Saturday, October 30, 2010

ጳውሎስ በቃለ ጉባዔው ላይ አልፈርምም አሉ

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!

ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።



የሚቀጥለው የተገኘው ከደጀሰላም ጦመር ላይ መሆኑን በቅድሚያ እንገልጻለን
OCTOBER 30, 2010

ሰበር ዜና:- አቡነ ጳውሎስ በቃለ ጉባዔው ላይ አልፈርምም አሉ
አርእስተ ዜና
(ደጀ ሰላም፤ ኦክቶበር 30/2010፤ ጥቅምት 20/2003 ዓ.ም):-
አቡነ ጳውሎስ ሐውልቱ እንዲፈርስ የታዘዘበትን እና የሁሉም ሊቃነ ጳጳሳት ስምምነት የተገለጸበትን ውሳኔ በያዘው ቃለ ጉባኤ ላይ ‹‹አልፈርምም›› በማለት እና ሲጠየቁም ዝምታን በመምረጥ ቀድሞ ሲገለጽ በቆየው እምቢታቸው ጸንተዋል፡፡

አቡነ ይሥሐቅ

አቡነ ጎርጎርዮስ
 ከፓትርያሪኩ ጋራ ሌሎች አራት ሊቃነ ጳጳሳትም በተለያየ ምክንያት የሐውልቱ መፍረስ የተገለጸበትን ቃለ ጉባኤ አልፈረሙም፡፡ ሲኖዶሱ ከ43 ያላነሱ በአገልግሎት ላይ የሚገኙ ጳጳሳት እና ሊቃነ ጳጳሳት በአባልነት ይገኙበታል፡፡
 የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የሐውልቱን ማስፈረስ ውሳኔ እንዲያስፈጽሙ በስማቸው ተለይቶ በመግለጫው ላይ መስፈሩን በመቃወም ለመፈረም ፈቃደኛ አልሆኑም፡፡ ብፁዕነታቸው ‹‹ከእኔ ስም ይልቅ ቢሮው ነው መጠቀስ ያለበት›› የሚል አቋም እንዳላቸው ተነግሯል፡፡
 አቡነ ይሥሐቅ፣ አቡነ መቃርዮስ እና አቡነ ጎርጎርዮስ (ከዚህ በፊት ሐውልቱን ሲቃወሙ ቆይተዋል) ‹ፓትርያሪኩ ሳይፈርሙ በፊት አንፈርምም› በሚል እና ሌሎች ምክንያቶች ለመፈረም ፈቃደኛ አልሆኑም፡፡
 በሕገ ቤተ ክርስቲያን ስለ ቅዱስ ሲኖዶስ የስብሰባ ሥነ ሥርዐት አንቀጽ ሁለት ንኡስ አንቀጽ 4/ሀ ሃይማኖትን እና ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን በሚመለከት ጉዳይ ከጠቅላላው አባላት ከአራት ሦስቱ እጅ በተገኙበት ሲኖዶስ በማድረግ በሙሉ ድምፅ ውሳኔ ማሳለፍ እንደሚገባ ተደንግጓል፡፡
በሕገ ቤተ ክርስቲያኑ አንቀጽ 15 ንኡስ አንቀጽ 1 ፓትርያሪኩ በተሰጠው ሐላፊነት መሠረት ሃይማኖትን እና ቀኖና ቤተ ክርስቲያን የመሠበቅ እና የማስጠበቅ፤ በአንቀጽ 16 ንኡስ አንቀጽ 1 መሠረት ደግሞ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ሃይማኖት የሚያፋልስ፣ ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን የማይጠብቅ፣ ቤተ ክርስቲያንን የሚያስነቅፍ ተግባር ፈጽሞ ከተገኘ፣ ታማኝነቱ እና ተቀባይነቱ በካህናት እና ምእመናን ዘንድ ተቀባይነት ያጣ ሆኖ ይህም በትክክል ከተረጋገጠ በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ከሥልጣን እንደሚወርድ ተደንግጓል፡፡
ፓትርያሪኩ ዛሬ ዘጠኝ ሰዓት ላይ በተጠራው ጋዜጣዊ ጉባኤ በቅዱስ ሲኖዶሱ አባላት ስምምነት የተደረሰበትን መግለጫ እንደሚያነቡ ይጠበቃል፡፡ መግለጫውን ለማንበብ ፈቃደኛ ካልሆኑ ብፁዓን አባቶች የወከሉት የሲኖዶሱ አባል እንዲያነቡት ይደረጋል ተብሏል፡፡

No comments: