Wednesday, October 20, 2010

ከደረቁም ደረቅ፣ ከእርጥቡም እርጥብና ከበሰበሰውም ብስብስ መሆን ይቻላልን?

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!

ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።


የተወደዳችሁ የገጻችን ተከታታዮች እንደምን አላችሁ? ክብሩና ምስጋናው የበዛው አምላክ አሁንም ለእርሱ ይሁን።

ባለፈው ከጀመርነው  ከመቀጠላችን በፊት በትላንትው ዕለት ተኮላ መኮንን (ተኩላው)  መረዋ በተባለው  ገጹ የለጠፈውን ተመልክተነዋል።  ለመጀመሪያ ጊዜ በሰባራ ምሑር ብዕራቸው ብሎ በመጥቀሱ ከሱ የተሻለና አቻ ሊሆነው የማይችለውንና በሀቅ የጨበጥነውን የዕውቀት መጠናችንን እውቅናን በመቀበሉ በልዩነታችንም እንዲሁ ይከፈትልህ ነው የምንል። በእርግጥ እኛ ጥሩ አማርኛ ጠሀፊዎች አይደለንም ፣ ይህንኑ ከመጀመሪያው  የገለጽነው ሲሆን ከዕለት ወደ ዕለት ለመማርና ለማሻሻል ከመጣር ወደ ኃላ አንልም። እዚህ ውስጥ የገባነውም በናንተ አጽራረ ቤተ ክርስትያንንና የጨበጣችሁትን የወያኔ ፭፪ ገጽ አስፈጻሚ  ሎሌነት ሚና፣ የዚሁም እንቅስቃሴ ውጤታችሁ ክፍል የሆነው  የሜይ፪ቱ ተግባራችሁ በማንነታችን፣ በባሕላችን፣ በሀገራችንና በሀይማኖታችን በአለም መድረክ አሉታን ያመጣብንና አንገታችንን ያስደፋን በመሆኑ ነው። ዛሬም ይህንኑ ተግባር እራስህንም  ስትነጥልና ስታወግዝ አናይህም በተቃራኒው ስትስተገብር እንጂ።  

አንድ ነገር መረዳት ያለብህ ስድብ ማለት ምን ማለት እንደሆነ የእንግሊዙንም ሆነ የአማርኛውን መዝገበ ቃላት ለማንበብ ሞክር የሚገባህ ከሆነ። አንተን በሙሉ አፋችን ውሸታምና ሌባ ነህ ብለን ብንጥፍ ያ ሀቅ ነው። ምክንያቱም ደጋግመህ ያንተ ያልሆነው  ሰርቀህና ዋሽተህ መገኘትን በሚገባ ቀደም ባለው ጥሁፋችን አስቀምጠነዋል። ባፍ ይጠፉ እንዲሉ ባዲሱም ጥሁፍህ ደግመህ ዋሸህ። “ዋሽተን አናውቅም ስንል ለአፋችን ሳንሆን ከልባችን ነው። ዋሽተን ያገኛችሁን እለት የመሞታችን የመጨረሻውም የመጀመርይውም ወቅት ሆነ ማለት ነው።“ ብለህ ትላንት አስነበብክ ከዚያ በፊት የናንተ ልሳን የሆነው መለከት የተባለው ሲመጣ ገጽህን እንደምትዘጋ የጣፍከውን ዘንግተህ ነው ወይስ የያዘህ ሰይጣን አስቶህ እንደ ውሻ መልሶ የሚያልከሰክስህ። ሴቷ ሱሪህን ካስፈታችሁ ቆይቷል አሁን ደግሞ በግልጽ መጦመር ጀምራለች እንጂ እንዳንተ ሀገር እያወቀው ማንነትህን ስሟን ደብቃ አልወጣችም፣ ቀዳዳና ዋሾነትን አቁመህ ፣ ከሰይጣን ጎዳና ወጥተህ ፣ ቃልህን ጠብቀህ ፣ የወያኔ መልዕክተኛነትህን ከቤተ ክርስትያን አውጥተህ ብትቀመጥ እኛም ልንተውህ በተገደድን። የዳላስ ህብረተስብም ባንተ ላይ መጠቋቀም አቁሞ ፣ ቤተሰቦችህም ባንተ አስነዋሪ ምግባር ከመሸማቀቅና አንገት ከመድፋት ቢተነፍሱ መልካም ነበር።    

ያለፈው ጥሁፋችን ያነገተው በሙሉጌታ (ሞላው) ወራሽ (ቀዳዳው) በተባለው  አጽራረ ቤተ ክርስትያን ግለሰብ ሲሆን ወደ ተቀሩት ከመዝለቃችን በፊት ትንሽ የምንጨምረው ይኖረናል።

ቀደም ብሎ ጀምሮ ከሚደርሱን አስታየቶች ውስጥ የዚህ ቀዳዳ ሚሽት ስለ ባሏ ጸረ ቤተ ክርስትያን ተግባር አታውቅም እንጂ ብታውቅ ኖሮ ትገታው ነበር የሚል ሲሆን፣ እኛ ግን በአስተያየቱ አንስማማም። ምክንያቱም ገጻችን በአለም ዙሪያ የደረሰ ከመሆኑም በላይ ዳላስን የሚያውቁ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩ ሁሉ በሚገባ የሚከታተሉት በመሆኑ በርሷና በትዳሯ ላይ እየተፈጸመባት ያለውን ጥቃት የሚያስገነዝባት አንድ እንኳን ዘመድ ወይ ወዳጅ የላትም? እርሷም ጥበብ በሰፈነበት የአለም ክፍል እየኖረች ይህን ካዳገታት ምኗን ነው ያገባት? ከጭቃ አድቦልብሎ ባሏ የፈጠራት የሱ ፍጡር ሆና እንደሱ የተለየች እስካሎነች በቀር፣ በጋብቻ ላይ ሲማግጥ፣ ከሕብረተሰቡ የተለየ ድርጊት ሲፈጽም በዚህም ሲለይ፣ ልጆቿ እንደ ሌሎች ህጻናት በቤተ ክርስትያን ውስጥ ተሳትፎ የማያደርጉ፣ ወዘተ…. ምነ አይነት ኦርቶዶክሳዊ ወላጅ ናት ሀይማኖቷን በዚህ የልጆቿ ዕድሜ የማታስተዋውቅ? የእውቀትና የትምህርት ድሀ ናት እንኳን ብንል ባሏም የእርሷ ቢጤ ነገር ግን ስለ ልጆቿ በቀለም ትምህርት ለመጎልበት የሚያስፈልጋቸውን ክትትልና እርዳታን እንዴት ልትሰጣቸው ትችላለች? የልጆቻቸውስ የወደፊት እድልና ፋንታ ምን ይሆን?  እንደኛ አስተሳሰብ ከሆነ ሁለቱም በትምህርትና በዕውቀት ያልገበዩት ነገር ግን በገንዘብ ሊገዙት የሚፈልጉት ዝና ክብርና ሥልጣንን ለመያዝ ማንኛውንም መስዋዕት ማድረግን ነው። በትምህርት ዜሮ መሆንና በአቋራጭ ድንቁርናን ለመሸፈን ያልዋሉበትን፣ያልወጡበትንና ያልወረዱበትን፣ ያልሰሩበትን ጨርሶም ያላነበቡትንና ምርምር ባላደረጉበት በሰሙት ጫፍ ብቻ አዋቂ ባለሙያ (ኤክስፐርት) ለመሆን የሚሞክሩ፣ አለማወቅንና አለመማርን እንደ እፍረትና ሞት በመቁጠር ለመጋረድ በሚያደርጉት ሀሰት ተግባር ከሚተበተቡ ህሊናቸውን ሰብስበው የሚገባውን እርምት በማድረግ ፊደል ቢቆጥሩ ለልጆቻቸውም ጥሩ ምሳሌነትን ባተረፉ።

ነገር ግን ሁሉንም በገንዘብ እወጣዋለው የሚል ህሊና ፈጣሪ አምላኩን  ይረሳውና ገንዘብ ብቻ ማምለክን ይያየዘዋል። በእውነትም ለሁለት አምልኮ መገዛት ስለማይቻል የቀዳዳውም ሚስት አስተያየት ሰጪዎች እንደሚሉት ሳይሆን የዛሬ ኑሮዋን የምታመልክና አልጋዋ ላይ እንኳን ብትይዘው ደንታም የማይሰጣት ግብዝ ፍጡር ሆና ነው የምትመሰል። የቧላም ሥነምግባር ምንም የማይሰማትና ህሊናዋ የደነዘዘች በመሆኗም ጭምር ነው ለእርሱ እኩይ ተግባር አካልነቷን እያስመሰከረች የምትገኝ። መጽሀፉም አንድ አካል አንድ አምሳል የሚለው ሀረግ ለነዚህ እርኩሶች ምሳሌ ባናደርገውም ባህሪያቸውን ያስገነዝባል እንላለን። እርሱን የተጠጋ ሁሉ ከችግር እንደማይወጣ ቅንና ትሁት የሆነው አስማማው የተባለው ወንድሙም የከይሲ ወንድሙን ምክር ተቀብሎ ይመሰል በፓርክሌንና ግሪንቪል መጋጠሚያ ላይ ያለውን የነዳጅ መሸጫ በሽያጭ ግብር ምክንያት ነው አሉ ካለፈው ቀዳሚት ጀምሮ ተዘግቶበታል።እንግዲህ የሙላው ቀዳዳውን ለዛሬ በዚሁ እምንቃጨው።

ሌላው የዚሁ ተመሳሳይ በሆነው መንገድ የለቀቀው ፣ በወቅቱ በከተማችሁ የታወቀውና በበጎ ስራው ይከበር የነበረው፣ የአቶና የጋሼ ስም ተሰጥቶት የነበረው፤ ምንም እንኳን ቀደም ሲል ከርሱ ጋር የንግድ ሽርክና ገብተው ሲፈርስባቸው እንዲህ አድርጎን ተለያየን እንጂ ወይንም ስራው ሲሻሽል ተመጣጣኝ ካሳ ተቀብዪ ነው የማይሉትን፣ ከእውነት የራቀና አሉባልታ የሚያናፍሱበትን ትተን በእውነትም ግለሰቡ በወቅቱ ጥሩ ኢትዮጵያዊም ነበር፣  የቸገረውን በተቻለው ረድቷል፣ ቤተ ክርስትያንም ስታቋቁሙ የተቻለውን አስተዋጾ አድርጓል ይህ ሀቅ ነው። ከኛ የሚለየው ለቤተ ክርስትያን ያደረገውን የንዋይ ስጦታን በመጠቀም ደብሩ ላይ ተጽእኖ ለማድረግ ሞክሮ ሳይሳካለት ሲቀር ወደ እርኩስ መንፈስና ተግባር መግባቱ ይህንንም ተከትሎ የመጣው ውጤት ያጠቃላይ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮችንና ባጠቃላይ የኢትዮጵያ ተወላጆችና ወዳጆችን ያሳዘነና አንገት ያስደፋው የሜይ 2ቱ ብጥብጥ ውስጥ በቀጥታና በተዘዋዋሪ ተሳትፎ ማድረጉ ነው። ይህ ግለሰብ ስሙ ኃይሉ እጅጉ ወይም ከቀን በኃላ በእርጅናውና በከተማችሁ አንቱ ተብሎና ተከብሮ በመቀመጫው ዘመን ቀዩ ሰይጣን የሚል ቅጥያ ስም ያገኘው።

ቀዩ ሰይጣን (ኃይሉ እጅጉ) በግል የንግድ ስራ ላይ ከኢትዮጵያ ጀምሮ ለብዙ አመታት የኖረና በዳላስም በቂ ንብረት ያደራጀ ጠንካራ ሰው ቢሆንም ከሕዝቡም ተስማምቶ የሚኖር ነበር። በቅርብ ጊዜ ወደ ትውልድ ሀገሩ በመመላለስ አንዳንድ የሚጠቀምባቸውን የስራ መስኮችን በመቃኘት ለመተግበር በሚያደርገው እንቅስቃሴ፣ ቀደም ሲልም አባ ጳውሎስ ይተዋወቅ ስለነበር ከርሳቸውም በጥግጊ አውቆትም ሆነ ሳያውቀው አዲስ ምህታት (ቫይረስ) ይዞ በመምጣት፤ ይህንኑ ለሚሰሙት ሁሉ ለመቀባት ሙከራው አልሳካለት በማለቱ ነበር። የእርሱ አዲሱ በሽታው የሚካኤል ደብር አባ ጳውሎስን እንዲቀበልና እንዲያድር የማድረግ ዘመቻ ነበር። እንደ አግባቡ ከሆነ ህሊና ያለው ማንም ሰው በተለይም እርሱ ከደብሩ ምስረታ ጊዜ ጀምሮ የደብሩ መሰረታዊ አቋም ምን እንደነበር በሚገባ የተረዳ ሆኖ ሳለ አድፍጦና ቀን ጠብቆ ፤ የደብሩ አባላት በማይፈቅዱትና በማይቀበሉት መንገድ ተጽዕኖ ማድረግ እንዲሁም ያለውን ስርዐት ማፍረስ ውስጥ ካለመግባት ተቆጥቦ ወይንም ከደብሩ አባልነት እራሱን ማግለልና ጣልቃ አለመግባት የሚገባው ተግባር ነበር። ነገር ግን እራሱን ከሌሎች አጽራረ ቤተ ክርስትያን ጋር አሰልፎ ደብሩን ለማፍረስ በግምባር ቀደምትነት ከሚንቀዠቀዡት አንዱ ሆኖ ተሰልፋል። በዚህ ሥነ ምግባሩ ደብራችሁን የአባ ጳውሎስ ገጸ በርከት ሊያደርግና ለውለታውም በኢትዮጵያ ውስጥ መሳካት ያቃተውን የንግድ ስራ ትብብር እንዲገጥመው ብሎም ወያኔ ያዘጋጀውንም ባለ ፭፪ ገጽ አጀንዳን ለማመቻቸት እየተሳተፈ እንደሚገኝ መረጃዎች ምስክር ናቸው። የግል የንዋይ ጥቅሙ እንዲሳካለት በመታወር ብቻ የሚያደርገው ምግባር ዕምነቱንና ሀይማኖቱ እንደሌለው፣ ብር ሆዳምነቱን ያስቀደመ አድርጎታል። ፈጣሪ አምላኩንም በዚህ ዕድሜው ክዶ ገንዘብ አምልኮቱን አስቀድሞ የገዛ ራሱ ያቆመውን ደብር ለሚከሱ ከአጋርነት አልፎም እንደ ጀብዱ እኔ ነኝ ደብሩን ለከሰሱት የጠበቃውን የምከፍል ብሎ የሚናገር ቀይ ሰይጣን ነው።

በእድሜውም ሆነ በብስለት ደረጃ ከርሱ የማይቀርቡት ጋር ዛሬ ደብራችሁን እየወጉ ካሉ እንደ ቀዳዳው ሙላው ጋር ጓደኝነት የገጠመውና የቀድሞ ወዳጆቹን አንገት ያስደፋ። የማታ ማታ እየቀረበ እድሜው የመሸበት መሆኑንም የዘነጋ መስሎ የሚታየው፣ በጌታ የመጠሪያው ቀን ላይ ያለ መሆኑ እንዴት ይዘነጋዋል? ሲሆን እርሱ ዛሬ በጥባጭ ሳይሆን ሽማግሌ በመሆን የተጣላና የተቀያየመ ቢኖር የማስታረቅና የማስማማት የጨዋ ስራና ምግባር  በማድረግ የፈጣሪን መምጫ መጠበቅ መሆን ነበር። ይህ በመረጃ ተደግፎ የሚገኝ የሱ አጽራረ ቤተ ክርስትያን ተሳትፎና የገንዘብ አስተዋጾ የዚህም ውጤት ሆኖ ደብሩ ያወጣውን የመከላከያ ወጪ ማስመለስ የግድ ነውና እንግዲህ እርሱንና ብጤዎቹ እንደ ሰፈሩ መሰፈር እንዲሉ ፣ የምታመልኩትና ኃይል የሰጣችሁ ገንዘብ ከናንተ ወዳችሁም ሆነ  ተገዳችሁ የምትተፏት መሆኑን ነው ከወዲሁ ማስገንዘብ የምንወደው።

ከዚ አልፈን ደግሞ ሰሞኑን ወደ ኢትዮጵያ ለመሄድ በዝግጅት ላይ የሚገኘውን የቀድሞ የኢትዮጵያ ሰራዊት የሻለቃ ማዕረግ አለው የሚባለውና ስረ መሰረቱም የሻገተ ጮሌ አርጎ ራሱን የሚቆጥረው አቶ ተፈራወርቅ አስፋው ነው። መደጋገም ወይም ኩረጃ ባይሆንብን፤ ስለዚሁ ግለሰብ በዚህ ሳምንት ውስጥ ሰንበቴ http://www.senbete.blogspot.com/ ላይ ብዙ ዘግቦበታልና ወደዚሁ ገጽ እንድትገቡ እየጋበዝን የራሳችንን ባጭሩ እንደሚቀጥለው እናቀርባለን። ይህ ግለሰብ ወደዚህ ዳላስ የመጣውና ለብዙ ጊዜ የኖረው በመንግሥት ድጎማ በሚደገፍ የቤት ኪራይ ውስጥ ነው። ከመምጣቱም በፈት የደርግ ወታደሮች ሳይቀሩ በተለይም መኮንኖችን ያለው የወያኔ መንግሥት አስሮ እንደነበር ገሀድ ነው። የተፈራ ግን ምንም ማስረጃ ልንጨብጥ አልቻልንም ይሁን እንጂ ተለጣፊ ሆኖ የሰራቸውን በማስረጃ እስናገኝ ድረስ ከዛ ብንታቀብም ባለሟል እንደነበር ትክክል ነው።

ዳላስ በገባበት ወቅትም መጀመሪያ የተጎዳኘው ከጸረ ወያኔ ጎራ ሲሆን እራሱን ተቃዋሚ አድርጎ  በተለያየ የድርጅት አባልና መሪ ብሎም ተቃራኒ ጎራ ማቋቋምን ነበር። የዳላስ ፎርትዋርዝ የኢትዮጵያን መረዳጃ ማህበር ከመቃብር በላይ ያለ ብቻ በመሆኑና ተቆርቋሪ  ያጣ ድርጅት በጠራው ጠቅላላ ስብሰባ የተገኘ በመጥፋቱ አጅሬው ዘው ብሎ ገብቶ ያለ ምርጫ መሪነቱን ያዘ። እዚህ ላይ የሱ ምንም ጥፋት የለውም። የአካባቢው ነዋሪ የሆነው አጠቃላይ ሕብረተሰብ ድክመት ነውና ከዚህ መማርና መሳተፍ ማድረግ ከጸጸት ያድናል። ይህ በመረዳጃ ማህበር መሪነት ዕድል ራሱን እንደፈቀደው በህረተስቡ ስም የተለያዩ ተግባራትን ያለ ታዛቢ እንኳን ሲቆምርበት ኖረ። የተለያዩ የከተማችሁን የፖለቲካ ድርጅቶችን እያኮላሸ አጠፋቸው። እርዳታን ከድርጅቱ የሚጠይቁትንም ግለስቦች እንዳይረዱ ነገር ግን የርሱ ደጋፊዎች ለሆኑ ብቻ ሲይመቻች ኖረ። ዳላስ በሚኖሩ የኢትዮጵያ ተወላጆች ላይ መረጃ እየሰበሰበ ለኢትዮጵያ መንግስት አቅራቢ ሆነ። ኒያላ ኢንሹራንስ ለተባለው በዚህ ሀገር ፈቃድ ለሌለውና ባለቤትነቱ የመሀሙድ አላሙዲን የተባለው ቱጃርና የጠቅላይ ሚኒስትር መለሰ ባለቤት አዜብ መስፍን ሲሆን ከሶስቱም የአሜሪካን ሀገር ወኪሎቻቸው የቀረው የናንተው ተፈራወርቅ ብቻ ነው። በመረዳጃው ማህበር በኩል የሚተዋወቃቸውን ሁሉ ኢትዮጵያ ላላቸው ንብረትና ዘመድ ጨምሮ የንብረትና የህይወት መድህን ሲሸጥ፤ በተመሳሳይ የመረጃ ስራውንም አብሮ ያካሂዳል።

ምንም እንኳን ባለፉት ጊዜያት ስለዚሁ መረዳጃ ማህበር ብዙ ስንጥፍና እርሱም ከአመራር ቢለይም፤ የወያኔን ሥራ ለመስራትና ቀጣይነት በሚኖረው መንገድ የሚገባውን መሰረት የጣለና ለወያኔ የ፭፪ ገጽ አራማጆችን ስግስጎ ከውጭ የሚመራቸው መሆኑን በማስረጃ የተደገፈ ነው። በመረዳጃው ማህበር ስር የተቋቋመው እድርም ቢሆን የእርሱና የጥቅም አጋሮቹ የሆኑት የነበትሩ እስትራቴጂ ነው። ድርጅት ማፍረስና ማቋቋም የተካኑ ቡድኖች የታጀበው ተፈራወርቅ ይህንን እድር በከፍትኛ ገንዝብ እያስከፈለ ቦታ ካስያዘና በቂ ቁጥር ላይ ሲደርስ ወደ ቀብር መድህንነት በማሸጋገር ከፍተኛ የመጦሪያ ገቢ ለማግኘት ነው። እንደሚባለው በአባል የ፵ ዶላር ከእድር አባላት የተሰበሰበው ገንዘብ ወደተባለው አላማ አለመግባቱንና እንዲያውም ለአባላቱ የጃንጥላ መድህን ገዝቷልና ሰው በሞተ ቁጥር ገንዘብ ይበላበታል የሚባል ሲሆን መረጃውን እንዳገኘን እንደ አግባቡ እናካፍላችኃለን።

ከዚሁ ሳንወጣ ደግሞ በመረዳጃ ማህበሩ ማህተም ምን አይነት ወንጀልና ሰዎችን የማስተላለፍ ሕገ ወጥ ተግባር በእርሱ መሪነት እንደሚደረግ  በሚቀጥለው ጥሁፋችን እናካፍላችኃለን፣ እስከዚያው በሰላም ቆዩን።
  

No comments: