Saturday, September 11, 2010

አፕልን ከአፕል ጋር ካለማነጻጸር ውድቀት

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!


ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።



አፕልን ከአፕል ጋር ካለማነጻጸር ውድቀት

በምኖርበት ሀገር የተለመደ የአባባል ዜይቤ ነው። የተወደዳችሁ የገጻችን አንባቢዎች እንዃን ለ፪ ሺህ ፫ የኢትዮጵያ አዲስ ዘመን በሰላም አብሮ አደረሰን፤ መጪው ዘመን የሰላም፣ የጤና፣ የፍቅር፣ የአድነት፣ የመቻቻልና የእድገት ዘመን ይሁንልን!

ቢያንስ የኢትዮጵያ ኦርቶድክስ ተዋኅዶ አነስተኛውን መስፈርት የሚጠይቀውን እውቀት ሳያሟሉ በሀይማኖቱ ስም ቅዱስ መጽሀፍን አስመልክቶ መንፈሳዊ ትምህርትን በገጾች እያወጡ ንጹኃንን ወደ ስህተት መንገድ መምራት ተገቢ አለመሆኑ እሙን ነው። በዚህ ምክንያት በተለያየ አጋጣሚ እንዳስገነዝብነው ዛሬም ዳላስ ላይ ተቀምጠው ከዚሁ ድርጊታቸው ያልተመለሱ ግለሰቦች የደብራችሁ የቅዱስ ሚካኤል እንዲሁም የአስተዳደር ቦርዱን በገጾቻቸው እየተተናኮሉ ቢገኙም የመጨረሻ እስትንፋሳቸው ላይ መሆናቸው የማይታበል ሀቅ ነው። እነዚሁ ገለሰቦች የሜይ ፪ በደብሩ ውስጥ የተፈጠረውን ብጥብጥ ጠንሳሽ፣ አድራጊና አስፈጻሚ በመሆን ያቀዱትን የልዑል እግዚሀብሔር ፈቃዱ ሳይሆን ቀርቶ በመክሸፉ ለሱ ክብርና ምስጋና ይሁን። ይህንኑ ድርጊታቸውንም ይዘውት በገቡት ምስል መቅረጫ በመዘገብ የቀረጹትን በዘመኑ እውቀት በመታገዝ ባሻቸው ከላልሰውና የነሱን ፍላጎት ሊያራምድ በተመቻቸ መንገድ አቀናብረው ከቴሌቪዥን እስከ ዩ ቲዩፕ በማሰራጨት በደብሩ ላይ ብቻ ሳይሆን ለማንኛውም የኢትዮጵያ ተወላጅና ወዳጆች፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮችና መሪዎች፣ በታሪካችንና በማንነታችን ላይ ውርደትን ያመጡ ከጉያችን የወጡ ወገኖቻችን ናቸው።

እናንተ የዳላስ ነዋሪ የሆናችሁ የኢትዮጵያ ሀረግ ያላችሁ ከፖለቲካ፣ ከዘር እንዲሁም ከእምነት ልዩነት ባሻገር በአንድነት በመሆን ይህን ደብር ያለበት እድገት ደረጃ በማብቃታችሁ ልትኮሩ ይገባችኃል። እኛም በዳላስ ጥቂት አመት ቆይታችን ከተረዳነው በጥቂቱ ደብሩ ከሚሰጣቸው አገልግሎት በተለይም አዳራሹን ለሀዘንና ለሰርግ እንዲሁም ለኮሚኒቲው መረዳጃ መሰብሰቢያ ማድረጉ በቀላሉ የሚታይ አይደለም። በዚህ አጋጣሚ ስለ ኮሚኒቲው ካነሳን በዋቢነት ከመጥቀስ የማናልፈው ከሳምንት በፊት የደብሩ አስተዳደርና የኮሚኒቲው አመራር ተገናኝተው በመካከላቸው ሊያቃርኑ የደረሱትን ችግሮቻቸውን ተወያይተው እልባት ሲሰጧቸው፣ በመካከላቸው ፈጥረው ሊያራርቋቸው የተንቀሳቀሱትን ግለሰቦች በተለይም የሁለቱም ወገን የቀድሞ የስራ አመራር አባላት ከነበሩት ውስጥ እንደሚገኙ ግንዛቤ ሲወስዱ፤ ሌሎች በገጾቻቸው እንደሚሉት የደብሩ አመራር አምባገነን፣ ውይይት የማይፈልግ፣ ወዘተ….. እንደሚሉት አለመሆኑን በተግባር አስመስክሯል። እንደቦርዱ አቋምና እኛም እንደምናምንበት ማንኛውም በክስ ፍርድ ላይ ያለ ጉዳይ ክሱ እልባት ሳያገኝ ከሳሽና ተከሳሽ ጉዳያቸውን በተመለከት ምንም አይነት ግንኙነት ማድረግ ብቻ ሳይሆን ይህንኑ በተመለከተ ከከሳሽ ወገን ወይንም የነሱን ሀሳብ ከሚያራምድ ጨምሮ ጋር መወያየት አይገባቸውም።

በተለይም በአንደኛው ገጻቸው ሰሞኑን የዳላስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ደብርን በወሲብ ምክንያት ችግር ካለበት የሌላ እምነት ድርጅት ጋር አነጻጽረው የጣፉት ጽሑፍ፣ በመላ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ እምነት አባቶችን እጅግ እያሳዘነ ይገኛል። እንደርእስ እንዳስቀመጥነው የአፕል ዘይቤን አስረግጠን በሜይ ፪ ካደረጉት አስነዋሪ ተግባር ያላነሰ አርገን ስለምናየው እነዚህ ወገኖች መልእክቱ እንደሚደርሳቸው እምነት አለን። ከዚህ ጋር አያይዘው የዘገቡት አሀዝ ከእውነት የራቀና ማንኛውም የደብሩ አባል እውነቱን ከሚመለከተው በማግኘት የነዚሁን ሀሰተኞችን ሴራ በመገንዘብ ቤተ ሚካኤልን መጠበቅ ይገባዋል።

እርሶስ ምን ይላሉ?

መልካም ዐመት!

1 comment:

Anonymous said...

አዎ!
ሁላችንም አፕልን ከአፕል ጋር ካለማነጻጸር ወደቀን!
ሁላችንም ዜሮ በ-ዜሮ ፤ ክፉኛ ውድቀት
እግዚአብሔር ለሁላችንም ልብ ይስጠን !!