Monday, October 18, 2010

ከደረቁም ደረቅ፣ ከእርጥቡም እርጥብና ከበሰበሰውም ብስብስ መሆን ይቻላልን?

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!

ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።


ከደረቁም ደረቅ፣ ከእርጥቡም እርጥብና ከበሰበሰውም ብስብስ መሆን ይቻላልን?

ለዚህ ጥሁፍ ከላይ መንደርደሪያ ያደረግነው  የተለያዩ ሒደቶችን በመዳሰስና በዚሁ ዙሪያ የጨበጥነውን ይዘን በመነሳት ለመቋጨትና ጭብጥ ለማስያዝ ይሆን ዘንድ ለማስገንዘብ ነው። የተወደዳችሁ የዚህ ገጽ ተከታታዮች ሰላምታችን በያላችሁበት ይድረሳችሁ። ለዚህ ሰአትም ፈቃዱ ሆኖ ላደረሰን አምላክ ክብርና ምስጋና ለእርሱ ይሁን። አሜን።

ውድ አንባቢያን ሆይ በጃችን የገባውን የሚቀጥለውን አዲስ ጦማር በመከፈቱ ደስታችን ከፍ ያለ ነው  ሌሎችም እንዲሁ እንዲሳተፉ ለብዙ ጊዜ ስንማጸን ነበር፣እኛ ስለዳላስ ብዙ ስላልኖርንበትና ከብዙ ወገኖቻችንም ሳንቀላቅል በስራ ምክንያት ርቀን ብንሄድም የናንተን መልካምና ሰላምን ዘውትር የምንጸልይ እንዲሁም የምንናፍቃችሁ ነን። ይህን አዲስ ገጽ የጀመሩትን ግለሰብ ገና ከመድረሳቸው  እንደ ድፍረት ባይቆጠርብንም አንዳንድ ስሞች በማር ወይም በወርቅ የቀቧቸው ላይ ልዩነታችን የሰፋ ነውና እርሳቸው ያላቸውም መረጃ ሳናቃልል እኛ ዘንድ የያዝናቸውን መርጃዋችን እንደ ወቅቱ አስገዳጅነት የምንለቀው ሲሆን፣ ያገትነው  በክፋት ሳይሆን ያለውን የጥሩና የመሻሻል አዝማሚዎችን እንዳያደናቅፍ ሲሆን፤ ሰላምና ፍቅር ሲሰፍን ግን ከማንም ሳናካፍል ከኛ ጋር ወደ መቃብር እንዲወርድ ብቻ ነው። ለገጹም አዘጋጅ ሙሉ ጤናና ኃይል እንዲሰጣቸው እየተመኘን ግለስቦችን አስቀድመው ከማወደስ ወደ ተበላሸውና እየተለወጠ ወደ ሚገኘው  የወቅቱ ጉዳይ ላይ በማተኮር ለወደፊቱ ተተኪ ትውልድ እንቅፋቶችን ማጽዳቱ ላይ ማተኮሩን፣  በሀቅና በመረጃ የተደገፉ መሆናቸው ላይ ጥንቃቄን መውሰዱን ስናሳስብ ለብልህ አይመክሩምና ማንነቶን ባይጦምሩት ደስ ባለን። በኛ ገጽም ስሞን እንዳልቀቡ እንግዲህ አደባባይ ኖትና እርም አውጪዎችም ሀዘን ቤት ይግቡ። ለማንኛውም  አድራሻው የሚከተለው ነው፡-
http://www.dfwethiopiancommunity.blogspot.com/

እናንተ በምትኖሩበት በዳላስ ቴክሳስ በጋርላንድ ከተማ ውስጥ የሚገኘውና በኢትዮጵያን ተወላጆችና ወዳጆች ትብብር ተመስርቶ የተቋቋመው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ደብር ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ያጋጠመው ኦርቶዶክሳዊ ፈተና ቸል የማይባል ቢሆኑም በእውነተኛ የኦርቶዶክስ ልጆች በጾም፣ በፀሎት፣ በምህላና አስፈላጊው በሆነው መንግድ ጭምር የመጣውን ፈተና እየተቋቋሙና እየተወጡት ይገኛል። በአለም ዙሪያ የሚገኙት የኦርቶዶክስ ልጆችም በጾምና በፀሎት ጭምር አብረዋቸው እየተሳተፉ እንደሚገኙ ከሚደርሱን አስተያየቶችና ለደብሩም ከሚያደርጉት ድጋፍ ለመረዳት በቅተናል።ለነዚህ ወንድሞችና እሀቶች በያሉበት ቅዱስ ሚካኤል ይማለዳቸው፣ ድካማቸውንም ይቀበላቸው እንላለን።

ወደ ጥቅሳችን ስንገባ፤ ወቅቱ ባላፈው አመት ማገባደጃ ላይ በዳላስ ከተማ ኮይት መንግድና ፮፻፫፭ አውራ ጎዳና ላይ በሚገኝ አንድ ሆቴል ውስጥ በደብሩ ላይ ያነጣጠረ በጥቂት ግለሰቦች ተቀነባብሮ በዕለተ ቀዳሚት ከሰአት በኃላ የተጠራ ስብሰባ ነበር። ግንባር ቀደም አቀናባሪዎች የነበሩት ስማቸውን መጥቀስ ካስፈለገ፡- ኃይሉ እጅጉ(ቀዩ ሰይጣን) እንደዚሁም ሙሉጌታ ወራሽ (ቀዳዳው) የሚል ተቀጥያ ስም በምግባራቸው ያተረፉት ሲሆኑ፤ አጃቢዎቻቸውም የነሱ ቢጤ አጽራረ ቤተ ክርስትያን ይገኙበታል። ከፍተኛ ዘመቻ አድርገው የጠሩት ስብሰባ እነርሱንም ጨምሮ በአሀዝ ከ፪፭ የማይበልጥ ግለሰቦች ነበሩ።

በዚህ ስብሰባ ማንኛውም አይነት የድምጽም ሆነ የምስል መቅረጫ ተሰብሳቢው የተከለከ ሲሆን ከአዘጋጆቹ አንዱ የሆነው መስፍን ወልደየስ የተባለው  ማህበረ ቅዱሳን እየተባለ ለሚጠራው ቡድን አባል፣ክፍሉ ታደሰ ለተባለው የወያኔ ወኪልያደረና የሱን መጽሄት “ዜጋ“ ለተባለው  እንደዚሁም የእርሱ ወንድም የሆነ ብርሀነማርቆስ ታደስ ሎሌ፣ ከሚካኤል ደብር የበጎ አድራጎት ገንዘብ ምዝበራ ቡድን አባልና እስካሁን ማወራረድ አቅቶት በሕግም እንዳይጠየቅ ደብሩን ለማበጣበጥና ለማፍረስ የሚንቀዠቀዥ ግለሰብ ብቻ የሚካሄድው ስብሰባ በምስልና በድምጽ ሲቀረጽ ማምሸቱ የታወቀ ቢሆንም፤ ሌላ ምስልና ድምጽ ቅርጽ የያዘ በሌላ ሰው በስውር የተቀረጸ ነው አሊያም ከመስፍን ላይ የተቀዳ ዳላስ በነበርንበት ወቅት ከወዳጃችን እጅ ላይ ለመመልከት በቅተናል።

የእለቱን ስብሰባ በፀሎት እንዲከፍት ይጠበቅ የነበረው ቀደም ሲል በቅስና በሚካኤል ደብር ሲያገለግል የነበረውና ከምዕመናት ከፍተኛ ተቃውሞ እየበዛበት መጥቶ የነበረው ታደሰ የተባለው ግለሰብ ነበር። ይህ ሰው እንዲለቅ ጫና የመጣበት በጥላቻ ሳይሆን በግል ሕይወቱ መዛባት ስንል፤በመጀመሪያ ባለቤቱ በትዳሯ ባደረገችው ግድፈት፣ ተከትሎም ዕምነቷን ጥላ ወደ ጴንጤ (ፕሮቴስታንት) መሄዷን በማወቃቸው ብሎም ተለያይቶ ቆይቶ አብረው መኖር በመጀመራቸው፤ የወሰደውን ክህነት አጥፍቶታልና ካሕናችን ሊሆን የተገባ አይደለም የሚል እንቅስቃሴና እሮሮ እያደር በመብዛቱ ፤ እርሱም ወኔ ተስኖት ሁሉን እርግፍ አድርጎ መመንኮስን ስላልቻለ፣ በፈቃዱ የለቀቀና በዚያም ቂም ይዞ ደብሩን ከሚወጉ ጋር እየወገነ የነሱን ስብስብ እየተገኘ ፀላይና ባራኪ የሆነ ፤ እንደምንሰማው የርሱ ቢጤዎችና የሱ ጎሳ ቋንቋ ተናጋሪዎች እንደዚሁም ለአባ ጳውሎስ ባደሩ አጫፋሪነት የግሉ የሆነ ቤተ ክርስትያን መክፈቱን ቢሆንም፤ በሰአቱ ደርሶ ግን የእለቱን ስብሰባ ለመክፈት ባይበቃም መደምደሚያውን በፀሎት ሲዘጋ የነዚህን አጽራረ ቤተ ክርስትያን መሰሪ ሥራ እንዲገፉበትና እንዲጠነክሩ ማበረታቻ ሰጥቷል።

በታደሰ አለመገኘት ምክንያት ስብሰባቸውን በወቅቱ የከፈተው ቅደም ሲል የዲያቆንና የቄስ እጥረት በነበረበት ወቅት ቅዳሴ ፀሎቱን በመቻላቸው ብቻ ነገር ግን መቅደስ ውስጥ ገብተው ለመሳተፍ የስርዐቱ ብቃት የጎደላቸውንና ያፈረሱ በነበሩበት የደቆነውን አረአያ የተባለውና በአሁኑ ሰአት የነዚሁ አጽራረ ቤተ ክርስትያን በደነቀሩት ኮሚቴ ውስጥ የሀይማኖት አማካሪ የሆነው ግለሰብ ነበር። ከነካካን አይቀር በወቅቱስ የመጀመሪያዋ ከሳሽ ባል የሆነው ኪዳኔ ምስክርስ እንደ ካህን መስቀል ይዞ አሳልሟል አይደል? ከዚሁ ስብሰባ ተካፋዮች ውስጥ አብዛኛው ከአስተያየት የታቀበ ሲሆን በተለይም  በሁለት ግለሰቦች ክርስትያናዊ ያልሆነ ንግግር እጅጉን የተደናገጠ ይመስል ነበር።
፩ኛው ግለሰብ እንደ ጀብዱ የተናገረው ውስጥ “ እኔ ለሚካኤል ቤተ ክርስትያን ሰዎች ወርሐዊ ክፍያቸውን እንዳያደርጉ፣ በማንኛውም ነገር የሚሰጡትን እንዲያቆሙ ከፍተኛ ዘመቻ እያደረኩኝ ነኝ“ ብሎ የተደመጠው ተኮላ (ተኩላው) መኮንን ነው።
፪ኛው ግለሰብ ደግሞ “እኔ ሚካኤል የምሄደው ለመታዘብ ነው ለፀሎትማ ሌላ ቦታ ነው“ ያለው ጸሀይጽድቅ ቤተማርያም የተባለው ሲሆን እነዚህ ሁለቱም የደብሩ አባል ያልሆኑ፣ ደብሩን በሀሰት የከሰሱ ናቸው።

ውድ አንባቢያን ሆይ! እነዚህ የኦርቶዶክስ ልጆች ናቸውን? በዚህ አለም ለመዝናኛም ሆነ ለትምህርት ወደምንገባበት ሁሉ የነጻ ግልጋሎት የለም፣ አገልግሎት ለመስጠት ወጪ  አለውና። አመኑም አላመኑም  መጥተው  ከመገልገል አልፈው  ሆዳቸውንም ሞልተው  ተዝናንተው  የሚወጡበት የሚካኤል ቤት አይደለምን? ባስተናገደና በመገበ ውልታው እንዲህ ነውን? አባል ሁነው  መብትና ግዴታቸውን ተወጥተው  ጥያቄም  ቢኖራቸው  በደንቡ  መሰረት በስርዐቱ መስተናገድ ሲችሉ ምን የሚሉት ክስ ነው መንፈሳዊውን አግባብ ባለው መንፈሳዊ መንገድ የማይፈታ? በባዕድ ምድር በባዕድ ሕግ ሊፈታ እንዴት ይቻላል? እንግዲህ እነዚህ ከሳሾች መሰረተ ቢስ ክሳቸውን ለምን ያደርጋሉ የሚለውን ለመመለስ ከየት ወዴት የሚለውን መንደርደሪያ በመንተራስ ጭብጡን ለመዳሰስ እንሞክራለን።

ፀሀይ ጽድቅ ወይም እስስት የመባል ተቀጥያ ስም  የወጣለት ለዛዛና ሽኮኮ ወደዘመመበት አጎንባሽ በዘመነ ደርግ አቀላማጭ ሱሪውን የፈታ ሆዳም መሆኑ ብቻ ሳይሆንጌቶቹን ተማምኖ የጨዋ ቤተሰብ ሴት ልጅ በሕገ ወጥ አስገድዶ  ደፍሮናጠልፎ  አንግቶ ይዞ ልጆች አስወልዶ በመጨረሻም ደርግ ሲወድቅ ወደአሜሪካ በመምጣት የሀሰት ፖለቲካ ጥገኛ የጠየቀ፣ የልጅቷም ቤተሰቦች የርሱን ለደርግ ያደረ በመሆኑና ባላቸው  የደርግ ፍራቻ ወደ ሕግ ሳይወስዱት የቀሩ። ይህቺን በሕገወጥነት ያነገታትን ሴት ወደአሜሪካን ሀገር የመኖሪያ ፈቃድ ከነልጆቿ ቢያወጣና ቢያስመጣትም ከአንተ ጋርማ ኑሮ ከደርግ ጋር አክትሟል ብላ መሄዷ ምን ማለት እንደሆነ ላንባቢ ትተን፣ ትላንት ጸረ ወያኔ ነኝ ያለና በሀሰት የፖለቲካ ጥገኛና ሞት ለወያኔ ያለ ዛሬ ተገልብጦ ለወያኔ የ፭፪ቱ ገጽ ተገዢ መሆኑ ማንነቱን በግልጽ ያስቀምጣል። ካለፈው ቦርድ ላደኩበት ቤተክርስትያን ብሎ የተሰጠውን ገንዘብ ወስዶ ለአባ ጳውሎስ እጅ መንሻና መሬት መቀባያ ያደረገ፣ በእጅ መንሻውና እርክብክቡን ጨምሮ በወቅቱ አዲስ አበባ ላይ የታተመው ጋዜጣ ላይ የወጣው ዘገባና ምስል ሲያረጋግጥ፥ ዳላስም ሲመለስ ለታባለው ደብር ያስገባበትን ደረሰኝ ያላወራረደ ተራ ዋልጌና አጭበርባሪ ነው። ለወያኔ ሞት ይመኝ የነበረ ከአዲስ አበባ ሲመለስ ለጠላው  ወያኔ የሺህ ዶላር ስጦታ የገባ ነገር ግን ለሚኖርብት ሀገር መንግስት ዛሬም እየዋሸና የሚገባውን የገቢ ግብር የማይከፍል ብቻ ሳይሆን ከመንግስትም  በሀስት እየተደጎመ የሚኖርበት ቤት ምስክር በማስረጃ ያለ ሲሆን እኛ በሀቅ ሰርተንና የገቢ ግብራችንን የምንከፍለውን ገንዘብ በሀሰት የሚዘርፍና የሚያዘርፍ ፤ ተግባሩም የተጋለጠ ዕለት ሁላችንንም የኢትዮጵያ ተወላጆችን አንገት የሚያስደፋ ነውረኛ ስለሆነ የአካባቢው ነዋሪ የኢትዮጵያ ተወላጅ የሆነ ሁሉ ይህንን ለሚመለከተው አካል የማስታወቅ የሕግ ግዴታ አለበት። እንደተረዳነው አከራዩም የኢትዮጵያ ተወላጅ መሆኑን ስለሆነ የምታውቁት ካላችሁ ማስገንዘቡ መልካም ነው እንላለን። የማታ ማታ ግን እኛም በሕግ ግዴታ አለብንና የጨበጥነውን ወደሚመለከተው ማስተላለፋችን አይቀሬ ነው።  

የዚሁ እኩይ የሆነው ሌላው  ተኮላ መኮንን(ተኩላው) ደግሞ የሚያመሳስላቸው፤በወቅቱ የደርግ ከዳተኛ በኃላም ጸረ ወያኔ የነበረ፣ በታክሲና የሻትል የግል ተዳዳሪ ሆኖ ለመንግስት የሚገባውን የገቢ ግብር የሚሰርቅ፣ በሀሰት ለረዥም ጊዜ በመንግስት የሚደጎም ቤት ኪራይ ውስጥ በመኖር መንግሥታችንና ሀገራችንን ሲመዘብር የኖረ፣ በተመሳሳይ የገቢ ምንጭ  የቤት ባለቤት የሆነ ግንዛቤውን ለአንባቢ ትተን፣ ቤተ ክርስትያኑ ተመስርቶ ከአበበ ብኃላ በ፭ ብር የወራዊ ክፍያ በአባልነት ለአጭር ጊዜ ተመዝግቦ የነበረ ለመሆኑ አረጋግጠናል። በወቅቱ የነበረው አስተዳደር የደብሩ መተዳደሪያ የሚሻሻልበት አስተያየት እንዲጠና በሰየመው ቡድን ውስጥ የቀለምም ሆነ የሀይማኖቱ የጠለቀ ዕውቀት ሳይኖረው ባፈጮሌነት የተሰየመ ግለሰብ ሆኖ እናገኝዋለን። እዚህ ቡድን ውስጥ የተሰባሰቡትና የከበቡዋቸው  ውስጥ ማንኛቸውም በአሜሪካን የሀይማኖትና የሕግን ስርዐት እውቀትም ሆነ ስለ ኦርቶዶክስ ዕምነትና የሕግ ስርዕት አስረግጦ ያለውን መስፈርት የማያሟሉ በመሆናቸው፤ በውስጣቸው ጮሌ ሆኖ የተገኘውም ግርማችው አድማሴ የተባለው ከአዲስ አበባ ከአባ ጳውሎስ ቢሮ በሚሰጠው መሪነት ቡድኑን ውስጥ ከታቀፉት መካከል ፍጽም መጨበጫውና መልቀቂያው ያልገባቸውን ዐይናቸውን በመሸበብና ህሊናቸውንም በመጋረድ ፤ ማሻሺያ የሚለውን መመሪያ በሙሉ የተጻረረ አዲስና ፍጹም የተለየ መተዳደሪያ ሕግና ደንብ አርቅቀው ካቀረቡት ውስጥ አንዱ የነበረ ነው። ይህ የታቀደው ሕግ በዚያን ዕለት አባላቱ ተቀብለው ቢፀድቅ፣ከመቅጽበት በስውር ያዘጋጅዋቸውን እነ….. የተባሉትን በአስተዳደር ላይ ማስቀመጥ ነበር። የቅዱስ ሚካኤል ፈቃዱ ባለመሆኑ በዚያው የስብሰባ ወቅት ነበር የአርቃቂው ቡድን የተባለው የልፋቱን ፍሬ ሳያቀርብ እርስ በርሱ የተናከሰውና እራሱንም የአርቃቂ ቡድን አፍርሶ የሞተው። የዚህ ቡድን አባል ሆኖ ለመስራት በዕምነቱ የጠነከረና በጾም በፀሎት እየተረዳ እንደዚሁም የሀይማኖቱንና የሀገሩንም ሕግ እውቀትን የሚጠይቅ ነው። እነተኩላው  ግን ይህንኑ ቀርቶ በቂ የቀለሙም ትምህርት የሌላቸው በመሆኑ የማመዛዘንና የመገንዘብ አድማሳቸው ጠባብ ስለነበር፤ ቃል የገቡለት ይኑር ወይም የስራ ፍሬያቸውን ማጣት አይታወቅም በሚካኤል ደብር ላይ የጥላቻ መንፈስ ከነሱ መውጣት የጀመረው። ገሚሱ የአርቃቂው ቡድን ከነሱ ሲለይ፣ እንርሱ ግን የሙጥኝ ብለው ስለቀሩ ዛሬ እንደነሱ አጽራረ ቤተ ክርስትያን ከሆኑ ጋር ቦድነው   ከፈጣሪያቸውና ከታቦት ጋር ጦርነት የገቡ።

የኦርቶዶክስ ዕምነት የሚጠይቀውን ሥርዐትና ትምህርት አውቀውና ንቀው ወይንም እንደ አርዮን ለመለየት፣ አልያም ልቦናቸውንም ሆነ ዕሊናቸውን ለዲያብሎስ ማደሪያ ወይንም ባለማወቅ የሚፈጽሙት ፀፀት እንዚህን አጽራረ ቤተ ክርስትያን የሚመሩና በተለያየ መንገድ ከሚደግፉት ውስጥም ለምሳሌ ቀዳዳው ወይም ሙሉጌታ ወራሽ የተባለው  በእርሱ ደንቆሮ መሀይም ጭንቅላት የሚመሩት የሚመስሉት ከሳሾች ከእጅ የማይሻሉ ዶማ ናቸው። በዋሾነት የሚኖርና በሀሰት ያለ ሕጋዊ ፈቃድ በህብረተሰቡ ውስጥ እየተሽሎከለክና ተንኮል እየፈጠረ ለፍተውና ደክመው ያጠራቀሙትን ገንዘባቸውን ከግብር አበሮቹ ጋር በመመሳጠር የሚያከስር የንግድ ቤት ውስጥ እንዲገቡና በአጭር ጊዜ ውስጥ ከስረው እንዲወጡ  ያደረጋቸውን ቤቱ ይቁጠረው። የዚሁ ሰላባ የሆኑትም ቢሆኑ ያላአግባብ ያፈሩት ገንዘብ፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለመክበር በሚያደርጉት ስግብግብነትና ከጠረቤዛ ስር የሚደረግ የሀሰት መዋዋል የሚያካትት ሲሆን፤ ሌላው ግን የዕውቀት ደርጃቸው ነው። በማንኛውም መስክ ያጠራቀሙትን ጥሪት ለእንደዚ አይነቱ ሌባ ጋር ከመደርራደር ይልቅ፣ በምንኖርበት አካባቢ ከብሔራዊ መንግሥት ስር ካሉ እንደ ስሞል ቢዝነስ አስተዳደር፣አይ አር ኤስ፣ ከተለያዩ የሀይማኖት ና መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች የነጻ ግልጋሎቶችን ማግኘት የሚቻል ሲሆን ባንኮችና ቼምበር ኦፍ ኮሜርስም ይረዳሉ። ከዚህም በተጨማሪ እንደ ንግድ ድርጅቱ መጠን የሕግና የንግድ አማካሪ ድርጅቶች በክፍያ የሚሰጡትም አገልግሎት ከብዙ ጸጸትና ከነቀዳዳው  አይነት ሌቦች እንድትጠበቁ በዚህ አጋጣሚ  እየጠቆምን የቀዳዳው ሰለባ የሆናችሁ ሁሉ የሕግ አዋቂዎችን በቶሎ ብታማክሩ ወይንም ጉድዩ በተፈጸመበት ክልል ወደሚገኘው አቃቤ ሕግ ወይንም ዲኤ መስሪያቤትና የፖሊስ ክፍል ወይንም ከሁለቱም መስሪያቤቶች አቤቱታ ማቅረብ ትችላላችሁ። የቋንቋም ችግር ቢኖርባችሁም በራሳችሁ በሚገባችሁ የሚያስተረጉሙ   ሙያተኞች የማግኘት ችግር የላቸውምና።በዚሁ አጋጣሚ አንዳንድ ወንጀሎች በኢትዮጵያን ተወላጆች መካከል በየቦታው እየተፈጸመ ወደ ሕግ እንዳይቀርብ በኮሚኒቲው  ውስጥ ተደብቆ እንደሚቀርና የኮሚኒቲውም ከሕግ አስከባሪው ጋር ግንኙነት ያልፈጠረ ዝግ ከሚባሉት የኢምግራት ኮሚኒቲ የሚቆጠር በመሆኑ፣ ለምሳሌ ያህል ለመጥቀስ ከአመታት በፊት በከተማችሁ ውስጥ ሕይወቷ በባሏ ቤተሰቦች ያለፈችው ወጣትናየጨቅላ ህጻን እናት ደም ዛሬም ይጮኃል። ባደረግነው  ሙ ከራ እንኳን ራሷን ልትገል መሳሪያ ነክታም የማታውቅ ቅን የዋህ ከድኃ ቤተሰብ የወጣች እንዲሁም ዘመድ የሌላት ምስኪን ደም በሁላችሁም የዳላስ ነዋሪ እጅ ያለ ነው። በተለይም የመረዳጃ ማህበር ነኝ ባዩ ድርጅትም ሆነ ጎረቤት የነበረው ተፈራወርቅ ይህንን የመሰለ የግፍ ግድያን መሸፋፈን በሕግም በሀይማኖት ያስጠይቃል።የሴቶች ማህበር የተባለውስ የከተማችሁ ድርጅት የተለያዩ አሉታን አያመጣም? የተወደዳችሁ አንባቢያን በተቻላችሁ ሁሉ ከዚህ ኃላ ቀር አመለካከት መለወጥ ይገባናል።ወደድንም ጠላን በምንኖርበት ሀገር እንደሀገሩ ሕጉንና ባሕሉን ጠብቀን የመኖር ግዴታችን ሲሆን ከነቀዳዳው አይነት ጩ ልሌም እንጠበቃለን።

ቀዳዳው በያዘው አጽራረ ቤተክርስትያን መንፈስ ማንነቱን ለመዳሰስ ከባድ አይደለም። በየስብሰባው በግልጥ እኔ ነኝ ጠበቃ ያመጣሁትም በገንዘብም የምረዳ እያለ እንደ ጀብዱ የሚናገር፣ አምላክና ታቦት የደፈረ ፣ በሚስቱ ላይ ሌላ ያስቀመጠ ፣ ፈፅሞ ኦርቶዶክሳዊነት የሌለውና ወያኔ ላወጣው ባለ፭፪ ገጽ መመሪያ ለማስፈጸምና ለወያኔ ታማኝ ሆኖ ለመገኘት ቤተ ክርስትያናችሁን ለገጸ በረከት ለማቅረብ ከሚሽቀዳደሙት አንዱ የሆነ፣ የሜይ 2ቱን የደብራችሁን ሁከት ጠንሻሽና በኃላም በዕለቱ ድርጊት አፈጻጸም ላይ የተሳተፈ፣በዚህም ድርጊቱ ከሚጠጣበት የጽዋ ማህበርና እቁብ የተባረረ ነው። ሰሞኑንም እንደ ተጨማሪ አድርጎ የያዘው የተባረረበትን እቁብ ማጥፋት ባለመቻሉ በከተማችሁ ከሚገኘው የግዮን ምግብ ቤት ባለቤት ጋር በመመሳጠር ቅጥረኛ እየላከ እቁቡን ለማስበጥበት ላለፈው ሁለት ሳምንት ገጠመኝ የደረሰንን ስንገልጥ እቁበተኞችም ሆኑ እቁቡ የሚካሄድበት ድርጅት ሳትደናገጡ  ከላይ እንደገለጽነው  እየመጣ ሰላማችሁንና ነጻነታችሁን ለሚነካ ባለጌ ቅጥረኛ ወደ ፖሊስ ማመልከትና እርምጃ በዛ እንዲወሰድበት ማድረግ እንዲሁም  ለግዮኑም ሰውዬ ሥርእት ካልያዘ እንደ ወዳጁ ቀዳዳው  ባስቸኳይ መገለል ነው።

ውድ አንባቢዎች በሚቀጥለው ተከታዩን ይዘን እስክንገናኝ በሰላም ቆዩን!

1 comment:

Anonymous said...

ካድናቂያችሁ አንዱ ነኝ ። ስትጽፉ ወደ ጎን አትሉም ቀልጥ እንጂ። ነገር ግን ችኩል ሆናችሁብኝ ዛሬ። ይሄውም ከሮቅ ሆናችሁ ስለምትመዘገቡት ውነታ እስከዛሬ ስንደነቅ፤ ኢንፎርሜሽን ከዳላስ የሚያቀብሉዋችሁን ሰዎች አስመልክቶ ዛሬ ትክክለኛ ኢንፎርሜሽን ሳይሰጥዋችሁ በመቅረቱ የተነሳ ይመስለኛል አዲስ ስለተከፈተው ብሎግና ስለመዘገበው የሰታችሁት አስተያየትና ማሳሰቢያ ትክክል ሆኖ አላገኘሁትም። በመጀመሪያ ጦርነቱን ብቻቸውን የተጋረጡ ሴት ናቸው ማለትም ዛሬ እናንተ የምትታገሉበት ሜዳላይ። የምትታገልዋቸው ትሁዋኖች እኮ ተሰብሰበው በተለያየ ቦታ በተደጋጋሚ ጦርነት የከፈቱት ወይዘሮ የሐረር ወርቅ ላይ ነበር እንጂ አንድም ሌላ ወንድ ወይም ሴት ላይ አልነበረም። የምመክራችሁ እኔ እነዚህ ኢንፎርሜሽን የሚሰጥዋችሁን ከወይዘሮ የሐረር ወርቅ ጋር እንዲያገኛኙዋችሁ ጠይቁና እናንተም አለን ያላችሁትን ማስረጃ እሳቸው ካላቸውና ከዚሕ ቀደምም ለሁላችን ከሰጡት ጋር አጣምራችሁ ትሁዋኖቹ በመላው አሜሪካን አገር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ውስጥ ገብተው እያገሙት ስለሆነ እየበጠበጡም ቶሎ ባንድነት አጥፉልን እኛም አብረናችሁ ነን። በሌላ በኩል እኝህ ሴት እኮ ከጊዜያቸው የቀደሙ ናቸው። ብዙው ሰው የጻፉትን አንብቦ መነጋገሪያ የሆነው ነገር ቢኖር ስለ አቶ ተኮላና እዬኤል በጎ ጎናቸውን ያስቀመጡት ነው። ምን አይነት እግዚአብሄር ሰላሙን የሰጣቸው ሰው እንደሆኑ እኮ የገርመኛል ሁሌም። መጥፎ ላደረግዋቸው ፈጽሞ ክፉ አጸፋ አይመልሱም ነገር ግን በእርግጥ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ለሚደረግ ማንኛውም ደባ ኮምፕረማይዝ አያደርጉም። ሕዝቡም የሚወዳቸው የሚያከብራቸው ለዚህ ነው።

ወይዘሮ የሐረር ወርቅ ሲቲ ኦፍ ዳላስ ስራ ካስገብዋቸው ኢትዮጵያውያን አንዱ ነኝ በዚህ አጋጣሚ ከብዙ አመት በሁዋላ እግዜር ይስጠልኝ እላለሁ ይችን ጊዜ ተጠቅሜ እስካሁንም ባለማለቴና ከጠላቶቻቸው ጋር በመታለል አድሜ ላደረኩት ሁሉ ትልቁ እግዜአብሄር ይቅር ይበለኝ።