Friday, October 15, 2010

በዕውነት ሀይማኖት አለኝን?

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!

ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።


በዕውነት ሀይማኖት አለኝን?

ሀይማኖት ምንድን ነው የሚለውን ጥያቄ በአጭሩ መንፈሳዊ እምነት፣ ይኸውም ከአምስቱ ህዋሳታችን ማለትም ማየት፣ መስማት፣ ማሽተት፣ ማጣጣምና መዳሰስ ውጭ የሆነና በእንግሊዘኛው አጠር ያለ ትርጉም ደግሞ የሚቀጥለውን የሚያካትት ሆኖ ተዘግቧል፡-
 (re·li·gion [ri líjjən](plural re·li·gions)
n
1. beliefs and worship: people's beliefs and opinions concerning the existence, nature, and worship of a deity or deities, and divine involvement in the universe and human life
2. system: an institutionalized or personal system of beliefs and practices relating to the divine
3. personal beliefs or values: a set of strongly-held beliefs, values, and attitudes that somebody lives by

የተወደዳችሁ የገጻችን ተከታታዮች እንደምን አላችሁልን? ደግሞና ደጋግሞ ክብሩና ኃይሉ የማያልቅበትና የሚመሰገነው ልዑል እግዚሀብሔር፣ አሁንም ለክቡር ስሙ  ምስጋና ለእርሱ ይሁን።

ለዛሬ ይዘንላቹህ የቀረብነው  እያንዳንዳችን ጊዜን ወስደን ራሳችንን እንድንመረምር፣ የክርስትና ሕይወታችንን እንድናውቅ ይረዳን ዘንድና ምን ያህልስ ለያዝነው የክርስትና እምነት መተገብርና እንክብካቤን እናደርጋለን የሚለውን እንድንዳስስ ስለሆነ ከዚህ በታች የቀረበውን ጥሁፍ በጥሞና እንድትከታተሉ እናሳስባለን።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተቀብለናል የምንል ሁሉ፤ ከእምነቱ የሚጠበቅብንን ሁሉ መፈጸም የግድ ነውና። ምክንያቱም ከሌላው የክርስትና እምነት የሚለየን ብዙ ነጥቦች ቢኖሩም የኛ ግን መሰረቱና መመራያው “ሀይማኖት ምግባር ነው“ የሚል ነው። ስለዚህም ሳይነጣጠል ሀይማኖትና ምግባር አብሮ የሚሄድ መሆኑን ማንኛውም የእምነቱ ተከታይ በሚገባ ጠንቅቆ የማያውቅ ካለ እርሱ/እርሷ ሀይማኖታቸውን አያውቁምና ከዜሮ መጀመር ይገባል።

ያለፉት አባቶቻችን ጦር ክተት የሚል አዋጅ ሲመታ ለሀገራቸውና ለሀይማኖታቸው ቀናኢ ሆነው ሲነሱ ካህንም ታቦት ይዞ ወጥቷል። እንደእኛ ዘመን የተሻለ እውቀት ሳይኖራቸው ጥያቄም ሳያደርጉ ለሀይማኖታቸውና ለሀገር ፍቅር በመቃጠል ቀፎው እንደ ተደፈረበት ንብ በመቆጨትና በቁጣ እንደወጣ ታሪኩ በማስረጃ ተደግፎ  ይገኛል። እኛስ ሀይማኖታችን ከውስጥም ሆነ ከውጭ ሲደፈርብን ያንን ያህል ቁጭት ይዘን በቁርጠኝነት እንፋለማለን?

በወቅቱ ከፍተኛውን የክህነት ሥልጣን ይዘው የነበሩት ኢትዮጵያዊው አቡነ ጴጥሮስ ለሀገርና ለሀይማኖታቸው ሲሉ ማንኛውንም ድለላ ብሎም ማስፈራሪያ አሻፈረኝ በማለት ደረታቸውን ለጥይት የሰጡ ቆራጥና ጀግና የሀይማኖት መሪ እንደነበሩ ለማንም የማይካድ ነው። ስለዚህ ይህ ሰማዕትነታቸው ከትውልድ ትውልድ የሚኖርና ሌላው የሀይማኖት ምግባራዊነት ታላቅ ተምሳሌት ናቸው። እኛስ ሌላው ጴጥሮሳዊ ነንን? ወይስ የስም ኦርቶዶክሳዊ ብቻ?

ኦርቶድክስ እምነት የተቀበልን ሁሉ ወይንም እምነቱን ተከታይ ነን የምንል ሁሉ ተግባራዊ እስካላደረግን ድረስ የስም ነጋጆች እንጂ ሀይማኖቱ የለንም አሊያም አናውቀውም ማለት ነው። ያመነ ሁሉ እምነቱን መንከባከብና የመጠበቅ ግዴታ አለበትና። ላመነበትም መስዋዕትን ጨምሮ መክፈልም ይገባዋልና። ለዚህም ነው የዘመኑ ኦርቶዶክስ ሀይማኖት ተከታዮች ነን ባዮች ከውስጥም ሆነ ከውጪ ለሚሰነዘርባቸው ጥቃቶችም ሆነ አጽራረ ቤተክርስትያን ወገኖች ጆሮ ዳባ ልበስ ወይንም አይተው እንዳላዩ ሆነው እንደሚገኙም እሙን ነው። እንግዲህ እምነቱን ከነምግባሩ ካልያዝነውና እምነታችንና ቤተ ክርስትያናችንን ተንከባክበን ካልጠበቅን ፤ ለሚተናኮሉም ካልተቋቋምን፤ ያለፉት አባቶቻችን የተውልንን የመስዋዕት አርያነት ካልተከተልን ኦርቶዶክሳዊነታችንን ከጥያቄ ነው የምንዶለው።

በተለይም በምዕራቡ አህጉር ውስጥ የሚገኙ ቤተ ክርስትያኖች አካባቢ ምዕመን ነን እያሉ ራሳቸውን የሚመጻደቁ ወገኖቻችን አውቀውም ሆነ ሳያውቁ ፣ ቤተ ክርስትያን ስለገቡና ስለወጡ ብቻ የእምነቱ ተከታይ አድርገው እራሳቸውን የሚቆጥሩ ፣ ረፈድ አድርገው በመግባት በአዳራሹ በቅዳሴና በትምህርት ሰአት ሌላ የሚከውኑ፣ ወይንም በሳምንት አንዴ ብቻ ብቅ በማለት ከወዳጅና ጓደኛ ፍለጋ ብሎም ወሬና ነገር ለመቃረም ፣ ወዘተ…የሚያደርጉ፣ የእግዚሀብሔርን ለእግዚሀብሔር የሚለውን አስራትና ሙዳየ ምጽዋት የማያደርጉ የመሳሰሉት የሀስት ኦርቶዶክሳዊያን ቁጥራቸው እየጨመረ መጥቷል። ከእነዚህ ኣይነቶችም ውስጥ አጽራረ ቤተ ክርስትያኖች የሆኑ ይደመሩባቸዋል። በየደብሩ እንደዚ አይነቶቹ የሀሰት ኦርቶዶክሲያኖች የሚቀሰቀሰው ኦርቶዶክሳዊ ያልሆነ የቤተክርስትያንን ሰላም ማደፍረስ ችግሮች በየቦታው እየተከሰተ ይገኛል። ለዚህ እርኩስ መንፈስ ተግባር የሆኑ የበግ ለምድ ለብሰው ከበጎች የተቀላቀሉትን አጽራረ ቤተ ክርስትያን እውነተኛ የኦርቶዶክስ ልጆችና እውነተኛ ካህናቶች የሆኑ ሁሉ ለሀይማኖታቸው ሲሉ ሊመነጥሩዋቸውና ሊያጠፋቸው ይገባል። የሀይማኖቱ እምነት አለኝ የሚል ኦርቶዶክሳዊ ሁሉ ከሁሉም በላይ ለፈጠረው አንድ አምላኩና እምነቱ ቀናዊ ካልሆነ፤ በወዳጅና ጓደኛ፣በጋብቻ ወይንም በስጋ ዝምድና፣ በማህበር ወይንም በድርጅት አባልነት፣ ጠለቅ ባለ እውቀት ወይንም አብሮ መኖር አሊያም በውለታ ብሎ ሀይማኖቱን ወይንም እምነቴ ብሎ የተቀበለውን በተለያየ መንገድ ሲቃወሙ  ሆነ ሲተናኮሉ ማሳለፍ ወይንም እምነቱን ሲፈታተኑበት በዝምታ ወይንም በይሉኝታ ማለፍ ወይንም ማሳለፍ በፍጹም ኦርቶዶክሳዊነት አይደለም።

ለዚህም በምሳሌነት በመውሰድ የምንጠቅሰው ከዚሁ የምዕራቡ ክፍለ አህጉር ውስጥ የናንተ የዳላሱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኢል ካቴድራል ደብር ቢሆንም ሌሎችም በአህጉሩ ውስጥ በተመሳሳይ ፈተና ያለፉ እንዳሉ ግልጽ ነው። ከሌሎች ተመክሮ እንዳገኘነው፤ እውነተኛ የኦርቶዶክስ ልጆች አንድ ሆነው ከስራቸው የፈለቁባቸውን አጽራረ ቤተ ክርስትያን ቡድን መምታት ብቻ ሳይሆን ከቤተ ክርስትያናቸው አጥፍተዋቸዋል፤ ወደ ፊትም ተመሳሳይ ፈተና እንዳይገጥማቸው ጠንቅቀው እየጠበቁ ይገኛሉ። እናንተም ዳላሶች እውነተኛ የኦርቶዶክስ ልጆች የሆናችሁ ሁሉ በእምነታችሁና በደብራችሁ ላይ የተነሱባችሁ እነዚሁ እምነቱ የሌላቸውና የደብራችሁ ጠላቶች ምን ቢቦድኑ፤ የሀሰት አሉባልታን በመካከላችሁ ቢያሰራጩ፣፣ በዘር፣ በጎሳ፣ በጋብቻና በስጋ ዝምድና፣ በጓደኝነትና ወዳጅነት፣ በጥቅማጥቅም በመደለል፣  በፖለቲካ ሊለያዩዋችሁ ቢሞክሩ፣ በአለም ፍርድ ቤት ላይ ቢያቆሟችሁ፣ በመተዳደሪያው ደንብ የመረጧችኃቸውን አስተዳዳሪዎችን የተመረጡበትን ሀላፊነት በቅንነት ስለተወጡና ለነሱ መጥፎ ተግባር አሻፈረኝ ስላሉ፣ የቤተ ክርስትያናችሁን መተዳደሪያ ሥርዐት ለመናድ ሲያውኳችሁ፣ ምእመናን የሚገባቸውን የቤተ ክርስትያን የንዋይ ስጦታና መባ እንደዚሁም በአባልነት የተመዘገቡት የአባልነት ክፍያቸውን  እንዳያገቡ ሲያሳድሙባችሁ፣ በአደባባይና በስብሰባቸው እኛ ሚካኤል የምንሄደው ለፀሎት አይደለም ነገር ግን የምንሄደው ለመታዘብና ነገር ለመፈለግ ነው ብለው የሚናገሩ፣ ፍጹም የኦርቶዶክስ እምነት የሌላቸው አዋኪያን፣  ወዘተ…… የከፈቱባችሁን አጽራረ ቤተ ክርስትያንና ጸረ እምነታችሁን  ምሽግ የምታፈርሱት እናንተው እውነተኛዎቹና በዳላሱ የቅዱስ ሚካኤል ደብር ያላችሁ የኦርቶዶክስ ልጆች ብቻ ናችሁ።

ዛሬም እንደትላንቱ አባቶቻችን በመስዋዕትነት ያቆዩልንን ይቺን ብቸኛና ብርቅዬ የሆነች የተዋህዶ ኦርቶዶክስ እምነታችሁን ለተተኪዎቻችን ለማቆየት የታሪክ ብቻ ሳይሆን የእምነቱም ግዴታና ሀላፊነት በናንተ ላይ ብቻ ነውና ይህን የቃቱባችሁንና የተነሱባችሁን ጠላቶች፤ በአመራር ላይ በተመረጡት የቦርድ አባሎቻችሁ መሪነት (እስካሁን ቦርዳችሁ እየከፈለ ያለው ተገቢ መስዋዕት ስለሆነ) በመታቀፍ፤ በሌሎች ከተማ ውስጥ ለተመሳሳይ ፈተና እንደተገበረው ሁሉ እናንተም የኦርቶዶክሳዊ ግዴታችሁን መወጣት ዛሬ ወይንም ነገ የማይባል የወቅቱ ግዴታችሁ ነው። ይህንን ግዴታችሁን ሳትወጡ ወይም ችላ ብትሉ፤ “መምጫዬን ማንም አያውቀውም“ ተብሎ እንደተጻፈው ሁሉ፤ በእምነታችሁ ለመጣ ፈተና በእምነታችሁ ጸንታችሁ አለመገኘት ሆኖ እንዳይቆጠርባችሁ፤ በጾም በፀሎት ጠንክራችሁና ሀይማኖታችሁን በምግባር ገልጻችሁ ፣ ደብራችሁን ተንከባክባችሁ በመጠበቅ፣  የጌታችንና መድህናችን የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ለኛ ሲል የከፈለውን እንደዚሁም አባቶቻችንና እናቶቻችን የከፈሉትን መስዋዕት በማስታወስ ፤ በማንኛውም መንገድ ተዝጋጅታችሁ መክፈል ያለባችሁን ተገብራችሁ ለዘላለማዊው መንግስቱ ትበቁ ዘንድ የተዘጋጃችሁ ሁኑ። ለዚሁም ልዑል እግዚሀብሔር የበቃችሁ ያድርጋችሁ። አሜን።


እርሶስ ምን ይላሉ?      

3 comments:

Anonymous said...

ኃይማኖት የግል ነው፤ ሀገር የጋራ ነው። ቀ.ኃ.ሥ
የሚገርመው ይኸ ሁሉ ቤተክርስቲያንን እና መባዋን ለምን አልዘረፍኩም በማለት ለመክሰስ፤ ለማፍረስ፤ ለመከፋፈል ካልሆነም ለማዘጋት ያበረው፤የሚርዋርዋጠውና፤የሚቅበዘበዘው ሁሉ ባገሩ የተጠላ፤ አወናባጅ እዚህ ሲመጣ ሃይማኖተኛ በመምሰል በነጠላ ታንቆ ከመሰሎቹ ጋር በመሆን ሊጸለይ የመጣውን ምእመን ሲገላምጡ፤ ሲሰድቡ፤ ሲተቹ ውለው እራሳቸው ጠፍተው የሚመለከታቸውን ሁሉ ያላሳበውና ያልጠበቀው ሃጢአት ውስጥ አስገብተው ይሄዳሉ። ይሄን ለማየት የሚፈልግ ሁሉ ከጸሎት በኋላ ወደ ደጀሰላም ብቅ ቢልና ጥግ ይዞ ቢታዘብ የሚታየው ጉድ በቪዲዮ ተቀድቶ ለፊልም ፕሮዳክሽን ቢቀርብ ጥሩ ሶፕኦፐራ ይወጣው ነበር። በዚህ ወቅት ከሳሽ፤ የከሳሽ ደጋፊ፤ አጫፋሪ የወሬ ሱሰኞችና፤ አድር ባይ አስመሳዮች ከሰላማዊው ሕዝብ ተቀላቅለው ይቆዩና ወደደጀሰላም ሲገቡ በየአይነታቸው ተከፋፍለው እያንዳንዱን ጠረጴዛ አንቀው የት እንዳሉ በመዘንጋት ከወዳጃቸው ከቦርድ ጀምረው ቤተክርስቲያን የሚያገለግለውን ሁሉ ሲቦጭቁ ውለው ይሄዳሉ።
ያለእኛ ክርስቲያን የለም የሚሉት እነዚህ የሉሲፈር ልጆች የሚመጡት እግዚአብሔርን ለማምለክ ሳይሆን የአባታቸውን ተልኮ ለማድረስ እንደሆነ ተግባራቸው ያጋልጣቸዋል። እነዚህ የተጠናወታቸው የአእምሮ ህመምተኞች ወደ ቤተክርስቲያን ሳይሆን ጤነኛ ዘመድ ቢኖራቸው ወደአማኔል ሆስፒታል ቢወሰዱ ምናልባት ይሻላቸው ይሆን ይሆናል። በርእሱ በቀደሞው ንጉሥ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ እንደተገለጸው እንኳን በምድረ አሜሪካ የሃይማኖት ነጻነት ባለበት ቀርቶ በኢትዮጵያም እንኳን እያንዳንዱ ግለሰብ በግሉ እንደሃይማኖቱ በነጻነት አምላኩን የማምልክ መብትና አገሩን ደግሞ በጋራ የመጠበቅ ግዴት እንዳለበት ነው።
እነዚህ እርጉማን ተውሳኮች ከወዴት አለም ይሆን የመጡት? በአይናቸው ያለውን ግንድ ሳያወጡ በሌላው ሰው አይን ያለውን ብናኝ ለማውጣት የሚደናበሩት ለምን ይሆን? እንደሚሉት ክርስቲያን ቢሆኑ ኖሮማ በቅጡ ማየት እንዲችሉ መጀመሪያ በነሱ አይን ውስጥ ያለውን ግንድ አውጥተው ከዛ በኋላ የሌላውን ሰው ችግር ሊረዱ በሞክሩ ነበር።
የእያንዳንዱ ሰው እምነትና ሃይማኖት የግሉ ሲሆን ግንኙነቱ ከሚያመልከው ከፈጣሪው ጋር እንጂ ከማንም ጋር ስላልሆነ የሌላውን ሰው ትቢያ ሃጢአት ለምታጋንኑ የሰንበት የነጠላ ክርስቲያኖች ያን ትታችሁ የራሳችሁን ተራራ ብትገፉ ይሻላችኋልና ታቀቡ። ቤተክርስቲያንን ለብዙ አመት ስትበዝብዙ ኖራችሁ አሁን ያ ሲቀርባችሁ በተለያየ መንገድ እያቆሰላችኋት ትገኛላችሁ፤ የፍርድ ቀን ተቃርቧልና ንስሀ ግቡ በማለት ክርስቲያናዊ፤ ወንድማዊና እህታዊ ምክራችንን እንለግሳችኋለን።
እግዚአብሔር ቤቱን ይጠብቅ፤ የሚጻረሯትን ሁሉ ወደነፍሳቸው እንዲመለሱ ይርዳቸው፤ አሜን።

Anonymous said...

Dallas St. Michael Cathedral

Status of the Church:
Officially, the Church by a unanimous decision and by choice is sitting in the middle (Geleltegna), it neither supports the Patriarch in Ethiopia, nor does it support the Patriarch in the U.S.A.
If that is the official status of the Church, then why was it sending $20,000 to the Pope in Ethiopia and asking the Pope to come and take over the Church?
Why was it run by Mahibere Kidusan? An organization whose head quarter is in Ethiopia, under the Pope whom we officially do not support, which has its own structure, bylaws, tax exempt status, registered as a charitable organization, has a branch coordinating office in Denver, Colorado, etc, etc.
Members of this organization had taken over this Church completely except for 2 Priests, and a few Board members. If they were able to get rid of the 2 Priests (Father and son) and the few Board members, there was not one thing that could have stopped them from telling everyone that do not agree with them to not come back. They had control of the keys to the Church, most of their members had keys to any part of the Church except for the holy of holies (Mekdus). They had access to the Church’s finances. They used the Church as their office, the school as their training ground, all of the equipment (computers, telephone, fax, copiers, etc, etc, etc) and supplies for FREE. They managed, administered, commanded and ordered everyone and everything in this Church under the nose of the people that had supposedly started this Church with their money, blood and tears. How is this possible? Think about it?

Major Players of the Church
There were and are still several players in the Church, the main ones include,
Mahibere Kidusan, Woyane/Paulos, The Negash, Bekele and Getachew group, etc. All of these groups were fighting to own the Church, and apply and impose their agenda, if they were not able to do that, they would not hesitate to destroy the Church as this has become a sad reality from the five and counting lawsuits. There is also the confused religious group who comes to Church to worship God.

Members Complaint
Members were heard complaining about a lot of things, the major ones included, “a do nothing Board, a Board that is spending our money as they like, they steal our money, they don’t listen to us, they are corrupt, they hire Priests that are against the official stand (Geleltegna) of the Church without the approval of the members. They allow the groups that are working against the church to grow and multiply in the Church with no control, they gave the Church away to Mahibere Kidusan, etc, etc, etc.
Who elected these people? We did; if we knew that they would be doing what they want and not what we elected them for, we wouldn’t have elected these rascals now it takes two-thirds of the congregation to throw them out. Why are we whining? Are we really concerned about our Church or is this just a lip service?
continued...

Anonymous said...

Continuation..
Solutions
• Who does the Church belong to?
The Church first belongs to God, Jesus Christ is the Head of the Church. Second, the Church belongs to the Christians that are members who are able and willing to protect it with everything they have, even with their life. Christ died for the Church, the apostles and many Christians lost their lives for the Church. Why are we not standing together and fight to save the Church? Do we have the guts?

• What are the responsibilities of the Memebers?
Members are owners and keepers of the Church, in order to do this, Members have to be:
Aware of what is going on in their Church,
Know if the people they elected are doing the job they elected them for,
Ask questions about any and everything that happens without their knowledge,
Take corrective actions with no hesitations,
Know what monies are collected, and where it is going,
Participate in every Church function, For example: board, committees, collections, singing, worship, etc., if you do not, then do not whine!!
Don’t whine and complain, talk, discuss, argue and take action.

• What are the responsibilities of the Board?
The first responsibility of the Board is to make sure that the CHURCH IS NOT BOUGHT OR SOLD by anyone to anyone.
Make every part of their duty transparent so that members could see and know what they are doing is legal and according to the bylaws.
Make decisions according to the bylaws and when necessary with the approval of the members,
Take responsibility for every action or decision they make,
Guard the Church, its property, its monies, and its members from any danger both inside as well outside of any influence that is standing against its teachings and existence.
Members of the Board should know that they are just members as everyone else, they are elected by their fathers, mothers, brothers and sisters of the Church to serve the Church and its members. They MUST know and need to be TOLD over and over again that they are not BOSSES, they are servants to God and the Church (members).

This was taken from the diary of our beloved member, who had sadly, unfortunately passed on to another realm to give Mahibere Saitan HELL!!