነውና።

የእግዚሀብሔርን ለእግዚሀብሔር መስጠት ለአማኒያን ተገቢ ነውና፣ አማኒያን ነኝ ብሎ እንደአማኒያን ወደ ቤተክርስትያን የሚገባ ሁሉ የተቻለውን ስጦታን ሲችል ካልሆነም ቢያንስ ምዳየ ምጽዋት ማድረግ ተገቢ ነው። ልቦናን ሳያጸዱ በእግዚሀብሔር ፊት መቆም ምንኛ ጎዶሎነት ይሆን? በምንሮበት ሀገር እንኳ ለማንኛውም አለማዊ ግልጋሎት ለምንቀበለው ዋጋ እንደምንከፍል ሁሉ፤ እድሜና ጤና ጊዜም ሰጥቶን ፣ ቤቱንም እንድንገባ ፈቃዱ ለሆነው ልዑል እግዚሀብሔርማ ምን ይገባዋል? ከሱ የሰሰትነውን እራቆታችንን እንደመጣን እራቆታችንን እንደምንሄድ መገንዘብ እንዴት ይሳነናል? የማይጠቅም ጥላቻችን ይዘን የሱ ተገዢ በመሆን አማኒያን ነን ለማለት እንዴት ያስችላል? በዚህ አዲስ ዘመን መጀመሪያ አዲስና የተቀደሰ መንፈስን በውስጣችን ይሰርጽልን ዘንድ የሁላችንም ጸሎት ይሁንልን እርሱም ይቀበልልን አሜን።

እርሶስ ምን ይላሉ?

4 comments:

Anonymous said...

ይድረስ ለዚህ ብሎግ አዘጋጆች

ባለፈው ሁለት ተከታታይ አቅርቦታችሁ ከወትሮው የተለየ ማለፊያ ጽሁፍ በመሆኑ በዚሁ ቀጥሉበት የኛም ተሳትፎ ይጨምራል። መልካም አመት ይሁንልን።

ካንባቢያን

Anonymous said...

ሰላም ዳላሶች

በኮሚኒቲው መረዳጃ ላይ ያነጣጠረውን መፈክር በሰአቱ በማውረዳችሁ ደስ ብሎኛል። ከቀድሞው የተሻለ ቶን የሚመስለው የአዲሱ አመት አቀራረባችሁ ብዙዎቻችንን ማርኮናል በዚሁ ቀጥሉበት።
በምታቀርቡት ሁሉ ለዳላስ ኮሚኒቲ ተቆርቃሪ ብቻ ሳይሆን የቤተ ክርስትያናችን ጉዳይ በጣሙን ያቃጠላችሁ ናችሁ እስካሁን ለሰጣችሁት ግልጋሎት ሳመሰግን ጌታ ይክፈላችሁ እላለሁ።በቤተ ክርስትያናችን ውስጥ ያለው ችግር ቀላል ባይሆንም በጸሎታችን ሀይልና በቅዱስ ሚካኤል ተራድይነት በቅርቡ መስመር እንደሚይዝ እርግጠኛ ነኝ። ቤቱንና ልጆቹን እርሱ ይጠብቃልና በአዲሱ አመት እናንተን የለውጠ የነሱንም ልብ ይለውጣልና በአሁኑ አያያዛችሁ ቀጥሉበት።

ብርቄ ከዳላስ

Anonymous said...

የእግዚሀብሔርን ለእግዚሀብሔር መስጠት ለአማኒያን ተገቢ ነውና፣ አማኒያን ነኝ ብሎ እንደአማኒያን ወደ ቤተክርስትያን የሚገባ ሁሉ የተቻለውን ስጦታን ሲችል ካልሆነም ቢያንስ ምዳየ ምጽዋት ማድረግ ተገቢ ነው። ልቦናን ሳያጸዱ በእግዚሀብሔር ፊት መቆም ምንኛ ጎዶሎነት ይሆን? በምንሮበት ሀገር እንኳ ለማንኛውም አለማዊ ግልጋሎት ለምንቀበለው ዋጋ እንደምንከፍል ሁሉ፤ እድሜና ጤና ጊዜም ሰጥቶን ፣ ቤቱንም እንድንገባ ፈቃዱ ለሆነው ልዑል እግዚሀብሔርማ ምን ይገባዋል? ከሱ የሰሰትነውን እራቆታችንን እንደመጣን እራቆታችንን እንደምንሄድ መገንዘብ እንዴት ይሳነናል? የማይጠቅም

Anonymous said...

Taken from Selam Tewahedo.. Do we even remember devil worshpers like Alemayehu, Tadesse with pente wife, Belay, Araya, Mesfin, etc. etc. were entering that MEKEDES making it thrashed. Who are we kidding. These people are still walking around damaging the Church and the names of good people when God should strike them down and bury them. What are we talking about. Mahibere Saitan should be draged out of that Church and thrown in jail for the crimes they committed, stealing God's money from the Church for their so called evil empire.
The real thiefs that stole St. Michael's Church's money are alemayehu desta, girma metaferia, efrem seleshi, mesfin woldeyes and their leader Kefetew Nega. You don't think we know, don't get us started. Wa! yegud keretit endayitereter! Leboch.

Anonymous said...
እንደ ፖለቲከኞች እኔ የቦርድ ደጋፊ ወይም የከሳሽ ወገን ተብሎ በሚለጣጥፈው የማላምንና በግሌ የሌለሁበትም ብሆን ግን በዚህች አንዲት ቤተ ክረስቲያን ላይ የሚደርሰውን ጥቃት ምንጊዜም ፈፅሞ ኣልቀበልም። ታዲያ እኔም በዚህች ባሳለፍናት የሰንበት ዕለት መነኩሴ አባታችን እያስተማሩ ሳለ ትልቁ አባታችን ደግሞ የቤተክረስቲያኑን ሊቀ-መንበር (ባልሳሳት አቶ ዮሴፍ)ን ጠርተው ሲያበቁ ወደ ቤተ-መቅደስ አስገብተው በር ሲዘጉ በማየቴ አዘንኩ። ባልንሰቀሰቅም አይኔ ግን በእንባ ተሞልቶ ነበር።

እንደ ሰማሁት በሴቶች በኩል ያለው በር በቀጥታ ወደ እቃ ቤት ማለትም ወደ መጽሀፍት፤አልባሳትና ሌሎች የቤተ-ክርስቲያኗ መገልገያ የሚያስገባ ሲሆን በወንዶች በኩል ያለው በር ግን በቀጥታ ወደ ቅድስቱ የሚያስግባ ነው። እባካቹህ ከተሳሳትኩ እንድታርሙኝ ካልተሳሳትኩም እኚህን አባት የምትቀርቡ ወንድሞች እህቶች ካላችሁ ቀርባችሁ ማነጋግሩ መልካም ነው።

በትምህርቱ ግን ጠነከርኩ።
September 10, 2010 11:55 AM