Friday, September 24, 2010

ይድረስ ለዳላስ ኢ.ኦ.ቲ.ሲ.

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!

ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።

የሚለጥቀውን በመልዕክት መቀቢያችን የተውልን ታዳሚያችን እንዳለ ለጥፈነዋል፤



ይድረስ ለ ዳላሰ ኢ. ኦ. ቲ. ሲ ደራሲ፤ ይህቸን በሚካኤል በቤተክርስቲያናቸን ዉስጥ የሚደረገውን ተንኮል በማየት የተሰማኝንና የተገነዘብኳቸውን አንዳንድ ዘገባዎች ከዚህ ከ (Comment) ቦታ አውጥተው ወደ በዋናው መድረክ ላይ ያስገቡልኝ ዘንድ በትህትና እጠይቃለሁ። እምን ጊዜ ደረስን !!!! ስምንተኛው ሽህ የሚባለው ጊዜ እየደረሰ ይሆን ??? ክርስቲያን ወደ ቤተክርስቲያን የሚሄደው ለመጸለይ ! የመንፈሳዊ ትምህርት ለመማር ! ጥፋት ሰርቶም እንደሆነ ንስሃ ለመግባት !.... ነበር ። በአሁኑ ጊዜ ግን የምናየው ብዙዎቹ የሚመጡት ለመጸለይ ስይሆን፤ ዛሬ ቤተክርስቲያናችን ውስጥ ምን ጥፋት ይሰራ ያሆን? ምን ይነገር ይሆን? ምን ይባል ይሆን? እነማን ይመጡ ይሆን? ሄደን እናደናግር እንጅ በልባችን ያለውን ቂምና በቀል “ይቀር በለን እኛም የበደሉንን ይቀር እንል ዘንድ” የሚለውን ጸሎት ልንጸልይ እንዳልሆነ በዛኛው እሁድ (August 29,2010) የነበረው የህዝብ ብዛት ያሳይ ነበር። ከነበሩት አዛውንት መካከል! ሁለተኛ እዚህ ቤተክርስቲያን እልደርስም ያሉት! ቤተክርስቲያን የከሰሱት! በሰላም ቀን ቤተክርስቲያን ይማይሄዱ ግር ግር አለ ሲባል ብቻ ካሜራቸውን ይዘው ብቅ የሚሉ! እነሱ የኛ ነው የሚሉት ቄስ ከሌለ ቀሳውስት ሲያስተምሩም ሆነ ሃሌ ሉያ ሲል እጆሮዋቸው ውስጥ ስፒከር ወትፈው መንፈሳዊ ያልሆነ መጽሃፍ የሚያነቡና ቄስ የሚዘልፉ! በሃሰት ፍርድ ሸንጎ ላይ ቀርበው በመሃላ የሚዋሹ! ባይ ሎው ለመለውጥ ብዙ ጊዜ አባክነን፤ እንዳንለውጥም ተከለከልን በዚህ ምክንያት ቤተክርስቲያኑን ማፍረስ አለብን ብለው የተነሱ ወንዶችና ሲቶች! የሸማቸውን ዘርፍ በግራና በቀኝ ትካሻቸው የለበሱ ተሳዳቢወችና ዘላፊውች! ቤተመቅደሱን ሞልተውት ማየት ትልቅ ትይንት እንደነበረ የማይካድ ሃቅ ነበር። ድሮ አገራቸን በነበርንበት ወቅት ሃይማኖትህ ምንድነው? ሲባል! የምንሰማው እስላም ውይም ክርስቲያን ነኝ ይሚለውን መልስ ለመጠበቅ እንደነበረ ሁላችንም የምናውቀው ጥያቄ ነበር። ክርስቲያን ነኝ ካለ ጥያቄው ያቆም ነበር በዚህ በዳላስ አካባቢ ግን ክርስቲያንነት ሌላ ጥያቄ ይዞ እንደቀረበ የምናየው ነው። ሲኖዶስ እንደ ሃይማኖት ተቆጥሮ የየትኛው ሲኖዶስ ክርስቲያን ነህ ወይም ነሽ? መባል ተጀምሯል። በበኩሉም አሜሪካ ያለ ክርስቲያን ቄስ ልጆችን ድቁና ከሰጠ እንደ ትልቅ ሃጢአት ተቆጥሮ በየ ብሎጉና በአፍ ድቁና በተቀበሉት ልጆች ላይ ውርጅብኝ መከናውኑ ይሚያስገርም አስጠያፊ ድርጊት መሆኑን የማያውቅ ምእመን ካሉ ንስሃ ግቡ መባል ይገባል። በመጨረሻው ሰንበቴ ብሎግ እንድተገለጸው የሚካኤልን ቤተክርስቲያን በቦርድና፤ ባስተናጋጅነት ሲያገለግሉ የነበሩት ባልና ሚስት ከኢትዮጵያ መንግስት ይዘው የመጡትን የሚካኤልን ቤተክርስቲያን መውረስ ባይሆንም ማዘጋት ዘዴና ተንኮል ለ ከሳሾችና ተባባሪዎች ለማስተላለፍ እቤታቸው ውስጥ የደረጉትን የማስተባበሪያ ግብዣ! ይሄን ቤተክርስቲያን አዘጋለሁ ትልቅ ቂም አለኝ! በህይዎቴ ለስልጣን ተዎዳድሬ ወድቄ አላውቅም! የሚካኤል ምእመን ግን ሳይመርጠኝ ቀርቶ አዋረዶኛል! የሚሉት ሻለቃ ለጋባዧ የላኩትን ኢማል ሳታነቡት የቀራችሁ ካላችሁ እንደገና አንብቡትና የሚካሄደውን ደባ ሁሉ ተረዱ። በነገራችን ላይ ፍርድ ቤት ቀርቦ በመሃላ ያነሳሁትን ቪዲዮ አልቆራረጥኩም (Edit ) አላደረግሁም ቪድዮ የማነሳው ክልጅነቴ ጀምሮ ነው በማለት የዋሸው ግለሰብ በ ጋርላንድ ፖሊስ የ ኢምግሬሽን አቋሙ እየተጠና መሆኑን ሰምተናል። ባፍ ይጠፉ በለፈለፉ ይባላልና በጥያቄን መልስ ጊዜ ከመዋረዱና ከመታሰሩ በፊት አገሩን ጥሎ ቢጠፋ ይሻለዋል ምንም አይነት ችግር እንዳይደርስበት ስለምንፈልግ ምክራችንን እናስተአልፋለን። የቀዳሐውን ኦሪጂናል ቪዲዎ አቅርብ ሲባል ምን ያቀርብ ይሆን? የለኝም ካለ በሃሰት መሰከርክ ሊባል ነው። ካቀረበ ቪዲዎው ሊፈተሽ ነው። በሁለቱም አቅጣጫ ጥፋት ላይ መውደቁ የማይቀር ስለሆነ ቢያስብበት ይሻላል። በልጅነቱ ኢትዮጵያ በነበረበት ጊዜ አባቱ ወይም ዘመዱ የገዙለት ቪዲዮ ማንሻ ምን የሚባል ነበር ሲባል አላስታውሰውም ሊል ነው ወይም ዋሸሁ? በማንኛውም ኢትዮጵያዊ መጥፎ ነገር እንዳይደርስበት መመኘት አግባብ ስለሆነ ይሄ ምክር ይድረሰው። መረዋ በተባለው ብሎግ “ ይህ ቤተክርስቲያን በአሜሪካ የሚገኙትን ጳጳስ ከተከተለ ደሜ ይፈሳል” የሚለውን አነጋገር አሁን ብቻ ሳይሆን ገና ሲጀመር ጀምሮ “የአሜሪካውን ሲኖዶስ ከተከተለ እንጋደላለን! ያለንን መሳሪያ ቡጢም ቢሆን ይዘን እንቀርባለን” ሲል የነበረውን ማስታወስ ይገባል! ደራሲው በተደጋጋሚ ቤተክርስቲያኑ በኢትዮጵያው ጳጳስ መተዳደር አለበት እያለ መጻፉን የማያውቅ ምእመን ይኖር ይሆን! ለምን ይሆን? ምን አጀንዳ አለው? ቤቱን አሽጦ ኮሚሽን ለማግኘት ይሆን? ወይስ ለጳጳሱ ከሚላከው ከገቢው 20% ለሱ ምናልባት 5%ቱ ቃል ተገብቶለት ይሆን። ሰሞኑን የሚነፍሰው ሌላው የተረመረዘ ዎሬ በማዎቅም ይሁን ባለ ማወቅ የተጻፈው፤ የቦርድ አመራረጥ ዘዴ ሲሆን ቤተክርስቲያንን በነጻ ማገልገል ለተማረና ላውቀ እንጅ ያልተማረ ወይም እንግሊዝኛ በደንብ ያላወቀ አይመረጥ፤ ሊቀ መንበርም አይሁን የሚል የተሳሳተ አስተያየት በዚሁ ብሎግ ማንበቤ አሳዝኖኛል። እነዚህ ግለሰቦች ትቂት ቆይተው ያልተማረ እቤተክርስቲያኑ አይድረስ ይሉ ይሆን ብየ ፈራሁ። ያለነው አሜሪካ ነው ፍርድ ቤት የቀረበ ሁሉ እንግሊዝኛ ካላወቀ አስተርጓሚ ይሰጠዋል። ቤተክርስቲያን የሚያገለግል በታማኝነት በትህተኝነት በመልካም ፈቃድነት እንጅ በመማር ወ ይም ባለመማር አይደለም። በዚሁ አጋጣሚ እንድታውቁት ያህል ያሁኑ ሊቀ መንበር ከማንም ያላነሰ እውቀት ብቻ ሳይሆን ትምህርትም ያለው መሆኑን ተረዱ። ከማንም የበለጠ ትህትና እና አስተያየት እንዳለው ለማሳየት የማይፈልግ የተቆጠበ አገልጋይ ለመሆኑ ማስረጃ አያስፈልገውም። እግዚአብሄር ይቅር ይበላችሁ። የሄን ጽሁፍ በብሎግዎ ካቀረቡልኝ፡ በሚከተለው ጊዜ የአሜሪካውን ሲኖዶስ መከተል ለቤተክርስቲያናችን ጥቅሙንና ጉዳቱን በዝርዘር እጽፋለሁ። እግዚአብሄር ይስጥለኝ። ለሁላችንም መልካም ቀን ይሰጠን ዘንድ አጸልያለሁ!!!! አሜን!.
By Anonymous on ከምንጩ ሁነው ያላገኙትን ከውጪ ይረካሉን? on 9/19/10  እርሶስ ምን ይላሉ?

No comments: