Thursday, September 30, 2010

ለማስታወስ ያህል

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!

ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።




ለማስታወስ ያህል

ባለፈው  ስለልጆቻችን ቀጣይነት በተመለከተ የተለያዩ አስታየቶችን ተቀብለናል። በዛሬው ደግሞ ትንሽ ወይም ትልቅ ሳይል ለሁላችንም ለማስታወሻ ይሆነን ዘንድ ከዚህ በታች ያለውን እንካፈለው ዘንድ አቅርበነዋል። የምንወዳችሁና የምንናፍቃችሁ የገጻችን ተከታታዮች በያላችሁበት እንደምን ከርማችኃል? በዚች ጦማር አማካይነትም የልዑል እግዚሀብሔር መልካም ፈቃዱ ሆኖ ላገናኘን ምስጋና ይሁን። አሜን።

ዘግይቶ እንደደረሰን የዘንድሮው የመስቀል ዳመራን የዳላሱ ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ከመቼውም ጊዜ አይነት በተለየ ታላቅና መንፈሳዊ በአል እንደነበር ነው የተረዳነው። እንደኛ እርቃችሁ ለምትኖሩም ሆነ ሳይሳካላችሁ ያልተገኛሁ ሁሉ የተዋጣለት የደመቀ በአል ነበር። የተጀመረው በተያዘለት መርሀ ግብር መሰረት በጸሎት ሆኖ ከዝያም በአሉን አስመልክቶ የቀረበው ወርብና መይዝሙር ብቻውን ባራኪ እንደነበር ነው። በተለይ ጣዕምና ለዛ የተሞላበት የእለቱ ትምህርት ታዳሚውን ሁሉ የባረከ እንደነበረ ለመረዳት በቅተናል። በተለይም ወጣቶቹ በትርዒት ያቀረቡት መንፈሳዊ ድራማ የተሰበሰቡትን በዐል አክባራዎችን እጅጉን ያስደሰተ ሲሆን፣ የእናትና የወጣት መዘምራን ተሳትፎ እንደዚሁም ሸነጥ ያደረጋቸው የቀድሞ መዘምራን እህቶችም በከበሮውና በዝማሬ እንዳደመቁት ለማወቅ በቅተናል።

ወደ እርዕሳችን ስንመለስ ፤ የዘመኑን ጥበብ ከእለት ወደ እለት ሳናሰልስ ለመታዳደሪያ የምንጠቀምበትም ሆነ ሲመቻቸው ብቻ ወደ ኮምፒተራቸው ቀርበው የኢተርኔት ተጠቃሚዎች ሁሉ በቅድሚያ ሊረዳን የሚገባ ምን አይነት ጥንቃቄ ማወቅ እንደሚገባን ነው። ልጆቻችንስ ምን ያህል ጥንቃቄን ያደርጋሉ? የምንጠቀምባቸው መገናኛዎች ሞባይል የስልክ ኢንተርኔትና እትመትን የምናደርግባቸውን ቁሳቁስን ጨምሮ ከአገልግሎት ስናወጣቸው ምን አይነት ዘዴ በመጠቀም እንሽራቸዋለን? የሚለውን ለማስረገጥ ስንሞክር ራሳችንን ባለሙያው ሳናደርግ እንደሆነ ግንዛቤ እንድትጨብጡልን በቅድሚያ እንጠይቃለን።

እያንዳንዳችን የተለያየ የእጅ ምልክት (አሻራ) ወይንም የዘር ምንጭ (ዲ ኤን ኤ) እንዳለን ሁሉ፣ እያንዳንዳቸው የዘመኑ ጥበብ ምርቶች ሁሉ የራሳቸው መለያ ግልጽ ወይም ስውር መለያ በአሀዝ፣ በፊደል፣ ወይም በስውር ምልክት (ባርኮድ) የራሳቸው መለያ እንዲኖራቸው ተደርገው እንዲመረቱ ለማንኛችንም ግልጽ ነው ። ይከውም መቼ ተሰሩ፣ ማን ሰራቸው፣ በየትኛው የማምረቻ መስመር ተሰሩ የሚሉትንና የመሳሰሉትን ጥያቄዎችን ሲያስተናግዱ፤ ከዚያም አልፎ በሰአቱ በምርቱ የተሳተፉትን  የሰው ኃይሎችን ብቻ ሳይሆን ከምርቱ ጅምር እስከ ሸማቹ ማንነት መረጃ ለማሰባሰብ የሚያስችል እንደሆነ እሙን ነው። በተመሳሳይ ሁኔታ ማንኛውም የኤሌክትሮኒክስ ልውውጦችንና ጉብኝቶችን በኢንተርኔት ስናካሂድ ይዘቱ በስውር ተቀርጾ ከምንገለገልበት ቁሳቁስ ጨምሮና በማለፍም በዳሰስናቸው ባዕዳን አገልግሎት ሰጪዎችም እጅ የሚገባ መሆኑን መረዳት አለብን። በአሁኑ ወቅት የተለያዩ መንግስታት በግልጽ እነዚህን የመሳሰሉ የኤሌክትሮኒክስ ልውውጦችን በገሀድ እንደሚከታተሉ ሲታወቅ በቁጥር ፩ ቅድሚያ ተጠቃሽ ሪፐፕሊክ ቻይና ስትሆን ትውልድ አገራችንም ወደዚሁ እያመራች መሆኗን የሚጠቁሙ ሂደቶች አሉ። ስለዚህም ይኽነን የመሰለ ልውውጥ የምናደርግ ሁሉ፤ የተለየ ግንዛቤን መውሰድ ብቻ ሳይሆን ቤተሰቦቻችንም ሆነ ወዳጆቻችንን ግንዛቤ አንዲኖራቸው ማድረጉን እናሳስባለን።

ልጆቻችን በተለይ የዘመኑን የኤሌክትሮኒክስ ግንኙነት ከህጻንነታቸው ስለሚጀምሩ አብረውት ነው የሚያድጉት ለማለት እንደፍራለን። እንደ ወላጆች አመዛዘን ምን ያህሉን እንዲጋለጡ ማድረግና በመገናኛው መስመር ላይ የወላጅ ቁጥጥር ወይም ማዕቀብ ማድረጉ ተገቢ ነው።

በተለይ ፌስ ቡክ፣ ቲውተር፣ ብሎግ፣ ወዘተ,,,,, ተጠቃሚዎች የሆንን በሙሉ በጣሙን መጠንቀቅ ያለብን የምንሰጣቸውን፣ የምንቀበላቸውን፣ ባጠቃላይ የምንሳተፍበትን ሁሉ ጥንቃቄ ማድረግ አስፈላጊ ነው።

ለምሳሌ በኛ የደረሰውን ለማካፈል ያህል፤ ከ1997 እ.ኤ.አ, ጀምሮ እስከ 2007 እ.ኤ.አ. በያሁ አገልግሎት የኢሜይል ግልጋሎታችንን ወደ ጉግል ስናዛውር ደልዘን የነበርናቸውን ከ፩፪ ሺህ በላይ የሆኑትን የላክናቸውንና ከዚያ የበለጠ የተቀበልናቸውን በሙሉ ባጋጣሚ ልንገልጣቸው በቅተናል። ይህም የሚያስረዳው ከኛ ወገን ከኮምፒተር ብንደልዝም አገልግሎት ሰጪው ግን አዝሎ እንደሚኖር ነው። በተመሳሳይ ማንኛውንም ዶሴ ከቆሻሻ መጣዩ ማኖር ብሎም ማጽዳቱ የሞኝነት እንድይሆንብን፤ በዋናው አእምሮ (ሀርድ ድራይቭ) ከጀርባ ተሰውሮ እንደሚኖር መዘንጋት በፍጹም አይኖርብንም። በተለይ እውቀቱ ያላቸው ወይም የጥበቡ ባለሙያዎች በቀላሉ ሊገልጡት ይችላሉና!

በልጅነት ወይም በወጣት አእምሮ በማንኛውም የብዙዋን መገናኛ በገሀድ የሚለቀቅ ሁሉ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቁሟት እንደዚሁም ወደ ሥራ ዐለም ለመግባት እንከን ሲሆን ለመመልከት በቅተናል። እንደዚሁም ሆነ ብለው ሌላውን በሚተናኮሉ (ለሳይበር ቡሊ) ተጋልጠው እስከ ሕይወታቸውን ማጣት (ለሞት) የበቁትን ወይንም የጤና ችግር የውደቁትን ታዳጊዎችን መዘንጋት የለባቸውም። የእለት እለት እንቅስቃሴቸውንም በነዚህ መገናኛዎች (በሶሻል ኔት ወርክ) የሚለጥፉም እስከ መኖሪያ ቤታቸው መመዝበርና ሌላም ወንጀል የደረሰባቸው እንዳሉ መታወቅ እንዳለበት ማስገንዘብ እንወዳለን።

የራስን ማንነት መሰረቅ (አይደንትቲ ስርቆት) ሰለባ ከመሆን ባሻገር ብዙ በገንዘብና በቁሳቁስ የወንጀል ሰለባ የተዳረጉት አስፈላጊውን ቁጥጥር ችላ በማለት ወይንም ባለማውቅ ስልሆነ ይህንኑም በየጊዜው እያነሱ ከቤተሰብ ጋር መወያየትና የተለያዩ ድኅረ ገጾችን ና ጥሁፎችን ማገላበጥ ጠቃሚ ነው።

ሌላው ማንኛውም  ጥሁፍ የምናትመው ማተሚያችን (ፕሪንተር) አይነትና መለያ ቁጥር ሁሉ ሳይቀር በታተመው ወረቀት ላይ (ወተር ማርክ) እንዳለው ማወቅ አለብን። ይኽ በዐይን የማይታይ ዱካ ነውና ከላይ እንደሰነዘርነው የማን እንደሆነ (ትሬስ) ለማወቅ በቀላሉ ማን እንደገዛው ብቻ ስይሆን በጥሬ ብር፣ በካርድ ወይንስ በብድር እንደገዛው ጭምር መረጃውን ማግኘት አይገድም።  ስለዚህም ማንኛውም በኤሌክትሮኒስ የሚዘገቡ ሁሉ ምንጫቸውም በቀላሉ እንደማይደርቅ ግንዛቤ ከጨበጥን ምንግዜም የመግቢያ ስማችንን ሆነ የሚስጥር መግቢያችን የሆኑትን ከኮምፒውተር ውጪ በሚገባ ቦታ መዝግቦ ማስቅመጥና ሚስጥሩነቱን መጠበቅ ተገቢ ነው። ይህንኑ ከማንም ሰው ሰውሮና ደብቆ መያዝ ያስፈልጋል፣ በቀላሉ ልናስታውሳቸው የሚገቡ ወይንም በአእምሯችን በቀላሉ የሚቀርጹና ለሌሎች ለመላ ምት የማይመች መሆን ይኖርበታል። አንዳንዶች የሶሻል ቁጥራቸውን፣ የትውልድ ቀኖቻቸውን፣ የቤተሰቦቻቸውን ወይም የቤት ውስጥ የእንስሳዎቻቸውን ስሞችና የመሳሰሉትን በቀላሉ የቀረቡዋቸው መላ የሚመቱበትን ይጠቀማሉና፤ አዲስ በምንከፍተው ማንኛውም አገልግሎት ሰጪ  ገጾች ማንነታችንን እንድንሞላ የሚጠይቁትን ገጾች በሚገባ ማስተዋልን ይጠይቃል።
እውነተኛ መረጃ አትስጡ ለማለት ሳይሆን ለማንና ለምን አላማ እንደምናደርገው ማወቅ በጣሙን ጥንቃቄን ይጠይቃል። ከዚህም ውጭ በግል በመሰረትናቸው የመገናኛ ምንጮችና በህዝብ መገልገያ በሆኑ አስተናጋጅ አውታሮች የምናስተላልፋቸውን ሁሉ መመርመር ይሻል።

በመጨረሻም ከአገልግሎት የምናሰናብታቸውን መጠቀሚያዎቻችንን በሚገባ ጠንቅቀን በውስጡ መረጃ (ዳታ) ይኖሩበት የሚችሉና የምንጠጠርባቸውን (ችፕስ) በሙሉ አውጠን ማጠናቀቃችንን ካወቅን በኃላ ቅሪት አካሉን በሚገባ ወደ (ሪሳይክል) ማስተናበሪያ ማስረከብ ሲሆን በእጃችን የቀረውን በጥንቃቄ ማስቀመጥ ወይንም ጥቅም ላይ እንዳይውል ማኮላሸት ተገቢ ነው።

ይኽንን በዚህ ቋጭተን እነ ተኩላው በከፈቱት ገጽ ያገኘነውን ለሚካኤል ሰይፍ ወኪል ላቀረብነው መጠይቅና ከናንተም ለደረሱን መልስ ለማግኘት ሞክረናል። እንዳገኘነው ከሆነ በተፈራ ወርቅ የሚመራውና በገጹ የለጠፈውን ቡድን ያነጋገረ እንደሌለና ከቦርዱ ጋር የተያያዘ ያውጡት ከእውነት የራቀና ውዥንብር የሞላበት ነው። ቀደም ሲልም ሆነ አሁንም እንቅስቃሴዎች ሊኖሩ ይችላሉ። እኛ እንደምናውቀው ከሆነና የዳመራው ዕለት አባታችን እንደአስተማሩን ስናገናዝብ የተገለጠልን፣ እነሱ የያዙት መስቀል የነዝያን ሁለት አማጺያን ወንበዴዎች ከጌታ ጎን የተሰቀሉበትን እንጂ የጌታችንና የመድሀኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን መስቀል አይደለም። ይህም ስራቸውን ሁሉም ምዕመን ተረድቶታል። እኛ ቀድሞ ልናነጋግራቸው ሞክረን ክሱን ለማቆም የሰጡት ምላሽ አባላት የመረጣቸውን አስተዳዳሪዎችን ለማውረድና ያለውን ሥርዐት ለመናድ እንጂ ለዘለቄታዊ ሰላም ፈላጊዎች አይደሉም። እነሱ ዛሬ ሊነዱ የተነሱት ሥርዐት አልበኝነትና ኢክርስቲያናዊነት ዛሬ ካልቆመ እነሱም ውንበር ሲይዙ ተመልሶ መጪና ሰይጣናዊ ጎዳና ነው ። ቤተ ክርስትያናችንም ሆነ ሥርዐቱ ለነሱ ተብሎ ለድርድር አይቀርብም።እያነጋገርናቸው ነው ያሉትንም  አዛውንቶች የምንውዳቸውና የምናከብራቸው ቢሆንም ከነዚህ ወገኖች ጋር ምንም አይነት ውይይት ቢያደርጉም ምንም አይነት ድርድር ውስጥ መግባት አያስፈልግም። ቦርዱም ማንንም አባል አላነጋግርም ያለበት ስፍራና ቀንም የለም። ቤቱ ቤተ እግዚሀብሔርና የሰላም እንጅ የአማጺያንና የኢክርስትያናት አይደለም። አባል ያልሆኑትን ስለ ቤተክርስትያናችን የውስጥ ጉዳይ አንወያይም። የከሰሱም ቢኖሩ ክሳቸውን ሳይዘጉ ምንም አይነት ውይይት ከፍርድ ስርዐት ውጭ አናደርግም የሚል ሲሆን፤ እኛም የሚካኤል ሰይፍ አባላትም ከየአቅጣጫው ያለውን እንቅስቃሴ በሚገባ የምንከታተል ሲሆን ማንኛውንም እውነተኝና ቀጥተኛ ችግር አስወጋጅ የሆነውን ፣ የቤተክርስትያናችንን ህልውና ከሁሉም በላይ ቅድሚያ የሰጠነው መሆኑንና የእነዚህ ጥቂት ግለሰቦች ህከትና እብጠት መስመር እንዲይዝ በጸሎት ሳይቀር ዝወትር የምናከናውነው ነው ። ባለፈው እናንተ እንደጣፋችሁት ወደ ምንጩ  ወደ ዕውንተኛው መንገድ  ወደ ቤታችንና ወደ ቤታችሁ በንስሀ እንቀላቀል ነው የምንል። የሀሰትና የጭፍንነት መንገድ ይጥፋ ነው የምንል ሲል የቡድኑ ተውካይ አስረድቶናል። የነዚያም ወገኖች ያላቸውን ምላሽ ቢልኩልን በደስታ እናወጣዋለን?


እርሶስ ምን ይላሉ?

2 comments:

Anonymous said...

የዚህን ገጽ አቀራረብ በጣም እየወደድን መጥተናል። በዚሁ ቀጥሉበት። ስለ ውድ ቤተክርስትያናችን የምጽፉትም ከልባችን ያለውን ነው። እንደምንረዳው ብቻ ሳይሆን እንደምንኖረውም የክርስትና ኑሮ ሌሎች ከየት እንዳገኙት ባናውቅም እኛም ያየነው ምንም የመብት የሚባል ጥሰት የለም። እንደልባችን ገብተን አምልከን፣ ደጀ ስላምም ተቋድስን ስንወጣ የጀመርነው ገና ከኪንግ ስትሪት ነበር። የነዚህ ከሳሽ ወገኖች ጥያቄ የኖርንበትን ሥርዐት ለመናድ ካልሆነና የግል አላማ ያላቸው ከልሆኑ በቀር፣ ገና ከአጥሩ በር እራስን መርምሮና የሱን መንፈስ ተላብሶ መግባትና የተሸክምነውን ግድፈታችንን አላቀን፣ አዲስ መንፈስ ተላብሰንና ተባርከን መመለስ እንጂ የምን መብት ነው? ቅስናውንም ለመውሰድ ማን ማንን አገተ? ስልጣንም ከሆነ አባል ሆኖ ግዴታውን ከተወጡና ምዕመኑ ከተቀበላቸው ማን ሊያቆማቸው? ከዚህ ያለፈ እንግዲህ የቅዱስ ሚካኤልን ስም አንሱና እኔም እንደሱ መብት አለኝና ቅዱስ ተኮላ ወይም ቅዱስ ተፈራ ወርቅ ብላችሁ ቤተክርስትያኑን ጥሩና አስጠሩልኝ ካልሆነ ማናችንም የደረስንባቸው የለም። ስለ እግዚሀብሔር ብላችሁ ተውን? የተረፈ እድሜያችንን ከታቦታችን ሳንርቅ እንጠብቅ? ለናንተ የሚወርደው ቅስፈት ለኛም እንዳታስተርፉልን አቤቱ ከፈተናህ፣ ከመዐተ ቁጣህ ሰውረን፤ እነሱንም ልቦና ለውጥ፤ ምህረትህንም ስጠን። አሜን። ብርቄ ከዳላስ

Anonymous said...

ብርቄ ማለፊያ ብለሻል። ቢገባቸውና ሀይማኖቱን የተቀበሉ ቢሆኑ ከዚህ ጽጸት በወጡ ነገር ግን የሰፈረባቸው ቅዱስ መንፈስ ስላልሆነ እርኩስ ሆነዋል። ተግባራቸውም ጽዩፍ ነውና እርሱ ይማራቸው። መስፍን ከዋሌ