ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።
እንኳን ለብርሀነ መስቀሉ በሰላምና በአንድነት ሁላችንም አደረሰን። የመስቀሉን ምስጢር ለተረዱት ሁሉና እውነተኛውን መስቀል ያገኙት መስቀሉ ወደ ቀናውና እውነተኛው መንገድ ሲመራቸው ፣ሌሎችን ግን አውቀውም ሆነ በግድፈት የተሳሳተውንየማይፈውሰውንና ኢክርስትያናዊ የሆነውን፤ የእነዚያን የሁለቱን ህግ አፍራሽና ከጊታችን ከቤዛችን የአለም መድሀኒት ጎን የተሰቀሉበትን መስቀል ተሸክመው በደሙ የዋጃትን ቤተ ክርስትያን ከሚተናኮሉ ይጠብቀን።
ካለፈው የቀጠለ፣
ወደ ጀመርነው ስንቀጥል፤ እኛም ሆነ ልጆቻችን ከሀይማኖታችን ጋር ያላችውን ግንኙነት ከብዙ በጥቂቱ ለመዳሰስ እንደሚቀጥለው እንሞክራል።
በዚሁ የምዕራቡ ሀገር የተወለዱ ወይንም ያደጉ ወጣቶቻችን ከቤተክርስትያን አካባቢ ለምን አይታዩም? እነርሱስ የቤተክርስትያናችን ቀጣይነት ይረከባሉን? በማለት መንደርደሪያ ብናደርግ ወዴት ያለ ግምገማ ያደርሰናል?
የዛሬዎቹ ወጣቶች እዚሁ ተወልደው፣ እንደ ስርዐታችን በክርስትና ተጠምቀው አልያም እዚሁ አድገው፤ ተገደውም ሆነ ወደው በእለተ ቅዳሴ ቁርባን ሲቀበሉ ለምስክርነት በቅተናል።የቀደሙት ወዴት አሉ? ያደጉበትንም ቤተ ክርስትያን የሸሹ ለምን ሸሹ? የአሁኖቹስ የነሱን ዱካ ይከተሉ ይሆን? ብለን ብንጠይቅ ፣ የመጀመሪያ ከቤተ ክርስትያናችን ለልጆቻችን እንደሚስማማ ሆኖ አለመቅረቡ ሲሆን ሌላው ምክንያት የኛው የወላጆች ቸግርን አገናዝበን ለመመልከት እድሉን ተጠቅመንብበት ቢሆን ለዚሁም ቀና አቀራረብ ብናደርግ ከዚህ ወቅታዊ ጥያቄ በልገባን ነበር። ግራ አልንም ቀኝ ከሀላፊነቱ ተጠያቂነት ወዴትም ማፈግፈግ አንችልም። ምናልባትም የመረጥናቸው አስተዳደር ኮሚቴዎች ድክመት ብለንም ልንቀባ መሞከርም ፍጹም ስህተት ነው። ተመራጩም ሆነ መራጩ ሌላውንም ምዕመን ጨምሮ አንድ ወጥ የሆነ አቀራረብን መፍጠር የግድ ነውና መንፈሳዊ አገልግሎት የሚሰጡትም አባቶች የነባራዊ ሁኔታን ተገንዝበው እቅዱ እንዲጣጣም የስኬታማነት ሚና ይጠበቅባቸዋል።እንደ ትውልድ አገራችን የመሰለ ቀጥተኛነት ያለው ግልባጭ (ኮፒ) ኑሮ እንደማንኖር ሁሉ ለተተኪው ትውልጃችን እንደ ሀገሩ ነባራዊ የሚጣጣም አቀራረብ በማድረግ እየጠፉ ያሉትን ወጣቶቻችንን የመቅረብና አስተምሮ ማመቻቸት የወቅቱ ግዴታ በጫንቃችን የተሸከምን መሆኑን ከሁሉም በላይ የመተግበር ኃላፊነታችንን መውጣት ግዴታችን መሆኑን ልናናስገነዝብ እንሻለን።
ዳላስ በኖርንበትም ሆነ እድሉን አጋጥሞን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታይ የሆኑ ቤተ ክርስትያን ባሉበት ከተማዎች በቆየንበት ወቅት የግላችን የሆነ ጥናቶችን ወስደን ነበር።በህጻንነታቸው ድቁናን ወስደው የቀጠሉበት በአሀዝ ማስቀመጥ ባንደፍርም አብዛኞቹ ከቀሳውስቱ ቤተሰቦች ውስጥ ይገኙበታል። በተረፈ ከምዕመናኑ ልጆች ያገኘነውን አሀዝ አለ ብለን ለማለት ከኛ የተሻለና የተሟላ ጥናትን ይጠይቃል።
በሌላ በኩል ወጣቶቹን በማነጋግር ያገኘው ውጤት ደግሞ ልብ የሚነካ ቅሬታቸውን ነበር።
እንደ ምሳሌ ለመጥቀስ ካስፈለገ፤ ወላጆቻችን ቀዳሚትን ይሰራሉ። እለተ ሰንበትን በማለዳ ቀስቅሰውን ቤተ ክርስትያን ይወስዱናል እንደደረስንም በማይገባን ቋንቋ ቅዳሴ ተብለን እንቅልፋችንን ሳንጠግብ ቁመን እናረፍዳለን፣ ቁረቡ እንባላለን፣ ምግብ ሳንበላ አናረፍዳለን፣ ከዛም ዳቦ ቀምሰን ወደ ቤታችን ወይም ማህበር ብለው ወይም ድግስ ይወስዱናል፤ እነሱ ብቻ ራሳቸውን ያስደስታሉ፣ ቀኑን በዛ አሳልፈን ለሚቀጥለው የትምህርት ቀን ይጀመራል፤ ከወላጆቻችን ጋር የምናሳለፈው የሳምንት መጨረሻ መራራ ነው፣ የትምህርት ቤት ጓደኞቻችን ምን አድርገው እንዳሳለፉ ሲነግሩን እኛ ግን የተለየ ስሜት ነው የሚያድርብን ስለዚህም ዕድሜያችን ሲደርስና ማመዛዘን ስንጀምር ከነሱ ጋር ሰንበት ላለማክበር ሁኔታዎች ያስገድዱናል በዚያው ጨርሰን እንቀራለን።
ሌሎቹ ደግሞ በኛ እድሜ እንደምንኖርበት ህርገር የሚያስተካከል እኛ በሚገባንና ሊጣጣም በሚችል መልክ ቤተ ክርስትያኗ ያዘጋጀችልንትምህርትም ሆነ አስተማሪዎች የሏትም ፤ ወላጆቻችንን ግዴታ ብቻ መወጣት በእድሜአችን ግድ ስለሆነብን እንጂ የነሱን ህይወት ያሳለፉበትን በግዴታ(ረፕሊካ) እንድንደግም አሊያም የኔ ልጅ ከነቶኔ ልጆች አያንስም በሚል የትምክህት ዘይቤ ስለሆነ የልጅነት ዕድሜያችንን ስለቀሙንናስለገፈፉን ፊታችንን አዙረናል ያሉንን ተገንዝበናል። ሊሎችም በጓደኞቻቸው ተጋብዘው በሄዱበት የሌላ ክርስትና ዕምነት ተማርክው የራሳቸውን የጠሉና ወይንም ወደ ባዕዱ የገቡትንም አይተናል። የናንተንም የሜይ ፪ቱን ብጥብጥ የተመለከቱ ወይንም የሰሙ አዝነውም ሆነ አፍረው ፤ በተለይም በትምህርት ወይንም በስራ ላይ ያሉትም ወጣቶች በሚቀርብላቸው ጥያቄ እንዲ ለዩ ምክንያት ያረጉትንም አግኝተናል።እድሜቸው የሚጠይቀውን የተቃራኒ ጾታ ጓደኝነት እንዳይኖራቸው የስጋ ዝምድና የሌላቸውንም ሁሉ ዘመድህ ወይንም ዘመድሽ እያልን ስለምንነግራቸው በዚያው አድገው ሲደርሱ በዚያው ይጠፋሉ።ሌላም ብዙና ከዚህም በአሀዝ የሚዘረዘሩ ነጥቦች ይኖራሉ።
እንግዲህ ወላጆች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ ምዕመናንና የነዚሁ የእድሜ ክልል ውስጥ ያሉና ከቤተክርስትያን ውስጥ የቀሩትን ወጣቶቻችን የጨምረ አንድ ወጥ ያለው አቀራረብ የሚወስድ ጥናትና ጉባኤን ማካሄድ የግድ ነው። ቤተክርስትያኗን አታስተምርም ብለን መናገር አንችልም። ነገር ግን ለምዕራቡ ሀገር ለሚኖሩት ተተኪዎቻችንከስር ጀምሮ እስከ አዋቂ እንደ እድሜው የሚስማማ አቀራረብ መንደፉ በተለይም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነትና ሥርዐትን በተመለከተ የአባቶች መልካም ፈቃድና ብቃትን የሚጠይቅ በመሆኑእነሱኑ መማጸን የግድ ነው። ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከምዕመናንም ሆነከአክራሪ አባቶች የከፋ ነቀፌታን እክል ሊገጥመው ስለሚችል ጥበብ የተሞላበት አቅርቦት እጅጉን ወሳኝ ነው። እንደ ቤተ ክርስትያኖቻችን አሀዝ ብዛት ቤተክርስትያኖቹ ውስን አገልግሎት ብቻ ሲሰጡ ነው የሚገኙት። ተከታዮቹ ወይንም ምዕመኑ ባጠቃላይ የኢትዮጵያ ተወላጆች ወይም ዘር ያላቸው ብቻ ናቸው ብለን አፋችንን ሞለተን በእርገጠኛነት ለመጥቀስ የሚገፋፉን ሂደቶች አያሌዎች ናቸው። ባለበት ከቀጠለም እድሜና የምዕመናኑ ቁጥር ውስን ሆኖ እንዳይቀጭ እያሳሰበን ይገኛል። እንደምናየው ከሆነበአንድ ከተማ ከአንድ ቁጥር በላይ በተከፈቱ ቤተክርስትናት አንዱ የሌላውን ምዕመን ወደእርሱ ለማምጣት እንጂ ሀይማኖት የሌላቸውን ወይንም የሌላ እምነት ተከታዮችን ብሎም የኢትዮጵያ የዘር ሀረግ የሌላቸውን ወደ እምነቱ እንዲመጡ የማድረጉ እንቅስቃሴ ወይንም ማስፋፋቱ ላይ አይታዩም። ለዚሁም የሚስማማ ጥራትና ብቃት ያለው አቀራረብ ይጎላቸዋልና ለተተኪ ትውልዱ እንደዚሁ መቀረጽ ያለበት ነው።
ይኽንኑ የእምነቱን ቀጣይነት በተመለከተ በቂ ጥናቶችን በሰፊው ያካተተ መርሀ ግብር መንደፍ ወርዶ ያለውንና የከበበውን ጉም ሊያጠፋ ባይሆን ሊቀንስ የምያስችልና ባስቸኳይ የሚተገበር መሆን ይገባዋል። የቤተክርስትያኖቹን አመራር የጨበጠውም አካል ይህንን ለመተግበርና ለማመቻቸት ወቅቱ ዛሬ መሆኑን የመገንዘብ ግዴታቸው መሆኑንእናሳስባለን። እኛ ለህይማኖታችን ቀጣይነት ስንቆም በሌላ በኩል ደግሞ አንድ ሀይማኖትና ዕምነት አለን ብለን ራሳችንንየምናስቀምጥ ደግሞ ፈሪያ እግዚሀብሔር መንፈስ በውስጣችን ሰርጾ፣ የተለያየንና የተከፋን፤በመካከላችን ያለውን ልዩነትና ፍልሚያ ከራሳችን አውጥተን ልዩነታችንን አጥፍተንና ያሉብንን የግል ፍላጎታችንን አስወግደንይቅር ለእግዚሀብሔር ተባብለን ቤተክርስትያናችንን ጠብቀንለተተኪዎቻችን የማሳለፍ ግዴታችንን ዛሬውኑ በመጀመር መተግበር የወቅቱ አንገብጋቢ ነው።
እርሶስ ምንይላሉ?
4 comments:
በጥቅሉ በጎና ይበል የሚያሰኝ ሀሳብ ነው።
ነገር ግን ሁሌ ይሚከንክነኝ ሀሳብ አለ;፡ ይህም የእኛ የኢትዮጵያን ሁሉን አዋቂነት ጸባይና ልብ።
የህክምና ዶክተር ያልሆነው ስለ ቅዶ ጥገና ሲተረተር፤ ሾፌሩ/ ስለ ትርራንስፖርቴሽን አናሊስስ ሲያደርግ፤ ሱቅ ነጋዴው ስለ ግሎባል ኤኮኖሚ ሲጨነቅ፤ የስምንተኛ ክፍል ተማሪው ስለ ሀገር ፖለቲካል ኤኮኖሚ፣ ሶሻል፤ ባህልና ወታደራዊ ተቋም ምን መሆን እንዳለበት ዚዝት…. አረ ስንቱ ; አዝማሪነትንን ቢንቅ እንኳ ሁሌ ግን ከዲፕሎማት/ ከሚንስትር/ ከፕሬዘዳንትንት ጭምር ሲሆን ነው የሚያረጀው።
አሁንም የጸሀፊው የግልና ማህበራዊ ኑሮውን ባላውቅም ግን ከላይ እንደጠቅስኩት ልጅ ኖሮት በዘረዘራቸው በጎ ፍሬ ሀሳቦች ዙሪያ የተዋጣለት ከሆነ እሰይው! ካለሆነ ግን እንደብዙ ነገራችን መበካከል እንዳይሆን እዚሁ በፕሪንስፕሉ ይቁምና ተግባሩን ውጤታቸው ለሰመረላቸው መተው ባይሆን ለልጅ ልጅ ከተመክሮ ማሰብ። አራት ነጥብ። ድግሪ የጫነና “ጤና ይስጥልኝ”ን፤ “እግዚአብሔር ይመስገን”ን የማይል ልጅ ይፈራው ቤተስብ ስለ ሀገራችን ቋንቋ ቢያወራ ከዚህ በኋላ ሊከብደን ይገባል። (በቁጭት ከሚነሳው ውጭ)
ዛሬ የብዙ ቤተሰብ ተልቁ አላማ ልጅን አስተምሮ ለድግሪ ማብቃት ሲሆን ከዛ ባሻገር ግን፤ ወለደም አልወለደ በልቡ ለቋንቋው፤ ለባህሉ፤ ለወጉ፤ ለሃይማኖቱ … ወዘተ ተዘርዝሮ የማያለቅ ፍላጎት አለው። ግና ሁሉም ከድግሪ ባልተናነሱ ጥረትን እንደሚፈልጉ ማን በነገረን!! ጆሮና የሚያስተውል ልብ ካለን ግን አሁንም ባይሆን ለልጅ ልጅ ማሰብ አዋቂነት ነው። አራት ነጥብ። “ልጆቻችን” በምናይበት ዓይን የእኛንም አስመሳይ አስትዋኦ በድፍረት እንመልከት።
እያንዳንዱ ቤተስብ ከማወቁ ጋር ኣላዋቂንቱንም ሆነ ደካማነቱን ይቀበል። ችሎታውን ይመን።
ከልጆቻችን በፊትም እኛን የፈሪሀ እግዚአብሔር ልብ ይስጠን።
ይድረስ Dallaseotc.blogspot.com መቼም ውነት ውሸት ሆና በተለያየ መልኩ ስትቀርብ ዝም ብሎ ማየት የእግዚአብሄርን መንገድ የምንከተል ሰዎች ህሌና አይፈቅድልንም ስለሆነ ከዚህ በታች የጻፍነውን አስተያየታችንን እኛም በዋነኛው አምዳችሁ ላይ እንድታወጡልን በትህትና እንጠይቃለን። እስካሁንም ላደረጋችሁት የውነት መድረክነት ትልቅ ምስጋና እናቀርባለን።
"ከምንጩ ሆነው ያላገኑኙትን ክወጪ ሆነው ይረካሉ?" በሚል አር እስት በሌላው ገጽ የጻፋችሁትን አስመልክቶ አስተያየት ሰጪዎች ትክክል ብለዋል። በዊርልፌርምና በመንግስት ቤትም ስለሚኖሩ ሰዎች ተወስትዋል። በእርግጥ ዌልፌርና የመንግስት ቤት የሚያስፈልገን ኢትዮጵያውያን አለን ከነልጆቻችን ይሄም ሃጥያት ወይም ወንጀል አይደለም። ነገር ግን በዌልፌርና የመንግስት ቤት እያጭበረበሩ ለረጂም ጊዜ ከኖሩትና ልጆቻቸውንም በዚሁ መልኩ ያሳደጉት የዛሬው የካርልተን ንዋሪ አንዱ ሻለቃ ተፈራ ወርቅ አሰፋ ናቸው። ዛሬ ግን በመንግስት ቤትመኖርንና በዌልፌር መደገፍን የምንጠቀመውን ኢትዮጵያውያን ሰነፎችና አጭበርብረው ይኖራሉ ለልጆቻቸውስ ምን አኩሪ ነገር ሊያወርሱ ነው እያሉም ይኮንኑናል። ጎረቤቶቻቸው የነበርነው ልጆቻቸውንም ባለቤታቸውንም አቅፈን ይዘን ከዛም እሳቸው ሲመጡም እጃችንን ዘርግተን ቤታችንን ከፍተን እረ ምን ያላደረግንላቸው እርዳታ ነበር ባቅማችን ። ያሉበትስ እንዳደረስናቸው አምላክና የፓለቲካ ድርጅታችንና ደጋፊዎች ጭምር የምናውቀው ሃቅ አይደለም ወይ። አሁን ድግሞ ቤተክርስቲያናችንን አስመልክቶ አዋቂነኝ ቀድማችሁ የመጣችሁት ከኔ በፊት ምንም አልሰራችሁም ከዌልፌርና ከመንግስት ቤት አልወጣችሁም እያሉ ያጣጥሉናል። እኛ እኮ ባቅማችን እንሰራለን ለቤተክርስቲያኑም ያለንን ለግሰናል እነሰጣለንም። ግማሾቻችንም የአካል ጉዳተኛች ነን የአይምሮ ሳይሆን። በስርቆት በማጭበርበርና በዘረፋ የኢትዮጵያ ሕዝብ አያውቀንም። በሌላ በኩል አንካሶች ፍርድ ቤት ቀርበው መሰከሩም እያሉ አንዳንድ ወዳጆቻችንን ይሳደባሉ ። አልፈውም ተረፈው ምስክሩ ብዙ የኢትዮጵያን ሕዝብ ያጭበረበሩ ስለሆኑ ለኤፍቢአይ ልንሰጣቸው ስለሆነ ሶስት ሺ የአሜሪካን ዶላር ዘመድ ለማስመጫ የሰጡትን ሁሉ ምስክር በማድረግ ላጋፍጥ ነው በሚል ተነስተዋል። ለመሆኑ ገንዘቡን የሰጡትስ ወንጀለኛ መሆናቸውን ሻለቃው ተረድተው ይሆን። በግለሰቡም ይሁን በባሌቤቱ የባንክ ስራ ቦታ ምንም የምታገኙት መወንጀያ አይገኝም።
ሻለቃ ተፈራ ወርቅ በምርጫ ያጡትን በጉልበት ለማግኘት የማያደርጉት ጥረት የለም። የቤተክርስቲያኑን ደጋፊ ሁሉ ልክ እንደ ቦርዱ አባላት እርስ በእርስ ለማጋጨት በማስመሰል የማይጽፉት ነግርና የማያጽፉት የለም በዚህ ብሎግ ላይ እራሱ ካየነው የቦርዱን ሊቀመንበር ለቦታው በቂ አይደሉም ይልቀቁ በሚል የጻፉት እራሳቸው ሻለቃው መሆናቸውን ደርሰንበታል። የቦርድ አባላቱ ሶስቱም ተመርጠው ነው እንጂ አስገድደው የተቀመጡ አይደሉም ልብ በሉ በድጋሚ።
ጅራፍ እራሱ ገርፎ እራሱ ይጮሃል እንደተባለው ከዚህ በታች ከብዙዎቹ ስድቦች መሃል በጥቂቱ አዋቂና ተምሬአለሁ የሚሉትና ግብረአበሮቻቸው የጻፉትን ተመልከቱት። እስቲ ማን ነው መሃይሙ ለመሆኑ።
merewametta.blogspot.com
Friday, February 12, 2010
ሲያዙአቸው የነበሩትን የቀድሞ ሊቀ መንበር አንቅሮ ለመትፋት ሰከንድ ያልፈጀባቸው ዶክተር ከአዲሱ ሊቀመንበር ጋር ለወራት ይቆያሉ ብለን አናምንም አዲሱ ሊቀ መንበር ምንም መሃይም ቢሆኑ ፈጣሪን ይፈራሉ ብለን በመገመት። የዛሬውን ሊቀመንበር ምንም ባለቤታቸው ቢቆጧቸው በመቆየት የሕዝቡ ፊት ግርፊያ ያንበረክካቸውና "ምነው ወሎ" ብለው ድንገት ይነሣሉ ብለን መተንበይ እንወዳለን።
Sunday, February 21, 2010
ታላቅ የኦርቶዶክስ ስብሰባ በዳላስ ቁጥር ፲፬
"የጠመጠመ ሁሉ ቄስ አይደለም የጠመደ ሁሉ ጎበዝ አራሽ አይደለም "
እንዴው በሚካኤል አቶ አበበ ጤፉ የትኛው የቤተክርስቲያኑ ኮሚቴ ውስጥ አገልግለው ነው ለመሪነት የደረሱት?
በወላዲቷ አቶ አበራ ፊጣ ናቸው ስለ ሃይማኖት ተቆርቋሪ ሆነው ግብረገብ እኛን ማስተማር ብቻ አይደለም ከፎቅ ላይ በመሆን የአባቶችን ሰበካ የሚቆጣጠሩት?
አቶ ሙሉአለም ናቸው የሩቅና የቅርብ እቅድ አውጥተው ምእመኑን የሚመሩት?"
Saturday, March 20, 2010
ይሻላታል ብለው ገዳም ቢሰዷት፤
ነካክተው ነካክተው አባባሱባት።
ብለው የተቀኙት ማን እንደነበሩ ስማቸውን ማስታወስ ተቸገርን እንጂ ቅኔው እንዳለ ትላንትና የተቀኘ ይመስል አሁንም አዲስ ነው። ቀደም ባለው ጊዜ ነው፡ {ሆይ ጉድ እኛም እንዳባቶቻችን የሰገሌ ጦርነት አቆጣጠር አይነት ቀደም ባለው ሰዓት ማለት ጀመርን፡} ወረታ በተባለው ከተማ አካባቢ የተሾመ ወረዳ አስተዳዳሪ እንኳን ወረዳ አጥቢያም ማስተዳደር እንደማይችል ሲያውቁ ያካባቢው አዝማሪዎቹ በጠጅ ቤት ስም እየጠሩ ማመሳሰል ጀምረው ምን ብለው ዘፈኑ አሉ መሰላችሁ።
ምድር እንኴን ሲያረጅ ያበቅላል እንግጫ
አቶ አበበ ነወይ የጋሽ ክፍሌ ልውጫ።
እኛም ይኸው እድሜያችን ከረመና እነ አቶ ሙሉአለም መሪዎቻችን እነ አቶ አበበ ጤፉ የኤኮኖሚ ጠበብቶች የጂኦግራፊ ምሁሮች የቤተክርስቲያን ደብተራዎች እሆኑበት ዘመን ደረስን። ነገ ደግሞ የላበኩ ዶክተር ከደጀ ሰላሙ መሬት ተጋርተው የሆነ መጋረጃ ጋርደው ነርሱን አቶ አበራን ተከተለኝ በማለት ድውያን እፈውሳለሁ ብለው ተነስተዋል ቢባል መከተል ነው እንጂ ምን ምርጫ አለን የሚለው ምእመን ይበዛ ይሆናል ብለን ብንጠራጠር የምትፈርዱብን አይመስለንም። ቤተክርስቲያናችን ከድጡ ወደ ማጡ ከገባ ቆየ
It is well said and it is a burning question. We need to pay immediate attention for such important issue. The time has changed, and those few individuals who are standing the way for the progress of our Church must stop the madness act. Those of you former elected done your time, leave for the next generation to carry the torch and the gable. Let the Fathers Priest understand the need of the young and give the tools needed to fit with the present time. Those who tried to hide their gilt and taking the Church to Court need to come clean from the sin and need to stop. Those who fighting to grab followers from the same faith than reaching out to for those none believer of the faith be ashamed of your work.
It is well said and it is a burning question. We need to pay immediate attention for such important issue. The time has changed, and those few individuals who are standing the way for the progress of our Church must stop the madness act. Those of you former elected done your time, leave for the next generation to carry the torch and the gable. Let the Fathers Priest understand the need of the young and give the tools needed to fit with the present time. Those who tried to hide their gilt and taking the Church to Court need to come clean from the sin and need to stop. Those who fighting to grab followers from the same faith than reaching out to for those none believer of the faith be ashamed of your work.
Post a Comment