Sunday, October 3, 2010

ቼኩን ማን ይጣፈው?

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!

ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።


ቼኩን ማን ይጣፈው?

እንግዲህ በምንኖርበት ሀገር በተለያየ መስክ የሕግ የበላይነት በሕጉ አንጻር ይስተናገዳል። ወደ ፍርድ ቤቶች ከሚቀርቡ ወይንም ከሚከፈቱ የተለያዩ የክስ አይነቶች ውስጥ አንዳንዶቹ ከመዝገብ ቤቱ አያልፉም። ሌሎችም ችሎት ተሰይመውባቸው ከሳሽና ተከሳሽ ልዩነታቸውን በበጎ ፈቃድና በስምምነት ያልቃል።  ከዚህ ያለፈውም ችሎት ተሰይሞበት ሁለቱም ወገን ከፍተኛ ጊዜና ንዋይ የሚያፈሱበት ረዘም ያለ ክርክር የሚያሳዩበት ሙግት ያካሂዳሉ። ይህ አይነቱ ሙግት እንደሁኔታው በዝግ ወይንም በክፍት ችሎት ሲሆን ፤ ወሳኝ ሆኖ የተቀመጠው አንድ ዳኛ ወይንም ከዚያ በላይ ሲሆን፤ ከዚህ ውጭም ለፈራጅነት አስተያየት እንዲሰጡበት ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት የሌላቸውን ያካባቢው ነዋሪዎች ሸንጎ (ጁሪ) ይሳተፉበታል። የተወደዳችሁ አንባቢዎቻችን እንደምን አላችሁ? በሱ ፈቃድ ዳግም እንድንገናኝ ፈቃዱ ለሆነውና ለተመሰገነው ልዑል እግዚሀብሔር ክብር ምስጋና ይሁን። አሜን!

ለብዙ ጊዜ ሲጠበቅ የነበረውና ለአመታት ብዙ ትግል የከፈላችሁበትን የልጆቻችሁን መንፈሳዊ ትምህርት በተመለከተ ፤ ያሳሰባችሁን ጨምሮ የዳላሱ የቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ደብር አዲስ የቀጠረውን መምህር ሥራውን ለመጀመር ወደናንተ ወደ ዳላስ መግባቱን በመስማታችን በጣሙን ደስ ብሎናል። ዳላስ በነበርንበት ወቅት እንደተገነዘብነው ለልጆቻችሁ የሚመጣጠን አስተማሪ ክፍተት እንደነበር ሲሆን ባለፈውም ጥሁፋችን ለማስረገጥ እንዳሸን ሁሉ፣ ዛሬ የቀጠራችሁት መምህር በጥራቱም ሆነ በብቃቱ የልባችሁን የሚያደርስና የልዑል እግዚሀብሔር መጠቀሚያ እንዲሆን አጥብቀን መጸለይ የሁላችንም ግዴታ መሆኑን ልናስገነዝብ እንወዳለን።

እንዳረጋገጥነው የታዳጊ ልጆቻችሁን  ጉዳይ እንዲያስተናግድ ተብሎ በጀት ተይዞለት የተቀጠረውን ሰራተኛ ለተቀጠረበት ተግባር ባለመዋሉ፣ የወላጅ ኮሚቴ ከአስተዳደሩ ጋር ብዙ አለመግባባት ያደረሰ አንዱ ታላቅ የውስጥ ችግር ነበር። ለዚህም ነበር የወላጅ ኮሚቴ ተቀጣሪው የሰራውን ማወቅና መገምገም ስላልቻለ ለተቀጣሪው ለራሱ የግምገማ ፎርም የሰጠውና እርሱም በተቀጠረበት መሰረት የተገበረው ባለመኖሩ አምኖ ባዶውን የመለሰው። ይህ በዚህ እያለ አስተዳደር ቦርዱ በማወቅ ይሁን ባለማወቅ አሊያም ብቁ የቦርድ አባል ጠፍቶ ይሁን ይህንኑ ለቦርድ ያልተመረጠ ተቀጣሪ የቦርዱ ቃለ ጉባኤ ወይንም ጠሀፊ ያደረጉት። በዚህም ምክንያት በማንኛውም የአስተዳደር ቦርድ ስብሰባ የሚቀርቡ ጉዳዮችን አጀንዳ አቅራቢና አስፈጻሚ በመሆን እራሱን ማኅበረ ቅዱሳን ብሎ ለሚጠራው ድርጅት ከፍ ያለ የገንዘብ ድጋፍ እንዲያገኝ ታላቅ ሚና የተጫወተና እስካሁን ያልተወራረደ ከፍተኛ ገንዘብ በእንጥልጥል ያለ ነው። ከዚሁ የቤተክርስትያን ምዕመን የሆናችሁና ሀገር ቤት ውስጥ ላሉ ቤተ ክርስትያን እርዳታ ጠይቃችሁ የተሳካላችሁ ምን ያህል አቤቱታ እንዳደረጋችሁ ወይም ጭራሹን ያልተፈቀደላችሁ መልሱን ለናንተ ስንተው ፣ ለነ ማኅበረ ቅዱሳን ግን እንዴት እንደነበር ያደባባይ ምስጢር ነውና በዚሁ እንቋጨው።

ስለ ገንዘብ ካነሳን ደግሞ ያልተወራረደው የገንዘብ ጉዳይስ ከምን ደረሰ የሚለውን ለመዳሰስ ካስፈለገ፣ ይህንኑ ጉዳይ እልባት እንዳይኖረው ከውስጥም ሆነ ከውጪ ድንቅፋት እየሆኑ ያስቸገሩ እንዳሉ በግልጽ ይታያል። ምክንያቱም እየተደረገ ያለው ወከባ ቦርዱን በሆነ ባልሆነ ምክንያት በሕግ የተያዘውን ጉዳይ ሁሉ እንሸምግል ባዩ፣ ከሕግ አማካሪዎች በሚቀርቡ ጥያቄዎች መልስን በማስተናገድ፣ አንዳንድ አስቸኻይ ጉዳዮችን መንገድ በማስያዝ የቦርዱ የስብሰባ ግዜ በማጣበብ መሆኑንን ብንርዳም፤ ቦርዶቹ ያለምንም የንዋይ ካሳ ሳያገኙና ከመተዳደሪያ ሥራቸውና ከቤተሰብ ጊዜ ወስደው መሆኑን እንገነዘባለን። ይሁንና በገንዘብ ጉድለት ወይንም ምዝበራ ሀላፊነት አለባቸው የሚባሉትም ከመጠየቅ ለማምለጥ ሲሉ የቦደኑት ከከሳሽ ጎራ ብቻ ሳይሆን የኮሚቴ አባል ሆነው ከውጪ የሚተናኮሉ ናቸው። ከነሱም የቦደኑ ከነሱ የማይሻሉ ቢሆኑም እውነትና ንጋት እያደር ይወጣል እንዲሉ የአምላክን ንዋይ የትም አይቀርምና ከተንኮል እርቆ ጥፋትም ካለ በስርዐት እልባት መፈለግ እንጂ አስቀድሞ በመተናኮል ከውርደት ማምለጥ እንደሌለ ማስተዋሉ የሚበጅ ነው።

ወደ እርዕሳችን ስንመለስ ቼኩን ማን ይጣፈው ? ለሚለው መነሻ ያደረግነው በዳላስ የኢትዮጵያ ኦር ዶክስ ተዋኅዶ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ደብር ላይ በአይነት አንድ፣ ነገር ግን በተለያዩ ግለሰቦች ሶስት የተለያዩ ክሶች ተመስርተው ይገኛሉ። የመጀመሪያው ክስ ከሳሾች በከሰሱት ጉዳይ ተረተው ለይግባኝ የበቁት መልሳቸውን በቅርቡ እንደሚያገኙ ሲታወቅ፤ ሁለተኛ ከሳሾች ደግሞ የደብሩ አባላት ሳይሆኑ ከሀይማኖቱ ጠላትነት የተነሳ ሌላው ሀሰታዊ ክስ ሲሆን፣ እንሱንም ከኃላ ያጀቡትና እርዳታን የሚያደርጉትና የማንን አጸያፊ ሥራ እንደሚሰሩ ለማንኛችንም ዕሙን ነው። የሶስተኛ ከሳሿም ብትሆን አባል ያልሆነችና ክርስትናው የሌላት የንዚሁ ጥቂት ግለስቦች አባሪ፣ የደብሩን ስርዐትና አመራር ልትንድ የመጣችና የሕግ አስከባሪ ትዕዛዝን አሻፈረኝ ያለች ሕገ ወጥ ግለሰብ፤ ጭራሹንም ክርስትና ምን እንደሆነ የማታውቅ ነች። የርሳንም ጉዳይ የካሳ ጥያቄ በመሆኑ ወደ ደብሩ የመድህን ድርጅት ተመርቶ በዛ የሚስተናግድ ነው። የሚገርመው የመጨረሻዎቹን ሁለት ክስ ከሳሽን ወክሎ የከሰሰው አንድ ጠበቃ ሲሆን፣ ስለታሪኩ ትንሽ ብንጠቅስ ግለሰቡ ቀደም ሲል በሥርዐት እክል ገጥሞት ከዳኝነት የተወገደ ሲሆን ጥብቅናው የጥብቅናን ሥነ-ምግባር የማይከተል ለመሆኑ ሁላችንም የምግባሩ ምስክሮች ነን። ከክሱ መሰሚያ ዋዜማ ምሽት በቴሌቪዥን ቀርቦ እኛን ፣ ትውልድ ሀገራችንን፣ ሀይማኖታችንን ፣ማንነታችንን በዐለም የሕዝብ ሸንጎ የኮነነና ያዋረደ እንደዚሁም ይህንኑ በማግስቱ ከጉዳዩ ጋር በማይገናኝ በፍርድ ቤት ውስጥ አቅርቦ የደገመ የለየለት……….. ሲሆን ይህንኑ ግለሰብ ለዚህ አሳፋርና አዋራጅ ምግባር ያመጣው ግለሰብ (ቀዳዳው) የተባለው እንድሰማነው የግል ጠበቃው ሲሆን፣ በገንዘብ የተሳተፉትና እንዲወክላቸው የቀጠሩት እንደዚሁም አብረው ቦድነው የሚያቃልጡ ሁሉ እስቲ ራሳቸውን ይመርምሩ? እንርሱ በርግጥ ሀይማኖታቸውን ያውቁታልን? እራሳቸውንስ እውነት የኢትዮጵያ ተወላጅና ተቆርቋሪ ነን ብለው ይቆጥሩ ይሆን? ኸረ የሀይማኖት ያለህ!
ኸረ ያገር ያለህ!  ምኑን ነው ወይስ ዘመን ገባን? ሀገርን ፣ ሀይማኖትን፣ ባሕልን፣ ወገንን አንገት ያስደፉ? ኽረ ፈጣሪ ልቅሶና ጸሎታችንን ስማ! ለቅሶቻችንን ታብስልን ጸሎታችንንም ትቀበል ዝንድ በአንዱ ልጅህ ለኛ ደህንነት በፈሰሰው ደሙ የነሱንም ስህተት የኛንም ግድፈት እጠብልን? ለማይልቅብህ ምሕረትህ ክብርና ምስጋና ይግባህ። አሜን!

እንግዲህ እርሱን ደፍሮ መንፈሱንም ረግጦ ወደ አለማዊው ፍርድ ቤት ሀይማኖትን ከሶ በዚህም ሀገርን፣ ሕዝብን፤ ሀይማኖትንና ባሕልንም አስደፍሮ፤ የራስን ማንነትም አዋርዶ በእንግዳ ሀገር ፍርድ ቤትም ተደርሶ ፤ የማታ ማታ አይቀሪ ነውና ከአንድ መርጋቱ። እኛ እንደምንገመግመው ከሆነ ከሳሾቹ ምንም የሕግ ነጥብ እንደሌላቸው ሲሆን ፤ የረባም ንዋይ እንደሌላቸው ነው። እስካሁን ድረስ የቅዱስ ሚካኤል ደብር የባንኩን ቼክ ሲጥፈው እንደነበር ሁሉ ያን የማስመለስ የግድ ነውና፤ ከኃላ ሆናችሁ እኔ ወይም እኛ ያላችሁ፣
ሁሉ ማንነታችሁ በሚገባ ተዘግቦ በማስረጃ ያለ ስለሆን አሁን ማምሻው ሰአት ደርሳልና፣ የጠበቅነውና የጠበቃችሁትና የተመጻደቃችሁበት የፍርድ ሰአት መጥቷልና ፌዝና ሳቁ አልቋልና አሁን ተረኛው እየለየ ነውና ማን ቼኩን ይጣፈው? በጊዜም ድርድር ለመግባት የሞከሩ እንዳሉም እየሰማን መሆኑ ባይደንቀንም የደብሩ ወጪ ግን መተካቱ አይቀሪ ነውና በሰፈሩበት መሰፈርም ይኸው ነውና እንግዲህ መክሰስ ብቻ ሳይሆን ግልባጫ እንዳለው ቀድሞን መገንዘብ መልካም ነበር።

እርሶስ ምን ይላሉ?          

2 comments:

Anonymous said...

It is quite known the losers are the one who will take the tap. Such individual are seen as difficult to the followers (parishioner) of our beloved Church in unfamiliar territory away from our mother land. We who live her in Ethiopia have seen the clip of the May 2nd, disturbance in your church and sadness deeply. Is it really happening in the USA? What is the massage from our Diaspora? Where is a civility? Etc….

I am not to say all apples are bad but it is the congregation responsibility to clean this few bad apples from the House of God. It is not allowed in any shapes or forms in our religion to crate disturbance in the Church or suit a Church. One knows his/her believe must know why he/she going to Church and practice according to the Church teaching, those who acted as the May 2nd or filling law suit on the Church, re-consider their act or need to stay out of the EOTC Faith.

Lakew from Addis Abeba,

Anonymous said...

አይ ጉድ በሰፈሩበት እንዲሉ እነዚህ ጉዶች የገቡበትን አላወቁም እንዴ? እስካሁን ቀዳዳው ሙላው የገባውን ቃል የአምስት ሺህ ዶላር ለምን ለኮሚኒቲው አይከፍልም? አሁን ደግሞ ቤተ ክርስትያኑ ከሚከሳቸው ተርታ ገባ። ሰሞኑን ያጋጠመው ብዙ ጉድ ያለ ነው የሚመስለው ከፊቱ ይነበባል ሀሳብና በሽታ የገባው ነው የሚመስል። የሚስቱን ድርሻ ከሚያጡት ውስጥ ኪዳኔ ምስክር ሲገኝ ሌሎችም እነ ግርማቸው፣ ተፈራወርቅ፣ ቀዩ ሰይጣን የሚሉት ሀይሉ፣ እባቡ አባቡ፣ ሀዋዝ፣ ወዘተረፈ በረድፍ ቆመው በቅርቡ ቼካቸውን ከሚጽፉት ጸረ ቤተክርስትያኖች ውስጥ ጥቂቶቹ ሲሆኑ፤ ጥሪት ያላቸውንማ አይዘለሉም። እነ ክፈተው ነጋ ሆነ ገድሉ የየራሳቸው ተራ ይጠብቃቸዋል። በተረፈ አዲስ ለልጆች የተቀጠረውን እንኳን ደህና መጣህልን እንለዋለን። ሰላም ሁኑ ብርቄ ከዳላስ።