Tuesday, October 12, 2010

እንደ ሊዲያ ልባችንን ይክፈትልን!

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!

ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።


እንደ ሊዲያ ልባችንን ይክፈትልን!

ልቤን ክፈተው፣ ልቤን ክፈተው፣
የልዲያን ልብ እንደከፈትከው።

ይኸን ጥቅስ የወሰድነው ለምን ወደ ቤተ ክርስትያን እንደምንሄድና በዚያም የሚሰጠውን የመንፈሳዊ ትምህርት በሚገባ ተረድተን መንፈሳችንን እንድናድስ እንደዚሁም እንባረክበት ዘንድ ለልዑል እግዚሀብሔር የምናቀርበው ፀሎታዊ የመዝሙር ጥያቄ ነው። የተወደዳችሁ የገጻችን አንባቢዎች እንደምን አላችሁ? እኛ የፈጣሪያችን ፈቃድ ሁኖ ደግሞ ለዚህን ሰአት በዚች ጦማር መልሶ እንድንገናኝ ላደረገልን ክብርና ምስጋና ለርሱ ይሁንልን። አሜን።

ባሳለፍነው  ዕለተ ሰንበት ወደ አሉን የዳላስ ወዳጆቻችንና የሚካኤል ሠይፍ ተወካይ ጋር በስልክ ባደረግነው እንደምን አላችሁ? በሚለው ጥያቄ ከተከፈተው ውይይት የተረዳነውን እውነታ መሰረት በማድረግ ነው።

የዳላሱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድርል ደብር ካሳለፍነው  እሁድ ጀምሮ በየዕለቱ ቅዳሴ ያለፉትን ብፁህ አቡነ ይስሀቅ ለደብሩ በሰጡትና ለእምነቱ ባደረጉት አስተዋጾ፣ የደብሩ አስተዳደር ከመንፈሳዊ አባቶች ተመክሮ በማስገባት ፣ ስማቸውን በፀሎት እንዲታሰብ መደረጉን የአስተዳደሩ ጠሀፊ ከቅዳሴ በኃላ ማስታወቁ፤ በቤተ ክርስትያን ውስጥ የተገኘው ምዕመን በሙሉ በጭበጨባ ተቀብሎ የደገፈው መሆኑን ስንረዳ አሁንም የደብሩን ገለልተኛ አቋም እንደሚደገፍ ግንዛቤን አስጨብጦናል። ጠሀፊውም በደብሩ ላይ ተከፍቶ ስለ አለው ክስ ሂደት ጎረፍ አድርጎት እንዳለፈ ጭምርም ተረድተናል። እንደዚሁም ደብሩ በቅርቡ ስለቀጠራቸውም መንፈሳዊ አባትና ታዳጊዎችንም በተመለከተ የተቀጠረውን መምህር  አስመልክቶም አጭር መግለጫ የሰጠ መሆኑን ተረድተናል።

ለጥቆም ትምህርቱን የሰጡት አባት ጠሀፊው በሰጠው የክስ ጉዳይ በጣሙን የተነኩ በመሆናቸው ፣ ለዕለቱ ያዘጋጁትን ትምህርትም በፍጹም የቀየሩና በዚሁ ዙሪያ በወቅቱ ፈጣሪ ያቀበላቸውን ብቻ የሰጡ መሆናቸውን በምዕመናኑ ዘንድ ዕምነትን አሳድሮባቸዋል። በወቅቱ ቅዳሴ ከተጀመረ በኃላና ብሎም በማብቂያው ላይ ከተገኙት ውስጥ ከሳሽ፣ አስከሳሽና አካሳሽ የሆኑት ግለሰቦችን ይጨምራል። እኝህ አባት ትምህርታቸውን ከመጀመራቸው በፊት ከላይ ባስቀመጥነው የመዝሙር ፀሎት ሲሆን፣ ትምህርታቸው የነጣጠረው በሙሉ ጠሀፊው ባስደመጠው የክስ ጉዳይ ዙሪያ ሆኖ እንዳረፈደ ነበር።

ክፉኛ በክሱ የቆሰሉ የሚመስሉት አባት፤ ከሳሾቹንና ቢጤዎቻቸውን በውል የማያውቋቸው ሲሆን በዚያ ስለመገኘታቸውም ምንም የሚያውቁት ነገር እንዴሌለ ነው። ስጋወደሙ በሚፈተትበት ቦታ እንዴት ስለ ክሱ ይነገራል?

ቤተ ክርስትያን የጠብ ወይንም የክስ ቦታ አይደለችም ብለው የተቃጠሉት አባት ከዚህ በፊት ሲያደርጉ እንደነበረው በበለጠ ሁኔታን ከመጽሀፍ ቅዱስ በማያያዝ ከሚገባው በላይ አስተምረዋል።

እንግዲህ እንደ ልዲያ ልባቸውን እንዲከፍትላቸው የሁላችንም ፀሎት መሆኑን ለማንም ግልጽ ነው። ይህንን ካልተረዱ ፣ ከድርጊታቸውም ባስቸኳይ ካልተገዱ፣ በሰውና በሀይማኖት አባቶች ትምህርትና ተግሣጽ ካልተቀበሉ፤ ምን መሆን አለበት ትላላችሁ? የሚለውን ጥያቄ ነበር ከየአቅጣጫው የተቀበልነው። የኛ የዚህ ገጽ አዘጋጆች መልሳችንን እንደሚከተለው ስናቀርብ እነዚህ ወገኖቻችን እንደኛው ሰዎች ናቸውና በደካማነት እየፈጸሙ ያለው ጥፋት መሆኑንን ደጋግመን ልናስገነዝባቸው መሞከራችንን ገጻችንና እናንተን ዋቢ አድርገን ነው። አሁንም ከዚያ ከመድረሳችን በፊት በታናሽነትና በትንሽነት ከግራቸው በታች ወድቀን፤ በጌታችንና በመድሀኒታችን በእየሱስ ክርስቶስ ሥም ነገራችሁን ከራሳችሁ ለዩ፤ እንደ ሊዲያ ልባችሁን ክፈቱ፣ ይህንን ሥራ እንደያዛችሁ ብትጠሩስ? መምጫውን ማንኛችንም ፈጽመን አናውቀውምና።

እንግዲህ ሁላችንም ወደ ቤተክርስያን የምንሄደው ለአንድ እምነትና ለአንድ ሀይማኖት ብቻ ከሆነ ፣ እርሱንም በሙሉ ልባችን አምነን ከተቀበልን ፣ ምን የሚሉት ልዩነት ንሮ ነው በመንፈሳዊው መንገድ የማይፈታው? መንፈሳዊ ካለመሆን ከዕምነቱ ውጪ በዐለም ፍርድ ቤት ምንም የሆነ ችግር ማስወገጃ መፍትሄ የለምና በከንቱ ሌላውንና ደብሩን ማመስ ራሱን የቻለ ሀጢያት ነው።
በከተማችሁም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ዕምነት መሰረት በዕውቀትም ሆነ በክህነቱ ከፍ ያለውን ዕውቀትና ሥልጣንን የተቀበሉ አባት የተደጋገመ ትምህርትን በሚገባ የሰጡ ሲሆን መስቀል ይዘው ተንበርክከው ለምነዋል። እኚህ ቆመስ የጉዳዩን እልባት ቁልፍም እንደያዙ የዘነጉ ካሉ ተሳስተዋል። ደጋግመው መክረውና አስተምረው ያልተቀበላቸውን ከእምነቱ መለየትና ማውገዝ የሥልጣናቸውን መብት ስለሆነ፤ ይህንን የፈጸሙ ዕለት የዐለም ሕግ ከሳሾች የተመኩበት ሁሉ ፈራሽ መሆኑን አውቀውታልን? እኝ አባት ድንግላዊ ያልሆነ የቤተክርስትያናችን ካህን ሊሰጠው የሚችለው የመጨረሻውና ከፍተኛው ማዕረግ ያላቸው ሲሆኑ፤ የእርሳቸውን ግዝት ለመፍታት ለማንኛውም ጳጳስ እጅጉን ከባድ ነውና። ምክንያቱንም የሚገባውን ትምህርት ሰጥተዋልና። ፍርድ ቤቱም ቢሆን ሀይማኖቱ ውስጥ የመግባት መብቱና ሥልጣኑ የተወሰነ በመሆኑ፤ የተከሳሹ ደብር ጠበቆች ይህንን ግዝት ከተፈፀመ ያላቸውን ማስረጃ ለፍርድ ቤቱ ካስገቡ የክሱ እልባት ያገኛል የሚል መልስ ነው ያለን።

እርሶስ ምን ይላሉ?  

4 comments:

Anonymous said...

AGAIN!!
What in God's name is going on in this Church?

If an inefficient board or an impotent and disgraceful membership cannot throw out these rascals that are trying to steal somebody else’s church, then you all might need to sell the church and get over it. Every Orthodox Christian around the world is sick and tired of reading all the filth written about our faith and our beloved church, watching a sorry video that disgraces our church and faith, listening to the thrash talk the idiots that call themselves association of the holy or the saints and their moronic and idiotic supporters that are ignorant about the Christian faith and arrogant and proud of their empty heads who never listen to anybody’s opinion but their own. All of the Churches that had similar problems took care of their problems one way or the other. You all need to learn from them and deject those criminals out of your church. Nobody is going to come and do it for you, you have to swallow the bitter pill and do it yourselves. America is a country of laws and justice, take these criminals to court and bankrupt them, if they do not have the means they should languish in jail. We know that they will rot in hell for suing their Christian brothers and sisters and the church and blaspheming the Holy Spirit (the unforgiveable sin!!).
Because of the prayer request pledged by members of the Dallas St. Michael Orthodox Church on the internet more than two years ago, starting with the troubles of mahibere kidusan; all of us that got the request fervently prayed for change and relief. We have heard that there have been some minor positive changes made, but it seems your problems never cease. So our future prayers should not be for peace or love, it should be for God’s wrath and to bring unspeakable plagues to consume these children of Satan that are driven to destroy the church and give our Orthodox faith a bad name.

Anonymous said...

ወንድሞች እነ አቶ ሰላም እንዴት ከርመዋል።

ይሄ ብሎግ የወይዘሮ የሐረር ወርቅ ነው በሚል ከከሳሾቹ በኩል ከሶስት ሰዎች ሲነገረኝ በጣም ልቤ አዘነ መክኒያቱም እኝ ሴት የሚካኤል ቦርድ ፕሬዘደንት እንዲለቁ ከስልጣን ቢፈልጉ በቀጥታ የሚናገሩ ከመሆናቸውም በላይ ሌላውንም ግለሰብ ከቦርዱ በስተጀርባ ሆነው ከሳሾቹንና ቦርዱን የሚያበጣብጡናቸው ብለው በፊትለፊት ለመናገርም ወደ ሁዋላ የማይሉ ሰው ስለውነት የተሰለፉ በመሆናቸው። በጣም ልቤን የነካኝ ከሌላ ቦታ ሳይሆን ከከሳሾቹ መምጣቱ ነው ብሎጉ የስዋነው እስዋነች የምትጸፍው በማለት። ለምን እንዲህ አላችሁ የሚል ጥያቄ ሳቀርብላቸው፤ ይመስላል እስዋ ከዚህ ቀደም ስምዋን ጽፋ ከበተነችው ጋር የሚል መልስ ሰጡኝ። ማንም ሳይጀምረውና ሳይነክው ለሕዝብ ቤተክርስቲያናችንን ዘራፊዎች ሊወስዱት ነው ብለው ያስታወቁ ሴት ለምን ደነው አሁን በድብቅ ይጽፋሉ ተብሎ የሚወራባቸው ማንን ለማወናበድ ይሁን ሰው እንደሆን ሁሉንም አውቅዋል። የሐረር ወርቅ የቦርዱም ወታድር ወይም የከሳሹ ዘበኛ መሆን አልችልም ሁሉም ያው ናቸው ካሉ እኮ ቆየ ይሄም በፊት ለፊት ነው። ምንድነው እነዚህ እነተፈራ ወርቅ ፍቅረማሪያም ዘውገ የሚባሉት የሚፈልጉት ከእኝህ ሰው። መከሰስ ይፈልጉ ይሆን?

በመጀመሪያ ወይዘሮ የሐረር ወርቅ ጋሻው ለንደዚህ አይነት ተልካሻ አባባል ጊዜም የላቸውም። እኝህ ሴት አንዱን ስራ ሲያሲዙ የታመመውን ወገን በነጻ ህክምና የሚያገኝበትን ሲያደርጉ ለወገን የሚጠቅሙና በነጻ ያለምንም ዱጎማ ጊዜያቸውን ሰጥተው የሚጠቅሙን ሰው ናቸው። እኔና እኔን የመሰሉትን የትግል ባልደረባዎቹን የባህር ሃይሉን ከአስራ ሶስት አመት የስቃይ ኖሮና ከዛም ታስረን ከነበርንበት ብዙ ሰው ብዙ ሞከራ አድርጎ እናም ደጋፊዎቻችንም ተስፋ ከቆረጥን በሁዋላ ጉዳያችን ወደ ወይዘሮ የሐረር ወርቅ ነብሱን ይማረውና በመቶ አለቃ ሳሙል ጥሩነህ አማካኝነት ተነግሮልን እግዚአብሄር ምስጋና ይግባው እኝህ ሴት ብቻቸውን የሚያሳድግዋትን ልጃቸውን ትተውና በገዛ ገንዘባቸው ወደ ዋሽንገተን ዲሲ ተጉዘው ባላቸው ታዋቂነትና የኢትዮጵያን ስዴተኛች ጉዳይ ማስፈጸም ልምድ ከየመን አምባሳደርና ዲፕሎማቲኮች ጋር ስብሰባ አድርገው በሁለት ቀን ውስጥ እንድንለቀቅ አድርገዋል። ከዛም አሁን በጽፈው ብዙ ቦታ ስለሚወስድና ይሄ ቦታውም ስላልሆነ እሳቸው የሰሩትን ትልቅ ታሪካዊ ስራ ማውሳት እንዴት አድርገው እዚህ አገር እንዳስገቡን ታሪክ አስቀምጦታል። ወደ አሜሪካን አገር አሁን ላለንበት ሰላማዊና ደስታ የተሞላበት ኖሮ ባለቤትም ለመሆን ያደረሱን ለልጆቻችን የትምህርት እድል እንዲኖራቸው ለዚህ ሁሉ ማእረግ ያበቁን ታላቅ ሰው ናቸው። በኝህ ባንዲስ ጀግና ኢትዮጵያዊት ላይ ከመጣሁ ጀምሮ የምሰማው ያሳዝነኛል ከልቤም አዝኛለሁኝ። ባለፈው ሰሞን ወይም አሁን ደግሞ ስማቸው በድጋሚ ሲነሳ ይሄውም የዚህ ብሎግ ባለቤት ናችው በሚል በድጋሚ አዘነ ልቤ።

ብዙ ሰው ያላወቀውን ልግለጽላችሁ ይሄም በተለይ ባንዱ ጉዋደኛችን ታፍኖ የተቀመጠ ነው እኝሁ ሴት ካስመጥዋቸው አንዱ። እኛ የባህር ሃይል ባልደረቦች የነበርነው ባለውለታችን በመሆናቸው ሌላው ቢቀር አንዲት ፕላክ በመስጠት እንሸልማቸው ብለን እየተዘጋጀን ባለንበት ወቅት ባለፈው አመት ትልቅ ደባ ነበር የተደረገው ኦነር እንዳናደርጋቸው እዚህ ዳላስ። በመሃላችን ሰርጎ ገብ የገባው ግለሰብ በሱ አማካኝነት ከማን እንደሚመጣ በጊዜው ባላውቅም፡ ኦነር አታድርግዋት እያሉ በጣም አዘንኩኝ ምን አይነት ሰዎች ያሉበት መጣሁ ነው ያልኩት። ባልቤቴም በጣም አዝና አለቀሰች። በመጨረሻም ያንን ሁሉ ደባ ተቁዋቁመን ወይዘሮ የሐረር ወርቅ የቀደሞው የኢትዮጵያ ባህር ሃይል ባልደረባዎችና ቤተሰቦቻችንን ከዛ የመረረና ዘግናኝ ሆኔታ ከየመን ኖሩና እስር ቤት አውጥተው ለዚህ ስላደረሱን ምስጋና ኦነር ልናደርጋቸው ችለናል በአንድ አምላክ ፍቃድ። ይሄንን ስል በመሃላችን የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ብቻ ሳይሆን የእስልምናና የተለያየ ሃይማኖት ተከታዮች የምንገኝበት መሆናችንንም ማስታወቅ እፈልጋለሁ በዚህ አጋጣሚ። የማትረሳኝ አንዲት የእስልምና ተከታይ የጉዋደኛችን ሚስት በሬዲዮ እንዳይነገር ሬዲዮን አቅራቢውና መረዳጃ ማህበሩ ቦርድ ከለከሉን ስንል ያነባችው እንባና መክፈልስ አይቻልም ብላ የጠየቀችን አይረሳኝም። አላህ እድሜ ይስጣት፡ እግዚአብሄር እድሜ ይስጣት የማይል የለም ወይዘሮ የሐረር ወርቅን።ታዲያ ከእንደዚህ አይነት ደግና ለወገን ተቆርቁዋሪ ኢትዮጵያውያን ጋር አብሮ በመተባበር ብዙ ወገንን መጥቀሚያ ስራ ልንሰራ ስንችል ሁላችንም ፤ ነገር ግን በማጥቃትና በሃሰት ስም በማጥፋት ሌላውንም የስም ማጥፋት ተባባሪ እንዲሆንና የጥላቻ ዘመቻ ማድረግ ብዙ በችግር ላይ ያሉትን የኢትዮጵያ ስዴተኛችና እርዳታ ከሁላችንም የሚጠብቁትን ወገኖቻችንን ተስፋ ከመግደል ተለይቶ የሚታይ ድርጊት ሊሆን አይገባም። እኛ ገና እንደመጣን ምንም ሳናደርግ በሃሰት ሚካኤል ከሁለት ቄሶች ጋር ቦርዱ ሲበጣበጥ የባህር ሃይሎቹ ናቸው ተባልን። አንድ ሰው ከመሃላችን ትክክለኛ ጥያቄ ስለጠየቀ ነበር። ያኔም ነገሩ እስኪጣራ ድረስ የሐረር ወርቅናት የባህር ሃይሉን ገና ከመምጣቱ አስተባብራ በሚል ነበር ያስወሩት እነ አቶ ፍቅረማሪያምና ተፈራወርቅ መንግስቱ የተአሉት ባለግሮሰሪ። አንዱን ጉዋደኛችንን እያፓዎች ነን ባዮች ሊደበድቡት ነበር የሐረር ወርቅ ዘመድ ነህ ብለው ነገር ግን አብረን ስለነበርን ዝምድና እንደሌለውና ምን እንደሚሉም እንዳልገባን ገልጸን እኛ ጉልበቱ አንሶን ሳይሆን በመነጋገር እንጂ በመደባደብ የምናምን ስላልሆነን ግለሰቡን ስም ስንጠይቀው ሮጦ ሊሄድ ችልዋል ይሄም ብዙ ሰው የሚያስታውሰው ነው ። የበኩሌን ሕሌናዬ እንዳይወቅሰኝ ይሄን ያህል ካልኩኝ በሁዋላ ወደ ፍርድ ቤት የሄዱት ጉዳዩን ቢተውት አምላክ እራሱ ስለሚያስተካክለው ለነሱም ጥሩ ዋጋ ይከፍላቸዋል።

በዚህ አጋጣሚ ጉዋደኛቼ ከነቤተሰቦቻችሁ ወይዘሮ የሐረር ወርቅን ኦነር ባደረግነበት ጃንዋሪ አስራምስት 2009 በተደረገው እራት ላይ በሰራዊቱ ስራትና ደንብ ተቀብለን በርላይ ጠብቀን ስላምታ ሰጥተን ከዛም ሚስቶቻችን ቡናውን ጎዝጉዘው መግቡ ቡፌው ተደርድሮና በተራ በተራ ሁላችንም ቾምቤ ጭምር በግጥምና በምስጋና ልክ እንደ አንድ መንግስት መሪ ወይዘሮ የሐረር ወርቅ ፊትና ልጃቸው ውይዘሪት ልእልት ፍት ያደረጋችሁት አኩሪ ስራ በውስጤ በደስታ እንድለመልም አድርጎኛል። ያንን ሁሉ ከውጪ በግርማ ታደሰ ሳናውቅ ሌትናት ተስፋሁንን ተጠቅሞባቸው ፕላኩላይ እንክዋን እንዲጻፍ የተባለውን ቀናንሶ እራሱ ወስዶ አሰራለሁ ብሎ ያደረገውን ስንሰማ በጣም ነው ያዘንኩት። ግርማ በመሃላችን እካለ ድረስ ሰላም ይፈጠራል ብዬም ስለማላምን ለሁላችሁም ስላም እየተመኘሁኝ ባለውለታችንን "እምቢ" ብለን የጠልዋቸውን እነዘውገን እነ ሻለቃ ተፈራ ወርቅን እነ አቶ በትሩን ሌሎቹንም አሸንፈን የሕሌና ግዴታችንን ስለተወጣን ጎበዞቹን ጀግና እላለሁ።

Dallaseotc.blogspot.com እናንተም ጅግኖች ናችሁ ሁሉንም እኩል በማስተናገዳችሁ። ምናልባትም አንዱ ወንጀል ተደርጎ የተወሰደባችሁ ለምን ወይዘሮ የሐረር ወርቅን እንዳሳደምንባቸው ይሄም ብሎግ አላደመም ነው ዳሩ ግን ምን ጥፋት አጥፍተው?

Anonymous said...

እንደ ሊዲያ ልባችንን ይክፈትልን ለሚለው ፀሁፍ አስተያት ካህኑ የካህንነታቸውን አስተምረዋል ነገር ግን እናንተ ሁሉን ሰው በናንተ መረዳትና የሀይማኖት እውቀት ልክ መገመትና ለማስፈራራት መሞከር ቂልነት ነው ክሱ እንዲቀር ብቻ የሳቸው ግዝት በጳጳስም አይዳኝ የመጨረሻው ምሁር ናቸው......ምናምን የተባሉት ሁሉ ዝባዝንኬዎች ናቸው የሳቸውን ግዝት የምትፈሩና ለካህን ስልጣን ክብር የምትሰጡ ቢሆን ገዝቻለሁ ስድብ ይቁም ያሉ እለት አልቅሰህ ንስሀ ገብተህ/ታችሁ/ ስድብህንና የጭቃ ጅራፍህን ታቆም ነበር ይሄ አስመሳይነት ነውና ይቅርብህ/ባችሁ/ የእርቅ ትምህርት በሁለቱም ወገን ላሉ ነው እውነተኝነት ካላችሁ አንተም ተው አንተም ተው ማለት ነው እንጂ በስማ በለውና ባልገባህ የሀይማኖት ትምህርት ትርጓሜ ገብተህ የጅል ማስፈራሪያህን ተው እዚህ ያለነው በህግም በፀሎትም በወንጌል ትምህርትም በባህላችን መሰረት በሽምግልናም አጣማችሁ ያገዘፋችሁትን ነቀርሳ ቆርጠን ለመጣል ጠርዝ ላይ ነንና ተወን ተወደደም ተጠላም ጊዜው የለውጥ ነውና ሁላችንንም/ንፁህ የተዋህዶ ልጆችን ለማለት ነው/በሚያስማማ መልኩ የደስታችን ቀንና የቤተክርስቲያናችን የትንሳኤ ቀን በቅርቡ ይሆናል። ባካችሁ ሚዛን ያለው ያልወረደ ፅሁፍ ፃፉ የሁሉንም አቅም የሚመጥን። የተዋህዶ ልጅ

Anonymous said...

The 3rd Anonymous: Good comment..
beside:
ቺካጎ ዳላስም አሉ?
ቦስተን ወረ ኢሉ?
ወይስ ውረ ኢሉ ዳላስ…
…. አይ አአ
…. በዓይኔ ቀናውብሽ
ትምህርት ተብሎ፤
ቁመት ተብሎ፤
ኢትዮጲያዊም ተብሎ፤ .. በአሜሪካ
.. …. አይ አአ
በዓይኔ ቀናውብሽ፤ “ስደት ለስም ይመቻልን” … ናቅሽ!!
ሰውየው/ ዎቹ መልካቸውን፤ ቁመታቸውን፤ …. ቢያዩ
በደበቁ (ግና ‘ወረ ኢሉ` ‘ወረ ባቦ’… አሜሪካም ከነ ሞፈር)
… አይ ኢትዮጵያ ውድ ሀገሬ … ኮራውብሽ ^^

ሃሃሃ