Sunday, July 25, 2010

የገደል ማሚቱ

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!

ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።



ሌላው ሸንጎ ሆነ የገደል ማሚቱ !

እንኳን ለቅዱስ ገብርኤል በዐለ ንግስ አደረሳችሁ ። በመካከላችሁ ተገኝተን የበዐሉ ተካፋይ ባንሆንም የደመቀ በዐል እንዳሳለፋችሁ ወዳጆቻችን በስልክ አውግተውናል ። እኛም በቦኒ ምክንያት ደረቅ መሬት ቆይታችንን ጨርሰን ፣ ቦኒ ምን ሰርታ አለፈች የሚለውን ቅድሚያ ግምገማ አጠናቀን መረጃችንንም ሰርተን ጨርሰን ነው ለዚህ ጥሁፍ የበቃነው ።

በዐላችሁ የደመቀ ከመሆኑም ባሻገር አሁንም በጣት የሚቆጠሩ ቅሬታቸውን ያልተው ወይንም …… ተስተውለዋል ። ለምሳሌም ሸንጦት ከበሮ እንዳይመታ ወይንም አምላኩን በከበሮ እንዳያመሰግን የኪዳኔ ምስክር ሚስትና ግምባር ቅደም ከሳሽና በፍርድ ቤት ከ2 ጊዜ በላይ የተረታች ጥሩአየር የተባለችው አሁንም ይግባኝ ብላ ደብሩን ፍርድ ቤት ያቆመችው ፣ ባለቤታን ከበሮ ለማስጣል ዛቻ ስታደርግ በአካባቢው የተገኙትን ምዕመናን ሁሉ ያስገረመ ትርዒት መሆኑን ስንሰማ እኛንም ገርሞናል ። ከዚህም አልፎ እንደ ልቧ ወደ ወጥቤቱ በመመላለስ እዚያ ውስጥ የሚያገለግሉትን እህቶች ስታሳቅቅ ማርፈዷን ከስፍራው የደረሰን ስለሆነ ፣ ቦርዱ በጉዳዩ ላይ መክሮ እንደ እርሷ አይነት ደብሩን የከሰሱት ላይ ማእቀብ መጣል ወይንም በሕግ እርምጃ ማስወሰድ ግዴታው ነው እንላለን ።
እንደዚህ አይነቶች ምክንያት ፈላጊዎችና ነገረኞችን በቅጡና በሩቁ ካልሆነ እስካሁን በፍርድ ቤት ያላገኙትን ዐይን አውጥተውና ደፍረው የከሰሱትንና ያሳዘኑትን ደብርና ምዕመን ንቀው ፣ እንደዚሁም ክሳቸውን ሳያቆሙና ንስሐ ሳይወስዱ መካከል መግባታቸው ሌላ ችግር ለመፍጠር መሆኑ የመንኮራኩር ጠበብትነትን የሚያስፈልገው ስላልሆነ ምዕመናኑም ሆነ ቦርዱ ሊመክሩበትና ቅድሚያ ትኩረት የሚያሻው ጉዳይ ነው እንላለን ።

ከዚሁ ሳንርቅ የኮሚኒቲው ሬዲዮ አቅራቢዎችና ወጋኞቻቸው የኛንና የናንተ የውድ አንባቢዎቻችን ብቸኛ ድህረ ገጻችንን ተቆጥተውባት የሚችሉትን ሁላ ሲጥሉባት ቆይተው ሰአት ስላልበቃቸው ለሌላ ጊዜ በቀጠሮ መዛታቸውን ስንሰማ እሰየው ለዛሬ ከተረፍን አላልንም ፣ እናንተም ቤታችሁን አጽዱ ነው ያልነው ። ያሉትንም ለመስማት ወደ ድህረ ገጻቸው ገብተን የእለቱን ሬድዮ ፕሮግራም በኢንተርኔት ብናገኝ ብለን ወደዚያ የሚመራን ወይም የሚጠቁመን በማጣታችን መልሰን ወደ ወዳጆቻችን ደወልን ። እነርሱም አዲስ ሞል የሚባል አለ ብለውን ያገኘነው http://www.hswebsite.com/Radio.html ሲሆን ያቆመው በ01/03/10 ። እንግዲህ እነ ጋሽ ዘውገ ዳላስ ያወራችሁት ለራሳችሁ ብቻ ስለሆነ በስማ በለው ባገኘነው ምንም እንኳ ምንጮቻችን የታመኑ ቢሆንም የሰበቃችሁትን ጦር የደሎደመ መሆኑን ከዚሁ እንገልጽላችኃለን።

አሁንም የወያኔ ሎሌ ክምችት የሆነ ድርጅት መያዛችሁን አረጋገጣችሁ እንጂ በዚህ ጉዳይ ዙሪያ በገጻችን የዘገብነውን ነጥብ በነጥብ ልታስተባብሉ አልሞከራችሁም ። ለነመንግስቱም ሆነ ደጀኔ አስተያየትም ቢሆን እኛ ኢንስቱትዮች ይጥፉ ብለን አላልንም ፣ አሁንም ወደ ገጾቻችን ከበልብ ጎራ በሉ እንላለን ። ከዚህ ከመድረሱ በፊት ኮሚኒቲውን በገጻችን በቂ ጥሪ አድርገንላቸዋል ፣ አልሰሙንም ! አሁንም ሩቅ አይደለም ። የሕብረተሰቡን ጥያቄ እስካሁን ማስተናገድ ደረጃ ኮሚኒቲው ያልበቃውና ሊያድግ ያልቻለው ፤ ሁሉን ሊያቅፍ ያልበቃው ለምንድን ነው የሚለውን ጥያቄ ለማስተናገድ እራሳችንን የምንጠይቀው “ ከዳላስና አካባቢው አትዮጵያዊና የኢትዮጵያ ተወላጆች ቁጥር ስንቱ እጅ ነው አባልነቱን ጠብቆ የሚከፍል የድርጅቱ አባል?” የሚለውን ጥያቄ መመለስ
ከቻልን ብዙዋኑን ያቀፈ እስከሆነ እኛም የምንለው አይኖረንም ። ከዚህም ቀጥለን ያለውን የድርጅቱን መተዳደሪያ አንቀጽ እስቲ አብረን እናንበው፡-
6.3 BOARD OF TRUSTEES (BOT):

6.3.1 A special Board of Trustees will be established to assist, guide and monitor the efforts associated with the campaign to raise funds and other activities in supporting the MAAEC (Building Committee, Famine relief, Radio etc.)

6.3.2 The five members of this Board of Trustees will be drawn from the larger Ethiopian Community, U.S. Citizens ( who are friends of Ethiopia and interested to provide leadership and guidance in areas of legal, financial and logistical issues), and other interested parties.

6.3.3 The BOT will work closely with the MAAEC Board to make sure that the funds for the planned Community Center are kept in a separate account and are used for that purpose only.

6.3.4 The BOT will have the legal authority to reside over the Board members and staffs to act as a monitoring agency over any issue within and without the organization.

6.3.5 The BOT disputes among the officers and others as needed

6.3.6 The BOT acts as a sounding board for new or pressing issues

ይህንን ያልነው ወጋኞቹ ጠቅሰው ከኛ ድህረ ገጽ ያወጉትን አጠፋ ለመመለስ ሳይሆን ይህን የመሰለ የመተዳደሪያ አንቀጽ በዳላስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ርዕሰ አድባራት ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ለማስቀመጥ ባለፈው ጥቂት አመታት ተሞክሮ ያደረጉት ግለሰቦች ስውር ድርጊት መሆኑን የተገነዘብን ስንቶች ነን? እነዚህ ግለሰቦች እነማን ናቸው? አሁንስ ምን እያደረጉ ነው? አውቆ የተኛን መቀስቀስ ባይሆንም የነቁት ግን የነዚህን ግለሰቦችና ቤተሰቦች በተለያየ ስም የከፈቷቸውን የግብረ ሰናይ ስሞችን ለማወቅ በዘመኑ ጥበብ በመረዳት ኢንተርኔታችሁን ቃኙበት እንላለን ። ይኼ ቦታ በመተዳደሪያው የተቀመጠው ለማን ይመስላችኃል? ማን ሊጦርበት ነው? በ3.3 ጀምሮ ያለው አንቀጽ ሙሉ መብት ከማንም በላይ የሚስጥና (ሱፕሪም ፓወር) እንደተፈለገ ሕጉንም መለወጥ (ቴክኒካል) መንገድ የሚከፍት ነው ። እነዚሁ ናቸው ቤተ ክርስትያኑን ያበጣበጡ ብቻ ሳይሆኑ አሁንም ያልተቆጠቡ ግለሰቦች ያልናቸው ። የመረጃውም ማህበር በቅርብ ከቤተ ክርስትያኑ ጋር ለረጅም ጊዜ አብሮ የተጓዘ ቢሆንም በነዚሁ መሰሪዎች የኃላ መሪነት በፈጠሩት ችግር ዛሬ ሆድና ጀርባ ናቸው ።

በቤተ ክርስትያኑ ውስጥ በተፈጠረው ችግር በተሳታፊነት ሚና የተጫወቱት የዚሁ ድርጅት የቀድሞ ቦርድ አባላት አሁንም ላሉት ቦርድ አባላት እንደ አባት አሳዳጊና መካሪ ብቻ ሳይሆኑ ተደማጭነታቸው የላቀ ነው። የሬዲዮ አቅራቢዎቹም የገደል ማሚቱ ናቸው። ሁሉም ይቅርና ለሕብረተሰቡ ቆሜ አለው የሚለው ይኽ ድርጅት ፣ በዐይነቱና በድርጊቱ ተወዳዳር ያልተገኘለትን ፣ በሚንቀሳቀስበትና መንበሩ ባደረገው ከተማ ፣ በራሱና በወገኑ መካከል ተደራጅተው (ኦርጋናይዝ ክራይም) በሜይ 2 በቅዱስ ሚካኤል ደብር የተፈጠረውን ብጥብጥ ያላወገዘ ፣ ያልኮነነ ፣ መግላጫም ያላወጣ ድርጅትና ሬዲዮ ዘጋቢውንም ጨምሮ ለኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ነው የቆምኩት ፣ ስሜን በገጻችሁ ተቻችሁ ብሎ የኛን ገጽ መንካቱ ማፈሪያ እንዳያደርጋችሁ ! ያ በአለም የተሰራጨው ቪዲዮ ሀይማኖትን፣ ዜግነትን፣ ሀገርን፣ ማንነትን፣ ወዘተ…….. ያዋረደ፣ ያቆሰለ ፣ ያስደፈረ ፣ ወዘተ …….. ድርጊት አፍንጫችሁ ሥር ከመፈጠሩ በፊትም ሆነ በኃላ ተሳትፍዎቻችሁ ምን ነበር ? እርምጃዎቻችሁስ ? በዛ ቪዲዮ ተወናዊያኖቹ እነማን ናቸው? ወያኔ እህትማሟቾች ፣ የጳውሎስ ሎሌ ምናሴ እህት ፣ ባሏ ሀዋዝ ለፎክስ ዜና ያቀናጀው፣ ባለቬዲዮው መስፍንና ግብረ አበሮቻቸው፣ ወዘተ……አሁንም በቤተ ክርስትያኑ ላይ ክስ አስተባባሪዎች የናንተው ቀድሞ ሊቀ መንበር ተፈራ ፣ በትሩ፣ ወዘተ……. ማለት ብዙ ይቻላል ። እኛ ብቻ ሳንሆን ሌላም ገጾች በመረጃ ያቀረቡት ብዙ ጉድ አለ ። እኛ እነዚሀን ግለሰቦችን ቀባሪ እንዲያጡም አንፈልግም ! ጥሩ ሲሰሩ እውቅና ከመስጠት መጥፎውንም ከመጠቆም ወደ ኃላ አንልም ። የሰሩዋቸውም ጥሩ ነገር የሉም ባንልም መዘገብ ከጀመርንበት ወቅት የሚጎዳኘውን ከወቅቱ ጋር ያለውን እንጂ ። አሁን በሬዲዮ የምትሉትን ከስማ በለው ይልቅ በመጣፍ መስመር ብንገናኝ ብዙ ለንማማር እንችላለን ። ብዙዎችንም የአካባቢውን ሕብረተሰብ እናሳትፋለንና ። በቅን ከመወያየት መተራረም ይቻላል እንላለን ። ምን ጊዜም ገጻችን ሊያስተናግዳችሁ ዝግጁ ነው ። በዚህ አጋጣሚ የናንተ ድርጅት ከሴቶች ማህበሩ ጋር ያለመግባባት አለ የሚባል ስለምንሰማ ከሁለቱም ድርጅቶች ወይም አባሎች መስማት እንፈልጋለን ? ያላችሁን ጣሉልን ጅምራችን ለቅን ነውና እንደአመችነቱ እንለጥፈዋለን ! ከቤተ ክርስትያኑም አካባቢ የምትሉት ካለ ጣፉልን?

እርሶስ ምን ይላሉ?

4 comments:

Anonymous said...

እረ ተመስገን ነው ቤተክርስቲያኑን የሚጠብቁ ሰዎች ከናንተ ጋር የሚነጋገሩ ቃልም የሚያቀብሉ መኖራቸው። ነገር ግን ትልቁን ነገር እረስተዋል። በዙ ገለጻ ለማድረግ ይቻል ነበር። ነገር ግን ስለ የኢትዮጵያ የጋራ መረዳጃ ማህበር አይደልም ከተማውስጥ ያለውን መሰሪና ጥሩውንም በጣም ጣንቅቃችሁ ስለምታውቁ ባጭሩ በጣም የሚያሳዝን ነገር የተሰራውን ለመግለጽ እንወዳለን። ይሂውም የቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ዛሬ ያውም የቅዱስ ገብረኤል ታቦት በወጣበትና አንዲት ድግ እናት በመሞታቸው ፍትሃተ ጸሎት በሚደረግበት ቀን ያለ አንድም የቦርድ አባል የቂዱስ ሚካኤልን ቤተክርስቲያን መድረኩን ከነ ስፒከሩ የያዙት ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ የጋራ መረዳጃ ማህበሩ ቦርድና ያው የእድሩም እነሱው ስለሆኑ እነሱው ናቸው በሁለት ስም አንድ አካል ማለት ነው። ሌላው መድረኩን ከመቆጣጠራቸው የተነሳ፡ የእድር ማስታወቂያ ዛሬ ብዙ ሕዝብ ስለተሰበሰበ ታስቦበት በመምካከር ቦታውን እንደተቆጣጠሩት ግልጽ ነበር ለሁልም ሕዝብ። በዚህን አይነት ቀን እስቲ ተመልከቱ የእድር ማስታወቂያና የትቦታና ሰአት ሁሉ ሳይቀር በመረዳጃ ማህበሩና በእድሩ የእሕዝብ ግንኙነት ተብሎ ያስቀመጡት በከተማው በወሬ ማቀበል የሚታወቀው በማበጣበጥም በሃሚትም እሱ ነበር ስፒከሩን ይዞ የዋለው።

ከቅዱስ ሚካኤል ቤተርክስቲአይን ከቦርዶ አንድም ሰው አዳራሹን እስከመጨረሻው የተቆጣጠረና ለማነጋገር ለጥያቄ እንክዋን በወለሉ አልነበረም። ዝግጅቱን የዘጋው ያው የጋራ መረዳጃው ሕዝብግኑኝነት የተባለው የወሬ እናት ነው። እነዚህ ሰዎች ቤተክርስቲያኑ የማስታወቂያም ክፍልም ሆነው በቻ ሳይሆን የዋሉት እስከመጨረሻው በተሰጣቸው የቁጥጥር ስልጣን በቤተክርስቲያኑ ቅጥር ግቢውስጥ ስለቆሙት መኪናዎች ሳይቀሩ አንዱን ብቻ ለመጥቀስ ያህል፡ ጆራችንን እስከሚያመን ድረስ አማሃው ስፒከር ይዞ ሥነስራአት በሌለው አነጋገር መኪና መንገድ የዘጋችሁ አላችሁ ስራ አላስኬድ አላችሁ ሰዎችን እያለ ሲለፈልፍ ስለነበር ቤተክርስቲያኑ ያለ ቦርድ ሃላፊዎች ነበር ዛሬን ያሳለፈው። ወደ ዳላስ ስትመለሱ የምትሉትን ለመስማት የምንጉዋጉዋ የብሎጋችሁ አንባቢዎችና አስተያየት አካፋዮች እነ ታደሰ ከመስኪት ።

Anonymous said...

ስላም ዳላስ ፡ እንክዋን አናንተንም ለገብረኤል አደረሳችሁ ኣያልን፡
ይችን ውነትን የጨበጠች መልክታችንን ለማስተላለፍ ያስነሳን ስለ ወይዘሮ ትሩ አይር የጻፋችሁትን ያነበበው ጉዋድኛችን ነግሮን ካነበብን በሁዋላ ሁላችንም የበኩላችንን እንድንጽፍ በተስማማንበት መሰረት ነው።

የወይዘሮ ጥሩ አየር ፍሰሃን ድርጊት ሁሉም ያየው አይደልም የተወሰነ ሰው እንጂ መክኒያቱም ጮሀው ባለመሰማቱ በአዳራሹ ውስጥ ያለው ሊሰማ አይችልም በተቀመጡበት አካባቢ ካልሆነ። ታዲያ ትልቁ ዳቦ ሊጥ ሆነ እንደተባለው ሆነና ግለሰብዋ ትናንትና ካደረጉት ይበልጥ የሚያስገርመውን ማወቅ ይኖርባችሁዋል ። ቃል አቀባዮቻችሁስ እንዴት የምትታገሉትን ድርጅት ቤተክርስቲያን ተቆጣጥሮ መዋሉንና በአሉንም መሪ እንደነበረ ነፈጉዋችሁ?

የቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ትናንትና በእድርና ከመረዳጃ ማህበሩ ጋር ምንም ግንኙነት የሌለው እድር ባለቤቶች የሁኑት ግልጽ ወያኔዎች ቤተክርስቲያኑን ከነድምጽ ማጉሊያው ሳይቀር በቁጥጥራቸው ስር ሆኖ ውልዋል። ይሄ ነው ህዝቡን የገረመው እንዴት መረዳጃ ማህበሩ እድሩ ቤትክርስቲያኑን ተቆጣጠረው ማስታወቂያ ሁሉ ያደርጋሉ፡ የታሉ የቦርዱ አባላት በሚል።

የቅዱስ ገብሬል አመታዊ በአልና የብዙ ኢትዮፕያውያንን ልጆች ያሳደጉ ብዙ ሰው የሚወዳቸ ደግ ሰው ፡ እናት ትሁት አድርገን የምናያቸው አርፈው በሃዘን ቀን እስቲ አስቡት የእድር መል እክት ማስተላለፊያ ቀን መቀጣጠሪያ መሆን ነበረበት? ለምን በሬዲዮናቸው አይለፈልፉም? አንድዋን ሴት በቅርብ ጊዜ ሲሳደቡ አልነበርም እንዴ ዘውገን አንተ ጅንጀሮ አሉ ተብሎ ሴትየዋ?

ዳኔል ጌተቸውና አብረሃም በቀለ።

Anonymous said...

በውነት የተባሉት ሁኔታዎች ተፈጥረው ከሆነ በጣም ያናድዳል። በበኩላችን ሁኔታዎቹን ለማጣራት ብዙ ጥረት አድርገን ነበር። ነገር ግን የተጣራ ኢንፎርምሽን ለማግኘት በጣም አስቸጋሪ ሁኔታ ገጥሞናል። ግማሹ ሰው የቦርዱ ማስታወቂያ ተናጋሪ አቶ ጤፉ የሚባሉት ናቸው እሳቸውም የእድር ተወካይ ስለሆኑ በሰርጎ ገብነት እያገለገሉ ነው ይላል። ግማሹ ደግሞ አዲሱ የወያኔ ታክቲክ በቦርድ መሀል ሰርጎ በመግባት መከፋፈል ስለሆነ አዲስ ለገቡት ድርጎ ቆርጦ እንዲሸረሽሩ እነየወሬ ቋት የተባሉትን ይዞ አማች ዘርማንዘር ሳይቀር ወደምዝበራው ለመመለስ ከፍተኛ ዘመቻ ላይ መሆናቸው ይነገራል። መስሏቸው እንጂ ሚካኤልማ ተአምሩን በተደጋጋሚ አሳይቶናል። እሬሳ ለመሸከም ሲሯሯጡ ያያችኋቸው ስዎች ለዚህ ቤተክርስቲያን እድገት ጣታችውን የማያነሱትና ይህን ቤተክርስቲያን ለዚህ ውድቀት ያበቁት ናቸው። ዛሬም አላረፉም!! ሚካኤል ቢታገስ ገብሬልን በእለቱ መፈታተን ሞክረዋል እስቲ የገብርኤልን አርጩሜ ደግሞ ይቅመሱት!! የኛ ጥያቄ በእርግጠኝነት እግዜአብሔርን የምታምኑ ስዎች ለቤተክርስቲያናችን ሰላም እድገትና ፍቅር እንጸልይ የሚል ሲሆን። የመሸታ ቤት ተግባራችሁን በቤተክርስቲያን መጠቀም የምትሞክሩት ደግሞ አወዳደቃችሁ አያምርምና በጊዜ ንስሀ ብትገቡና ወደእግዚአብሄር ቤት ስትመጡ ደግሞ በቅጥር ግቢ ውስጥም ሆነ ከግቢ ውጭ ሆናችሁ እግዚአብሄርን ምህረት ብትለምኑ ይሻላችሁ ይመስለናል። ይህ ምክራችን ካልጣማችሁ ብዙ አትታመሙ እግዚአብሄርን ከነመልአክቶቹ ስለሆነ የደፈራችሁት ከጎናችሁ ታገኙታላችሁ። ቤተክርስቲያናችንን እንዳረከሳችሁ እግዚአብሔር ለእናንተ ያዘጋጀውን አይንፈጋችሁ።

Anonymous said...

Dallaseotc,
ይሄ ብሎጋችሁ በጣም ተወዳጅ እየሆነ ከመምጣቱም በበለጠ በዚህ በዳላስ ፎርት ወርዝ፤ የሚገርማቸው በአለም ዙሪያ ያሉ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ፍቅር ይዞዋቸዋል ከዚህ ብሎግ። ወያኒ ከነ ጭፍሮቹ በጣም ፈርትዋችሁዋል። በቃ እያንቀጠቀጣችሁ ያላችሁት እናንተ ብቻ ናችሁ ከብሎግ ሁሉ።

ዘውገና መንግስቱ ሞሴ፤ ሰለሞን ሃመልማል አፓርቺኒስቱ፤ ግርማ ንጉሴ በድብቅ ለወያኔ ሲሰራ የነበረ በዘውገና በመንግስቱ በምናሴ አማካኝነት ብሎም ቀደም ብሎ ተደብቆ በገባው ሙስጠፋ ወያኔነቱን አረጋግጦ ጠበሉን ተጠምቆ የመጣ ነው። ማህበራችን ላይ ያለውን ሁሉም የሚያወሳው ነው በቅርብ ጊዜ። ልክ እንደ ጸሃይ ጽድቅ ግርማ ታደስም የተቀበለውን የስራ ድርሻውን ካልተወጣ በየቦታው እየሄደ የወያኔን ታላቅ መሪነት መሬቱ ይወሰድብታል እረ ሌላም ነገር። ዘለዚህ እነዚህ በአንድላይ ሲሰሩ የኖሮ ካሃዲዎች አሁንም እየሰሩ ያሉ ስለሆኑ ለወያኔና ለሌሎቹም ጊዜያችሁን አታቃጥሉ እነሱ ላይ። እናንተ ስለነሱ ስታወሩ ቤተክርስቲያኑ ውስጥ ዘው ብሎ ለመግባት የሚያደርጉት ዘዴ ነው። ባለፈው ሳምንት የሚካኤልን ቤተክርስቲያን አዳራሻ ተቆጠጥረውት የነበርው ሃቅና ገሃድ ነው።

አስመራጭ ኮሚቲ ሆኜ ስምንት አመት ሰራሁ የሚለው ቀን ቆጠራም የማያውቅ እንደ ወረደ ያለ መሃይም ነው። በስምንት አመት ውስጥ ሁለት ቀን በውሽት ለማስመሰል ለተደረግ የእርስ በእርስ የወያኔዎችና የኢንቪስትመንት ያደረጉ ሰዎች እንደ መንግስቱና ሚስቱ አበባ አይነት ስምንት አምት ማገልገልን አያሳይም። ካላንደር መቁጠር አስተምሩት ። ብርሃን ዳኛቸው የተፈራወርቅ ሁለተኛ ሚስት በመሆንዋና ባል እየገዛች አምጥታም ከነልጆቹ ሰውዬው ሊቀመጥ ባለመቻሉ ጥልዋት ስለ ሄድ ያላት እድል እንደስዋው እንደ እባብ ሹልክ እያለ ቁጭ በይ ስትባል የምትቀመጥ ተነሽ ሲላት የምትነሳ ፡ የሴቶችን ድርጅት ስም አጥፊ ስትባል የምታጠፋ ነች።

መደረግ ያለበት፡ እነዚህ የሕዝብ ሰላምና አንድነት ጽሮች ከሬዲዮኑም ማስወጣትና ቦታውን ብትክክለኛ ኢትዮጵያውያን መተካት ነው። የመረዳጃ ማህበር ውስጥም ያሉትን ጽረ ኢትዮጵያውያን አሁን በሚገባ ሕዝቡ አውቀናቸዋል ያለምንም ጥርጣሪና ይሆናል አይሆንም በማያሰኝ ሁኔታ ስለዚህ ጠላቶችን ወያኔዎችንና አብረዋቸውም በመሆን እድሜ እየጨመሩ ያሉትን መንጠሮ ማስወጣት ነው። ከቤተክርስቲያኑም እንዳስወጣናቸው አሁንም ቦርድ የጠራ እንዲሆን አቶ አበበ ንጋቱን ነገር ግን በጣም እንድናስብበት ያስፍፈልጋል። ሰውዬው እድር ውስጥ ካሉበት ወያኔን አሁንም በተፈራወርቅና በበትሩ በኪዳኔ አለማየሁ በዘውገ አማካኝነት በተለይ በመንግስቱ ሞሴ በኩል እያገለገሉ ነው ማለት ነው። ያለፈው እሁድ የምግብ ቤቱን አዳራሽ እንደ ልብ የእድሩ ንግድ የማስታወቂያ መድረክ ሆኖ ማርፈዱ የአቶ አቶ አበበ ንጋቱ እጅ ያለበት ይመስላል እንደዚያም ይሸታል።

Dallas.eotc, selam thank you long live dear.