Thursday, July 8, 2010

አወገዘ ውግዘት

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!

ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።




 የቤተ ክርስትያን ሕግና ሥርዐት የሆነው ፍትሐ ነገሥት፣ ቄስም ሆነ ዲያቆን በሀገሩ የተሾመውን ኤጲስ ቆጶስ ንቆ ፣ አቃሎ ለብቻው ቤተክርስትያን ከሰራ ኤጲስ ቆጰሱ እስክ ሶስት ጊዜ ጠርቶት ካልመጣ እሱና እሱን የመሰሉት ከሹመታቸው ይሻራሉ ይላል (ፍትሐ ነገስት አንቀጽ 8 ረስጠብ 19)። ቄሱ እንካ ያል ሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ቤተ ክርስትያን መክፈት ቀርቶ ያለበትን ቤት ክርስትያን ትቶ ወደ ሌላ ቤት ክርስትያን ከሄድ እንዲመለስ ተነግሮት ካልተመለሰ ከሹመቱ ይሻራል ይላል። (ፍትሐ ነገስት አንቀጽ 6 ረስጣ 14 ነቂያ 14)።

ይህንን ከመዘርዘራችን በፊት በቀደሙት ፓትሪያኮች የሥልጣን ዘመን ብዙ የኦርቶዶክስ ቤ/ክ ከአገር ውጭ በብዛት ተከፍተዋል። የአሁኑም ፓትሪያክ በስደት ጊዜቸው ከላይ ያለውን ሕግ አፍርሰውና ሰበካቸውን ጥለው ፖለቲከኛ ሁነው ሀገር ጥለው ሲኮበልሉ ፣ ጳጳስ ነኝ ብለው ቤ/ክ ሲከፍቱ ኖረዋል። እንደ ደንቡማ ክሕነት ያለው ከከፋው ወደ ገዳም እንጂ ስደቱ ወደ ምእራብ ሀገሮች ባልሆነ። ስለዚህ ከቤተ ክህንት ፈቃድ ውጭ ቤተ ክርስትያን መመስረትና የፓትሪያክ ስም ሳይጠሩ መቀደስ የጀመሩት ራሳቸው አቡነ ጳውሎስ ናቸው። የኢትዮጵያ ሕዝብ በፖለቲካ ምክንያት ወደውጭ አገር መሰደድ ከጀመረ በኃላ በየደረሰበት አገርም ህብረቱን (ግንኙነቱን) የጀመረው ፖለቲካውንና ሃይማኖቱን አቀላቅሎ ነው። አብዛኛው ከ45 አመት በላይ ያለው አማኝ ሃይማኖቱን ይወዳል እንጂ ስለሀይማኖቱ ቢጠየቅ በቂ መልስ ለመስጠት የሚያዳግተው ስለነበር፣ በልቡ ብቻ የሀይማኖቱን ፍቅር ይዞ ተሰደደ። የፖለቲካውንና የሀይማኖቱን ለዩነት በሚገባ ለይቶ የተረዳ ባለመኖሩ በፊቱ መልካም መስሎ የታየውን ብቻ በመከተል የቻለውን ሁሉ ሲያደርግ ቆየ።

በመጨረሻም ደርግ ሲወድቅ ወደ ኢትዮጵያ ከመመለሳቸው በፊት በሎስ አንጀለስ ለተሰበሰበው ምዕመን ይቅርታ በመጠየቅ ‘እስካሁን ድረስ በትግርኛ ቋንቋ ሳላገለግላችሁ ስለቀረሁ ይቅርታ‘ ብለው ትግራዊያንን ከሌላው ለይትው ይቅርታ በመጠየቅ፣ በሀይማኖት መካከል ዘረኝነትንና ፖለቲካን አቀላቅለው መርዝና ፍትፍት የተናገሩትም ራሳቸው አቡነ ጳውሎስ ናቸው። በግፍ ተሰደድን የሚሉት የጳጳሳቱ ቡድንም ቢሆን የትክክለኛ ሀይማኖተኞችን ልብ የሚይዝ አንዳችም ነጥብ የላቸውም፣ በስተጀርባው ብዙ ከሀይማኖት መንገድ የወጣ ዘረኝነት የኑፋቄና የፖለቲካ ችግር ያለባቸው ሰዎች የሚበዙበት ቡድን ነው። ከዚህም በተጨማሪ አገር ውስጥ ያሉት የውጭዎችን እንዲሁም የውጪዎች አገር ውስጥ ያሉትን አወጋግዘው ነው ያሉት። ስለዚህ መዳፈር ባይሆንብን አንድም በኦርቶዶክስ እምነት ክህነቱን ተቀብሎ ያለ የተረፈ የለም ማለት ነጥብ ላይ ያስደመድማል።

ስለዚህም ባለፈው ሰንበት እለት ከወዲይ ሰፈር ስለውግዘት ቃኘንና ወደ ዳላስ ወዳጃችን ደውለን ካረጋገጥን ከረምን ። ቀደም ሲል ለኛ ያልወጣልን ስም አልነበረም፣ ምህላም ላይም ብንሆን እውነተኛውን ከመናገር ወደ ኃላ አንልም። እኛ ቦርዱን ጥሩ እስከሰራ ድረስ ከጎኑ እንደምንሆን ሁሉ ከመንቀፍም ወደ ኃላ አንልም። ከተቃዋሚዎችም የምንለየው ለዚህ ነው። እንግዲህ ወደ ቁም ነገሩ ስንገባ ለምን ቦርዱ ይህንን እርምጃ ወሰደ? አስገዘተ? ገዛቹስ ከግዝት የደረሰውስ? ሥልጣኑስ? የሚለውን አንባቢዎቻችን እንዲያጤኑትና የራሳቸውን ግንዛቤና አቃም እንዲወስዱ እየጠየቅን እኛ የምንለው አለን።

ከቦርዱም ሆነ ከመነኩሴው እንድተገለጸው አምዳችንን መዝጋት ስለማይችሉ ትምህርት ይስጡበት ሲሉ ምን አይነት እንደ ሆነ ቢገልጹልን በወደድን፣ ለነገሩ እስካሁን አምዳችን በተለያየ ርእስ ላይ ለህብረተሰቡ ግንዛቤ እየሰጠና እያወያየ መሆኑን ከትምህርት ካልገባ ፤ ስህተቶች ገሀድ ካልተወያየንበትና ካልተማመርንበት ፤ ለምርምር ካልበቃንብት ፤ ወዘተ……ሲያበሩን ባቻ የምንበራ ወይም ሲያጠፉን ብቻ የምንጠፋ ኣሊያም የመብት ጥያቄን መጋፋት እንዳይሆን እንላለን።
“ሰንበቴ የለ ተቆጪ ዳላስ የለ አፍጣጭ
 ቦርድ ተገኘ በግላጭ።“ ያለን ወዳጃችንን እይስታውስን መላ የኦርቶዶክስ ምእመን ወደ ዳላስ ቅዱስ ሚካኤል ዌብ ሳይት እየገባ አስተያየቱን እንዲሰጥልንና ውግዘቱ በመነሳቱ ብዙ ከኛ የተሻሉ ድህረ ገጾች እንዲወጡ መንገድ ይከፍታል ብለን ስለምናምን ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። በሌላ በኩልም ‘ የቆጡን አወርድ ብላ የብብታን ጣለች‘ እንዲሉ ቦርዱ  የወሰደው እርምጃ ውጤት ግን እሩቅ አይሆንም። ቀደም ባለው ስለመኖክሴው አባት ስንጽፍ ፣ በግል ጊዜአቸው ስላለው ባያገባንም፤ ወደ አፓርትማቸው የሚነጉደው ትራፊክ ቁጥር አብዛኛው ደብሩን ሲያደሙት የኖሩ አሁንም ያልተኙት መሆናቸው የዚህም ነጸብራቅ ውጤቶች ባለፈው እሁድ ገሀድ ሆናል።

በከተሜ ሽውዳ ወይም ሞሳ ከግዞቱ እንዲሉ እንግዲህ እንደህጻን ተረት ትረት እያልን እንስጨብጣችህ፡-

ተረት ትረት በሉን የላም በረት!

በአንድ ሀገር ውስጥ በአንድ ከተማ የሰፈሩ ስደተኞች ነበሩ። እንደአቅማቸውና እንደእምነታቸው በሰፈሩት ከተማ ውስጥ አንዲት ቤተ ክርስትያን አቁመው ከቆዩ በኃላ ቄስ ከትውልድ ሀገራቸው ያስመጣሉ። ያስመጣቸው ሁለቱም ቄሶቸ ባለትዳርና ልጆች ያላቸው ነበሩ። አንደኛው ወጣት ሲሆን ሌላው የጨመተ ነበር። በቅርብም ተጎራብተው ሲኖሩ ወጣቱ ገንዘብ ስለሚወድ ሌላ ስፍራም ተቀጥሮ ይሰራ ነበር አሉ። የሌላኛው እየደረሰ ያለው ወጣት ልጅና የወጣቱ ቄስ ሚስት ትውውቃቸው እየጠበቀ በመምጣቱ ለባላ አልመች በማለታ በትዳራቸው ችግር ገባ አሉ። በመጨረሻም ስትባልግ ተይዛ ከቤት ውጣች። ይባስ ብላም ሀይማኖታን ለወጠች። ጰነጠጠች። መቼም በኦርቶዶክስ እምነት ከአንድ በላይ ቅስናን የሚያፈርስ ነገር አይጣል ነውና መልሶ ታርቆ አስገባት። የጎረምሳው አባት ግን ጉዳዩን ሲያውቅ ፣ የልጁን ድቁና ገፎ ወደ ትውልድ ሀገሩ ሲመልሰው እንዳይመጣም ገዝቶ የላከው የወጣቱን ቄስ ቅስናና ትዳር ሊመልሰው ነበር አሉ። ነገር ግን በህጉ ወጣቱ ቄስ መለያየትና መመልኮስ አሊያም ቅስናውን ማፍረስ ሲገባው ክህነተ ስልጣኑን እየተጠቀመ ነው አሉ። ምን ይህ ብቻ ከነበረበትም ደብር በዘርና በፖለቲካ በመመረዙ ክርስትና ልጆቹን፣ የዘርና የጎሳ ተወላጆቹን ይዞ የራሱን ቤተ ክርስትያን ከፍቶ ያገለግልበት የነበረው ደብር ሲሆን ለመቀማት ካልሆነም ለማጥፋት ሌት ተቀን ጥፋቱን ተያይዞት ይገኛል አሉ። የነበረበት ደብር በሰደትኞች የተቃቀመ ስልሆን ከሀገር ቤቱ አስተዳደር ነፃ የሆነ በመሆኑ እርሱም ለሀገር ቤቱ መሪ በቁዋንቃና ባገር ልጅነቱ በማድላት የሰውና የፖለቲካ ሰራተኛ ሆነ አሉ። ተፈጸመ።

ከዚህ ተረት ጋር የሚገናኝ በዳላስ ከተማ ሁለት የጊዮርጊስ ቤተ ክርስትያኖች አሉ። አንደኛው የሰባተኛው የሚሉት ውስጡ ባቀፈው ነው አሉ። ሌላው ግን እስካሁን ገለልተኛ የነበረ ከዚህ በፊት ያሳሰብነው ትንቢት ባይሆንም ገሀድ እየመጣ ነው አሉን። በተረቱ የወጣቱ ቄስ የመሰለ የዚህን ቤተ ክርስትያን አመራር ለሀገር ቤቱ ለማስረከብ በአመራሩ ውስጥ ገብቶ እያመቻቸ መሆኑን ከዚሁ ሹክ እንበላችሁ። እነሱንም ታገሉ እያልን  መላ ኣማኝ ጸንቶ በጾሎት እንዲለምንላቸው እንጠይቃለን። እንደሚታወቀው አንድ የነበሩትና ከሚካኤል ወጥተው የከፈቱት ባለመግባባት የተከፈሉ ናቸው ብለውናል።

እርሶስ ምን ይላሉ

No comments: