Wednesday, October 27, 2010

አቡነ ጳውሎስ ሐውልት እንዲፈርስ

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!

ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።


ቅጂ ከሪፖርተር

(በየማነ ናግሽ)

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ትናንት በዋለው ዓመታዊ ስብሰባ፣ በቦሌ መድኃኔአለም ቤተክርስቲያን ቅጥር ጊቢ ተሰርቶ የነበረው የፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ ሐውልት እንዲፈርስ፣ ከኢትዮጵያ ሚሌኒየም ጊዜ ጀምሮ በየቤተክርስቲያኑ ቅጥር ግቢዎች የሚገኙና ምስላቸውን የያዙ ቢልቦርዶች እንዲነሱ መወሰኑን ምንጮች ለሪፖርተር ገለጹ፡፡ ካለፈው ዓርብ ጥቅምት 12 ቀን 2003 ዓ.ም. ጀምሮ ቅዱስ ሲኖዶሱ ባካሄደው ዓመታዊ ስብሰባ ከፓትርያርኩ ጋር በተያያዘ ውሳኔዎችን ያስተላለፈ ሲሆን፣ በአዲስ አበባ ቦሌ መድኃኔአለም ቅጥር ጊቢ የሚገኘው በፓትርያርኩ ምስል የተሠራው ሐውልት፣ ከቤተክርስቲያኗ ሕግጋት ውጪ ነው በሚል እንዲፈርስ ቅዱስ ሲኖዶሱ በሙሉ ድምፅ መወሰኑን ምንጮች ገልጸዋል፡፡

እንደ ምንጮቹ ገለጻ ከሆነ፣ ቅዱስ ሲኖዶሱ በዚሁ ዓመታዊ ስብሰባው ከትናንት በስቲያ በፓትርያርኩ ዙሪያ አንዳንድ ጉዳዮች ለውይይት የቀረቡ ሲሆን፣ ከእነዚህም መካከል የፓትርያርኩን ምስል የያዙ በየቤተክርስቲያኑ ቅጥር ጊቢዎች የሚገኙ ቢልቦርዶች፣ የፓትርያርኩ 18ኛው በዓለ ሲመታቸውን በማስመልከት ስለተሠራው ሐውልትና ጳጳሳትን እርስ በርስ ያናቁራሉ ስለተባሉ አንዳንድ ግለሰቦች ማብራሪያ እንዲሰጡ ፓትርያርኩ ተጠይቀዋል፡፡

ለትናንትና ምላሽ ይዘው እንዲቀርቡ በቅዱስ ሲኖዶስ ጥያቄ የቀረበላቸው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ፣ በመጀመሪያ ምንም ስህተት እንዳልሠሩ የተከራከሩ ቢሆንም፣ በተለይ ሐውልቱን በተመለከተ ግን መመረቁን አላውቅም የሚል ምላሽ መስጠታቸውን ምንጮች አረጋግጠዋል፡፡

የሐውልቱንና የቢልቦርዶቹን መሠራት በተመለከተ ከቤተክርስቲያኗ ሕግ ውጪ መሆኑን ሕግን አጣቅሰው የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት የተከራከሩዋቸው ሲሆን፣ በመጨረሻም ስህተት መሆኑንና እንዲፈርስ ሲሉ የሲኖዶሱ አባላት በሙሉ ድምፅ መወሰናቸው ታውቋል፡፡

ቅዱስ ሲኖዶስ ይህንን ውሳኔ የሰጠው፣ ‹‹የተሰራው ሥራ ከአበው ትውፊትና ከቤተክርስቲያኗ ሕግ በተፃራሪ ነው›› በሚል መሆኑን ምንጮች አክለዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ፣ ወ/ሮ እጅጋየሁ በየነ የተባሉት ግለሰብ አባቶችን እርስ በርስ በማጣላት የሚታወቁ ስለሆነ ወደ መንበረ ፓትርያርኩ ቅጥር ግቢ እንዳይገቡ ሲኖዶሱ የተስማማ ሲሆን፣ ውሳኔው በቤተክህነት አስተዳደር ሥራ አስኪያጅ ደረጃ እንዲሰጥ መደረጉን ምንጮቹ አረጋግጠዋል፡፡

በአጠቃላይ ሲኖዶሱ ቤተክርስቲያኗን በሚመለከት ባደረገው ውይይት፣ የፓትርያርኩ አመራር ቤተክርስቲያኗን እንደጎዳት፣ ሥርዓት አልበኝነት መስፈኑን፣ ሙስና መንሰራፋቱንና አምባገነንነት በገሐድ መታየቱ በዋነኛነት ተጠቅሷል፡፡

ከትናንት በስቲያ በዋለው የሲኖዶሱ ስብሰባ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ የነበሩት ሊቀ ማዕምራን ፋንታሁን ሙጬ እንዲነሱና በሀገረ ስብከቱ ላይ ያደረሱት ጥፋት ካለ በኦዲት ተጣርቶ በሕግ ተጠያቂ እንዲሆኑ ተወስኗል፡፡

1 comment:

Anonymous said...

ከኦክሊፍና ሳውዝ ዳላስ ነጋዴዎች ኢትዮጵያውያን ምክር።
ጎዲ ጎዲ የሚባለው ሱቅ ኦክሊፍ ውስጥ የሚገኝ፤ የቀን ገቢው በጣም ከፍተኛ ከመሆኑ በላይ የማይመኘው ኢትዮጵያዊ አልነበረም በተለይ እናንተ ቀዩ ሴጣን በሚል ስም ያወጣችሁለት ። ሁላችንም ብንመኘውም ልንገዛው እንደማንችል እናውቅ ነበር ባካባቢው የራሳችን ሱቅ ያለን ኢትዮጵያውያን በሙሉ ፤ ባለቤቱ አልሸጠውም ስላለን በምንም አይነት ብሎን ስለነበረ ። ውነትም ቀዩ ሴጣን እንዳላችሁት ቀይ ሴጣን ነውና የጉዲ ፤ ጉዲን ባለቤት አስገድሎት እስቶሩን ወሰደው ። እርጉዝዋም ጥቁር አሜሪካንና ታሪክዋ ውነት መሆኑን የምናውቅ ብዙ ነን ። እኛን ያስጨነቀንና ልንነግራችሁ የመጣንው አሁን የአባ ጳውሎስን አርቲክል በመለጠፋችሁ እንዳያስገድላችሁ እናንተንም ለማለት ነው። ተጠንቀቁ አደራ። ያአማቱም አቃቂ መንገድ ወያኔ ቦታ ሰጦት የመጣው ዱባ የአዲስ አበባ ምግብ ቤት ሊያመቻች ስለሚችል ግድያን ፤ ጠንቀቅ በሉ እንዳትቀደሙ ሚካኤል ይጠብቃችሁ።